Saturday, June 9, 2012

በዋልድባ ጉዳይ ከ20 በላይ ወጣቶች ታስረዋል


(አንድ አድርገን ግንቦት 2 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- የዋልድባ ገዳም ጉዳይ አሁን ወደ ሌላ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል ፤ የመወያያ መድረኮች ውጤት እያመጡ አይደሉም ፤ መንግስት ዘነዘና የዋጠ ይመስል የአቋም ለውጥ ማድረግ ተስኖታል ፤ የሚሰራውን ስራ አሁንም ገዳሙ ላይ ተጽህኖ የለውም ብሎ አምኗል ፤ ባሳለፍነው ሳምንት ከ3ሺህ የሚበልጥ የአካባቢው ነዋሪ ተቃውሞውን በቦታው ላይ መግለጹን ገልጸን ነበር ፤ ከዚህ ተቃውሞ በኋላ 10 የሚሆኑ የገዳሙ አባቶችን የአካባቢው ባለስልጣናት ሰብስበው አነጋረዋቸው እንደነበረ ለማወቅ ችለናል ፤ በቀጣይ ሰኔ 7 ፤ 2004 ዓ.ም ተጨማሪ የስብሰባ ፕሮግራም መያዛቸውን ጭምር ፤ ከዚህ በፊት የተደረጉት የስብሰባ ውጤቶች መስማት ባንችልም አሁንም ስብሰባዎች እየተደረጉ ናቸው ፤ ከእነዚህ ስብሰባዎች በተጨማሪ ባሳለፍነው ረቡዕ የአካባቢውን ወጣቶች በመሰብሰብ ስለ ግድቡ ለማወያየትም ባለስጣናቱ ሞክረው ነበር ፤ በስብሰባው ላይ የተገኙት በርካታ ወጣቶች ስብሰባውን አድርገው ከጨረሱ በኋላ በያዙት አቋምና ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ አማካኝነት ከየቤታቸው እና በተገኙበት እየተለቀሙ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው  ወደ እስር ቤት ገብተዋል  ፤ ለእስር የሚፈለጉ ሰዎች ወሬው እንደደረሳቸው ግማሾቹ ጎንደርና ሌሎች ቦታዎች ሲሸሹ ብዙዎች ደግሞ “ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?” ወደ ሮሜ ሰዎች 8 ፤ 35 በማለት መታሰርን መርጠው እዚያው አሳሪዎቻቸው ይጠባበቃሉ ፡፡ ጉዳዩ የእምነትና በእምነት ስለሆነ የሚመጣውን ነገር ሁሉ ለመቀበል ተዘጋጅተዋል ፤  ወንጌሉ እንዲህ ይላል “ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ” ማቴዎስ ወንጌል 10፤28

Wednesday, June 6, 2012

በአንድ አይናችን በቤተክርስትያን በአንዲት እምነታችን በተዋህዶ አትምጡብን


(አንድ አድርገን ግንቦት 30 ፤ 2004ዓ.ም)፡- በቤተል ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን በቦታ ጉዳይ በተነሳው ግጭት በርካቶች ተጎድተዋል ፤ በዚህ ቦታ ይገባኛል በማለት ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማው ህጋዊ ካርታ ሲኖረው ቤተክርስትያኒቱም ህጋዊ ካርታ እጇ ላይ ይገኛል ፤ የአካባቢው ሰው በቦታው አማካኝነት ክፉኛ ስለተበሳጨ የሚሆነውን ነገር ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በአትኩሮት ሲከታተል ነበር ፤ ማክሰኞ እለት በልበ ሙሉነት ምንም እንደማይሆኑ ከክፍለከተማ የተወከሉ ሰዎች እና ጥቂት ፖሊሶች ስራቸውን ቦታው ላይ ሲጀምሩ ተቃውሞ ከምዕመኑ ማስተናገድ ጀመሩ ፤ የነበረውን ሰው ለመበተን  ሲሞክሩ በያዙት የፖሊስ ሀይል ስላቻሉ ተጨማሪ የፖሊስ ኋይል ከአካባቢው  ጣቢያ እንዲመደብላቸው በመጠየቅ ከ40 የሚበልጡ ፖሊሶች በአካባቢው ላይ ከደቂቃዎች በኋላ መምጣት ችለው ነበር ፤ እነዚህ ፖሊሶች የመጡት ከአንድ መሳሪያ እና ከፖሊስ ዱላ ጋር ብቻ ስለነበረ ከህዝቡ የሚወረወረውን ድንጋይ መቋቋም ሲያቅታቸው ለፌደራል ፖሊስ አድማ በታኝ ልዩ ኋይል በመገናኛ ሬዲዮ በመነጋገር የችግሩን ጥልቀት በማስረዳት ኋይል እንዲጨመርላቸው ጥያቄ አቀረቡ ፤ በዚህ ጊዜ በቦታው ላይ የነበረው ፖሊስ ወደ አርባ ቢጠጋም የህዝቡን ተቃውሞ ግን መመከት አልቻሉም ነበር ፤ ይህ የሚያሳየው ከ40 በላይ ፖሊሶች መቆጣጠር ያልቻሉት የህዝብ ተቃውሞ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ነው፡፡  

Tuesday, June 5, 2012

በቤተል ጊዮርጊስ ከይዞታ ጋር ተያይዞ በተነሳ ተቃውሞ ሁለት ሰዎች ሞቱ

(አንድ አድርገን ግንቦት29 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ቦታው ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተል ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ሲሆን ይህ ቦታ አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙት ሰፊ ቦታ ካላቸው አብያተክርስያናት አንዱ ነው ፤ ቦታው ህጋዊ ካርታ ያለው ቢሆንም አጥር ግን የለውም ፤ በዚህ መሀል ባዶ ቦታ ነው በሚል ከቤተክርስትያኒቱ ቦታ ላይ መንግስት በመቁረስ ለሙስሊሞችና  ለተለያዩ መሰረተልማቶች በሊዝ የሸጠ ሲሆን ይህን ያወቁት የአካባቢው ነዋሪዎች በመሰባሰብ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ክፍለ ከተማ ድረስ ሂደው ጉዳዩን መንግስት ላስቀመጣቸው ሃላፊዎች ቢያስረዱም ሰሚ አላገኙም ነበር፤ በዚህ ሰዓት “እናንተም መታችሁ ቦታውን ታጥራላችሁ እኛም ዝም ብለን አንመለከታችሁም” በማለት በቁጣ ሊመለሱ ችለዋል ፤ ይህ ከሆነ በኋላ የቤተክርስያኒቱ ቦታውን ሲታጠር በቦታው በመገኝት የተመለከቱ ክርስትያኖች ባነሱት ተቃውሞ አንድ ወጣትና አንድ ፖሊስ በግጭቱ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል ፤የተፈጠረው ሁኔታ ያልተጠበቀ እና ተቃውሞውም ይበረታል ብሎ ያልጠበቀው መንግስት የክርስትያኖቹን ቁጣ በቀላሉ ለማብረድ ባለመቻል በአከባቢው የነበረው የፖሊስ ኋይል ህዝቡን ለመበተን በቂ ባለመሆኑ ከፌደራል ፖሊስ በርካታ የታጠቁ ፌደራል ፖሊሶች ወደ ቦታው በመምጣት ለተቃውሞ የወጣውን ህዝብ በአስለቃሽ ጭስ በትነዋል ፤ አስለቃሽ ጭሱ ወደ ጊዮርጊስ ቤተክርስያን ግቢ ውስጥ ሲተኩሱ ተስተውሏል ፤ በርካቶችም ለእስር ተዳርገዋል ፤ ይህ ተቃውሞ እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ የህዝቡ ተቃውሞ በመቀጠሉ አካባቢው ውጥረት ነግሶበት አምሽቷል ፤ በዚህ ሁኔታ ህዝቡ ክፉኛ የተቆጣ በመሆኑ መንግስት ያለአግባብ የሸጠውን የቤተክርስትያኒቱን ቦታ ካልመለሰ ከዚህ የባሰ ነገር እንዳይፈጠር ያሰጋል ፤ በአሁኑ ሰዓትም የጦር ካምፕ ይመስል ቦታው በከፍተኛ የፖሊስ ሀይል እየተጠበቀ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡

ጠላት ደስ አይበለው

የማኅበረ ቅዱሳንን ፳ኛ ዓመት በዓል አከባበር - በአርባ ምንጭ ማእከል

Monday, June 4, 2012

የዋልድባን ገዳም እናድን የሚሉ ሰላማዊ ሰልፎች በዓለም ዙርያ ሲካሄዱ ውለዋል


በ Addisu Abebe | Washington From VOA news
ሙሉውን ዘገባ ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ፡

ዛሬ ማለዳ ከዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ተነስቶ ወደ ውጪ ጉዳይ መሥራ ቤት የተጓዘውን የዋሽንግተኑን ሰልፍ ተከታትለን ነበር

