Tuesday, March 26, 2013

ወቅታዊ ምላሽ “ለኤልያሳውያን” መርሃ ግብር





(አንድ አድርገን መጋቢት 17 2005 ዓ.ም)፡- አዲሱን የኤልያሳውያን አስተምህሮ በማስመልከት  መጋቢት 25 አውቶቡስ ተራ አካባቢ የሚገኝው በተለምዶ አዲሱ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በመምህር ምህረት አብ አማካኝነት ምዕመኑን የማንቃት እና ከዚህ አይነት አስተምህሮ ራሱን እንዲጠብቅ የሚያስችል ትምህርት ለመስጠት ታቅዷል ፤ በተጨማሪም ነብዩ ኤልያስን የሚመለከት የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ምን እንደሆነ በአባቶች ይቀርባል ፡፡ እርስዎም በመርሀ ግብሩ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል፡፡

ከዚህ በታች የምታት ፎቶ ኤልያሳውያን አራት ኪሎ በሚገኝው መሰብሰቢያ አዳራሻቸው አርቲስት ጀማነሽ ፕሮግራም ስትመራ ነው…. የሚለብሱት ልብስ ፤ ከጀርባ ያለውን መስቀል ፤ የእምነታቸውን መጠሪያ ያስተውሉት፡፡



20 comments:

  1. Enezih gibzoche Kelemu erasu sedomawyan yemitekemut Ayinet mehonun enka alastewalum

    ReplyDelete
  2. By the way, does anybody notice. The kind of flag at the back is very much similar to the Gay association flag? So, are these people Elsawian or Sedomawian?

    ReplyDelete
    Replies
    1. When I see the David's star, it made me say "are they the new Felasha, (Jews)"?

      Delete
  3. አርማቸው ለምን ባለስድስት መውጊያ የዳዊት (ወይም የሥነ ፍጥረት) ኮከብና አንክህ የተባለው የግብጾች መስቀል (መግለጫውን ከታች ይመልከቱ) ሆነ ? አይሁድ ነን ለማለት ፈልገው ይሆን ? ይሄ ልዩነት ብቻ ከክርስትና እምነት ውጭ እንደሆኑ ያሳያል ፡፡ በተለይ መደቡን ጥቁር ቢያደርጉት ደግሞ ሰይጣንን የሚያመልኩ ሰዎች የሚጠቀሙበትን ዓይነት ይሆን ነበር ፡፡ ትርጉማቸውን የሚያውቅ ቢያካፍለን መልካም ነው ፡፡

    የዳዊት ኮከብ በቀይ ቀለም በማድረጋቸው ደግሞ Magen David Adom የተባለውንም ያመለክታል ፡፡
    The Magen David Adom (Hebrew: מגן דוד אדום‎, abbr. MDA or Mada) isIsrael's national emergency medical, disaster, ambulance and blood bankservice. The name means "Red Star of David".

    ትክክለኛው የዳዊት ጋሻ ወይም ባለ ስድስት ጠርዙ ኮከብ በነጭ ቀለም ነው ፤ በቢጫ ሲሆን የእልቂት (Holocaust) መታሰቢያ ነው ፤ በሰማያዊ ቀለም የሚሠራው ደግሞ የአሁኗን እሥራኤል ባንዲራ ለማመልከት ነው ፡፡

    The Star of David, known in Hebrew as the Shield of David or Magen David (Hebrew מָגֵן דָּוִד;Biblical Hebrew Māḡēn Dāwīḏ [maːˈɣeːn daːˈwiːð], Tiberian [mɔˈɣen dɔˈvið], Modern Hebrew[maˈɡen daˈvid], Ashkenazi Hebrew and Yiddish Mogein Dovid [ˈmɔɡeɪn ˈdɔvid] or Mogen Dovid) is a generally recognized symbol of Jewish identity and Judaism.[1] Its shape is that of ahexagram, the compound of two equilateral triangles. The hexagram has been in use as a symbol of Judaism since the 17th century, with precedents in the 14th to 16th centuries inCentral Europe, where the Shield of David was partly used in conjunction with the Seal of Solomon (the hexagram) on Jewish flags. Its use probably derives from medieval (11th to 13th century) Jewish protective amulets (segulot).
    The term "Shield of David" is also used in the Siddur (Jewish prayer book) as a title of the God of Israel.

