Saturday, March 19, 2016

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአፋን ኦሮሞ የቅዳሴ መጽሀፍ አስመረቀች




አዲስ አበባ መጋቢት 102008 (ኤፍ..) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአፋን ኦሮሞ የቅዳሴ መጽሀፍን ዛሬ አስመረቀች። መጽሀፈ ቅዳሴው የቋንቋው ተናጋሪ የሆኑ የክልሉ ተወላጆች በቀላሉ እንዲረዱትና እንዲያስቀድሱ የተዘጋጀ ነው። 10 ዓመት ያህል በፈጀው በዚህ የትርጉም ስራ ላይ የቤተ ክርስቲያኗ ብጹዓን አበው ሊቃነ ጻጻሳትና ሊቃውንት እንድሁም የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ተሳትፈውበታል። 516 ገጾች ያሉት መጽሀፈ ቅዳሴው 14ቱን የቅዳሴ ሂደቶች ያካተተ መሆኑም ተነግሯል።

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልእክት ቤተ ክርስቲያን ሁሉን አቀፍ ሆና በእኩልነት የምታገለግል መሆኑን ገልጸው፥ በቀጣይ በሌሎች ቋንቋዎች ይሀው ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። በምረቃው ላይ የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሃላፊዎችና የክልሉ ተወላጆች ተገኝተዋል።
 


No comments:

Post a Comment