Saturday, January 23, 2016

በ“ኦርጋን” ብንዘምር ምን አለበት?



ከጥንት ጀምሮየምን አለበት?” መዘዙ ብዙ ነው፥የግድ የለሾች መፈክር ነው።እግዚአብሔር መሐሪ ስለሆነ ኃጢአት ብሠራ ምን አለበት?” እንደ ማለት ነው።ንስሐ ከመግባት ይልቅ እግዚአብሔርን መሞገት የፈለገ ሰው፡-“ኰንኖ ኃጥአን ኵሎሙ ኢይደልወከ ምንተ ፥አፍቅሩ ጸላእተ ክሙ እንዘ ትብል አንተ ፤ፈራጅ ዳኛ እግዚአብሔር፡-በጠላቶችህ ኃጥአን ላይ ልትፈርድ አይገ ባህም፥አንተ ጠላቶቻችሁን ውደዱ ብለሃልና፤በማለት እንደተናገረውም ሊሆን ነው።ወይም ሲቆርብ ሲያቆርብ የኖረ በደለኛ ሰው፥ንስሐ ከመግባት ይልቅ፡-“ዘበልዐ ሥጋየ ወዘሰትየ ደምየ፥ ሕይወት ዘለዓለም የሃሉ ምስሌየ፤ብለህ ተናግረህ፥በወንጌል ተጽፎ ይገኛል ቃልህ፤ይኸንን ተላልፈህ ተኰነን ብትለኝ፥አብረን እንወርዳለን እኔ ምንቸገረኝ፤በማለት እንዳፌ ዘው መሆኑ ነው። -አዳምና ሔዋን በምክረ ከይሲ ተነድተው፥በምን አለበት? የዕፀ በለስን ፍሬ መብላታቸው አልጠቀማቸውም። ዘፍ፡፪፥፲፯።

Monday, January 18, 2016

አባትነት እንዲህ ነበረ 3 ፡




አንድ አድርገን ጥር 10 2008 .
የእምነት አባቶቻችን የጌታ ደቀመዛሙርት ህይወታቸው እንዴት አለፈ?
1.ማርቆስ:- እስኪሞት ድረስ በአሌክሳንድርያ ግብፅ ጎዳናዎች በፈረስ ታስሮ እየተጎተተ ህይወቱ አልፋለች
2.ሉቃስ:- በግሪክ ሰቅለውት ህይወቱ አልፋለች
3.ማቲዎስ:-በቆንጨራ ተቆርጦ ሞቷል::
4.ዮሐንስ:-
5.ጴጥሮስ:-ተዘቅዝቆ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞቷል::
6.ቶማስ:- በህንድ በጦር ተወግቶ መስዋእት ሆኗል::
7.ጳውሎስ:-በአሰቃቂ ሁኔታ ተገርፎ አንገቱ ተቆርጦ ህይወቱ አልፏል::
8.ስምዖን:-ግማሽ ለግማሽ ተቆርጦ ነው ተቆርጦ::
9.ማቲያስ:-በድንጋይ ተወግሮና አንገቱ ተቆርጦ::
10.ይሁዳ:- በጦር ተወግቶ::
11.እንድርያስ:-በስቅላት ህይወቱ አልፏል::
12.ያዕቆብ:-በእየሩሳሎም አደባባይ አንገቱ ተቆርጦ የሞተ::
13.በርተለሚዎስ:-በግርፋት ህይወቱ አልፏል::
ሁሉም መልካሙን ገድል ተጋደሉ ክርስቶስን ካዱ ሲባል አይሆንም ብለው አንገታቸውን ለካራ ሰውነታቸውን በዘይት ለመቀቀል ለግርፋት ለስቅላት አሳልፈው ሰጡ

ፕትርክና እንዲህ ነበር 2 !



 አባ ባስልዮስ ዘቂሳርያ እና አባ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ

አንድ አድርገን ጥር 8 2008 .

