
ከመጀመሪያው አርሶ አደር ጋር የተደረገ ውይይት..
መቼ ነው ዝናብ እናንተ ጋር
የዘነበው ?
ዝናቡ ሃምሌ 20 አካባቢ ነበር የጀመረው ፤ ትንሽ ጥሎ ሲያበቃ ፤ አድሮ ሲያካፋ አድሮ ሲያካፋ ከአስራ አምስት ቀን
በኋላ በዚያው ቆመ፡፡
ዝናቡ ቆላው ላይ ብቻ ነው ያልጣለው?
ሌላ ቦታ ላይ ዝናብ ጥሎላቸዋል ?
እኛ አካባቢ ብቻ ነው ወደ ላይ(ደጋው ክፍል) ይሻላል፡፡
ከአሁን በኋላ ዝናብ የምጠብቁት
መቼ ነው ?
መጋቢትን ይዘን ወደ ሚያዚያ…
አካባቢው የበልግ ዝናብ አለው
?
የለውም ፤ አያውቅም ፤
አሁን ለከብቶች የሚሆን ነገር
ምንድነው የምታገኙት ?
ዘንድሮማ ምን አለን ? ከብቶቻችንን እየሸጥን ነው የምናበላቸው ምንም
ስለሌለን …..
ከብቶቻችሁን ሽጣችሁ ይህን ጊዜ
እንዴት ነው የምትዘልቁት ?
መቼስ ተፈጥሮ ከታረቀን ከመጋቢት ጀምሮ ከጣለልን ከብቱም
ብላጊ(ዝናብ ጥሎ የሚበቅል) ያገኛል ፤ ቦታውም ትንሽ ይለመልማል እኛም ማሽላ እንዘራለን ፤ መንሥትም እተባበራችኋለሁ ከጎናችሁ
ነኝ ይላል ፤ አንግዲህ ልናየው ነው፡፡
መንግሥት እስከ አሁን ያመጣው ነገር አለ ? የተሰጣችሁ ነገር አለ ?
የለም
፤ ባይሆን በሴፍቲኔት ፕሮግራም ታቅፈን ብር እየተረዳን ነበር፡፡
በምን ያህል ጊዜ ነው የሚረዷችሁ በወር በወር ነው.. ወይስ ?
በወር
አይደለም አልፎ አልፎ ይረዱና…
ምን ያህል ይረዷችኋል ?
በቤተሰብ 1000 ብር
፤ አራት የቤተሰብ አባል ያለው አስርም ያለው እኩል ነው የሚረዳው፡፡(በአካባቢው ሴፍቲ ኔት ፕሮግራም ምግብ ለስራ የሚባል አይነት
ነው የሚገኝው ፤ ገበሬውን በቀን ሥራ ያሰሩትን በቤተሰብ 30 ብር ይታሰብለታል)
1000 ብር አሁን እህል ይገዛል ?
እስከ አሁን ይገዛ
ነበር አሁን ግን ሊወደድ ነው ፤ ከዚህ በፊት በቆሎ ኩንታል 600 ብር እንገዛ ነበር አሁን ግን ዋጋው ይቃናል ፤ እንጃ…..
እርሻው እንዴት ነው….

ከሁለተኛው አርሶ አደር ጋር
የተደረገ ውይይት..
ባለፉት ዓመታት ዝናብ እንዴት ነበር አካባቢያችሁ ላይ?
ባለፈው ዓመት እስከ
ጥቅምት ዝናብ ነበር ፤ ብዙም ምርት አግኝተን ነበር ፤አሁን ግን ምንም የለውም …
አካባቢያችሁ የበልግ ዝናብ አለው ?
አካባቢው ቆላ ስለሆነ
በልግ አያውቅም ፤ መሕር ብቻ ነው ያለው ፤ በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ነው የሚያገኝው ፤ በዚያች ነው ከዓመት ዓመት የምንዘልቀው
፤ ከወዲያ ግድም ያሉት ሁለት ጊዜ የሚያገኙ አካባቢዎች አሉ ፤ ይህ ግን ቆላ ስለሆነ አንድ ጊዜ ነው የሚያገኝው፡፡ መሬቱ ዝናብ
ካገኝ እስከ ሁሉት ዓመት የሚሆን ምርት ይሰጣል፡፡ ካገኝ ችግር የለውም ፤ ዝናብ ግን ያጥረዋል….
ከአሁን በኋላ መቼ ነው የሚዘንበው ?
መጋቢት ተከትሎ ሚያዚያን
ከጣለ ፤ ዳጉሳ ማሽላ ስለሚያዝ እሱን እንዘራለን ፤ ከዚያ ወዲህ ቢጥል ሀገሩ በበልግ ማሽላ ያበቅል ነበር ፤ ቦታው ሁሉን ያበቅላል
ችግር የለም ነበር ፤ አሁን ዝናቡ ነው ችግር የፈጠረብን..
ወደዚህ ስንመጣ ብዙ ቦታዎች እህል ደርቋል ፤ እህሉ አሯል ፤ ምንድነው
የሚደረገው ይሰበሰባል ?
