Monday, August 15, 2011

ብፁዕ አቡነ ሚካኤል አረፉ




ብፁዕ አቡነ ሚካኤል
የሰሜን ምዕራብ ትግራይ የሽሬ እንዳሥላሴ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን በአብርሃም እቅፍ ያሳርፍልን። ለወዳጅ ዘመድ በሙሉ መጽናናትን ያድልልን።
(ዝርዝሩን ወደፊት እናቀርባለን።)

Sunday, August 14, 2011

በቅዱሳን ደም መጠየቅ እንዴት ያስፈራል?


በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል የተፈጠረን የሰው ልጅ ነፍስ ማጥፋት ታላቅ ክፋት፣ ታላቅ በደል ነው፡፡ ይህንንም ጌታችን ‹‹እናንተ ግብዞች ጸፎችና ፈሪሳውያን የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ፣ የጻድቃንንም መቃብር ስለምታስጌጡና ‹በአባቶቻችን ዘመን ኖረን በሆነስ በነቢያት ደም ባልተባበርናቸውም ነበር ስለምትሉ ወዮላችሁ፡፡ እንግዲያስ የነቢያት ገዳዮች ልጆች እንደሆናችሁ በራሳችሁ ላይ ትመሰክራላችሁ፡፡ እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ሙሉ ፤እናንተ እባቦች የእፉኝት ልጆች፣ ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ? ስለዚህ እነሆ ነቢያትንና ጥበበኞችን ፃፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ፤ ትሰቅሉማላችሁ፤ ከእነርሱም በምኩራባችሁ ትገርፋላችሁ፤ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤ ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሰዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ፡፡›› በማለቱ እንረዳለን፡፡ (ማቴ 23፥29-36)

በቅዱሳን ደም መጠየቅ እንዴት ያስፈራል? ጌታችን ‹‹ወዮላችሁ››፣‹‹እናንተ እባቦች፣ የእፋኝት ልጆች››፣ ‹‹ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ?›› ‹‹በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ›› በማለቱ የበደሉን ታላቅነት ፤ የቅጣቱንም አስከፊነት አመልክቷል፡፡ ወንድሙን ከገደለው ቃየል ሳይማር በነፍሰ ገዳይነት የተገኘው ላሜሕ ‹‹እኔ ጎልማሳውን ለቁስሌ ብላቴናውንም ለመወጋቴ ገድዬዋለሁና ቃየልን ሰባት እጥፍ ይበቀሉታል፤ ላሜሕን ግን ሰባ ሰባት እጥፍ›› ብሏል፡፡ (ዘፍ 4፥24)

‹እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ››

ስለሚያስቷችሁ ሰዎች ይህንን ጽፌላችኋለሁ 1ኛ ዮሐ.2፥27

ሐሰት አንናገርም፤ እውነትንም አንደብቅም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተነጣጠረው የ”ተሐድሶ” ዘመቻ ውጥን ብዙ ዐሥርት ዓመታት ያለፉት ቢሆንም ከ1992 ዓ.ም. የካቲቲ ወር ጀምሮ ግን ማኅበረ ቅዱሳን ተጨባጭ በሆኑ የምስልና የድምፅ ማስረጃዎች ዘመቻውን በማጋለጥ የቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ሲኖዶስ ውግዘት ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡ ከዚያ በኋላ “ተሐድሶ” ስልቶቹን በመቀያየር ሃይማኖታችንን ለማጥፋትና በሌላ ፕሮቴስታንታዊ አስተምህሮ ለመተካት የሚያደርገውን ሩጫ ቀጥሏል፡፡ በመሆኑም ማኅበረ ቅዱሳን ካለፈው ነሐሴ 2002 ዓ.ም ጀምሮ ይፋዊ የሆነ ከእነዚህ ሴረኞች ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ እንቅቃሴ ጀምሯል፡፡ የሐመር መጽሔት ልዩ እትምን በማዘጋጀት የተጀመረውን አገልግሎት በሌሎችም በኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ከካህናቱ ከሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና ከሕዝበ ክርስቲያኑ ጋር ፊት ለፊት በተደረጉ ውይይቶች በመታገዝ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል፡፡ በዚህም የ”ተሐድሶ”ን ምንነት፣ መሠረት፣ ግብና ዓላማ፣ ስልት፣ ያለበትን ደረጃ፣ በሌሎች እኅት አብያተ ክርስቲያናት ፈጥሮት የነበረውን ቀውስና መዘዝ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዒላማ ለማድረግ በይፋ በተለያዩ የኅትመት ውጤቶች እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለማብራራት ጥረት ተደርጓል፡፡

ፈቃደ እግዚአብሔርን እንዴት ማወቅ ይቻላል?