    Ankh - Also known as the Egyptian Cross, the Key of the Nile, the Looped Tau Cross, and the Ansate Cross. It was an Ancient Egyptian symbol of life and fertility, pre-dating the modern cross. Sometimes given a Latin name if it appears in specifically Christian contexts, such as the crux ansata("handled cross").

    ReplyDelete
  4. the way the cross is drawn is also kind of different. The pentagon like picture is david's star. I wonder how devil covers people's mind on this kinds of issues.

    ReplyDelete
  5. yechin seateyo wed memeher girma wesdwat yeha erkuse menfes new ...jemaneshe weda aydelem ye dabilos sira new ...wey fetena!

    ReplyDelete
  6. Check http://en.wikipedia.org/wiki/Religious_symbolism
    to see what their symbols are. It is combination of Judism and Pagan. The star is named "Star of David" and is symbol for Judism while the "To'o" is the symbol for Paganism specifically Ankh.

    Sorry for them. But let us be aware about it.

    ReplyDelete
  7. By the way,is the person behind Jemanesh memihir maneyazewal? He looks like that.

    ReplyDelete
  8. ሰላም ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።

    በመጀመሪያ መስቀልን ስድስት ማእዘን ካለው ኮኮብ ጋር ምን አገናኜው? ሌላ ምስል፤ ምንም ይሁን ምን፤ ከመስቀል ጋር እኩል መንበር እንዴት ተሰጠው? ስድስት ማእዘን ያለው ኮኮብ በክርስትና ታሪክ ውስጥ ኖሮ አያውቅም። በኃሳዊያነ መሲሕ በፕሮተስታንቶች (ምእራባውያን) አስፋሪነት (አሰባሳቢነት) በቴልአቪቭ አሁን ሠፍረው ክርስትናን የሚያውኩት “አይሁድ ነን” ባዮች “የዳዊት ኮኮብ” እያሉ የሚይዙት ከሆነ የሃሰት የሆነ የጣኦት ኮኮብ ነው። ልበ አምላክ ዳዊት እንዲህ አይነት ኮኮብ ምልክት አድርጎ አያውቅም። ምንም እንኳን ክርስቶስ ከዳዊት ልጅ ተወልዶ በአይሁድ ከሳሺነት በመስቀል ላይ የዋለው ነቢዩ ዳዊት ካለፈ ከአንድ ሺህ አመት በኋላ ቢሆንም ለልበ አምላክ ዳዊት አሁን ምልክቱ መስቀል እንጂ የጣኦት ኮኮብ አይደለም። ይህ አሁን “አይሁድ ነን” ባዮች የሚጠቀሙበት የኮኮብ ምልክት የጣኦት አምላክ የሬፋን ኮኮብ እንደሆነ ቅዱስ መጽሐፍ በትንቢተ አሞጽ ም ፭፥ ፳፮ አስፍሮታል። እንዲያውም የስድት መቶ ስድሳ ስድስት ቁጥር አካል ነው ምክንያቱም መስቀል መቆም በሚገባበት ቦታ ይህ የጣኦት ምልክት ቆሟልና። እኔ የምጠራጠረው ኤልሳውያን ነን የሚሉት በሚሠሩት ነገር ውስጥ እነዚህ አገራችን ውስጥ ለውስጥ የሚበጠብጡት የ”አይሁድ ነን” ባዮች እጅ ይኖርበት ይሆናል ብየ ነው።