ለከብቶች
ይሆናል ፤ ለከብት የማይሆንም አለ፡፡
ውሃ የሚታቆር በአካባቢያችሁ የለም ? ምንጮችስ ?
የለም
፤ ምንጮች ደርቀው ነው በችግር ላይ ችግር የሆነው…
መንግሥት ርዳታ ይሰጣል ?
ድርቅ ከበላው እንረዳለን
እያለ ነው ፤ አሁን እየመዘገበ ነው ፤ እንጃለት የሚረዳው ሕዝብም በርክቷል ፤ ሕዝቡ እርዳታ ያስፈልገዋል ፤ እስከሚቀጥለው
ዓመት ዝናብ ዘንቦ ምርት እስኪሰበሰብ እርዳታ ስፈልገዋል ፤ ቦታው ቆላ ነው ሰኔ ላይ ትንሽ ቢጥል መስከረም ላይ የሚደርሱትን እንዘራ
ነበር፡፡ ምስር ቦሎቄ አተር ይደርሳል፡፡
እስከዛ ከብቶቹ እንዴት ይዘልቃሉ ?
አካባቢው ላይ ያለው ውሃ እያጠረ እያጠረ ሲሄድ በሽሎ(ራቅ ብሎ የሚገኝ ወንዝ) መሄዳችን አይቀርም ፤ እሱም ስለሚርቅ
ብዙ ችግር ነው ገና የሚያጋጥመን …
ወደዚህ ስንመጣ ከብቶች የሚጠጡበት
የነበረው ወንዝ መንገዳችን ላይ ያለው ደርቋል
መቼ ዘንቦ ውሃ ይኖረዋል እሱ…
ከዚህ አካባቢ የሚብስ ቆላ አለ
?
በደላንታ ፤ በመቅደላ ፤ በሳይትን ግርጌ የሚብሱ ቆላዎች አሉ ፡፡
አጂባር ገበያ ነበርን ገበሬው
በሬውን እየሸጠ ነው ፤ ታዲያ በሬ ተሽጦ ምን ይኮናል ?
አዎን እየሸጥን ነው ፤ ጊዜውን ለመግፋት
በአንድ ቀበሌ ስንት አባወራ
ይኖራል ? እርዳታስ እንዴት ነው የሚሰጠው?
እስከ ሁለት ሺ አባወራ ይኖራል ፤ ቀበሌው ደግሞ በቀጠና የተከፋፈለ ነው፡፡ እስከ አሁን የሚረዳው ጠና ጠና ያለበት
ነበር ፤ ዘንድሮ ግን ሁሉም ችግረኛ ነው፡፡ ዝናብ ለሁሉም ስላልጣለ ሁሉም ይረዳ እየተባለ ነው፡፡
ይህ አካባቢ ምንም ያለ ዝናብ
ተስፋ የለውም ?
ምንም የለውም ፤ በ77 ዝናብ መላውን ቀርቶ ሀገሩ ለቆ ነው የወጣው ፡፡ በጅማ ፤ በወለጋ በኢሊባቡር በአሶሳ በቴፒ
ሕዝቡ ተበትኖ ቀርቷል ፤ ዝናብ መለስ ሲል ግማሹ ሲመለስ ሌላው በዛው ቀርቷል ፤ ከፊሉ ሲሰደድ ከፊሉ እዚህው በርሃብ አለቀ ፤
ይህን ጊዜ ከብቱም ሰውም የሚበላው አጥቶ እየወደቀ ነበር ፤ መንግሥትም ያኔ ሲረዳን ነበር ፤ ተመጽዋቹን አጅባር ሜዳ ላይ ሰብስቦ
እህል በአየር እየጣለ ሲረዳ ነበር ፤ በ1977 ምንም አንዲት ዝናብ አልጣለም ነበር፡፡
መፍትሄው ምንድነው ፤ ዝናቡ በቀረ ቁጥር እንዲህ የሚሆን ከሆነ ?
መፍትሄው ተወን እስኪ…. እኛ አሁን ቁጭ ያልነው እግዚአብሔርን አምነን ነው ፤ ከቀረ ያው መሄድ ወይም ሞት ነው ፤ ሌላ መፍትሄ የለውም፡፡ ፈረንጅ ብሏል አሉ ፤ በ1928 የመጣ ጊዜ ‹‹እንዲያው ሀበሻ ስራሽ ምንድነው አለ ?›› ዝናብ ከጣለ እንዘራለን መሬቱም ያበቅላል አሉት አባቶች ፤ ‹‹ ጉድሽን ልይ ብሎ ዝናብ ቢጠፋ ምን ትበያለሽ ያለው ነገር በ77 ደረሰ ›› አለ፡፡ ተው እስኪ ዝናብ ከቀረ መልቀቅ ነው ፤ መሄድ ነው ፤ መሞት ነው ይኽው ነው ….
yasazinal
ReplyDeleteI like your writings
ReplyDeleteYasazinal
ReplyDelete