Tuesday, April 2, 2013

የአዲርቃይ ፍርድ ቤት ‹‹ዋልድባ አይታረስ›› ያሉትን ወጣቶች በአሸባሪነት ከሰሰ

  • የአዲርቃይ ፍርድ ቤት ገዳማችን አይታረስም በማለታቸው ወጣቶችን በአሸባሪነት ከሰሰ
  • በዛሬማ የሚገኙ ነዋሪዎች በወጣቶቹ ላይ ምስክርነት አንሰጥም በማለታቸው እንግልት እየደረሰባቸው ነው
  • የሰሜን ጎንደር ጸጥታ ክፍል ክሱ በአሸባሪነት መሆን አለበት በማለት ትዕዛዝ አስተላልፏል
  • የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከገዳሙ በረከት ለመቀበል የመጡት ማስፈራሪያ እና ፍተሻ (strip search) ተደረገባቸው
  • የጣሊያኑ ኮንስትራክሽን ሌላ አማራጮችን እንፈልግ ብሏል
  • የወልቃይት ነዋሪም እርሻውን እንዲቀጥል እስከሚመጣው ዓመት ምንም ነገር እንደማይኖር እየተነገረው ነው
(From Save Waldeba):- የዛሬ ዓመት አካባቢ ይሆናል የዛሬማ ወጣቶች ከመንግሥት ጋር ገዳማችን አይታረስም፣ የአባቶቻችንን ድንበር አናስነካም በማለት ከመንግሥት ታጣቂዎች ጋር ግብግብ የተፈጠረው፥ በወቅቱ የክልሉ ባለሥልጣናት በቦታው ተገኝተው ከዛሬማ ነዋሪዎች ጋር ስብሰባ አድርገው የዛሬማን ነዋሪ ውሳኔ እንዲሰጥ እያስፈራሩ ባሉበት ወቅት ነበር ጥቂት ወጣቶች የአባቶቻችንን ድንበር አናስነካም፣ ገዳማችንንም ፈቅደን አናሳርስም በማለታቸው ጥቂቶቹን በወቅቱ ወደ እስር ቤት ሲከቷቸው የተቀሩት አምልጠው ጫካ ገብተው ገዳማችንን ማንም ሊነካውም፣ ሊደፍረው፣ ሊረግጠውም አይገባም በማለት ጥሪያቸውን ሲያቀርቡ ቆይተዋል የአካባቢውንም ገበሬ ማኅበራት፣ የሃገር ሽማግሌዎችን በማነጋገር እንዴት ዓይናችን እያየ ገዳማችንን የማንም አማቄላውያን (አረማውያን) መፈንጫ ይሆናል፣ ይሄ ቦታ እኮ የቅዱሳን ማረፊያ፣ የግዑሳን መጠጊያ ለእኛ ለተዳደፍነው እረፍት፣ በረከት፣ ቅድስና ለማግኘት የምንሄድበት እንጂ እንዴት እነዜህ አረማውያን ዛሬ እንደፈለጉት ያደርጉታል በማለት ተቃውሟቸውን በከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት ከሃገረ ስብከቱ ሃላፊዎች ቢያቀርቡም የተወሰኑ የመንግሥት ሃላፊዎች በሃገር ሽማግሌዎች ምከሯቸው እና ወደ ቤታቸው እና ቤተሰባቸው ይመለሱ በማለት አግባብተው ወደ ሃገራቸው እና ቤተሰባቸው ከተቀላቀሉ የሦስት ወይም ሁለት ወር አይበልጣቸውም ነበር።

