Tuesday, June 12, 2012

በርካታ ቤቶችን የበላው የሐዲያ ቃጠሎ እስካሁን መንስዔው አልታወቀም


(*** Reporter ***):- በደቡብ ክልል ሐዲያ ዞን በታህሳስ ወር በተለያዩ ቀናት 140 ቤቶችን የበላው የእሳት ቃጠሎ መንስዔ በእስካሁኑ ሒደት አልታወቀም፡፡ በዞኑ ሰሮ፣ ሻሼጌ፣ ጌሌቦ፣ ሚሻና ጊቤ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ቤቶች በታህሳስ ወር ውስጥ በ15 ተከታታይ ቀናት ድንገተኛ እሳት እየተነሳ መውደማቸው ይታወሳል፡፡ የቃጠሎው ሁኔታ አነጋጋሪ ሆኖ የሰነበተ ከመሆኑም በላይ፣ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አካባቢውን እንዲጎበኙ ምክንያት ሆኗል፡፡

የዞኑ ፖሊስ ባልደረባ ኢንስፔክተር ክብነህ አበበ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አቶ ሽፈራውአካባቢውን በጐበኙበት ቀንም ቤቶች ተቃጥለው ነበር፡፡ ፖሊስ አስፈላጊውን ክትትልናምርመራ እንዲያደርግ አቶ ሽፈራው ለዞኑ ፖሊስ መመርያ ሰጥተዋል፡፡ በዚህ መሠረት ፖሊስ ደፈጣ በማድረግ የእሳቱን መንስዔ ለማወቅ ጥረት ቢያደርግም፣ የተገኘ ፍንጭ አለመኖሩን ኢንስፔክተር ክብነህ ገልጸዋል፡፡ “ሰው ነው የሚለኩሰው? የሚለውን ለማጣራት ሙከራ አድርገን ነበር፡፡ ሰው ስለመለኮሱ ግን መረጃዎች ልናገኝ አልቻልንም፤” ሲሉኢንስፔክተሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ 

Monday, June 11, 2012

ዝቋላን መልሰን እናልማ

“ይህን ቦታ ወደ ቀድሞ ሁኔታ የመመለስ ሃላፊነት አለብን”
(አንድ አድርገን ሰኔ 4 ፤ 2004 ዓ.ም )፡- የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም መጋቢት 9 ፤ 2004 ዓ.ም ለቀናት በዘለቀው እና ለማጥፋት አዳጋች የሆነው እሳት ደኑ ላይ ብዙ ጉዳት እንዳደረሰ ይታወቃል ፤ በጊዜው እሳቱን ለማጥፋት በርካታ ምዕመናኖች ከአዲስ አበባ ፤ ከአዳማ እና ከደብረዘይት ወደ ቦታ አምርተው የተቻላቸውን ሁሉ አድርገው እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ እሳቱን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ይታወቃል ፤ ይህን በእሳት ምክንያት ገዳሙ ያጣውን ደን መልሶ ለማልት የ‹‹ደጆችሽ አይዘጉ›› መንፈሳዊ ማህበር የመጀመሪያ ዙር የዛፍ ተከላ ፕሮግራም ሰኔ 24 እና ሰኔ 25 ቦታው ድረስ በመሄድ በሺህ የሚቆጠሩ ምዕመናና የሚሳተፉበት የጉድጓድ ቁፋሮ እና ዛፎችን የመትከል መርሀ ግብር አውጥቷል በዚህ የተቀደሰ መንፈሳዊ አገልግሎት ገንዘብ ያላችሁ በገንዘባችሁ ጉልበት ያላችሁ በጉልበታችሁ ትሳተፉ ዘንድ ጥሪያቸውን ያስተላልፋሉ ፤ ይህን የዛፍ ተከላ ፕሮግራም ለመርዳት የምትፈልጉ ሰዎች ችግኞችን በመግዛት ፤ ብር በማዋጣት እና ቦታው ድረስ በመሄድ የጉልበት አገልግሎት መስጠት ይምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ወደ ገዳሙ የሚደረገው የጉዞ ቀን ቅዳሜ ሰኔ 24 2004 ዓ.ም ሲሆን የመመለሻ ቀን ደግሞ እሁድ ሰኔ 25 ይሆናል ፤ ይህን የተቀደሰ አላማ ላይ አሻራዎን ለማሳረፍና ከአባታችን ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በረከት ለመቀበል የምትፈልጉ ሰዎች የትራንስፖርት ወጪዎትን ብቻ በመሸፈን ማህበሩ ባዘጋጀው የጉዞ መርሀ ግብር ላይ በመገኝት የታሪካዊውን ገዳም ደን መልሶ የማልማት ፕሮግራም ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ዛፍ የመትከል መርሀ ግብሩ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ሰዎች ጉድጓድ ለመቆፈር የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችን (ገሶ ፤ ዶማ ወይም አካፋ) መያዝ ይጠበቅቦታል ፤