    ምስጋና ለመድኃኔ ዓለም።
    ኃይለሚካኤል።

    ReplyDelete
    Replies
    1. የሬፋን ኮከብ ተብሎ በትንቢተ ዓሞጽ የተጠቀሰው የዳዊት ኮከብ ተብሎ በተለምዶ የሚታወቀው ቅርጽ ኣይደለም!
      ሬፋን (Repham) የሚባለው ኮከብ የጥንት ከነዓናዊያን፤ ግብጽ፤ ካርታጎናዊያንን አና ዮናናዊያን ያመልኩት የነበረው (ክሮኖስ) ተብሎ ይታወቅ የነበረው ጦኦት በዘመናችን ሳተርን ተብሎ የሚታወቀውን ፮ኛውን ፕላነት የሚያመለክት ነው፡፡
      What is known as the star of David...... ባጭሩ ዓለማቀፋዊ ምሕዋርን የሚያመለክት የጆመትሪክ (Gematria) ንድፍ ሲሆን በተለይ የዓለም ወቅታዊ የሳምንታት፣የወርኅ፣የዓመታትን፣ የሱባዐያት፣ የኢዮበልዮ ዑደቶችን በውስጡ ያካተተ የሂሳብ ንድፍ ነው፡፡
      በውስጡ (፫ ፬ ፫) (፬ ፫ ፬) (፫ ፬ ፫) (፬ ፫ ፬)..................እያለ ዘላለማዊ ዑደቱን የሚያከናውን የሂሳባዊ ስልት ውጠት ነው።
      ኣይሁዳዊያን ይህን ምስል በ ፩፱ኛው ምዕት መጨረሻ አንደ ሰንደቅ ዓላማቸው ኣድርገው ሲወስዱ የተነሱበት ምክንያት የዳዊት ዓርማ ነው ብለው ሳይሆን በታልሙዳቸውና ካባላ በሚባለው የጥንቆላ መጽሓፋቸው በትውፊት የዕስራኤል ምልክት [12 sons of Jacob (Israel) plus1 female] ነው ተብሎ በጸሓፊዎቻቸው ስለተገለጸ ነው።
      If you connect all the angles on the diagram you will find 12 equilateral triangles of 60 degrees inclination which makes the total angular sum of 720 degrees.
      ፯፻፳ ደግሞ የፅዮን ምልክት ነው በኢትዮጵያ የፊደል ገበታ ሰንጠረዥ :-
      ፅ = ፮፻
      ዮ = ፺
      ን = ፴
      ፮፻ + ፺ + ፴ = ፯፻፳ = ፅዮን
      በበለጠ ለመረዳት የየኔታ አስረስ የኔሰውን "ጠቃሚ ምክር" አና "የካም መታሰቢያ" የሚለውን መጽሓፋቸውን ፈልገው ያንብቡ።

      Delete
    2. ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።
      እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።

      ወዳጄ ለይኩን ስለ ትምህርቱ እግዚአብሔር ይስጥልኝ። እውቀትን አስገብይተውኛል።
      ኃይለሚካኤል።

      Delete
  9. They are trying to create a new sect. Jemanesh ere arfesh tekemechi! Endet new Elias lanchi tayito lelelaw yaletayew? This has a kind of similarity with Protestant....they say jesus talk to me...He send me message from heaven etc. Anyway, andeaderegenoch we thank you for the inmformation....sayikatel bekitel endelu...the information helps a lot to stop them from going farther.

    ReplyDelete
  10. ጀማነሽ ሰለሞን የተዋጣለት አርቲስት ናት፥፥ ነገር ግን ለኢትዮጵያ ፍቅር የሌላት የኢትዮጵያን ጠላት በምንም ለመርዳት
    የማትመለስ ሴት ናት፥፥ መረጃ በይኖረኝም የዚች እህት ጉዳይ ምነልባትም ወያኔ በሩቅ ካስቀመጠው ኦርቶድክስን ማዳከም እና ኢትዮጵያዊነትን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ መቅበር ጋ ሊያያዝ ስለሚችል ጉዳዩን የምትከታተሉ ሰዎች የዚህችን ሴት እንቅስቃሴ በጥንቃቄ አጥኑ፥፥

