(አንድ አድርገን መጋቢት 21 2008 ዓ.ም ፡- የምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኝ ሲሆን ይህ ቤ/ክ በ1986 ዓ.ም በአካባቢው ምዕመናን እንደተመሰረተ ይነነገራል፡፡ የቤተክርስቲያኑ ይዞታ ወደ 80ሺ ካሬ
የሚጠጋ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ከተሰሩ ወይም በመሰራት ላይ ከሚገኙ እጅግ ግዙፍ ከሚባሉ አብያተክርስቲያናት ውስጥ አንዱ
ሊሆን የሚችል ሕንጻ ቤተክርስቲያን እያስገነባ ይገኛል፡፡
የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር በተለያዩ ስራዎች ለተሰማሩ አስራ ሁለት ግለሰቦች በወር 157,332 ወርሐዊ ኪራይ የሚያገኝ ሲሆን
ከ7ሺህ ካሬ በላይ የሚገኝውን ቦታ ደግሞ በካሬ ሜትር ከ5 ብር እስከ 8 ብር ከግለሰቦች እንዳከራየና ወርሃዊ ኪራይ እንደሚሰበስብ የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ድረ-ገጽ ላይ
ሰፍሮ ይገኛል፡፡