“የማይቀርበት ታላቅ የበረከት ስራ….”


ይህን አላማ ለመርዳት ወይም መርሀ ግብሩ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሰዎች  ለበለጠ መረጃ (0911-201649 ፤ 0911-216440 ፤ 0913-255249 ፤ 0911-015623 ፤ 0924-373474) በመደወል ሙሉ መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡


Sunday, June 10, 2012

ኢትዮጵያ ግብረሰዶምንና አራማጆቹ ምዕራባዊያንን አወገዘች

‹‹ትልቁ ሀብታችን ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ነው›› አቡነ ጳውሎስ


*Reporter* ትናንት በአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ በ‹‹ግብረሰዶምና ተያያዥ ማኅበራዊ ቀውሶች›› ላይ ለመነጋገር በተጠራው አገራዊ ኮንፈረንስ የተገኙት የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የፓርላማ አባላት፣ ወጣቶችና ሌሎች የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ‹‹ግብረሰዶምንና ግብረሰዶም የሚያስፋፉ ምዕራባዊያንን›› አወገዙ፡፡ በዚሁ ታሪካዊና አንገብጋቢ በተሰኘው አገራዊ ኮንፈረንስ ላይ ከ2,000 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ አምስቱ ዋና ዋና የሃይማኖት ተቋማት የኦርቶዶክት ተዋህዶ፣ የእስልምና፣ የካቶሊክ፣ የወንጌላዊት መካነ ኢየሱስና የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ያወጡትን የግብረሰዶማዊነት የተቃውሞ መግለጫ በአንድ ድምፅ እንደግፋለን ብለዋል፡፡ ግብረሰዶማዊነትን ካልተቀበላችሁ በማለት የሰብዓዊ መብት ጥያቄ የሚያነሱና ዕርዳታ እንከለክላለን ለሚሉ የምዕራብ አገሮችም ‹‹ዕርዳታቸው በአፍንጫችን ይውጣ›› የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በስብሰባው ላይ የተገኙት የሃይማኖት ተቋማትን በሙሉ ወክለው ጉባዔውን በፀሎት የከፈቱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ፣ ‹‹ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት ሕግ ሳይጻፍ ጊዜ ጀምሮ ከእግዚአብሔር ጋር ትውውቅ ነበራቸው፤ የዛሬ ሳይንቲስቶችም ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ መሆንዋን ይናገራሉ፤›› በማለት በዓለም ላይ ያሉ ሕዝቦች በሙሉ እርስ በርስ ተረጋግጠዋል፤ ብቸኛ ነፃ አገር ኢትዮጵያ ነች ብለዋል፡፡ ‹‹አሁንም የተረገጡትና የማንነት ቀውስ ያለባቸው ወገኖች ተናገሩ ብላ የምትሰማ አይደለችም፡፡ ባህላችን አልተለወጠም፣ ታሪካችን አልተቀነሰም፣ ማንነታችን አልተበረዘም፤ እንዲሁ ዝም ብለን የምንለወጥ አይደለንም፤›› ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