‹‹የኤልያስ አምላክ›› አዲስ ቪሲዲ በቅርብ ቀን


(አንድ አድርገን መጋቢት 24 2005 ዓ.ም)፡- ራሳቸውን ኤልያሳውያን የ‹‹ተዋሕዶ›› ልጆች በማለት በመጥራት በመንቀሳቀስ ላይ ያሉት ወገኖች አስተምህሯቸውን በሰዎች ጭንቅላት ላይ መጫን ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል፡፡ ቤተክህነቷ በመሀል 4 ኪሎ እየተገኝች አነሱ እዛው አጠገቧ ስራቸውን ሲሰሩ አልሰማውም አላየሁም በማለት ዝምታዋ ተስማምቷት መቀመጧ ብዙዎችን አስገርሟል፡፡ ኤልያስ ወርዷል የሚሉትን ሰዎች መንገድ ትክክል አለመሆኑን ምዕመኑ ያውቀው ዘንድ ሰባኪያን በተለያዩ አውደ ምህረቶች አስተምህሮው የገባቸውን ያህል ትምህርት እየሰጡ ይገኛሉ ፤ በዚህም ሳምንት መርሀ ግብር የያዙም ሰባኪያንም ይገኛሉ ፤ ነገር ግን ይህ አካሄድ ያልተመቻቸው ጥቂት ምዕመናን ለምን ሰባኪያን ከማስተማራቸው በፊት ቤተክርስቲያኒቱ በኤልያስ ላይ ያለውን አስምህሮ ለምዕመኑ አታሳውቅም ? እነዚህ ቡድኖች የቤተክርስቲያኒቱን ስም በመጠቀም ምዕመኑን ግራ እንዳያጋቡት ለቤተክርስቲያኒቱ አማኞች መልዕክቷን ለምን አታስተላልፍም ? ኤልያሳውያን ተለጥፈው የሚሰሩት ስራ ከስርዓተ ቤተክርስቲያን ውጪ መሆኑን ለምን አትናገር ? በማለት ቀድሞ ቤተክርስቲያኒቱ በሊቃውን ጉባኤ መልስ መስጠት አለባት የሚል ሃሳባቸውን ይሰጣሉ ::  
አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ‹‹የኤልያስ አምላክ›› የሚል አርዕስ ያለው ቪሲዲ በዲያቆን ዳንኤል ክብረት አዘጋጅነትና በጌልጌላ መንፈሳዊ መዝሙር ቤት አዘጋጅነት ስራው ተጠናቅቆ በቀጣይ ሳምንት ለማድረስ የህትመት ስራው እየተሰራ መሆኑን መረጃ ደርሶናል ፡፡ ሌሎች ሰባኪያንም የስብከት መርሀ ግብራቸውን በቪሲዲ በማሳተም ለመልቀቅ ማሰባቸውን ለማወቅ ችለናል፡፡ 

ስብከቱ ገበያ ላይ እንደዋለ ከሀገር ውጪ ላሉ ምዕመናን ብሎጋችን ላይ ለመለጠፍ እንሞክራለን፡

Monday, April 1, 2013

አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን ለመገናኛ ብዙሀን የላከችው ደብዳቤ



ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ፡፡
“…
ወበሠሉስ፡ዕለት፡አነስኦ፤”
“...
በሦስተኛው፡ዕለት፡አነሳዋለሁ፤ዮሐ፤፪

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
፯፼፭፻፭ ዓመተ ፍጥረት ፩፼፸፪ ሱባኤ ፻፶ እዩቤልዩ አመ ፳፭ ለየካቲት፡፡
ለሰው ልጆች በሙሉ

የእናታችሁን የቅድስት ምድር የኢትዮጵያን ጥሪ ተቀበሉ! ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛና መዳኛ መሆንዋ ለዘመናት በተነገረላት ትንቢት በተሰጣት ተስፋ መሰረት ትንሳኤዋን ሊያረጋግጥ ኃያል ባለስልጣን ቅዱስ ኤልያስ ከብሔረ ህያዋን መጥቷል፡፡

ቅዱስ ኤልያስ ከነህይወቱ በእሳት ሠረገላ ያረገ ማንም ሊቃወመው ወይም ሊያስቆመው የማይቻለው ተፈጥሮን የማዘዝ ስልጣን የተሰጠው ታላቅ ነቢይ ነው፡፡ይህ ነው ለቅድስት ሀገሩ ለኢትዮጵያ ቀናኢ ሆኖ የተነሳው፡፡