    ReplyDelete
  11. በተጨማሪ ደግሞ ማንም እየመጣ አምላክ የስጠንን ጸጋ ሁሉ እየወሰደ ሊያረክስ ቢፈልግ እያስረከብን መሸሸት የለብንም። ምንጊዜም ቢሆን ሰይጣን የኛ የሆነውን ነገር ወስዶ ለራሱ ማድረግ ነው የሚፈልገው። ለምሳሌ፥

    ሶዶማውያን ቀስተዳመናችን ወስደው የሶዶም ባንዲራ ቢያደርጉት
    ኃሳዊያነ መሢሕ ወንጌላችን ወስደው ቢያጣምሙትና የማታለያቸው መጠቀሚያ ቢያደርጉት
    ሶዶማውያን የትዳርን ነገር ወስደው ለሰዶማዊ ጋብቻ ቢጠቀሙበት
    ኃሳዊያነ መሢሕ ከበሯችንና ጽናጽላችን ወስደው የዳንስ ቢያስመስሉት
    አሁን ደግሞ በጾማችን አድረገው አመሳስለው ሊሠርቁ ቢመጡ
    እነዚህ “ኤልሳውያን” ደግሞ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማችን፣ማተባችን እና ተዋሕዶ የሚለውን ስማችን ወስደው መጠቀሚያ ሊያደርጉ ቢሞክሩ እነሱ ነኩት እያልን ጥለንላቸው ልንሄድ አይገባም።

    ሁሉንም በእግዚአብሔር ኃይል ማሸነፍ አለብን።

    እግዚአብሔር ይመስገን።
    ኃይለሚካኤል።

    ReplyDelete
    Replies
    1. አቶ ኃይለሚካኤል ፍቅራችን ዛሬም እየጠነከረ ነው ፡፡ "ሶዶማውያን ቀስተዳመናችን ወስደው የሶዶም ባንዲራ ቢያደርጉት" ያሉት ፣ የትኛው ነው ደግሞ ለኛ ተብሎ የተፈጠረ ቀስተ ዳመና ? ለኖኀ በምልክትነት የቆመውን ከሆነ ካመነበት ለዓለም ሕዝብ ሁሉ የተገባ የቃል ኪዳን ምልክት ነው ፤ ነገሩን ለማወቅ በመጓጓት ነውና የምጠይቅዎት ፣ በቀና ልብ ቢያስረዱኝ ፡፡

      Delete
    2. አቶ ኃይለሚካኤል አይደለሁም ፤ ኃይለሚካኤል ነኝ። እግዚአብሔር በኖኅ በኩል የሰጠንን ቀስተ ዳመና ሶዶማውያን የሶዶም መለያ ሰንደቅ አላማ ሊያደርጉት ይገባል ነው የሚሉት? እኔን መነዝነዝ ሱስ ሆኖብዎት ነው ወይስ ይህን ያህል መሠረት ለቀዋል? እግዚአብሔር ይቅር ይበልዎ።

      Delete
  12. ወዳጄን ስለመልስዎ በጣም አመሰግናለሁ ፤ ጥያቄ ያነሳሁት ፣ ኢትዮጵያን የቀስተ ደመና ባለቤት አድርገው ስለጻፉ እንጅ ሱስም አልያዘኝም ፤ መስመሬንና መሠረቴንም አልለቀቅኩም ፡፡ ምን ጊዜም አዲስ ትምህርት ስመለከት እደነግጣለሁ ፤ መግለጫውን ለማጣራት የመጠየቅ አባዜ አለብኝ ፡፡ የዘመኑ ትውልድ ደግሞ ከመጽሐፍ ቃል ውጭ አዳዲስ ሃሳቦችን ማፍለቅ ልማድ እያደረገ ስለመጣ ፣ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንንና ቤተ ክርስቲያናችንንም ለመንቀፍም ሆነ ለማስነቀፍ ሲተጋ ስመለከት በምችለው ለመከላከል የማደርገው የትግል ስልት ነው ፡፡ ሲጽፉልን ከተጠነቀቁ እንዲህ አልባሌ ጥያቄዎችን አላቀርብብዎትም ነበር ፡፡ ልብ ይበሉ ፤ እኔ በማስነብበውም ሆነ ርስዎ ከሚጽፉት ሰዎች ተነስተው ፣ የኢኦተቤ እምነቷ እንዲህ ነው ብለው ነገ መልሰው ይሞግታሉ ፡፡ ያንን ለማስቀረት ረጋ ብሎ ማሰብም የሚበጅ ይመስለኛል ፡፡
    ሰላም ይሁኑልኝ

