Wednesday, October 9, 2013

ጆሮ የለመደው ዜና ‹‹የአብያተ ክርስቲያናት ቃጠሎ››


ኢሳት ዜና :-ሰማያዊ ፓርቲ  ባወጣው መግለጫ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በምስራቅ ጎጃም በአዋበልና አነደድ ወረዳ የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስትያናት ከሚያዚያ እስከ ነሐሴ 2005 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ብቻ በእሳት ተቃጥለው በቤተክርስቲያናቱ ውስጥ የሚገኙ ነዋየ ቅድሳት፣ ልዩ ልዩ አልባሳት፣ ብዙ መጽሐፍትና ንብረት መውደሙን ጠቅሷል።ፓርቲው እንዳለው የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት በኩል ምክንያቱ ታውቆ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሠድ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ሰሚ ጆሮ አላገኙም፡፡
ጉዳዩንም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቀው በክልሉ ቴሌቪዥን በዜና መልክ እንዲገለፅ ያደረጉት ጥረትም አለመሳካቱን አትቷል፡፡በአንድ አካባቢ በተለያየ ጊዜ በተደጋጋሚ በቤተክርስትያን ላይ የማውደም ተግባር ስምንት ጊዜ ሲፈፀም በሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን አንድም ቀን አለመገለፁና በመንግስት በኩል መፍትሔ አለመስጠቱ ፓርቲውን እንዳሳሰበውም ተገልጿል፡፡

Monday, October 7, 2013

‹‹አክራሪነት የቤተክርስቲያኒቱ ዓላማና ተልዕኮ አይደለም›› አባ ኃ/ማርያም መለሠ(ዶ/ር)

  • ቤተክርስቲያኗ ቅንጣት ያህል ከሰላም ውጪ ተናግራ አታውቅም ፡፡
  • በክርስትና ‹‹አክራሪነት አለ›› የሚባለው ነገር ያልተለመደ ነው፡፡  ‹‹እየታየ ነው››  የሚባሉ አባባሎች አሉ፡፡ አክራሪነት ሳይሆን ጽንፈኝነት ሊኖር ይችላል፡፡
  • ጥያቄ፡- መንግሥት የአክራሪነት ዝንባሌ በሙስሊሙ ብቻ ሳይሆን በኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖት ሥር ባለው ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› ውስጥ እንዳለ ተናግሯል፡፡ ይህን እንዴት ይመለከቱታል ?

ዶ/ር አባ ኃ/ማርያም መለሠ የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ሥራ አስኪያጅ ከዕንቁ መጽሄት 6ተኛ ዓመት ቁጥር 101 መስከረም 2006 ዓ.ም ዕትም ጋር አጠር ያለ ቆይታ በአክራሪነት ዙሪያ አድርገው ነበር ፡፡ አንባቢያን ዘንድ ቢደርስ ጠቃሚ ሆኖ ስላገኝነው እንዲህ አድርገን አቅርበነዋል፡፡

ዕንቁ ፡- የአክራሪነት መሰረቱ ምንድነው?
ዶ/ር አባ ኃ/ማርያም፡-እያንዳዱ ሰው የራሱ የሆነ አመለካከት ይኖረዋል፡፡ ያ አመለካከት በሃይማኖት ፤ በፖለቲካ ፤ በሌሎች አይዲዎሎጂዎች ወይም ጽንሰ ሃሳብ (ርዕዮት) ላይ ሊመሰረት ይችላል፡፡ ለማስፈጸም እንደፈለጉት ግብና ዓላማ  በዚያ ላይ ያላቸውን አቋምና የተለያዩ ዝንባሌዎች ለአክራሪነት መሰረት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

Sunday, October 6, 2013

ቀጣዩ የኢሕአዴግ ኢላማ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› ይሆን?