ፈቃደ እግዚአብሔርን እንዴት ማወቅ ይቻላል?» የሚለው የሰው ሁሉ ጥያቄ ነው። ብዙዎቻችን መመዘኛችን ሥጋ ዊ በመሆኑ ፈቃደ እግዚአብሔርን ለማወቅ፥ ለመቀበልም እንቸገራለን። የሚነገረው ሁሉ ለኅሊናችን መልስ ስለማይሆን አጥ ጋቢ መልስ አላገኘሁም እንላለን። ለምሳሌ፦ ከአይሁድ የተላኩ ካህናትና ሌዋውያን፦ መጥምቀ መለኰት ቅዱስ ዮሐንስን፦ «እንኪያስ አንተ ማነህ? አንተ ኤልያስ ነህን?» ባሉት ጊዜ፦ «አይደለሁም ፤» ብሏቸዋል። ዮሐ ፩፥፳፩። ነቢዩ ኤልያስ በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ቢያርግም በስሙ የተነገረ « እነሆ፥ ታላቋና የምታስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳትመጣ ቴስብያዊው ኤል ያስን እልክላችኋለሁ።» የሚል ትንቢት አለ። ሚል ፬፥፭። ይኽንን ይዘው ነው፥ «ኤልያስ ነህን ?» ያሉት። ዮሐንስ «አዎን ነኝ፤» ማለት ይችል ነበር። ምክንያቱም ጌታችን ፦ «ልትቀበሉትስ ብትወዱ ፥ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው።» በማ ለት እንደመሰከረለት በሁሉ ኤልያስን ይመስለዋልና። ማቴ ፲፩፥፲፬። ነቢዩ ኤልያስ፦ ፀጉራም ፥ጸዋሚ ፥ተሐራሚ፥ ዝጉሐዊ፥ ባሕታዊ ፥ ድንግላዊ ነው። ቅዱስ ዮሐንስም ልብሱ የግመል ፀጉር ሆኖ፦ ጸዋሚ ፥ ተሐራሚ ፥ ዝጉሐዊ ፥ባሕታዊ ፥ ድንግ ላዊ ነው። ይሁን እንጂ «አይደለሁም፤» ያለው፦ «ነኝ፤» የሚለው እውነት ለአይሁድ ለኅሊናቸው መልስ ስለማይሆን ነው። ለእኛም ስለ ፈቃደ እግዚአብሔር የሚነገረው እውነት ሁሉ ለኅሊናችን መልስ አይደለም። 

ገንዘቤን ሳትሰጠኝ ትሄዳለህን?


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዘቁስጥንጥንያ፣ ኤጲፋንዮስ ዘቆጵሮስ እና ቅዱስ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም እኒህ ሦስቱ በአንድነት ሲማሩ አድገዋል:: ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስነትን በተሾመ ጊዜ ሰይጣን ልቡን በፍቅረ ንዋይ አታለለው /ተዋጋው/ ከዚህም የተነሣ በሚገኝበት አዳራሽ የወርቅ ሰሃን የብር ፃህል ጽዋ አሠርቶ ነበር:: ኤጲፋንዮስ ይህን እየሰማ ሲአዝን:: ከእለታት አንድ ቀን ቦታይቱን እጅ የሚነሣ መስሎ ሊመክረው ቢመጣ በዚሁ አዳራሽ ተገኝለት:: ወንድሜ የቆጵሮስ ሊቃውንት ደጋግ እንደሆኑ ታውቃለህ:: በዚህ አዳራሽ ልገኝላቸው ስጠኝ አለው:: ሰጠው:: እየሰበረ ለነዳያን ይመጸውተው ጀመረ:: ገንዘቤን ስደድልኝ ሲለው ቆየኝ እያለ ሰነበተ:: በሚሄድበት ጊዜ ሄድሁልህ አለው:: ገንዘቤን ሳትሰጠኝ ትሄዳለህን? ብሎ ልብሱን ያዘው:: ዘወር ብሎ እፍ ቢለው ሁለት ዓይኑን ነሣው /አጠፋው/:: ከጫማው ወድቆ ያለቅስ ጀመር:: አንዱን ለዝክረ ነገር ትቶ አንድ ዓይኑን አብርቶለታል:: እርሱም ይህ ምክር ተግሣጽ ሆኖት እስከ ዕለተ ሞቱ ሲመጸውት ኑሯል:: ሲሞት አንድ አላድ እንኳን አልተገኝበትም:: በረከቱ ትድረሰንና ብጹ አብ ቅዱስ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም “ኑባሬ ሃይማኖት” በተሰኘው የነገረ ሃይማኖት መጸሐፉ የታወቀ ሊቅ ነው:: /ከዚህ ምን እንማራለን?/