Saturday, June 9, 2012

በዋልድባ ጉዳይ ከ20 በላይ ወጣቶች ታስረዋል


(አንድ አድርገን ግንቦት 2 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- የዋልድባ ገዳም ጉዳይ አሁን ወደ ሌላ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል ፤ የመወያያ መድረኮች ውጤት እያመጡ አይደሉም ፤ መንግስት ዘነዘና የዋጠ ይመስል የአቋም ለውጥ ማድረግ ተስኖታል ፤ የሚሰራውን ስራ አሁንም ገዳሙ ላይ ተጽህኖ የለውም ብሎ አምኗል ፤ ባሳለፍነው ሳምንት ከ3ሺህ የሚበልጥ የአካባቢው ነዋሪ ተቃውሞውን በቦታው ላይ መግለጹን ገልጸን ነበር ፤ ከዚህ ተቃውሞ በኋላ 10 የሚሆኑ የገዳሙ አባቶችን የአካባቢው ባለስልጣናት ሰብስበው አነጋረዋቸው እንደነበረ ለማወቅ ችለናል ፤ በቀጣይ ሰኔ 7 ፤ 2004 ዓ.ም ተጨማሪ የስብሰባ ፕሮግራም መያዛቸውን ጭምር ፤ ከዚህ በፊት የተደረጉት የስብሰባ ውጤቶች መስማት ባንችልም አሁንም ስብሰባዎች እየተደረጉ ናቸው ፤ ከእነዚህ ስብሰባዎች በተጨማሪ ባሳለፍነው ረቡዕ የአካባቢውን ወጣቶች በመሰብሰብ ስለ ግድቡ ለማወያየትም ባለስጣናቱ ሞክረው ነበር ፤ በስብሰባው ላይ የተገኙት በርካታ ወጣቶች ስብሰባውን አድርገው ከጨረሱ በኋላ በያዙት አቋምና ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ አማካኝነት ከየቤታቸው እና በተገኙበት እየተለቀሙ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው  ወደ እስር ቤት ገብተዋል  ፤ ለእስር የሚፈለጉ ሰዎች ወሬው እንደደረሳቸው ግማሾቹ ጎንደርና ሌሎች ቦታዎች ሲሸሹ ብዙዎች ደግሞ “ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?” ወደ ሮሜ ሰዎች 8 ፤ 35 በማለት መታሰርን መርጠው እዚያው አሳሪዎቻቸው ይጠባበቃሉ ፡፡ ጉዳዩ የእምነትና በእምነት ስለሆነ የሚመጣውን ነገር ሁሉ ለመቀበል ተዘጋጅተዋል ፤  ወንጌሉ እንዲህ ይላል “ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ” ማቴዎስ ወንጌል 10፤28

Wednesday, June 6, 2012

በአንድ አይናችን በቤተክርስትያን በአንዲት እምነታችን በተዋህዶ አትምጡብን


(አንድ አድርገን ግንቦት 30 ፤ 2004ዓ.ም)፡- በቤተል ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን በቦታ ጉዳይ በተነሳው ግጭት በርካቶች ተጎድተዋል ፤ በዚህ ቦታ ይገባኛል በማለት ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማው ህጋዊ ካርታ ሲኖረው ቤተክርስትያኒቱም ህጋዊ ካርታ እጇ ላይ ይገኛል ፤ የአካባቢው ሰው በቦታው አማካኝነት ክፉኛ ስለተበሳጨ የሚሆነውን ነገር ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በአትኩሮት ሲከታተል ነበር ፤ ማክሰኞ እለት በልበ ሙሉነት ምንም እንደማይሆኑ ከክፍለከተማ የተወከሉ ሰዎች እና ጥቂት ፖሊሶች ስራቸውን ቦታው ላይ ሲጀምሩ ተቃውሞ ከምዕመኑ ማስተናገድ ጀመሩ ፤ የነበረውን ሰው ለመበተን  ሲሞክሩ በያዙት የፖሊስ ሀይል ስላቻሉ ተጨማሪ የፖሊስ ኋይል ከአካባቢው  ጣቢያ እንዲመደብላቸው በመጠየቅ ከ40 የሚበልጡ ፖሊሶች በአካባቢው ላይ ከደቂቃዎች በኋላ መምጣት ችለው ነበር ፤ እነዚህ ፖሊሶች የመጡት ከአንድ መሳሪያ እና ከፖሊስ ዱላ ጋር ብቻ ስለነበረ ከህዝቡ የሚወረወረውን ድንጋይ መቋቋም ሲያቅታቸው ለፌደራል ፖሊስ አድማ በታኝ ልዩ ኋይል በመገናኛ ሬዲዮ በመነጋገር የችግሩን ጥልቀት በማስረዳት ኋይል እንዲጨመርላቸው ጥያቄ አቀረቡ ፤ በዚህ ጊዜ በቦታው ላይ የነበረው ፖሊስ ወደ አርባ ቢጠጋም የህዝቡን ተቃውሞ ግን መመከት አልቻሉም ነበር ፤ ይህ የሚያሳየው ከ40 በላይ ፖሊሶች መቆጣጠር ያልቻሉት የህዝብ ተቃውሞ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ነው፡፡  