ይህ ጽሁፍ በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የተጻፈ ሲሆን ፤ ሳንቆርጥና ሳንቀጥል ከመጽሄቱ ላይ ያገኝነውን እንዲህ አቅርበነዋል ፤ አንባቢ ጽሁፉን የራሱ ሚዛን ላይ ማስቀመጡ ለራሱ ትተናል ፤ ጋዜጠኛው በአቅሙ የቻለውን ያህል ካለበት ነባራዊ ሁኔታ ፤ ከሰማውና ካሳለፈው በመነሳት ነገን ለመጠቆም ጥረት አድርጓል….
ተመስገን ደሳለኝ

Wednesday, October 2, 2013

እርቀ ሰላም




( አንድ አድርገን  ሀምሌ 15 ፤ 2010 ዓ.ም ) ፡- ፡- መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል “ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም ፤ ነገር ግን  ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው ። ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።” 
የፍቅር እጦት እንጂ ሰውም በወንድሙ ላይ በክፋትና በአመፅ አይነሳምና ቃየል አቤልን በምቀኝነትና በጥላቻ ተነሳስቶ እንደገደለው ሁሉ ዛሬም ብዙ ቃየላውያን በወንድሞቻቸው ላይ በትዕቢት እና በእብሪት ተነሳስተው የሚሞት ስጋቸውን ለመግደል ያሴራሉ። መግደል ለእነርሱ እጅግ የቀለለ ተግባር ነው፤ ቀድመው ህሊናቸውን ገድለዋልና። ማሳት ለእነርሱ እጅግ የቀለለ ተግባር ነው፤ ቀድሞ ህሊናቸውን ስተዋልና። ነገር ግን ዛሬም አሁንም በዚች ቅጽበትም በንስሃ ለተመለሰ ሁሉ ምህረት አለ። ከጥፋት መንገድ ዘወር ላለ መዳን ይሆንለታል። ነገር ግን እንደቀደመው ጊዜ በክፋትና በተንኮል ለመመላለስ ልቡን ያደነደነ፣ ፍቅርን የገፋ፣ ምህረትን የናቀ፣ ለወገኖቹ መጥፊያ ያሴረ፣ ጥላቻን ያነገበ እርቅን የጠላ ሰው ወይም ቡድን የኋላ ኋላ በታላቅ አወዳደቅ መንኮታኮቱ አይቀርም።

‹‹ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በኋላ ይቅር ማለት ያለበት ሕዝብ ነው›› የሀገር ሽማግሌ አባቶች

(አንድ አድርገን መስከረም 23 2006 ዓ.ም)፡-  ከዓመት በፊት ጉዳያቸው በቅዱስ ሲኖዶስ የተያዘው በተሀድሶ ኑፋቄ አስተምህሮ ሲሰሩ የነበሩ ቡድኖች በአሁኑ ሰዓት ከሳምንታት በፊት እርቅ ለማውረድ በሚል እሳቤ ታች ላይ እያሉ ይገኛሉ፡፡ እነዚሁ ወገኖች ከ2 ዓመት በፊት የሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም  እና በአካባቢው አብያተክርስቲያናት ላይ ችግሮች በተፈጠሩበት ወቅት ሕዝቡን አንድ በማድረግ እና በማስተባበር ከምዕመኑ ፤ ከአገልጋዮችና ከአሕጉረ ስብከቱ በኩል ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸውን የሀገር ሽማግሌ አባቶች በሊቀጳጳሱ በኩል ለማግኝት እና ይቅርታን ለመጠየቅ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ሊቀጳጳሱ በእርሳቸው በኩል ይቅርታን እንደሚቀበሉት ነገር ግን ጉዳዩ በሲኖዶስ የተያዘ በመሆኑ መልሱን ከላይ እንዲጠብቁ መልስ የሰጧቸው ቢሆንም ጥያቄያቸውን በአህጉረ ስብከቱ እና በምዕመኑ መካከል በመሆን በወቅቱ የተፈጠረውን ችግር በማርገብ ፤ ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ቤተክህነትና ፓትርያርክ ጽ/ቤት ድረስ በርካታ መኪኖችን በመኮናተር ከ300 በላይ ምዕመንን በማስከተል አቤቱታቸውን በሕጋዊ መንገድ እንዲቀርብ ያደረጉትን በህዝቡ ዘንድ አመኔታ ያላቸውን የሀገር ሽማግሌ አባቶችን ይቅርታን ለመጠየቅ ፤ ሰላም ለማውረድና በእነርሱ በኩል ወደ ምዕመኑ ለመድረስ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ እንደ ብዙዎች አስተያየት ይህ አካሄድ ምዕመኑን በቀላሉ ይቅርታውን እንዲቀበል በተጽህኖ ፈጣሪ የህዝብ ተወካዮች አማካኝነት እንደመምጣት ቆጥረውታል ፡፡ ጥያቄው የቀረበላቸው አባቶች ‹‹ በወቅቱ ብዙ ሰዎች የተደበደቡ ፤ የታሰሩ ፤ የተፈነከቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ምዕመናን ስላሉ እኛ በግል ተጠርተን ይቅር የምንለው ነገር አይደለም ፤ ይቅርታም መጠየቅ ካለበት ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በኋላ ሲሆን ይቅርም ማለት ያለበት ሕዝብ ነው እንጂ እኛ ተወካዮች አይደለምን ›› በማለት መልስ እንደሰጡ ከቦታው ያገኝነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ይህን ጉዳይ እስከ ጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ድረስ መልክ በማስያዝ በተሀድሶነት ክስ የቀረበባቸው ቡድኖች በቀጣይ የሲኖዶስ ስብሰባ ወቅት ጉዳዩ በአጀንዳ መልክ ተይዞ በቅዱስ ሲኖዶስ እንዲታይላቸው ለማቅረብ ሃሳብ እንዳላቸውም ተገልጿል ፡፡  በርካቶችም ‹‹ይቅርታው›› ከላይ ይሁን ከውስጥ አሁንም ጥያቄ እያነሱበት ይገኛሉ፡፡