ይህ የሰው ልጆች ሁሉ ሊያውቁትና ሊገነዘቡት የሚገባ እውነታ ነው፡፡ስለዚህም ይህንን እጅግ ታላቅ አስፈሪና ጥልቅ ሃይማኖታዊ ምስጢር በተመለከተ በታላላቅ አባቶች ትንታኔና ትምህርት የሚሰጥበት፤ጥያቄና መልስ የሚካሄድበት ጉባኤ ከጽዋ ማኅበሬ ጋር በመሆን በመስቀል አደባባይ በኤግዝቢሽን ማእከል በአዳራሽ ቁጥር 3 የካቲት ፳፰ (28) ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታላቅ ጉባኤ አዘጋጅቻለሁና እናንተም በዚህ በአባቶቻችን “…በሦስተኛው ዕለት አስነሳዋለሁ” ተብሎ ተሰይሞ ልዩ ክብር ወደተሰጠው የኢትዮጵያ ትንሣኤ ወደሚታወጅበት የሰንበት እረፍት ፣ሠማያዊትና ዘላለማዊት ተዋህዶ፣ሕግና ነቢያት እና ሌሎች ታላላቅ ቅዱስ ኤልያስ የገለጻቸው ምስጢራት በሚነገሩበት በእዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ እንድትገኙልኝ በአክብሮት ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡


ተዋናይት ጀማነሽ ሰሎሞን (እምነ አስራተ ዳዊት ዘኢትዮጵያ፡፡)

ማኅበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ አሐቲ የሰማይ ጉባኤ ዘቅድስት ቤተክርስቲያን ቅድመ መንበሩ ለእግዚእነ ወእመ ኩሉ ፍጥረት ወላዲተ አምላክ የጽዋ ማኅበር፡፡

‹‹ሃይማኖቱን ጠልተው መቃብሩን መናፈቅ አያስኬድም›› አቡነ ገብርኤል


(አንድ አድርገን መጋቢት 23 2005 ዓ.ም)፡- አቡነ ገብርኤል ከ14 ዓመት በፊት ከጦቢያ ጋዜጣ ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ስለ ተሃድሶያውያን ፤ በወቅቱ ስለተነሱ መናፍቃን ፤ ስለኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሁኔታ ፤ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንዴት ከእናት ቤተክርስቲያ ተለይታ ራሷን እንደቻለች ፤ በወቅቱ ሲያስተዳድሩ ስለነበረው ስለ ኢየሩሳሌም ገደማት እና ሌሎች ጉዳዮች ብፅዕ አቡነ ገብርኤል ያስቃኙናል፡፡ ሙሉውን በPdf ያንብቡ

ከቃለ መጠይቁ የተወሰደ
በመንግሥት ለውጥ ጊዜ
ደርግም አለፈ ፤ ኢህአዴግም ተተካ፡፡ ኢህአዴግ ከአቡነ መርቆሪዮስ ጋር አብሬ አልሰራም አለ፡፡ ኢህአዴግ በግንቦት ወር 1983 ዓ.ም ሥልጣን ከያዘ በኋላ በሐምሌ ወር ወደ 22 የሲኖዶስ ሊቃነ ጳጳሳት ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ጉባኤ አድርገን ነበር፡፡ ያንን ጉባኤ የመሩት አሁን በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ታምራት ላይኔ ነበሩ፡፡ እሳቸው በወቅቱ “አቡነ መርቆሪዮስ ከደርግ ጋር የወገኑ ብዙ ገንዘብም የሰጡ እና ዓላማቸውን የሳቱ አባት ስለሆኑ በምንም አይነት ከእሳቸው ጋር አንሰራም” ነበር ያሉት፡፡ በዚህ ምክንያት እሳቸው እስኪወርዱ ድረስ  ለጳጳሳቱ ደመወዝ ፤ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የስራ ማስኬጃና  ለሠራተኛው ደመወዝ እንዲሆን ከመንግሥት ይሰጥ የነበረው በጀት እንዲቆም ተደረገ፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ በየቦታው እሳቸውን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ፡፡ ፓትርያርኩ እስከ መጨረሻው ድረስ እንደ አቡነ ቴዎፍሎስ ተጎትተው አልወረዱም፡፡ ራሳቸው በገዛ ፈቃዳቸው ይቅርብኝ ብለው ሥልጣናቸውን ተዉ፡፡የወር ደመወዝ እየተቀበሉ ፤ መኪናም ተመድቦላቸው ብሥራተ ገብርኤል አካባቢ እንዲቀመጡ ተደረገ፡፡