    ReplyDelete
  13. የዳዊት ኮከብ ወይም ጋሻ የሚባለውን በተመለከተ
    ስለሃይማኖት ጉዳይ ባንፈልገውም እንድንመረምረው አጋጣሚው ተፈጥሯል ፡፡ የሁለቱ ሶስት ማዕዘናት (the two triangles) ቅርጽ ጥምረት ስለምን የዳዊት ኮከብ ወይም ጋሻ ተባለ ለሚለው ጥያቄ ጸሐፊያን የተለያየ መግለጫ አላቸው ፤ በንባብ የቃረምኩትን ለማካፈል እንደሚከተለው አቀናጅቻለሁ፡፡

    ለአይሁዳውያን ወይም እሥራኤላውያን በታሪክ የእምነታቸውና የትንቢታቸው መሠረቶች አብርሃም ፣ ሙሴና ዳዊት ስለሆኑ ፣ ማንኛውም ጉዳይ እነዚህን ቀደምት አባቶች ከነካ አይሁዶች የሚሉትን መቃኘት ግድ ይላልና እነርሱው ከጻፉት ውስጥ እኒህን ነቅሻለሁ ፡፡

    በአይሁድ አጻጻፍ ዳዊት የሚለው ስም “ Daleth - Vav or Waw – Daleth” ከሚሉት ፊደላት በመነሳት ደቨደ (DVD) ተብሎ ነው የሚጻፈው፡፡ እኒህ ፊደላት ደግሞ በቁጥር 4 – 6 – 4ን ይወከላሉ ፤ ድምራቸውም 14 ስለሚሆን ተአምርን ፣ ኃይልን ፣ የእግዚአብሔር ፈቃድን ያመለክታል (በማቴዎስ የተመለከተውን የዘር ሐረግ ቆጠራ ያስተውሏል) ፡፡

    ጸሐፍት በጥንቱ የዕብራይስጥ አጻጻፍ Daleth የሚለው ፊደል “እኔ ደ ያልኩት” ሲጻፍ ፣ በሦስት ማዕዘን ቅርጽ ፣ በግሪክ ዴልታ የሚለውን ይመስል ስለነበር ፣ ይኸው የሦስት ማዕዘን ቅርጽ ምልክት የዳዊት ጋሻን ለመወከል ጠቅሟል ይላሉ ፡፡ ስለዚህም ሁለቱን /የመጀመሪያና መጨረሻ ፊደሎች “Daleth”ን ብቻ በመጠቀም/ ሁለቱን የትሪያንግል ቅርጽ (እንደተጠቀሰው ከዳዊት ስም ጋር በመያያዛቸው ምክንያት) በማነባበር ወይም በማቆላለፍ የዳዊት ጋሻ ፣ ወይም የዳዊት ኮከብ ብለውታል ፡፡ ይኸን ቅርጽ ከታሪክ ተመራማሪዎች** ይልቅ የሃይማኖታቸው ተመራማሪዎች ትልቅ ሥፍራና ትርጉም ይሰጡታል ፡፡ ወደላይና ታች ያሉትን ሹል ጫፎች የእግዚአብሔርንና የዚህን ዓለም ትስስር ያመለክታሉ ይላሉ ፡፡ ሦስቱ ጉኖች ደግሞ ሦስቱን የአይሁድን ክፍሎች /ከአሮን ዘር የመጡ ካህናትን ፣ ከሌዊ ዘር የመጡትንና የያዕቆብ ልጆችን ፣ እሥራኤልን/ ያመለክታሉ ፡፡

    ቃሉ በ“Judaism 101” በእንግሊዝኛ እንደሚከተለው ሠፍሯል ፡፡
    A. Kohanim - Priest. A descendant of Aaron, charged with performing various rites in the Temple. This is not the same thing as a rabbi.
    B. Levites -
    1) A descendant of the tribe of Levi, which was set aside to perform certain duties in connection with the Temple;
    2) Son of Jacob (Israel). Ancestor of the tribe of Levi./
    C. Israel.