Monday, September 30, 2013

‹‹የበደልናትን ቤተክርስቲያንን እንክሳለን ፤ ይዘን የወጣነውን ህዝብ መልሰን እናመጣለን ፤ ላጠፋነው ጥፋትም ቤተክርስቲያኒቱ ይቅርታ ታድርግልን›› ተሀድሶያውያን


ከእንቁ መጽሄት እንዳገኝነው
(አንድ አድርገን መስከረም 20 2006 ዓ.ም)፡- ጉዳያቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ተይዞ በመታየት ላይ የሚገኝው የበጋሻው ደሳለኝ እና የያሬድ አደመን ጉዳይ በእርቅ መንገድ መፍትሄ እንዲፈለግለት በመንቀሳቀስ ላይ የምትገኝው ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ መሆኗን ከቤተክህነት አካባቢ ያገኝነው መረጃ ያመለክታል፡፡  መረጃው እንደሚያመለክተው በጋሻውና ያሬድ አደመ ‹‹የበደልናትን ቤተክርስቲያንን እንክሳለን ፤ ይዘን የወጣነውን ህዝብ መልሰን እናመጣለን ፤ ላጠፋነው ጥፋትም ቤተክርስቲያኒቱ ይቅርታ ታድርግልን›› ማለታቸውና እርቁን መፈለጋቸው ታውቋል፡፡

