ለትውስታ፡- የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኔዓለም ቤተ
ክርስቲያን በሶስት ዓመት ውስጥ 4.6 ሚሊየን ብር መመዝበራቸው ተገለጠ (ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ የጥቅምት 2006
ዓ.ም ዕትም)
- የታገድነው በደብሩ የተፈጸመውን ከፍተኛ የገንዘብ ምዝበራ በማጋለጣችን ነው (ሰበካ ጉባኤው)
- ጉዳዩን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ ዲቪዚዮን ተይዟል፡፡
(አንድ አድርገን ጥቅምት 28
2006 ዓ.ም)፡- በአዲስ አበባ ደቡብ ክፍለ ከተማ የሚገኝው የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን
የሰበካ ጉባኤ ጳግሜ 3 ቀን 2005 ዓ.ም ሕገ ወጥ ተግባር ፈጽሟል
በሚል በመታገዱ ችግር መፈጠሩ ተገለጸ፡፡
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና
ስራ አስኪያጅ የመጋቢ ሐዲስ ቀሲስ ይልማ ቸርነት ፊርማና ማኅተም ያለበት በቁጥር 450/25/06 በቀን 03/01/2006 ዓ.ም
የተጻፈ ደብዳቤ እንደሚያመለክተው የደብሩ ሰበካ ጉባኤ የታገደው የሥራ ዘመኑን መጋቢት 12 ቀን 2005 ዓ.ም ቢያጠናቅቅም ሌላ
የሰበካ ጉባኤ ሳይመረጥ በመቅረቱ በተለያየ ጊዜ ጭቅጭቅ ንትርክና ሁከት እንዲፈጠር በማድረጉ ማታገዱ ይገልጣል፡፡