    ሌላው ከዚሁ ምልክት ትርጉም ላይ የሚጨምሩት ፣ የውስጥና የውጭ መስመሮቹን በመቁጠር አሥራ ሁለቱን የእሥራኤል ነገዶች ያማለክታል ማለታቸው ነው ፡፡ ሌሎች ደግሞ በራዕይ 3፡1 የተጠቀሰውን ሰባት መናፍስት ከዚሁ የዳዊት ኮከብ (ስድስቱን ጠርዞችና በመሃል ያለውን ባለ ስድስት ጐን ቅርጽ ለማለት) አያይዘው እንደሚከተለው ይተረጉሙታል ፡፡

    Spirit 1) YHWH (Himself in totality/unity), sometimes implied as KETER or ETARAH (crown/will)--see Isaiah 28:5. Spirit 2) Spiritual Wisdom (chokhmah). Spirit 3) Earthly Understanding (binah). Spirit 4) Counsel (et-sah) Spirit 5) Power (gevurah) Spirit 6) Knowledge of YHWH (da'at) Spirit 7). "Fear" (i.e. respect, seeing the need to prostrate before the power) of YHWH (yirah).
    The Magen David has six points and the seventh is the HOLE in the middle that is the TIFERET, the harmony of YHWH.

    ከመጽሐፍ ቃልም አስረጃችን ነው የሚሉት የሚከተሉትን ኃይለ ቃሎች በመጥቀስ ነው ፡፡
    - “አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፥ ከእስራኤል በትር ይነሣል፥ የሞዓብንም ማዕዘኖች ይመታል፥ የሤትንም ልጆች ያጠፋል።” ዘኁ 24፡17
    - “ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፥ ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል።” ኢሳ 11፡1
    - “እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።” ራዕ 22፡16

    አንዳንዶቹ እንዲያውም የዳዊት ኮከብ የሚያመለክተው ፣ ራሱን እግዚአብሔርን ነው ይላሉ ፡፡ ድል አድራጊው ዳዊት ፣ ድሎቹን ሁሉ በራሱ ችሎታ ሳይሆን በእግዚአብሔር ርዳታና እገዛ አግኝቷልና ፡፡ መዝሙር 18፡3ዐ-31፡36 ይመልከቱ ፡፡

    እንዲህ እንደተጻፈው ቢባልም አንዳንድ አይሁድ ኦርቶዶክሳውያን ግን የዳዊት ኮከብ የሚባለውን ይቃወማሉ ፤ ምክንያቱም ከምትሃት ሥራ ጋር የተያያዘ ስለሚያደርጉት ነው፡፡

    ** የታሪክ ተመራማሪዎች መግለጫ ደግሞ እንዲህ ይነበባል ፡- “The Magen David (shield of David, or as it is more commonly known, the Star of David) is the symbol most commonly associated with Judaism today, but it is actually a relatively new Jewish symbol. There is really no support for that claim in any early rabbinic literature.”

    ምንጮች፡- http://therefinersfire.org
    http://www.jewfaq.org/index.shtml

    ReplyDelete

  14. ABet geta yasebachu ye'geta ewenet edayesbek sewen bewri ere atamesut. esan geta yadenatal aned ken bechem geta lehulu motalena. ye'yenanet amelakes mehreta ab yemetelut yemetemekubet mechi temarena geta gen yasebew min yebalal. teyakena meles seset yersu teyaki sayemles geta lemeta eko new. min teshalew geta hoy asebew.

    ReplyDelete