Tuesday, June 5, 2012

በቤተል ጊዮርጊስ ከይዞታ ጋር ተያይዞ በተነሳ ተቃውሞ ሁለት ሰዎች ሞቱ

(አንድ አድርገን ግንቦት29 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ቦታው ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተል ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ሲሆን ይህ ቦታ አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙት ሰፊ ቦታ ካላቸው አብያተክርስያናት አንዱ ነው ፤ ቦታው ህጋዊ ካርታ ያለው ቢሆንም አጥር ግን የለውም ፤ በዚህ መሀል ባዶ ቦታ ነው በሚል ከቤተክርስትያኒቱ ቦታ ላይ መንግስት በመቁረስ ለሙስሊሞችና  ለተለያዩ መሰረተልማቶች በሊዝ የሸጠ ሲሆን ይህን ያወቁት የአካባቢው ነዋሪዎች በመሰባሰብ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ክፍለ ከተማ ድረስ ሂደው ጉዳዩን መንግስት ላስቀመጣቸው ሃላፊዎች ቢያስረዱም ሰሚ አላገኙም ነበር፤ በዚህ ሰዓት “እናንተም መታችሁ ቦታውን ታጥራላችሁ እኛም ዝም ብለን አንመለከታችሁም” በማለት በቁጣ ሊመለሱ ችለዋል ፤ ይህ ከሆነ በኋላ የቤተክርስያኒቱ ቦታውን ሲታጠር በቦታው በመገኝት የተመለከቱ ክርስትያኖች ባነሱት ተቃውሞ አንድ ወጣትና አንድ ፖሊስ በግጭቱ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል ፤የተፈጠረው ሁኔታ ያልተጠበቀ እና ተቃውሞውም ይበረታል ብሎ ያልጠበቀው መንግስት የክርስትያኖቹን ቁጣ በቀላሉ ለማብረድ ባለመቻል በአከባቢው የነበረው የፖሊስ ኋይል ህዝቡን ለመበተን በቂ ባለመሆኑ ከፌደራል ፖሊስ በርካታ የታጠቁ ፌደራል ፖሊሶች ወደ ቦታው በመምጣት ለተቃውሞ የወጣውን ህዝብ በአስለቃሽ ጭስ በትነዋል ፤ አስለቃሽ ጭሱ ወደ ጊዮርጊስ ቤተክርስያን ግቢ ውስጥ ሲተኩሱ ተስተውሏል ፤ በርካቶችም ለእስር ተዳርገዋል ፤ ይህ ተቃውሞ እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ የህዝቡ ተቃውሞ በመቀጠሉ አካባቢው ውጥረት ነግሶበት አምሽቷል ፤ በዚህ ሁኔታ ህዝቡ ክፉኛ የተቆጣ በመሆኑ መንግስት ያለአግባብ የሸጠውን የቤተክርስትያኒቱን ቦታ ካልመለሰ ከዚህ የባሰ ነገር እንዳይፈጠር ያሰጋል ፤ በአሁኑ ሰዓትም የጦር ካምፕ ይመስል ቦታው በከፍተኛ የፖሊስ ሀይል እየተጠበቀ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡

ጠላት ደስ አይበለው

የማኅበረ ቅዱሳንን ፳ኛ ዓመት በዓል አከባበር - በአርባ ምንጭ ማእከል

Monday, June 4, 2012

የዋልድባን ገዳም እናድን የሚሉ ሰላማዊ ሰልፎች በዓለም ዙርያ ሲካሄዱ ውለዋል


በ Addisu Abebe | Washington From VOA news
ሙሉውን ዘገባ ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ፡

ዛሬ ማለዳ ከዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ተነስቶ ወደ ውጪ ጉዳይ መሥራ ቤት የተጓዘውን የዋሽንግተኑን ሰልፍ ተከታትለን ነበር

Sunday, June 3, 2012

የተሐድሶና ምንፍቅና አራማጁ ስራ አስኪያጅ ሆኖ ተሾመ

  • ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን የአሜሪካ 3ቱ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆነ
(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 24/2004 ዓ.ም፤ ጁን 1/ 2012/READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በተሐድሶነቱ የሚታወቀውና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወ/ሮ እጅጋየሁን ተክቶ የፓትርያርኩ ቀኝ እጅነትን የተረከበው ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን በአቡነ ጳውሎስ ፈቃድ በአሜሪካ የሚገኙት የሦስቱም አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆኖ መሾሙን ምንጮቻችን እየገለፁ ነው። ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በአሜሪካ ሥራ አስኪያጅነትን ሥልጣን ተረክቦ እንዲሠራ የተሾመው ኃ/ጊዮርጊስ በተሐድሶ እምነት አራማጅነቱ በግልጽ የሚታወቅና ዓላማዎቹን እና እምነቶቹን በተለያዩ የተሐድሶ ብሎጎቸ በይፋ በማስተላለፍ የሚታወቅ፣ ከዚያም አልፎ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን ከተሐድሶዎቹ ብሎጎች ጋር በማገናኘት ደብዳቤዎቻቸው በዚያ እንዲስተናገዱ እና ምእመኑ ከንጽሕት እምነቱ ተናውጾ በኑፋቄ ትምህርት እንዲበከል ከፍተኛውን እንቅስቃሴ የሚያድርግ ግለሰብ መሆኑ ይታወቃል።

Saturday, June 2, 2012

የቀረብን የእግር ጉዞ ብቻ ነው


(አንድ አድርገን ግንቦት 25 ፤ 2004 ዓ.ም)፡-የማህበረ ቅዱሳንን 20ኛ ዓመት በማስመልከት የእግር ጉዞ ለማድረግ አንድ  ቀንና  ጥቂት ሰዓት ቀርተውታል  ፤ እኛም ቲኬቱን በ100 ብር ገዝተን ጉዞውን እንደ ባለፈው የሐዊረ ህይወት ጉዞ ይሆናል ብለን ጠብቀን ነበር ፤ በዚህ ጉዞ ከ 20 ሺህ በላይ ምዕመናን ይገኛሉ ተብሎ ታስቦ ነበር ፤  ድንገት በሞባይሌ የጉዞ ፕሮግራም ወደ ጉባኤነት እንደተቀየረ  ከጠዋቱ 4፡00 ጀምሮ በቤተክህነት አዳራሽ እንደሚካሄድ የሚያሳስብ የጽሁፍ መልዕክት ደረሰኝ ፤መልዕክቱም አንዲህ ይል ነበር “Our Dear families ! sorry because of Betekehenet our journey is changed to Gubae at betekehenet hall. Starting from 4:00 am morning’’   መልእክቱን አንብቤ ስጨርስ ለምን? ብዬ በመጠየቅ ወደ ማህበሩ ድህረ ገፅ ገብቼ ስመለከት “ግንቦት 26 ቀን 2004 ዓ.ም ከማኅበረ ቅዱሳን 20ኛ ዓመት የምሥረታ ክብረ በዓል ጋር ተያይዞ ሊካሔድ የነበረው የእግር ጉዞ መርሐ ግብር ጠቅላይ ቤተ ክህነት መጻፍ ያለበትን ደብደቤ ባለመጻፉ በታቀደለት  መሠረት ሊከናወን አልቻለም፡፡” የሚል መልዕክት አነበብኩኝ ፤