- ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ አሁንም በአብ ቀኝ ቆሞ ያማልዳል፤›› አሰግድ ሣህሉ
- ‹‹የክርስቶስ ሥጋ እና ደም ተቀበልንም አልተቀበልንም ለውጥ የለውም›› አሰግድ ሣህሉ
- ‹‹የእውነት ቃል አገልግሎት›› የተባለ የተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ድርጅት የመሠረተ ነው
- ‹‹ሙሉ ወንጌል›› አማኞች የጸሎት ቤት በተካሄደው ጉባኤ ላይ ከመሰሎቹ ጋራ ተካፍሎ ሲወጣ ተደርሶበታል
የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ አራማጅ - አሰግድ ሣህሉ እንደ ማሳያ
አሰግድ ሣህሉ በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን የዉሉደ
ያሬድ ሰንበት ት/ቤት የተሐድሶ ኑፋቄን ለማስፋፋት፣ አንዳንድ የሰንበት ት/ቤቱን ወጣቶች ከእናት ቤተ ክርስቲያን ወደ ‹‹ሙሉ ወንጌል››
አዳራሽ ለመውሰድ ሲያደርግ የቆየውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ በጥብቅ ሲከታተል በቆየው የሰንበት ት/ቤቱ ሥራ አመራር ኮሚቴ የተዘጋጀው
ባለ 40 ገጽ ሰነድ ያስረዳል፡፡ እንደ ዘገባው ማብራሪያ አሰግድ ሣህሉ ከሚኖርበት ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 11/12 የቤት ቁጥር
417 በተለምዶ ቡልጋሪያተብሎ ከሚጠራው የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል - የከርቸሌው ሚካኤል አካባቢ
ያለሰበካው ወደ ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን መጥቶ በዉሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት በ1985 ዓ.ም የተመዘገበው ሰንበት
ት/ቤቱ በወቅቱ ያጋጠመውን የአገልግሎት መዳከም ተመልክቶ ስውር የተሐድሶ ኑፋቄ ተልእኮውን ለማራመድ እንዲያመቸው ነው፡፡