Tuesday, October 18, 2022

"ተናበን እንዳንሰራ እንቅፋት የሆነብን ምንድን ነው?" ሲሉ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ጠየቁ ።

 

ጥቅምት 7 ቀን 2015 ዓ.ም (አዲስ አበባ) :- የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም በባለፈው በጀት ዓመት የተሰሩ በርካታ ክንዋኔዎችን ዛሬ ጥቅምት 7 ቀን 2015 ዓ.ም 41ኛው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ በተካሄደበት ላይ በሪፖርት አቅርበዋል ። ብፁዕነታቸው በሪፖርቱ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ሐዋርያዊ ክንውን ፣ ሐዋርያዊ ተልዕኮና መንፈሳዊ አገልግሎትን በተመለከተ የተሰሩ ሥራዎችን ፣በአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ የተሰሩ ስራዎችን ፣የምግባረ ሠናይ ዘርፍን በተመለከተ ፣ የልማት ድርጅቶችን እነዚህንና ሌሎችም መሰል ተግባራትን በተመለከተ በንባብ አሰምተዋል ።

ብፁዕነታቸው በመጨረሻም መሠረታዊ የመወያያ አጀንዳዎች የሚሆኑ መነሻ ሐሳቦችን አቅርበዋል። ብፁዕነታቸው ካቀረቧቸው መነሻ ሀሳቦች መካከልም


Ø  ስለ ሀገራችን ሰላም የቤተ ክርስቲያን አስተዋጽኦ ምን ይሁን ?

Ø  በቤተክርስቲያን እና በምእመናን የሚደርሰውን ግፍ በምን መልኩ ማስቆም ይቻላል ?

Ø  የቤተ ክርስቲያን ሕልውና ለማረጋገጥ (አብነት ትምህርት ቤት ለማስቀጥል፤ ሰንበት ትምህርትን ከማጠናከር አንጻር፤ ስብከተ ወንጌል ከማስፋፋት አንጻር ?)

Ø  በጀት አጠቃቀም ላይ ያለውን ችግር እንዴት እንፍታው?

Ø  የቤተ ክርስቲያንን ምጣኔ ሀብት እንዴት እንጠብቀው?

Ø  ከመንበረ ፖትርያርክ እስከ አጥቢያ ድረስ ተናበን እንዳንሰራ እንቅፋት የሆነብን ምንድን ነው ?ተናቦስ ለመሥራት ምን እናድርግ ?

Ø  የቤተ ክርስቲያንን ክብር እንዴት ጠብቀን እናስጠብቅ ?

Ø  ቤተ ክርስቲያናችን ለተጎዱት ከመድረስ ይልቅ ጉዳት ደረሰብኝ ባይ ሆናለች ስለዚህ ከዚህ ለመላቀቅ መፍትሄው ምንድን ነው ?

Ø  ሙስናን እንዴት አድርገን ከቤተ ክርስቲያን እናላቀው? የሚሉ መሰል ጥያቄዎች ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሪፓርት ቀጥሎ ለተሰብሳቢዎቹ የተሰጠ ሲሆን ከቀትር በኋላ ውይይት ይድረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

No comments:

Post a Comment