ዲያቆን መልአኩ እዘዘው
በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ ፤ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ ›
እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለ
ኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር። ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና። ተነሡ አትፍሩም አላቸው።ዓይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም። የማቴዎስ ወንጌል 17፡1-8
በቂሳርያ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ ለሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ ጠይቋቸው አንዳንዶች ከነቢያት አንዱ ነህ ይሉሃል፣ አንዳንዶች ሙሴ ነህ ይሉሃል፣ ሌሎች ደግሞ ኤልያስ ነህ ይሉሃል እያሉ መለሱለት ጌታችንም መልሶ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ ሲጠይቃቸው የሐዋርያት አፈጉባዔ ሊቀ ሐዋርያት ቅ/ጴጥሮስ ‹አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ነህ› ብሎ በመመስከሩ ጌታም ‹የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ በሰማይ ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ…› ተብሏል፡፡