Sunday, November 2, 2014

ይድረስ ለፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ

እንደ ቤተክርስቲያን ልጅነታችን ኃላፊነታችንን ለመወጣት ‹‹አንድ አድርገን›› ይህን መልዕክት ለቅዱስነታች እንዲመጥን አድርጋ በወረቀት ፕሪንት በማድረግ በፖስታ ቤት በኩል ለመላክ እየተዘጋጀች ትገኛለች ፡፡ መልዕክቱ ቢደርሳቸውና ቢያነቡት መልካም ነው ፡፡ መልዕክቱ ደርሶ በአማሳኞቻቸው ታፍኖ ቢቀር እኛ ሃላፊነታችንን ተወጥተናል፡፡ (ከ15 ዓመት በፊት አቡነ ማትያስ ከምድረ አሜሪካ ሆነው ለቅዱስ ሲኖዶስና ለፓትርያርኩ(አቡነ ጳውሎስ) የሚልኩት ደብዳቤ አሁን የከበቧቸው ሰዎች  ፓትርያርኩ ጋር እንዳይደርስ በማድረጋቸው ምክንያት በጋዜጦች መልዕክታቸው ታትሞ መበተኑ ይታወሳል፡፡)

 የቀጠለ...........................
 ‹‹ሹመት በአግባቡ ካልሠሩበት ሺህ ሞት ነው›› 
ጀማል ሐሰን አሊ(የአሁኑ ገብረ ሥላሴ
...................
እንግዲህ ብፁዕ ፓትርያርኩ እነዚህን ነውረኞች ሰብስበው ነው ማህበረ ቅዱሳንን ለማፍረስ ሲዶልቱ የከረሙልን፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዋና ዋና የአስተዳደር ቦታዎች በሃይማኖት የለሽ ወንበዴዎች እንዲሞላ በማድረግ፣ ገንዘቧን በመበዝበዝ ቤተ ክርስቲያንን በትክክል ቅኝ እየገዛችኋት ያላቸሁትስ እናንተ ናችሁ እንጂ ሌት ተቀን ደፋ ቀና ብለው በዕውቀታቸው፣ በገንዘባቸውና በጉልበታቸው የሚያገለግሏት ልጆቿ አይደሉም፡፡ የማኅበሩ አባላትስ ባለትዳር እንኳን ሆነው ቤታቸውን ትተው ስለ ቤተክርስያን አገልግሎት ሲሉ በማኅበሩ ሕንፃ ላይ ሰሌን አንጥፈው 3 እና 4 ሰዓት እንቅልፍ እየተኙ ሲነጋም ተነሥተው ወደ ዓለማዊ የመንግሥት ሥራቸው የሚሄዱ መሆናቸውን ነው የምናውቀው፡፡ ማኅበሩም ከሚሰጠው ዘርፈ ብዙ አገልግሎት በተጨማሪ እውነተኛውን የክርስናውን ገጽታ በዓለም ላይ በተግባር እያሳየ ያለ የቅድስት ኢትዮጵያን ማንነትም በዓለም እየሰበከ የሚገኝ፣ የጌታችንንና የሐዋርያትን ትምህርት ሳይበረዝና ሳይከለስ ለትውልዱ ለማስተላለፍ ሌት ተቀን የሚተጋ የቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጇ መሆኑን ነው የምናውቀው፡፡ በተግባርም እያየን ያለነው ይህንኑ ነው፡፡

ብፁዕነትዎ በእርግጥ እርስዎ እስካሁን ያደረጓቸው ማኅበሩን የማፍረስ ሙከራዎችና ወደፊትም የሚያደርጓቸው ሙከራዎች በግልጽ የሚያሳዩን አንድ ግልጽ የሆነ ነገር ነው፡፡ ይኸውም ወደ ፕትርክና መንበር ላመጡዎት ካድሬዎች ታማኝነትዎንና ታዛዥነትዎን በተግባር ለማሳየት እየሞከሩ እንደሆነ ነው የሚገባን፡፡ ብፁዕነትዎ እርስዎ ማኅበሩን ለማፍረስ ደፋ ቀና ባሉባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሀሳብዎን ባለመቀበሉ ‹‹ብቻዬን ነኝ፣ በሥራም አልታገዝኹም›› በማለት በቅዱስ ሲኖዶሱ ላይ ታላቅ ወቀሳ ሲያቀርቡ ዋና ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ‹‹ቅዱስነትዎ አዝዘው ምን ያልተፈጸመ ነገር አለ? ያልተፈጸመ ነገር ካለ ለጉባኤው በይፋ ይገለጽ›› ሲሉ ለጠየቁዎት ጥያቄ ለምን በማስረጃ የተደገፈ ምላሽ አልሰጡም? ብፁዕነትዎ እርስዎ መልካም እስካሰቡ ድረስ ቅዱስ ሲኖዶሱ ከጎንዎ የማይቆምበት ምን ምክንያት አለ? ለምን ከቅዱስ ሲኖዶሱ ተለይተው ብቻዎትን ሆኑ? ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትንስ በኃይል እስከማስፈራራት ድረስ ያደረስዎት ነገር ምንድነው? ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቡነ ማቴዎስ ‹‹ሕገ መንግሥት ለሁሉም እኩል ነው፤ ለእገሌ ሚኒስትር እናገራለሁ፤ ለእገሌ ደኅንነት እደውላለሁ እያሉ አያስፈራሩን›› በማለት በግልጽ እስኪናገሩዎት ድረስ ያደረስዎት ነገር ለምን ማኅበሩ አልፈረሰልኝም ነው? በባለፈው ዓመት 2006 . በሰኔው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ጆቢራዎቹ አማካሪዎችዎ የሆኑት ‹‹የጨለማው ቡድን አባላት›› ድንገት ቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ ዘለው በመግባት ‹‹እኛኮ እስከ አንገታችን ድረስ የታጠቅን ሰዎች ነንእያንዳንዳችሁን እንደፋችኋለን…›› ብለው በብፁዓን አባቶቻችን ላይ ፎክረውባቸው እንደወጡ አንድ ሊቀ ጳጳስ አባት በአካል ነግረውኛል፡፡ ብፁዕነትዎ አባ ማትያስ ሆይ እውነቱን ልንገርዎት የመንግሥት ካድሬዎች በትእዛዝ መልክ የሰጡዎት ይህ ማኅበሩን የማፍረስ ሀሳብዎት መቼም አይሳካልዎትም! ምክንያቱም አንደኛ ከእግዚአብሔር ጋር ታግሎ ያሸነፈ ማንም ስለሌለና እግዚአብሔር ከማኅበሩ ጋር፣ ማኅበሩም ከእግዚአብሔር ጋር ስለሆነ ማኅበሩ እንደተቋምነቱ መቼም ሊፈርስ አይችልም፡፡ ሁለተኛውና ዋናው ነጥብ አንድ ወዳጄ እንዳለው ማኅበሩ በአሁኑ ሰዓት ተቋም ብቻ ሳይሆን ውሳጣዊ አስተሳሰብ ጭምር ነው፡፡ ‹‹ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰማይ ያለ አገልግሎት በምድርም የሚከናወንባት ስለሆነች አስተምህሮቷና የአምልኮ ሥርዓቷ ሳይበረዝና ሳይከለስ ለቀጣዩ ትውልድ መተላለፍ አለባት፣ ይህችንም ቤተ ክርስቲያን በዕውቀቴ በጉልበቴ በገንዘቤ አገለግላለሁ›› ብሎ በፍጹም ቆራጥነት የተነሣ ትውልድ ሁሉ ማኅበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ምናልባት ተቋሙን (ሕንፃውን) ማጥፋት ይቻል ይሆናል ይህንን አስተሳሰብ ግን በፍጹም ማጥፋት አይቻልም፡፡ እንዲያውም እንቅስቃሴውን የበለጠ ያጠናክረዋል፡፡ ሊሆን የሚችል ነገር ባይሆንም እንዳው እንበልና ብፁዕነትዎ ካድሬዎቹና እርስዎ በዙሪያዎ የሚያንዣብቡ ጆቢራዎቹም አማካሪዎችዎ በአንድ ላይ እንዳሰባችሁት ማኅበሩን በተቋምነቱ ብቻ ብታፈርሱት በቤተ ክርስያቲያናችና በሀገራችን ላይ እጅግ ከፍተኛ ጉዳት ነው የሚደርሰው፡፡ ከሚደርሱት ጉዳቶችም ውስጥ የተወሰኑትን ብቻ እየጠቀስኩ ለማሳየት እሞክራለሁ፡-
1. ማኅበረ ቅዱሳን ‹‹አብነት /ቤቶች የቤተ ክርስቲያኒቱም ሆነ የሀገሪቱ የዕውቀት ማዕከል ናቸው›› የሚል ጽኑ አቋም ስላለው ሊቃውንቱ መምህራን ከችግርና ከተረጅነት እንዲወጡ የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ማኅበሩ እስካሁን ድረስ እኔ የማውቃቸው እያንዳንዳቸው በሚሊዮኖችና በሺዎች ሚቆጠሩ ብሮች ወጪ የተደረገባቸው 180 በላይ ፕሮጀክቶችን በማጥናትና በመተግበር በኢትዮጵያ በአራቱም ማዕዘን በሚገኙ በተለያዩ ገዳማትና አብነት /ቤቶች ላይ ተግባራዊ አድጓል፡፡ በዚህም ገዳማቱ ከልመና ወጥተው ራሳቸውን እንዲችሉ አድርጓል፡፡ ብፁዕነትዎ እርስዎና ጆቢራዎቹ ግብረ አበሮችዎ ማኅበሩን በተቋምቱ ብታፈርሱት ወደፊት ገና ብዙ የሚሠራባቸው እንደነዚህ ያሉ ገዳማት ለከፍተኛ ችግር እንደተዳረጉ ይቀራሉ፤ መነኮሳቱም ይበተናሉ፡፡
2. ለአብነት ተማሪዎቹ አዳሪ /ቤት በመሥራት ለመምህራኑም ሆነ ለተማሪዎቹ ደመወዝ እየከፈለ በማስተማር ማኅበሩ ለነገው የሁለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን ዕድገት የበኩል አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል፡፡ ብፁዕነትዎ እርስዎና ጆቢራዎቹ ግብረ አበሮችዎ ማኅበሩን በተቋምቱ ብታፈርሱት እነዚህ ማኅበሩ ደመወዝ እየከፈላቸው የሚያስተምራቸው የአብነት ተማሪዎች ይበተናሉ፡፡ መምህራኑም ወንበራቸውን አጥፈው ጉዳኤያቸውን ይበትናሉ፤ በዚህም የነገ የቤተ ክርስቲያን ተተኪ ትውልድ አይኖረንም ማለት ነው፡፡ በወር 300 ብር ደመወዝ (ይህችውም ደመወዝ ተብላ) የሚከፍላቸው እያጡ ሊቃውንቱ ወንበራቸውን እያጠፉ ጉባኤያቸውን እየበተኑ ባለበት በዚህ ወቅት ቤተ ክህነቱ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ሊሠራ ፈቃደኛ እንዳልሆነ እናንተው ጠንቅቃችሁ ታውቁታላችሁ፡፡ በጣም የሚገርመው 2005 . ብቻ ጠቅላይ ቤተክህነቱ 50 የሀገረ ስብከቶች ጠቅላላ ካገኘው ገቢ ከዓሥር ሚሊዮን ብር ላይ አንዷን ፐርሰንት (አንድ በመቶ) እንኳን ለአብነት መምህራት ደመወዝ አለመክፈሉ ነው፡፡
3. ማኅበረ ቅዱሳን በሀገራችን ባሉ 32 በላይ በሚሆኑት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚማሩ ኦርቶዶክስ ተማሪዎችን በማሰባሰብ ከዓለማዊው ትምህርታቸው ጎን ለጎን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እንዲማሩና ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ትውልድ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ በግል ኮሌጆችም እንዲሁ፡፡ ማኅበሩ 1985 . ጀምሮ ካሪኩለም በመቅረጽና የመማሪያ መጻሕፍት በማዘጋጀት ወጣቱን የተማረውን ትውልድ በዕውቀቱ በጉልበቱ በገንዘቡ ቤተ ክርስያቲንን እንዲያገለግል ከማድረጉም በላይ ታሪኩን፣ ባሕሉን፣ ማንነቱን ጠንቅቆ የሚያውቅ ቤተ ክርስቲያኑንና ሀገሩን የሚወድ ትውልድ ፈጥሯል፡፡ ለዚህም በዓለም ተበትነው የሚገኙ የተዋሕዶ ልጆች በቂ ምስክር ናቸው፡፡ ብፁዕነትዎ እርስዎና ጆቢራዎቹ ግብረ አበሮችዎ ማኅበሩን በተቋምቱ ብታፈርሱት ከየዩኒቨርሲቲውና ከየኮሌጆቹ ተመርቀው የሚወጡት እነዚህ በሚሊዮን የሚቆጠሩት ኦርቶዶክሳዊ ተማሪዎች እንደሌሎቹ ሃይማኖት የለሽ ተማሪዎች ሆነው በተለያዩ ሱሶችም ጭምር አብረው የሚመረቁ ይሆናሉ፣ ሃይማኖታቸውን ክደው በመውጣት ወላጆቻቸውንም ያስክዳሉ፡፡ ማንነቱን፣ ሃይማኖቱን፣ ባሕሉን…. የማያውቅና የማይወድ ግድ የሌለው ዝርው ትውልድ ይፈጠራል፡፡ ይህ ደግሞ የካድሬዎቹም ዋነኛ ዓላማ ነው፡፡ በዩኒቨርሲቲዎቹ መግቢያና መውጫ በሮች ላይ እንደ አሸን የፈሉ የሺሻና የዝሙት ቤቶች በተዘዋዋሪ መንገድ እንዲስፋፉ ማድረጋቸውም ለዚሁ ነው፡፡
4. የቤተ ክርስቲያንን የውስጥና የውጭ ጠላቶች የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በመበረዝና ስልታቸውን እየቀያየሩ ኑፋቄያቸውን የሚያሰራጩትን መናፍቃን ማኅበረ ቅዱሳን እነርሱ በፈለጉት መጠን አላንቀሳቅስ እንዳላቸው ራሳቸው መናፍቃኑ ባወጧቸው መጽሔቶቻቸው ላይ መስክረዋል፡፡ አሕዛብም እንዲሁ፡፡ ብፁዕነትዎ እርስዎና ጆቢራዎቹ ግብረ አበሮችዎ ማኅበሩን በተቋምቱ ብታፈርሱት እነዚህ የውስጥና የውጭ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ሕዝበ ክርስያኑን ከነቤተ መቅደሱ ለመረከብ ዝግጁ ሆነው እየጠበቁ ስለሆነ ቅድስት ቤተ ክርስያንን የመናፍቃን መናኸሪያ ያደርጓታል፡፡ ብፁዕነትዎ እርስዎ በባለፈው በጥቅምት 5 ሪፖርትዎ ላይ የኦርቶዶክስ ምእመናን ቁጥር ‹‹በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን›› ሪፖርት ከማድረግ ውጭ ቤተ ክህነቱ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም የሠራው ነገር እንደሌለ ያውቁታል፡፡ እንዳውም ቤተ ክህነቱ ራሳቸውን መናፍቃኑን በመዋቅሩ ውስጥ አስገብቶ ከፍተኛ ኃላፊትም ጭምር በመስጠት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሸክም አበዛባት እንጂ እርስዎም ሆኑ ቤተ ክህነቱ ሕዝበ ክርስቲያኑ ከመናፍቃ ቅሰጣ ለመታደግ ምንም የሠራችሁት ሥራ እንደሌለ እናውቀዋለንኮ፡፡ ጭራሽ ይባስ ብላችሁ ቅዱስ ሲኖዶሱም በሚቀርቡለት ማስረጃዎች መሠረት መናፍቃኑ ተምረው መመለስ ካልቻሉ ከቤተ ክርስቲያን ተወግዘው እንዲለዩ እንዳያደርግ ተፅዕኖ ስትፈጥሩበት ኖራችኋል፡፡ የመናፍቃኑንንም መረጃዎች ከሊቃውንት ጉባኤ ቢሮ ውስጥ ተሰርቀው እንዲወጡ በማድረግ ጉዳያቸው እንዳይታይና ውሳኔ እንዳይሰጥበት ስታደርጉ ለመኖራችሁ ራሳቸው የሊቃውንት ጉባኤ አባላት አባቶች ምስክሮች ናቸው፡፡
ይህን ዓይነት አገልግሎት የሚሰጥ የቤተ ክርስያን አካል የሆነን ማኅበር እርስዎ በሰበሰቧቸው ሕገ ወጥ ስብሰባዎች ላይ ‹‹ከአልሸባብ የተለየ አላደረገም›› ተብሎ ሲወራ ብፁዕነትዎ እንዲያው ትንሽ እንኳን አባትነት አልተሰማዎትም? እንኳን ሰው ሰይጣንምኮ ይታዘባል! እንዲህ ዓይነቱን ስብሰባ በቤተ ክርስቲያንና በልጆቿ ላይ ለማካሄድ እንዴት ፈቃደኛ ሆኑ? ሌላው ይቅር እንዲያው የቤተ ክርስቲያን ልጆች ከአልሸባብ ጋር ከሚያመሳስሉ ሰዎች ጋር ሲዶልቱ መዋልን እንዴት ኅሊናዎ ቻለው? ብፁዕነትዎ ለዚህ አእምሮዎ አንክሮ ይባል በእውነት! አልሸባብ ማለትኮ ‹‹ክርስቲያኖችን ባገኛችሁባቸው ስፍራ ሁሉ ግደሉዋቸው፣ ያዙዋቸውም፣ ክበቡዋቸውም፣ እነርሱንም ለመጠባበቅ በየመንገዱ ተቀመጡ›› (ቁርአን ሱረቱ አል-በቀራህ 2191 እና ሱረቱ አል-ተውባህ 95) ‹‹ኢስላም ያልሆኑት ሰዎች ቅጣት መገደል ወይም መሰቀል ወይም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በማፈራረቅ መቆረጥ ወይም ከሀገር መባረር ነው›› (ቁርአን ሱረቱ አል-ማኢዳህ 533) የሚሉ የሃይማኖት መመሪያ ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ነቢያቸውና አባታቸው መሐመድም በሐዲሱ ላይ ስለራሱ ሲናገር ‹‹እኔ ድል አድራጊ የሆንኩት በሽብር ነው›› “Allah’s Apostle said, ‘I have been made victorious with terror.’” (Sahih Bukhari: 452220) በማለት በግልጽ እንደተናገረው ‹‹ዓለም በሙሉ እስኪሰልም ድረስ ጂሃድ አውጃችሁ ተዋጉ›› የሚል መመሪያ ያለው ነው፡፡ በዚህም መሠረት ዛሬ እነ አልሸባብ ቢችሉና ቢመቻቸው ሰይፋቸውን መዘው ዓለምን በአንዲት ጀምበር ቢያሰልሙ ደስ ይላቸዋል፡፡ ለዚህም ነው እነዚያን በየሚዲያው የምናያቸውንና የምንሰማቸውን የሚዘገንኑ አደጋዎች በማድረስ የሺዎችን ሕይወት እየቀጠፉ ያሉት፡፡ እነዚያን አሠቃቂዎቹን አደጋዎች በማድረስ የብዙዎችን የንጹሐን ሕይወት ከቀጠፉ በኋላ ያሰሙት የነበረው ፉከራም ጂሃድ ዓላማቸውን የሚያሳኩበት ዋነኛ መንገዳቸው መሆኑን ነው፡፡ "Allah is our objective, the Quran is our Constitution, the Prophet is our leader, and Jihad is our way."
የማኅበሩ ልጆች ግን መመሪያዎቻቸው ገዳማትና አብነት /ቤቶች አይዘጉ፣ የቤተክርስቲያን አምልኮቷና ሥርዓቷ አይበረዝ፣ ስብከተ ወንጌል ይስፋፋ የሚሉት ናቸው፡፡ አባታቸው መድኃኔዓለምም ‹‹ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ የሚረግሟችሁን መርቁ›› (ማቴ 544) የሚል መመሪያ ያለው ነው፡፡ ምንም እንኳን በጠላትነት ብትነሱበትም ማኅበሩን በቦምብና አንገትን በመሰየፍ ዓለምን ሊያጠፋ ከተነሳ አሸባሪ ከአልሸባብ ጋራ መመደብ ጤነኛ አስተሳሰብ ነው ብዬ አላምንም፡፡ ብፁዕነትዎ ሁለቱ አካላት (ማኅበረ ቅዱሳንና አልሸባብ) በአንድ አፍ ሲጠሩ ዝም የሚል አንደበት ከወዴት ተገኘ በእውነት? ምነው ‹‹እንግዲህ በጎ ለማድረግ ዐውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው›› ይል የለ እንዴ መጽሐፉ! ያዕ 417፡፡
ብፁዕነትዎ እርስዎ እነዚያን ሕገ ወጥ ስብሰባዎች አድርገው ማኅበሩን በአሸባሪነት አስፈርጀው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትንም በአጸያፊ ቃላት እንዲሰደቡ በኋላ በተካሄደው 33ኛው አጠቃላይ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ላይ ከየአህጉረ ስብከቱ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚደግፍ ሪፖርት ነው የቀረበልዎት፡፡ በዚህም እርስዎ ንዴትዎን መቋቋም አቅቶዎት ታይተዋል፡፡ ሪፖርቱና የእርስዎም ሁኔታ እራስዎትን ከትዝብትና ከግምት ውስጥ እንዲገቡ አደረገዎት፡፡ በሀገራችን 4ቱም አቅጣጫ ያሉት አህጉረ ስብከቶችኮ ማኅበሩ በያሉበት የሠራውንና እየሠራ ያለውን ነገር በተግባር የሚያዩ ናቸው እንጂ በስማ በለው የሚንቀሳቀሱ ስላልሆኑ እውነቱንም ስለሚያውቁት ነው ሁሉም አህጉረ ስብከቶች በየሪፖርታቸው ላይ ስለማኅበሩ የመሰከሩት፡፡ አሁንም በጥቅምት 18 ቀን 2007 . በቀትር በኋላ በቅዱስ ሲኖዶስ የስብሰባ ውሎአችሁም እርስዎና ብዙዎቹ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ወደለየለት የከረረ ንግግር አምርታችሁ እንደነበር ስብሰባውም በድንገት እንደተቋረጠ ተነግሮናል፡፡ በዚህም ወቅት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ‹‹በቤታችን ውስጥ አክራሪና አሸባሪ የሚባል አንድም አካል የለንም›› ‹‹ዓላማዎ ማኅበሩን መዝጋት ነው፣ ማኅበሩ በሕጉ ይሔዳል እንጂ አይዘጋም›› ‹‹ሲኖዶሱን መስለው ከሲኖዶሱ ተግባብተው ይሒዱ፣ የያዙት አካሔድ ትክክል አይደለም›› እያሉ ነው ሲሞግቱዎት የነበሩት፡፡ እርስዎም በዚህ አቋምዎ ከቀጠሉ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ከእርስዎ ጋር እስከመወጋገዝ እንደሚደርሱ እስኪያስጠነቅቁዎት ድረስ ከቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት አባቶቻችን አተካራ ውስጥ ገብተው ከርመዋል፡፡ ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ፊቅጦር የንጉሡ የዲዮቅልጥያኖስ ባለሟል የነበረ ቢሆንም ንጉሡ ጌታችንን በካደ ሰዓት ቅዱስ ፊቅጦር ዲዮቅልጥያኖስን ‹‹ንጉሥ ሆይ ክርስቶስን በምታፈቅረው ጊዜ አፈቀርኩህ ወደ አንተም መጥቼ ሳገለግልህ ኖርኩ፤ ክርስቶስን በጠላኸው ጊዜ ግን እኔም ጠላሁህ፣ ቤትህንም ጠላሁ›› ነው ያለው፡፡ ብፁዕነትዎ ዛሬምኮ ቅዱስ ሲኖዶሱን የሚቃረን ልዕልናውንም የሚጻረር አባት፣ ቤተ ክርስቲያንንም በተዘዋዋሪ መንገድ የሚጎዳ አባት ወይም ንጉሥ ከመጣ ይህንን አሜን ብሎ የሚቀበል የቤተ ክርስያን ልጅ የለም፡፡
ካድሬዎቹ በትግል ላይ ሳሉ ገና ከመሻው ይህችን ‹‹እንቅፋት›› የሆነችባቸውን ቤተ ክርስቲያንን የማፍረስ ዕቅድ የነበራቸው መሆኑን የህወሓትን ድርጅት ከመሠረቱትና ታጋይ ከነበሩት ውስጥ አንዱ / አረጋዊ በርሄ ከበቂ በላይ የሆነ ምስክርነታቸውን ሰጥተውናል፡፡ እኚሁ የቀድሞው የህወሓት መሥራች ለዶክትሬት ድግሪ ማሟያቸው “A Political History of TPLF; Revolt, Ideology and Mobilization in Ethiopia” በሚል ርእስ በጻፉት ጥናታዊ ጽሑፋቸው ላይ እውነታውን ፍንትው አድርገው ገልጸውታል፡፡የቀድሞው ሚኒስቴር አሁኑ ፓስተር ታምራት ላይኔ ከሀገር ከወጡ በኋላ እንደተናገሩት በሀገር ውጭና በሀገር ውስጥ ያለውም ምእመን በሁለት ሲኖዶስ እንዲመራ ያደረጉት እነርሱ (ካድሬዎቹ) መሆናቸውን በግልጽ ተናግረዋል፡፡ ይህንንም ያደረጉት ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስን ከመንበራቸው በማንሣት ድርጅቱን (ሕውሓትን) ከትጥቅ ትግል ጀምሮ ከውጭ አገር ገንዘብ በመሰብሰብ ሲያግዙ የቆዩትን ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ በመተካት መሆኑን የቀድሞው ሚኒስትር አምነው ከተናገሩ በኋላ ‹‹ሁለቱ ሲኖዶሶች አሁን ቢታረቁልኝ ደስ ይለኛል›› እያሉ በለበጣ ያሾፉብን ከድርጅቱም ሆነ ከሀገር ወጥተው ‹‹ጌታን አግኝቼዋለሁ›› ብለው በግልጽ ፕሮቴስታንት መሆናቸውን ከወጁ በኋላ ነው፡፡ በጣም የሚገርመው መንግሥት የቤተ ክርስያኒቱንም ሆነ የማኅበሩን እንቅስቃሴ የማቀጨጭ ዓላማ እንዳለው የቀድሞዎቹ የመንግሥት አካላት መሪዎች በዚህ መልኩ ምስክርነታቸውን የሰጡን መሆናቸው ነው፡፡
የቀድሞው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዴኤታ የበሩት አቶ ኤርሚያ ለገሠም ሀገር ለቀው ከወጡ በኋላ ባሳተሙት ‹‹የመለስ ትሩፋቶች›› በሚለው መጽሐፋቸው ላይ የጠቀሱትን በጣም ብዙ ነገር አለ፡፡ 
ገዥው መንግሥት በአሁኑ ሰዓት በብዙ መልኩ እየለፋባቸው ካሉት ነገሮች ውስጥ አንዱ የኢትዮጵያን ታሪክ ዳግም የመጻፍ አካሄድ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክ የመቶ ዓመት ታሪክ ብቻ እንደሆነ አድርጎ በመጻፍና በማስተማር አዲሱን ትውልድ የቀድሞዋን ኢትዮጵያን ሳይሆን ‹‹አዲሲቷን›› የመቶ ዓመት ታሪክ ያላትን ኢትዮጵያን በማስተዋወቅ ላይ ለመሆኑ ኢቲቪ በቂ ምስክር ስለሆነ ምናልባትም የተጻፉ የመንግሥት የፕሮፓጋንዳ ሰነዶችን መመልከት ላያስፈልግ ይችላል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ማኅበረ ቅዱሳን ከመቶ ሺህ በላይ የሚሆኑ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን በአንድ ዓመት በሚያስመርቅበት የግቢ ጉባኤ ትምህርቱ ላይ የኢትዮጵያና የቤተ ክርስቲያኗ ታሪክ የመቶ ዓመት ሳይሆን የሦስት ሺህ ዓመታት ታሪክ እንደሆነ በደንብ በመረጃ አስደግፎ ያስተምራል፡፡፡ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚአብሔርም እንደሆነች መጽሐፍ ቅዱስን እየጠቀሰ በደንብ ያስተምራል፡፡ በዚህም ማኅበሩና ገዢው መንግሥት ተቃራኒ ገጽታ እንዲኖራቸው ግድ ሆኗል፡፡ ታሪኩን፣ ማንነቱንና ባሕሉን ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ በሃይማኖት የጎለመሰ፣ በምግባር የታነጸ፣ ለቤተ ክርስቲያኑና ለሀገሩ ቀናኢ የሆነ የነቃ ትውልድ ማኅበሩ በመፍጠሩ በካድሬዎች ጥርስ ውስጥ እንዲገባ አድርጐታል፡፡ የመንግሥትን ውስጠ ምሥጢር የሚያውቁ ዓለማዊ ጋዜጠኞች ከዛሬ 5 እና 4 ዓመት በፊት ቀጣዩ የኢሕአዴግ ዋነኛ ዒላማ ማኅበረ ቅዱሳን እንደሆነ ሲነግሩንኮ በወቅቱ የጋዜጠኞቹን ሀሳብ ልብ አላልነውም ነበር፡፡ የመንግሥት ሰላዮች የሆኑ ነገር ግን በየአድባራቱ የሚሾሙ ካድሬ አባቶች፣ የመመሪያዎች ቦታዎችን ከሕጋዊና ፍትሐዊ አሠራር ውጭ ለዓመታት በሓላፊነት የተቆጣጠሩና በስብከተ ወንጌል ስም የሚቀመጡ ግለሰቦች እነዚህ ሁሉ በጋራ ቤተ ክርስቲያንን የፖሊቲካ አውድማ ከማድረጋቸው በተጨማሪ ለተሃድሶ ምንፍቅና መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረግ ቤተ ክርስያንን በእጅጉ እየጎዷት ካሉ ሰዎች ጋር መወገን በራሱ በማኅበሩ እያስታከኩ የቤተ ክርስያንን ጥፋት ማፋጠን ነው፡፡ 

እንደነ ዐፄ ካሌብ ያሉት ደጋጎች ነገሥታት የወርቅ ዘውዳቸውን ከጌታችን መካነ መቃብር አስቀምጡልኝ ብለው ወደ ኢየሩሳሌም በመላክ ልብሰ መንግሥታቸውን አውልቀው ዓለምን ንቀው አንዲት የውኃ መንቀልና አንዲት ምንጣፍ ብቻ ይዘው መንኩሰው ከቶ ዓለምን በዐይናቸው እንዳያዩ በመማል ዋሻ ገብተው በመዝጋት በጾም በጸሎት ተወስነው ነው የኖሩት፡፡ ብፁዕነትዎ እርስዎ ግን ኢየሩሳሌምን ጥለው መጥተው ለምድራዊ ሹመትና ግዛት ብለው ‹‹አሸባሪዎች›› ላይ የሚነጣጠረውን ጥይት በቤተ ክርስያንና በልጆቿ ራስ ላይ እንዲነጣጠር እያደረጉ ነው፡፡ ማኅበሩ በአሁኑ ሰዓት በጥቂቱ 5 ያላነሱ መደበኛ ጠላቶች እንዳሉት ይታወቃል፡፡ የገዥው መንግሥት ካድሬዎች፣ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን የሆኑ አክራሪ ሙስሊሞች፣ ፕሮቴስታንቶች፣ ተሃድሶዎች፣ የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጠላቶች እነዚህ ሁሉ ዘመቻቸው በማኅበሩ ላይ ነው፡፡ ለምን እነዚህ ሁሉ አካላት በማኅበሩ ላይ በጠላትነት ተነሡበት? የሚለውን ጥያቄ በትክክል መመለስ የቻለ ሰው የማኅበሩን ማንነት ጠንቅቆ ዐውቆ ከማኅበሩም ጎን ቆሞ ስለ ቤተ ክርስያን ህልውና ሲል የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግ አለበት ብዬ አምናለሁ፡፡
 
ለከፋፍለህ ግዛው ፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለማቸው የማትመቻቸውና የቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ ዕድገት የማይፈልጉት የመንግሥት ካደሬዎች አባ ማትያስ እርስዎን አንደበት አድርገው በመጠቀም በጋራ መክራችሁ የቤተ ክርስያኒቱን የጀርባ አጥንት የሆነውን ማኅበር ካፈረሳችሁ በኋላ ለካድሬዎቹ ‹‹እንቅፋት›› የሆነችባቸው ቤተ ክርስቲያንን የቅርጫ ሥጋ ልታደርጓት እየተዘጋጃችሁ ስለመሆኑ ሁሉም ገብቶታል፡፡ ዕዳው ገብስ ሆኖበት ነው እንጂ የእናንተን ሥውር ዓላማ አብዛኛው ሕዝበ ክርስቲያን ይልቁንም ለቤተ ክርስቲያን ቅርብ የሆነው አማኝ ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡ ስለዚህ ብፁዕነትዎ በዚህ በምታደርጉት ሥውር የክፋት ድርጊታችሁ ምክንያት አማኙ ሕዝበ ክርስቲያን አባትነታችሁን አክ እትፍ ብሎ አንቅሮ ከመትፋት ውጭ ሌላ የሚያስገኝላችሁ አንዳች ፋይዳ የለም፡፡ ምናልባት የምድር ዋጋችሁ የካድሬዎች ጭብጨባና ሙገሳ ሊሆን ይችላል፤ የሆድ ሙላትና የደረት ቅላት፣ የፊት ማማርና አባት መስሎ መታየትን በትርፍነት ሊያስገኝላችሁ ይችላል፡፡ ይህም በምድር የምታገኙት ትርፋችሁ ይሁን እንጂ የሰማዩን ዋጋችሁን ደግሞ መድኃኔዓለም ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ ሊቀ ሐዋርያት ለሆነው ለቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ግልገሎቼን አሰማራጠቦቶቼን ጠብቅበጎቼን አሰማራ›› (ዮሐ 2115-17) ብሎ መንጋዎቹን አደራ የሰጠው እውነተኛው እረኛ መድኃኔዓለም ግን የራሱ የክርስቶስ እንደራሴዎች አድርጎ የሾማቸውን እረኞች በቅዱስ ጴጥሮስ በኩል የሰጠውን አደራ መልሶ መጠየቁ አይቀርም፡፡ ‹‹በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ›› (ሐዋ 2028) ብሎ መመሪያ የሰጣችሁ አምላክ ለቃሉ የታመነ ነው፡፡ ‹‹ለራሳችሁ ተጠንቀቁ›› የሚለው ይሰመርልኝ! ‹‹ተጠንቀቁ›› ማለት ማስጠንቀቂያ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ማስጠንቀቂያ ደግሞ ከቅጣት በፊት የሚነገር የንስሓ መልእክት መሆኑን አንደኛ ክፍል የገባ ተማሪም ቢሆን ያውቀዋል፡፡ ‹‹የሚያልፈውንና የሚጠፋውን ፈልገን ብንደክም የማያልፈውንና የማይለወጠውን ብንተው ልብ እንደሌላቸው እንስሳት እንሆናለን፡፡ የዓለምም ፍቅር ነፍስን ታጠፋለች፡፡›› የሚል ድንቅ ምክር በገድለ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡


ማጠቃለያ፡-

 እኔ በግሌ የማኅበሩ አባላት በሥራቸው ሁልጊዜ የማይሳሳቱ ናቸው ብዬ አላስብም፡፡ ለሚሠራ ሰው መሳሳት ግብሩ ነው፡፡ ፍጹም የሆነውና ከስሕተት የጸዳው አገልግልት የመላእክት አገልግሎት ብቻ ነው፡፡ ማኅበሩ እንደተቋምነቱ ሳይሆን የማኅበሩ አባላት በተናጠል በሥራ ሂደት ላይ የሠሯቸው ስሕተቶቸ እንኳን ቢኖሩ ስሕተቶቹን ነቅሶ በማውጣት መምከር፣ ማስተማር፣ መመሪያ መስጠት፣ ስሕተትን ማረም፣ መገሠጽይህ አባትነት ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ግን የክርስቶስ እንደራሴ የሆነ እረኛ አባት መንጋዎቹን ለአውሬ አሳልፎ ቢሰጥ ምናልባት በጎቹ በአውሬ ላይበሉ ይችላሉ ነገር ግን ድርጊቱ ራሱ እረኛው ቸር ጠባቂ አለመሆኑን ነው የሚያሳብቅበት፡፡ ብፁዕነትዎ አባ ማትያስ ሆይ በአሁኑ ሰዓት እየተካሄደ ባለው በዚህ በጥቅምቱ ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባም ላይ ቢሆን እርስዎ ከቅዱስ ሲኖዶሱ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እሰጥ አገባ ውስጥ እንዳሉ እየሰማን ነው፡፡ እኔም በአካል የማገኛቸው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ይህንኑ ነግረውኛል፡፡ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስለ እርስዎ ብዙ ፍራቻዎች አሏቸው፡፡ እያዘኑልዎትም ነው፡፡ እኔም ይህን መልእክት ልጽፍ የቻልኩበት ዋነኛ ምክንያት እርስዎ ቅድስት ቤተ ክርስያንን ሊጎዳ የሚችል አገደኛ የሆኑ ሥውር ሥራዎችን በመሥራት ምድራዊውን መንግሥት ለማገልገልና ዓላውን ለማስፈጸም ደፋ ቀና ሲሉ ድንገት የነፍስ ኪሳራ እንዳይገጥምዎት ስለፈራሁ ነው፡፡ እባክዎትን እየተጓዙበት ያለውን መንገድ በንስሓ ይመለሱበት! ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ተቃራኒ ሆነው እስክምን ድረስ ሊጓዙ እንደሚችሉ የሚያውቁት እርስዎ ነዎት፡፡ ትናንት አሕዛብ የነበርን ዛሬ ግን በቤቱ ያለን እኛም እየታዘብንዎት ‹‹አሕዛብ ሸሆች ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ለጠላት አሳልፈው አይሰጡም የኦርቶዶክስ እምነት አባት የሆኑት ፓትርያርክ ግን ልጆቻቸውንአሸባሪእያሉ ለጠላት አሳልፈው እየሰጡ ነው›› እያልን አንማዎት! የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና በመጻረርና ቤተ ክርስቲያንን በእጅጉ የሚጎዳ ሥውር ሥራ በመሥራት የክርስቶስን አካል አያድሙ! አይሁድስ መድኃኔዓለምን አንድ ጊዜ ሰቅለውታል፣ መድኃኔዓለም ክርስቶስ እንደራሴ አድርጎ የሾማችሁ እናንተ ‹‹አባቶቻችን›› ግን በሹመት ዘመናችሁ እየሰቀላችሁት አትኑሩ! ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ተቃራኒ ሆኖ በርዕሰ መንበርነት መቀመጥ በራሱ አደጋ ነው፡ በቤተ ክርስቲያን ላይ ሊመጣ ላለው ጥፋት በመንገድ ጠራጊነት ማገልገል ይሄ ከንቱነት ነው በእውነት! ቅዱስ ቃሉ ‹‹የጥፋት ርኩሰት በማይገባው ሥፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢ ያስተውል›› ነው የሚለው፡፡ ማቴ 2415 የቅዱሳን አባቶችንና የቅዱሳት እናቶቻችን ጸሎት በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በቅድስት ኢትዮጵያ ላይ የሚገኘውን የዲዮቅልጥያኖስን ሰይጣን ኃይሉን ቀጥቅጦ ይጣልልን! የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንንና ሀገራችንን ይጠብቅልን! አሜን፡፡

17 comments:

  1. Dear brother ገብረ ሥላሴ,

    Thank you very mach for your wonderful insite. May the Holly Trinity be always with you, may God protect you from evels. May the prayer of our inocent fathers and mothers be with you.
    You have advised, taught and corrected the mistaken fathers. You did your part. Please be vigilant.

    Dear readrs, please let us pray for our Orthodox Tewahedo Church and as well let us pray for and tribute our brother ገብረ ሥላሴ for his brave works of the past couple of years and in particular of his work posted above.

    Cher Yaseman.

    Your brother in Christ

    ReplyDelete
  2. egezabher ybarkh!!ewnaten mmasker krestanawe gedat now berta tre mesekernatna abable new ytnagerkaw dengle maream yasrat lege mone yenew tekmw yeanew ewmeton yanagral leb yestatchw nesea yegbou alblezey ymmataw ketat kalla aydelame ab mathyas!!

    ReplyDelete
  3. God Bless Ethiopia and it's people !

    ReplyDelete
  4. ‹‹የጥፋት ርኩሰት በማይገባው ሥፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢ ያስተውል›› ነው የሚለው፡፡ ማቴ 24፡15

    ReplyDelete
  5. የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና በመጻረርና ቤተ ክርስቲያንን በእጅጉ የሚጎዳ ሥውር ሥራ በመሥራት የክርስቶስን አካል አያድሙ!

    ReplyDelete
  6. God bless You /..my brother
    ‹‹በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ›› (ሐዋ 20፡28)

    ReplyDelete
  7. ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ተቃራኒ ሆኖ በርዕሰ መንበርነት መቀመጥ በራሱ አደጋ ነው፡፡

    ReplyDelete
  8. ክርስትናውን ንቆ አቃሎ አለምን መስሎ የሚኖር ሰው በኩርነቱን ለሆዱ ጊዜያዊ ፍላጎት በሸጠው በያዕቆብ ወንድም በኤሳው ተመስሏል፡፡ አባታችን የእረኝነት ኃላፊነትዎን ዘነጉ፥ የቤተ ክርስቲያንን ልጆች ለጠላት አሳልፈው ሰጡ፥ "ለኃጢአተኛ የፍጻሜ ተስፋ የለውምና፥ የኅጥኣንም መብራት ይጠፋልና። ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ከዓመፀኞችም ጋር አትደባለቅ።" የሚለዉን ቅዱሱን ቃል ያዘነጋዎ ምድራዊ ስልጣን ወይስ ፍቅረ ንዋይ መልሱን ለእርስዎ ትቻለሁ። አይርሱ ይህች ትውልድ እግዚአብሔርን የምትፈልግ ናት፥ የያዕቆብን አምላክ ፊት የምትፈልግ።" (መዝ26:6)

    ReplyDelete
  9. God be with you all the time

    ReplyDelete
  10. Andadrigen, Please send this article to all papasat. They may get a chance to give it to the Patriarch.
    Sam

    ReplyDelete
  11. ይህ እኮ የፕሮቴስታንት መር የሆነው የወያኔ/ህወኃት መንግስት ድርጊት ነው፡፡
    ለመሆኑ የፌዴራል ጊዳይ ተብየው ሚንስተር ሽፈራው ተ/ማርያም የ24 ሰዓት ሥራና ሴራ ምን እንደሆነ አታውቁምን
    ለመሆኑ ለአባ ማትያስ ዘ ወያኔ ተዋት ማታ ትዕዛዝ የሚሰጠው ክርስቶስ ጌታ ሳይሆን ሽፈራው እንደሆነ አታውቁምን
    መፍትሄው ሚሊዮኖች ኦርቶዶክሳውያንና ይህንን ፕሮቴስታንቶች ወያኔ የረከሰ የአጋንንት መንግስት በልዩ ልዩ መንገድ መፋለም ብቻ ነው፡፡

    ReplyDelete
  12. አሜን! ዎንድሜ ተባረክ የአገልግሎት ዘመንህ ይርዘም!!!

    ReplyDelete
  13. selm ethioia , le abatachin abun mathias melkam ye sera zemen. regem edmine yisteln...........

    ReplyDelete

  14. ‹‹አሕዛብ ሸሆች ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ለጠላት አሳልፈው አይሰጡም የኦርቶዶክስ እምነት አባት የሆኑት ፓትርያርክ ግን ልጆቻቸውን ‹አሸባሪ› እያሉ ለጠላት አሳልፈው እየሰጡ ነው›› እያልን አንማዎት! የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና በመጻረርና ቤተ ክርስቲያንን በእጅጉ የሚጎዳ ሥውር ሥራ በመሥራት የክርስቶስን አካል አያድሙ!

    ReplyDelete
  15. The socalled mahibrekidusan is ceaselessly humilating the true church servants at the expense of its financial motifs and ambition to control the EOTC and privatize all what belongs to the church.To this end, this profitable organizations doing its best in scolding church servants and defaming them all the time since its establishment, just like the python cited the Revelation of St John.

    ReplyDelete
  16. በጣም ደፋር ነህ በትክክል የተጠመቀ ሰው እንዲህ አባትን አይደፍርም። እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ።

    ReplyDelete
  17. ‹‹አሕዛብ ሸሆች ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ለጠላት አሳልፈው አይሰጡም የኦርቶዶክስ እምነት አባት የሆኑት ፓትርያርክ ግን ልጆቻቸውን ‹አሸባሪ› እያሉ ለጠላት አሳልፈው እየሰጡ ነው›› እያልን አንማዎት! የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና በመጻረርና ቤተ ክርስቲያንን በእጅጉ የሚጎዳ ሥውር ሥራ በመሥራት የክርስቶስን አካል አያድሙ!

    ReplyDelete