Friday, September 27, 2013

የእግዚአብሔርን ተዓምር ተመልከቱ



(አንድ አድርገን መስከረም 17 2006 ዓ.ም)፡- ቦታው በሶርያ ሀገር ነው፡፡ የቤተክርስቲያኑ ስም saydania ይባላል:: ቤተክርስቲያኒቱ እንደተለመደው የዘወትር ፀሎት ለህዝቡ ፤ ለዓለምም እያደረሰች ባለችበት ሰዓት አንድ ሰው ወደ አንድ መነኩሴ እማሆይ Marina Almaloof ቀርቦ ‹‹ስለት ለመስጠት ነበር እባክዎን ይሄን ብር ሳጥን ውስጥ ያስገቡልኝ›› ይላቸዋል  ፤ በእጅ የያዘውን 160ሳ.ሜ የሆነውን ሻማ ‹‹ይሄን ደግሞ በስዕለ ማርያም ፌት ያብሩልኝ ፤ እኔ በጣም ሰለምቸኩል ነው›› ይልና በፍጥነት ከቤተመቅደሱ ይወጣል ፡፡ መነኩሴዋም ክብሪት በማንሳት ‹‹አቤቱ የሰራዊት ጌታ የዚህን ሰው ስለቱን ተቀበለው›› እያሉ ክብሪቱን ጫሩ ፤ ሻማው ጫፍ አቀረቡት ሻማው ሳይቃጠል ክብሪቱ ተቃጥሎ አለቀ ፤ በድጋሚ ሞከሩ ሞከሩ ሻማው ባለመቃጠሉ እየተገረሙ ከወደ ቤተክርስቲያኒቱ ደጃፍ ጩህት ተሰማ መነኩሴዋም ወደ ጩህት ቦታው በፍጥነት ወጡ ፤ ከታች ከበስተመጨረሻ ደረጃው ላይ አንድ ሰው ወድቆ የሞተ ሰው ተመለከቱ፡፡‹‹ ይሄ አሁን ስለት የሰጠኝ ሰውየ አይደለምን?›› በማለት የተፈጠረውን ሁኔታ ለማስረዳት ስልክ ለአካባቢው ፖሊስ ደወሉ ፤ ፖሊስም በፍጥነት ቦታው ላይ በመገኝት ነገሩን አጣራ ፤ ሁኔታውን ሁሉ ከመነኩሴይቱ በመጠየቅ ተረዳ ፤ ልጁ ቤተመቅደስ ይዞ ገብቶ እንዲለኮስ የፈለገውን ሻማ ፖሊስ ተቀብሎ ሲመረምረው በውስጡ ዳይናሜት TNT የተባለ አደገኛ ተቀጣጣይ ፈንጆች የተሞላ ሁኖ አገኝው፡፡ ይህን ያደረገውን ሰው የሚያውቅ አልተገኝም ፤ ሰውየው በልብ ድካም ነው የሞተው ተባለ ፤ ወላዲተ አምላክ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ህዝቧንም ቤተክርስቲያኑንም በዚህ ተዓምር ታደገች ልመናዋ ምልጃዋ በእኛ ላይ  ይሁን አሜን! 

Sunday, September 22, 2013

“ይህ መስቀል የቤተክርስቲያኒቱ የክብር መገለጫ ነው” መጋቢ ሃዲስ ፍሰሃ


  • ለህዝብ የሚታየው ፓትሪያርኩ በተገኙበት ነው ፤
  • በየእለቱ ከ3ሺህ ሰው በላይ ቦታውን እየጎበኘ ነው
(አዲስ አድማስ ቅዳሜ መስከረም 11 2006 ዓ.ም)፡- በአቃቂ ቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ከሰማይ ወረደ የተባለው መስቀል ፓትርያርኩ በተገኙበት ለህዝብ እንዲታይ መግቢያ መንገድ እስኪሰራ ድረስ የተራዘመ ሲሆን፣ በመስቀሉ ላይ የሳይንስ ምርመራ እንደማይፈቀድ ተገለፀ፡፡ ከሶስት ሳምንት በፊት በፍንዳታ ድምፅና በብርሃናማ ቀስተደመና ከሰማይ ወረደ የተባለው መስቀል፣ በሚቀጥለው ሳምንት መስከረም 19 ቀን ለህዝብ ይታያል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ፓትርያርኩ የሚገኙበት ስነስርዓት ለማዘጋጀት ጊዜው እንደተራዘመ የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪዎች ተናግረዋል፡፡ መስቀሉ ለህዝብ የሚታየው ቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ ማቲያስ በተገኙበት ስነስርዓት መሆን አለበት መባሉን አስተዳዳሪዎች ጠቅሰው፤ መንገዱ ጭቃ ስለሆነ ጠፈፍ ብሎ ለመኪና እስኪስተካከል ድረስ ቀኑ መራዘሙን ገልፀዋል፡፡ ቀኑ ገና እንዳልተወሰነና ለፓትሪያርኩ ጋር ውይይት እየተደረገበት ነው ያሉት የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪዎች፤ ስነስርዓቱን ህዳር 11 ቀን ለማካሄድ እንደታሰበ ጠቁመዋል፡፡

‹‹ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ሆኖ የገደለው ሰው የለም›› ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

 ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከዕንቁ  መጽሔት መስከረም 2006 ዓ.ም እትም ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር ‹‹አንድ አድርገን›› ፍሬውን ከላይ ዝርዝሩን ከታች አድርጋ እንዲህ አቅባላችኋለች


