በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው ሁለት መነኮሳት መንግስት በአሸባሪነት ጠርጥሬአችኋለው ብሎ ያሰራቸው ናቸው። የዋልድባ ገዳም መነኮሳት ሲሆኑ፤ አባ ገ/እየሱስ ኪ/ማርያም እና አባ ገ/ስላሴ ወ/ሃይማኖት ይባላሉ። አለም በቃኝ ብሎ በገዳም መቀመጥም አይቻልም ማለት ነው። የዋልድባ ገዳም መፍረሱን በመቃማቸው ነው አሸባሪ ተብለው ለእስር የተዳረጉት። መነኮሳቱ ከ2004 ጀምሮ አቤቱታቸውን ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ በተደጋጋሚ ቢያቀርቡም ምላሽ አለማግኘታቸውንም ይናገራሉ። መነኮሳቱ በማእከላዊ ቆይታቸው ድብደባ ሌሎች ኢ ሰብአዊ ድርጊቶች እንደተፈፀመባቸው ተናግረዋል። ክስ ተመስርቶባቸው ቂሊንጦ ከወረዱ በኋላም ዛቻ እና ማስፈራሪያ እንዳልተለያቸው እንዲሁም ከሌሎች አብረዋቸው ከሚኖሩ እስረኞች ጋር አብረው እንዳይበሉ እና እንዳይጫወቱ ጫና እየተደረገባቸው መሆኑንም ተናግረዋል።
ችሎታቸውን ለመከታተል የምትፈልጉ ቀጣይ ቀጠሯቸው ህዳር 14 ነው። ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት።
No comments:
Post a Comment