ምንጭ :‐ የሃይማኖተ አበው ትርጓሜ የብራና ቅጅ ያልታተመ

Friday, August 12, 2011

ቅዳሴ ማርያም...ንባቡ እና ትርጓሜው

አባ ሕርያቆስ የደረሰው 
ከቀድሞ አባቶች ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ንባቡ እና ትርጓሜው 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሊቃውንት እንደ ፃፉትና እንደ ተረጎሙት

በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የሚያምኑ እና የሚማፀኑ ሁሉ ውዳሴዋን እና ቅዳሴዋን በመማርና በማስተማር በመፀለይም ጭምር እንዲጠቀሙበት መፅናናትም እንዲያገኙበት ከአበው ሲወርድ ሲዋረድ የቆየውን ንባቡን ከነትርጓሜው በዚህ መልክ አቅርበንላችዋል፡፡

ይህን የእመቤታችንን ቅዳሴ ማርያም በዚህ በፍልሰታ በፆም ወራት ቤተክርስትያን ተገኝተው ለመስማትም ሆነ ለማንበብም ለማይችሉ በተለያየ ሀገራት ለሚገኙ ወገኖች በቀላሉ እንዲያነቡ ተደርጎ የተዘጋጀ

THE VIRGIN'S FAST



The Pope Shenouda III series on the topic of “The holy virgin saint Mary” 

Deacon Hibret Yeshitila

The Church celebrates the fast of our Lady the Virgin beginning with the first of Mesra, (the 7th of August). It is a fast for which people care very much, and they practice it with forceful ascetism. Some add days to it, in regard of the great love of people for The Virgin.

The fast of The Virgin is an occasion for spiritual renaissance in the majority of churches.

They prepare a spiritual program for daily sermons, and daily masses too in some churches, even the churches which are not named by the name of The Virgin. There is a great feast for our Lady The Virgin, which is celebrate  in her ancient church in Mostorod.

'' ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ” ሉቃስ 18:14


 ዲያቆን ሳሙኤል ብርሃኑ

ከላይ ያለውን ቃል የተናገራው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ቃሉንም የተናገረው እራሳቸውን ስለሚያመጻድቁና ሌላውንም ስለሚንቁ ሰዎች በምሳሌ ሲያስተምር ነው። ሁለት የተለያየ ህብረተሰብን የሚወክሉ ሰዎች ለጸሎት ወደ ቤተ መቅደስ እንደሔዱ እና ሁለቱም ስመ እግዚአብሔርን ጠርተው ጸሎት ቢያቀርቡም አንደኛው ብቻ ጸድቆ ወደቤቱ እንደ ተመለሰ ይናገራል።ለጸሎት እንደ ሄዱ ከተነገረላቸው መካከል አንዱ ፈሪሳዊ ነው።

‹‹የኢትዮጵያ ድኳኖች ሲጨነቁ ዐየሁ›› ዕንባ 3.7




ኢትዮጵያ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአሥራት አገር ናት፡፡ ሊቃውንትም ነቢያት የተነበዩትን ትንቢት የቆጠሩትን ሱባዔ መሠረት በማድረግ ቅድስት ድንግል ማርያም በኪደተ እግሯ ኢትዮጵያን መባረኳን ያስተምራሉ፡፡ ነቢዩ ዕንባቆም «የኢትዮጵያ ድኳኖች ሲጨነቁ ዐየሁ፤» ዕንባ. 3፡7 ብሎ የተናገረው ቃለ ትንቢት እመቤታችን የኢትዮጵያን አውራጃዎች ለመባረኳ ማስረጃ መሆኑን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይተረጉማሉ፤ ያመሠጥራሉ፡፡

አኰቴት ዘተዋሕዶ አዲስ የቴሌቪዥን መርሐ ግብር

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን እምነት ፤ ስርዓት ፤ ትውፊት እና ታሪክ የሚያስተምር አዲስ የቴሌቪዥን መርሐ ግብር 
እሁድ ከቀኑ 6፡30 – 7፡30
EBS ቴሌቪዥን በመላው ዓለም  ይሰራጫል፡፡


‹እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ››