Tuesday, July 9, 2013

ተሀድሶያውያን በክብረ መንግሥት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ‹‹መተዳደር የምንፈልገው በቦርድ ነው›› በማለት ለመንግሥት ማመልከቻ አስገቡ




(አንድ አድርገን ሐምሌ 3 2005 ዓ.ም)፡- በአሁኑ ሰዓት በሰፊው የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ መልሶ በማገርሸት ከሚገኝባቸው አጥቢያ አብያተ ቤተክርስቲያናት መካከል ሐረር ቅዱስ ሚካኤል ፤ ሆሳዕና ቅዱስ ሚካኤል እና ክብረ መንግስት ቅዱስ ሚካኤል ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ከእነዚህ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት መካከል ግን የክብረ መንግስት ቅዱስ ሚካኤል በከፍተኛ ሁኔታ በማገርሸቱ ምክንያት በቅዱስ ሲኖዶስ አንተዳደርም የሚሉ ጥቅት ግለሰቦች ( በአሜሪካው የተሐድሶ ክንፍ መሪቀሲስ’’ ተስፋዬ መቆያና እና የዱባዩ የተሐዲሶ ክንፍ መሪቀሲስተስፉ የሚመሩ የተሐዲሶ መናፍቃን) በአሁኑ ጊዜ ለክብረ መንግሥት የመንግሥት አካል የምንተዳደረው በቦርድ ነው በማለት ማማልከቻ አስገብተዋል፡፡ 


 ከክብረ መንግሥት የሚወጡ ሰባኪያን ወንጌላውያን ነን ባዮች በአሁኑ ጊዜ በደቡብ ኦሮሚያ በሚገኙ አኅጉረ ስብከቶች በቦረና ጉጂ እና ሊቤን ዞኖች ውስጥ በመሰግሰግ በሰፊው የተሐድሶን እንቅስቃሴ በማስፋፋት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል አቶ ታምራት የሚባሉ የሀገረማርያም ዙርያ ( የቡሌ ሆራ ) ወረዳ ቤተክህነት ኃላፊ ሆነው ከተመደቡበት ጊዜ ጀምሮ በአካባቢው ሰፊ ሁከትና ረብሻ እንዲፈጠር ከማድረግ ባሻገር በቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳያቸው በመታየት ላይ የሚገኙትን የተሀድሶ መናፍቃን የፊት መስመር ተሰላፊዎች እነ በጋሻው ደሳለኝን በመጋበዝ በቅርቡ በሁለት የገጠር ወረዳዎች ( በፍንጨዋና በመልካ ሶዳ ) በድምሩ 60,000 ( ስልሳ ሺህ ) ብር በማሰባሰብ ሰፊ የተሐድሶች ጉባኤ እንዲካሄድ አድርጓል፡፡ ይህ ጉዳይ በሊቀ ጳጳሱ እንዳይታወቅ ሰፊ የከለላ ስራ የሚሰራ በአሁኑ ሰዓት ተዘዋዋሪ ሰባኪ በመባል በአቡነ ገብርኤል የተሰየመው የክብር መንግስቱ/ጥላሁን ነው፡፡ በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ ከሰኔ 28 አስከ ሰኔ 30 2005 ዓ.ም በክብረ መንግሥት ቅዱስ ሚካኤል የተደረገውም ጉባኤ በሀገረስብከቱም ይሁን በሊቀ ጳጳሱ በተጻፈ ደብዳቤ ቢታገድም እኛ የምንተዳደረው በቦርድ ነው በማለት ጉባኤው ከቤተክርስቲያንቱ ዕውቅና ወጪ ከመደረጉም በተጨማሪ አቶ በጋሻው ደሳለኝ እንደተለመደው ቅዱሳንን የመሳደብ ግብሩን በዚህም ጉባኤ እንዲቀጥል አድርጎታል፡፡ ታዲያ ከክብረ መንግሥት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርሰቲያን የወጡ እነ ተስፋዬ መቆያ ፤ተስፉ ፤እነ ታምራት፤ እነ ጥላሁን በሀገር ውስጥም ይሁን በወጪ ሀገር ቅድስት ቤተክርስቲያንን የማፍረስ ዓላማ ይዘው ከተነሱ ክብረመንግሥት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ለመገንጠል ከጣሩ እነዚህ ወገኖች ማናቸው? በቅዱስ ሲኖዶስ የማይመራው የክብረ መንግሥት ቅዱስ ሚካኤልስ የማነው? የእነ ተስፉ እና የእነ ተስፋዬ መቆያ ዓላማ ክብረ መንግሥት ቅዱስ ሚካኤልን እንደ ዱባይ ቅዱስ ሚካኤል ቆርጦ ለማስቀረት ይሆን?


(በአንዳንድ ችግር ‹‹አንድ አድርገን›› ለጥቂት ሳምንታት አቋርጣ የነበረው መረጃ የማስተላለፍ ሂደት ከሳምንታት በኋላ ትቀጥላለች፡፡)

4 comments:

  1. ቅዱስ ሲኖዶስ አፋጣኝ መልስ ሊሰጥበት ይገባል በውጭ ዓለም የምንሰማው ቤተክርስትያንን የመገንጠል ሴራ በአገራችንም ላይ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ነውና እንንቃ አባቶቻችን ጳጳሳት ይህንን ነገር መልስ ያስፈልገዋልና ስለ ቅድስት ቤተክርስትያን ሰላምና ሕልውና ስትሉ አንድ ነገር አድርጉ። ለእናንተ ለመናፍቃኑ ደሞ ቤተክርስትያንን ለቀቅ አድርጉልን አቶ በጋሻው እና ቲፎዞችህም እንዲሁም አቶ ተስፋዬ መቆያ አንተ አስመሳይ እንዲህ የታገሰ አምላክ አንድ ቀን ትመለሳለህ ብሎ ነው ሲበዛ ግን በደሙ የመሰረታትን ቤተክርስትያን ለማፈረስ ተነስተሃልና ያፈርስሀል በነገራችን ላይ እስቲ አንዳንዴም የእመቤታችንንም ሥም መጥራት ልመድ ሆ ረስቼው የሌለህን ከየት ታመጣዋለህ የእመቤታችን ፍቅር ዝም ብሎ ይገኝ መስሎሃል ጮኧ ስለተናገርክም የሰበክ ይመስልሃል ደግሞ ልንገርህ ሊቀመልአኩ በጣም ታግሶሃል.....ቀሪውን ዘመንህን የንስሐ ያድርግልህ....

    ReplyDelete
    Replies
    1. Hi ,why do we hide the truth. why do we curse them? They donot wan to be the part of false ,corrupted, and government owned sinod . Let them leave and we will join them. It is better to worship God and follow him than following damn(sorry for using the word) two faced persons.
      God is great.

      Delete
  2. realy why you want to hid the truth.it is the time to preach reality.there is no savior except God...Jesus.they are right

    ReplyDelete
  3. አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል አለው። act 9:5

    ReplyDelete