Sunday, June 3, 2012

የተሐድሶና ምንፍቅና አራማጁ ስራ አስኪያጅ ሆኖ ተሾመ

  • ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን የአሜሪካ 3ቱ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆነ
(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 24/2004 ዓ.ም፤ ጁን 1/ 2012/READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በተሐድሶነቱ የሚታወቀውና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወ/ሮ እጅጋየሁን ተክቶ የፓትርያርኩ ቀኝ እጅነትን የተረከበው ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን በአቡነ ጳውሎስ ፈቃድ በአሜሪካ የሚገኙት የሦስቱም አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆኖ መሾሙን ምንጮቻችን እየገለፁ ነው። ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በአሜሪካ ሥራ አስኪያጅነትን ሥልጣን ተረክቦ እንዲሠራ የተሾመው ኃ/ጊዮርጊስ በተሐድሶ እምነት አራማጅነቱ በግልጽ የሚታወቅና ዓላማዎቹን እና እምነቶቹን በተለያዩ የተሐድሶ ብሎጎቸ በይፋ በማስተላለፍ የሚታወቅ፣ ከዚያም አልፎ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን ከተሐድሶዎቹ ብሎጎች ጋር በማገናኘት ደብዳቤዎቻቸው በዚያ እንዲስተናገዱ እና ምእመኑ ከንጽሕት እምነቱ ተናውጾ በኑፋቄ ትምህርት እንዲበከል ከፍተኛውን እንቅስቃሴ የሚያድርግ ግለሰብ መሆኑ ይታወቃል።

Saturday, June 2, 2012

የቀረብን የእግር ጉዞ ብቻ ነው


(አንድ አድርገን ግንቦት 25 ፤ 2004 ዓ.ም)፡-የማህበረ ቅዱሳንን 20ኛ ዓመት በማስመልከት የእግር ጉዞ ለማድረግ አንድ  ቀንና  ጥቂት ሰዓት ቀርተውታል  ፤ እኛም ቲኬቱን በ100 ብር ገዝተን ጉዞውን እንደ ባለፈው የሐዊረ ህይወት ጉዞ ይሆናል ብለን ጠብቀን ነበር ፤ በዚህ ጉዞ ከ 20 ሺህ በላይ ምዕመናን ይገኛሉ ተብሎ ታስቦ ነበር ፤  ድንገት በሞባይሌ የጉዞ ፕሮግራም ወደ ጉባኤነት እንደተቀየረ  ከጠዋቱ 4፡00 ጀምሮ በቤተክህነት አዳራሽ እንደሚካሄድ የሚያሳስብ የጽሁፍ መልዕክት ደረሰኝ ፤መልዕክቱም አንዲህ ይል ነበር “Our Dear families ! sorry because of Betekehenet our journey is changed to Gubae at betekehenet hall. Starting from 4:00 am morning’’   መልእክቱን አንብቤ ስጨርስ ለምን? ብዬ በመጠየቅ ወደ ማህበሩ ድህረ ገፅ ገብቼ ስመለከት “ግንቦት 26 ቀን 2004 ዓ.ም ከማኅበረ ቅዱሳን 20ኛ ዓመት የምሥረታ ክብረ በዓል ጋር ተያይዞ ሊካሔድ የነበረው የእግር ጉዞ መርሐ ግብር ጠቅላይ ቤተ ክህነት መጻፍ ያለበትን ደብደቤ ባለመጻፉ በታቀደለት  መሠረት ሊከናወን አልቻለም፡፡” የሚል መልዕክት አነበብኩኝ ፤

Thursday, May 31, 2012

በዋልድባ ከሶስት ሺህ ሰው በላይ ለተቃውሞ መንግስት ላይ ተነሳስቷል

  •   ስብሰባው ላይ ለመገኝት በመኪና ሲመጡ የነበሩ የመንግስት ባለስልጣናት መኪናቸው መንገድ ላይ ተገልብጧል
  • “እኛ ምንም ኮሚቴ ማቋቋም አያስፈልገንም የምንፈልገው ስራውን እንድታቆሙ ብቻ ነው ፤ የህዝቡን ጥያቄ ረግጣችሁ ስራውን ብትቀጥሉ ግን ሌላ ነገር ውስጥ እየገባን መሆኑን እወቁት” የአካባቢው ነዋሪዎች
  •    ከአምስት በላይ ጎጆዎች ከ60 ኩንታል በላይ እጣን በእሳት ተቃትሏል
(አንድ አድርገን ፤ ግንቦት ተክለኃይማኖት ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ዋልድባ የሀዘን ድባብ ከጣለበት ሰንበትበት ብሏል ፤ መንግስተ በጉዳዩ ላይ የቤተክርስትያኒቱን አባቶች ለማወያየት የተስማማ ቢመስልም አሁንም ዋልድባን ማረሱን ተያይዞታል ፤ ትላንትና በቪኦኤ ላይ ባገኝነው መረጃ መሰረት ለትንሽ ጊዜያት ስራውን ካቋረጠ በኋላ ከዚህ ቀደሙ በባሰ ሁኔታ  በሰፊው ማረሱን ጀምሯል ፤ ይህን የተመለከተ ትላንት የአድርቃይ እና አካባቢው ከሶስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች  የተቃውሞ ድምጻቸውን ለማሰማት ወደ ቦታው እንደወረዱ ቃላቸውን ለቪኦኤ ከቦታው ሆነው ያስተላለፉት አንድ መነኩሴ ተናግረዋል ፤ አሁንም በግሬደር ሬሳዎችን እየፈነቃቀለ ይገኛል ፤ “ መንግስት አይከሰስ መሬት አይታረስ” እንደሚባለው ተረት መንግስትን የቤተክርስትያኒቱን ገዳም ከማፈራረስ እረፍ የሚለው አካል አልተገኝም፡፡

“መቻቻልን የማያውቅና ለዲሞክራሲ ፀር የሆነ ሃይማኖትን መቻል አይጠበቅብንም” መጋቢ ዘሪሁን

  • “ይህ በልዩነታችሁ ያጌጠ የመቻቻል ባህል ሁሌም ከእናንተ ጋር የሚቀጥል እንደይመስላችሁ ፤ ኢትዮጵያ ገና አልተፈተነችም፡፡” ዶ/ር አብዱላህ

(አንድ አድርገን ግንቦት ጊዮርጊስ 2004 ዓ.ም)፡- ባለፈው ሰኞ ከሰዓት ለሀገሪቱ ከጥቂት ዓመታ በፊት የእግር እሳት የሆነባት መንግስም ለመቆጣጠርና ለማስቆም ያልቻላቸው ጉዳዮች አንዱ በሀይማኖት አካባቢ ያለን ችግር ነው ፤ በመሰረቱ ቤተክርስያናች የዚህን ችግር ገፈት ቀማሽ እንጂ ችግሩን ካመጡት ጎራ የምትመደብ አይደለችም ፤ በፊት በፊት ከአክራሪ ሙስሊሞች የሚደርሰው ጉዳት ነበር አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰው ፤ አሁን ባለንበት ጊዜ ግን መንግስት የሚያካሂደው የልማት ስራ የቤተክርስያኒቱ የነገ ህልውና ላይ የሚታይ ችግር እየፈጠረ መሆኑን እያስተዋልን እንገኛለን ፤ በጊዜው ከኢህአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያምና ሌሎች ጥቂት ባለሥልጣናት  በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን አዲሱ ትልቁ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሃይማኖት መቻቻል ዙሪያ  ዙርያ ለመምከር  ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር እና ከተለያዩ ሀገራት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር ተሰብስበው ነበር፡፡

Wednesday, May 30, 2012

1500 ዓመት ያስቆጠረው የአቡነ ገሪማ ገዳም ሙዚየም ተመረቀ

(Reporter ):- አንድ ሺሕ አምስት መቶ ዓመታት ባስቆጠረው የአቡነ ገሪማ ገዳም የተሠራው አዲስ ሙዚየም ግንቦት 18 ቀን 2004 ዓ.ም. ተመረቀ፡፡ በትግራይ ክልል በዓድዋ ወረዳ የሚገኘውና ከገዳሙ እኩል ዕድሜ 1500 ዓመታትን ያስቆጠረ የወንጌል መጻሕፍትና ጥንታውያን ቅርሶች ላሉበት ገዳም ዘመናዊ ሙዚየሙ የተገነባለት ከ400 ሺሕ ብር በላይ ወጪ ነው፡፡

መምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቱያን የቅርስ ጥበቃና ምዝገባ የቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምርያ ኃላፊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የፈረንሣይ መንግሥት በሰጠው ከ400 ሺሕ ብር በላይ ዕርዳታ መሠረት ጥንታዊው ሕንፃ ታድሶና ተዘጋጅቶ ለቤተ መዘክር አገልግሎት እንዲውል ተደርጓል፡፡