አባ ባስልዮስ በአፍ በመጣፍ መናፍቃንን ሲቀጠቅጥ የኖረ ቅዱስ አባት ነው። አባ ማትያስ ግን የቤተ ክርስቲያን ደጆቿን ሀራጥቃዎች ይቀጠቅጧት ዘንድ እሺታቸውን እንደገለፁ ሰማን።

አባ ባስልዮስ መናፍቃን ምእመናንን ባሳደዷቸው ጊዜ ምእመናንን አይዟችሁ እያለ ያጽናናቸው ነበር፣ አባ ማትያስ ግን የቤተክርስቲያንን ልጆች የሚያሳድዱ ተሀድሶ መናፍቃንን አይዟችሁ እንዳሏቸው ሰማን።
አባ ባስልዮስ ምእመናን ከተሳደዱባት ቤተ ክርስቲያን ከሀድያን እንዳይገቡባት ቤተ ክርስቲያንን በዘጸሎቱ ዘግቶባቸው ነበር፣ አባ ማትያስ ግን ለሀራጥቃዎች ቤተ ክርስቲያንን ወለል አድርገው እንደከፈቱላቸው ሰማን።

ፕትርክና እንዲህ ነበር 1 !




አንድ አድርገን ጥር 2008 .

ሶስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት
፩ኛ. ሹመታቸው በመንፈስ ቅዱስ ነበር፡፡ ለመጨረሻ ከቀረቡ ሶሰት ዕጩዎች መካከል በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ረጂም ጸሎት ከተደረገ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ይምረጥ ተብሎ በዕጣ ነው የተመረጡት፡፡

፪ኛ. ጵጵስናም ሆነ ፕትርክና ከተሾሙ ጊዜ አንስቶ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው አለባበሳቸው የገዳማውያን አባቶቻችን ልብስ ነበር፡፡ አልፎ አልፎ ለክብረ በዓላት የጵጵስና ልብሳቸውን ይለብሱ ነበር፡፡
 
፫ኛ. ፕትርክና እስከተሾሙበበት ቀን ድረስ የሚጓዙት ባዶ እግራቸውን ነበር፡፡

፬ኛ. በበዓላት ቀን ወደ አብያተ ክርስቲያናቱ የሚሄዱት በግብዣ/በጥሪ ሳይሆን በራሳቸው ፈቃድ ነበር፡፡

፭ኛ. የሚጠበቁት በሰለጠነ ጠባቂ ወታደር(Security Guard) ሳይሆንጠባቂዬ መንፈስ ቅዱስ ነው!” ብለው ከቦታ ቦታ የሚዘዋወሩት እንደ አንድ ምዕመን ነበር፡፡ ከመንበረ ፓትርያርክ ወጥተው በአቅራቢያው ወዳሉት አብያተ ክርስቲያናት የሚጓዙት በእግራቸው ስለነበር መንገድ ላይ ብዙ ምዕመናንን ለረጅም ጊዜ ሳይሰለቹ ቆመው መስቀል እያሳለሙ ይባርኩ ነበር፡፡

፮ኛ. ከቦታ ቦታ የሚዘዋወሩት ሕዝብን እንደሚፈሩ የመንግስት ባለስልጣናት በጥቋቁር ሽፍን መኪኖች ሳይሆን በእግራቸው ነበር፡፡
 
፯ኛ. ዘመናቸውን በሙሉ ልክ እንደ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ሁሉ ፀጥታ ከሠፈነበት ከገዳም ወጥተው ጫጫታ በበዛበት ከተማ መኖራቸው ያስለቅሳቸው ነበር፡፡

፰ኛ. እስካሁን በሕይወት ያሉ ጳጳሳት እንደሚመሰክሩት ሹመት፣ የቤተ ክህነት ሥራ፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪነት ሰው ሲሾሙ ዘር፣ ዝምድና፣ የፖለቲካ ሁኔታ እና ከዚህ ጋር የሚያያዙ ቆሻሻ አስተሳሰቦች ቦታ አልነበራቸውም፡፡

፱ኛ. በቅርብ የሚያውቋቸው ሲናገሩ ቅዱስነታቸው ሌትና ቀን የሚያሳስባቸው ጠባቂ ሆነው ለተሾሙለት ምዕመን ድኅነት፣ የአብያተ ክርስቲያናት፣ የገዳማት እና የአብነት ትምህርት ቤቶች ጉዳይ እንጂ ስለራሳቸው ክብር አልነበረም፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ሆይ የአባቶቻችንን የተቀደሰ ዘመን መልስልን!