·   ኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ አመኔታ ያለው የዕምነት ተቋም የለም፤ ጠንካራ እምነቶች ግን አሉ፡፡
· ማኅበረ ቅዱሳን እስከ አሁን ድረስ አክራሪ ሆኖ ያመጣው ነውጥ፣ ያስነሳው ነገር፣ የደበደበው፣ የገደለው ሰው፣ ያቃጠለው ቤተ እምነት የለም፡፡
·  ማኅበረ ቅዱሳንን አክራሪ ለማሰኘት የሚያበቃ ምንም፣ አንድም መከራከሪያ ሊያመጡ አይችሉም፡፡ ከሳቸውም በፊት የነበሩት ሌሎች ሰዎች እንደ እርሳቸው ብለዋል፡፡
·         ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ የሚሰነዘሩ ሐሳቦች ምንጫቸው መታየት አለበት፡፡  ‹‹ቂጣም ከኾነ ይጠፋል፤ ሽልም ከኾነ ይገፋል›› እንደሚባለው በተያዘው ሐቅ መቀጠል ነው
·    ማኅበሩ አንድ የሚጎድለው ነገር ቢኖር ማስረዳት ነው፡፡ መልስ መስጠት እንጂ ቀድሞ የማስረዳት ነገር ውስጥ ብርቱ አይደለም፡፡
·        ‹‹ይህች ቤተ ክርስቲያን ተጠብቃ፣ ሥርዐቷን ይዛ ወደሚቀጥለው ትውልድና ዘመን መሻገር አለባት›› የሚሉትን አካላት ነው አሁን ‹‹አክራሪ›› ማለትና ዝም ማሰኘት ነው የሚፈለገው
·        በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ አክራሪነትን ሊያበቅል የሚችል መሬት አይገኝም፡፡
·        የምንመሠርታቸው ተቋማት ለምን እንደ ሐበሻ መድኃኒት ድብቅ እንደሚኾኑ ይገርመኛል
  •    ‹‹ መቻቻል›› የሚለውን አልቀበለውም…. ቻለው ተብለህ የምትኖረው ኑሮ ማለት ነው፡፡
  •    እኔ በኢትዮጵያዊነቴ የሙስሊም ወገኔን በዓል ገዝቼዋለኹ፡፡ ሙስሊሙም የእኔን በዓል ገዝቶታል፡፡ እርሱም በእኔ እምነት እድናለኹ፤ እኔም በእርሱ እምነት እድናለኹ፤ አላልንም እንጂ በባህላችን አንዳችን የሌላችንን በዓል ገንዘብ አድርገነዋል፡፡
  •    ለምን ሚዲያው ይለየናል? እኛ ያልተያየነውን ለምን የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሚለያየን እላለኹ፡፡ በሕግ ደረጃ ብሔራዊ በዓል ነው ተብሎ ከተደነገገ በኋላ በሚዲያ በኩል ልዩነቱ ለምን ይመጣል?
  •    ኢትዮጵያውያን ከሥር ሆነን ያዳበርነው ከወደላይ ትልቅ ችግር ይፈጠርበታል፡፡
  •    መልካሙ ገድልም ደግሞ ከሦስት አካላት ጋራ የሚደረግ ነው፡፡ አንደኛ፡- ከራስ ጠባይዕ ጋራ፣ ሁለተኛ፡- ከሰይጣን ጋራ፣ ሦስተኛ፡- ከተለያዩ አካላት ማለትም ሃይማኖትኽን፣ ቤተ ክርስቲያንህን ወይም እምነትህን ለማፍረስ ከተነሡ ወገኖች ጋራ፣ ከመናፍቃን፣ ከከሐድያን፣ ከአላውያንና ከሌሎች አካላት ጋራ የምታደርገው ተጋድሎ ነው፡፡
  •  ‹‹ቀኝኽን ለሚመታኽ ግራኽን ስጥ›› የሚል ክርስትናን የምንከተል በመኾናችን እስከአሁን አባቶቻችን ሞተዋል እንጂ አልገደሉም፡፡