Sunday, September 28, 2014

ኅዳር 25 ቀን 2006 ዓ.ም ፡ ‹‹የመስቀል በዓል›› በዩኔስኮ የሰው ልጅ መንፈሳዊ ባህላዊ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበበት ቀን

·  በብሔራዊ ደረጃ መስቀል የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ባህላዊ ቅርስ ተብሎ በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ነሐሴ 14 ቀን 2003 .. በቁጥር 0001 ተመዝግቧል፡፡
  • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሚከበሩት የአደባባይ በዓላት አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ እንደምትሠራ ቤተ ክህነት አስታወቀች፡፡ 
        አንድ አድርገን መስከረም 18 2007 ዓ.ም
 
ከብሔራዊ እስከ ዓለም ቅርስነት  ኦርቶዶክሳዊቷ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ካሏት ቅዱሳን በዓላት መካከል በዐውደ ምሕረትም በሕዝብ አደባባዮችም ከምታከብራቸው ውስጥ መስከረም 17 ቀን በየዓመቱ የሚከበረው የመስቀል በዓል ይገኛል፡፡  

መስቀል በዋነኛነት ክርስቲያናዊ ሃይማኖታዊ በዓልነቱን የያዘ ከባህል መገለጫዎች ጋር ምእመኑና ኅብረተሰቡ በመላዋ ኢትዮጵያ በአንድነትና በኅብረት የሚያከብረው ታላቅ በዓል ነው፡፡
ከአንድ ሺሕ አምስት መቶ ዓመታት በላይ ሲከበር የኖረው የመስቀል በዓል ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንና ከምእመኖቿም አልፎ ካለው መንፈሳዊና ባህላዊ እሴት በመነሣት ዩኔስኮ (በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት) 2006 .. ኅዳር ጀምሮ በዓለም ቅርስነት መዝግቦታል፡፡ 

ኢትዮጵያ እስከ አምና ድረስ በዓለም ቅርስነት ለዘመናት ተመዝግቦላት ሲታወቁ የነበሩት ተፈጥሯዊና ታሪካዊ፣ መልክአ ምድራዊም ግዙፍ ቅርሶች (ታንጀብል) ብቻ ናቸው፡፡ እነዚህም በአፍሪቃ ግንባር ቀደም ሆና የተገኘችባቸው ዘጠኝ የዓለም ቅርሶቿ የአክሱም መካነ ቅርስ፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የጎንደር አብያተ መንግሥት፣ የሐረር ጁገል፣ የስሜን ተራራ ብሔራዊ ፓርክ፣ የአፋር፣ የኦሞ እና የጥያ የፓሊዮንቶሎጂና የአርኪዮሎጂ ስፍራዎች፣ እንዲሁም የኮንሶ ባህላዊ መልክአ ምድር ናቸው፡፡
አገሪቱ ካላት ግዙፍ ቅርሶች ባልተናነሰ እንደ በሐውርታዊነቷ (ባለ ብዙ ብሔረሰብ ሀገርነቷ) ሀገሬውንም ሆነ ዓለምን የሚያስደምሙ መንፈሳዊ/ ረቂቅ ቅርሶች (intangible heritages) እያሏት እስከ 2006 .. ኅዳር ወር ድረስ አንድም አለማስመዝገቧ ጥያቄ ሲያጭር ኖሯል፡፡ 
ቱሪስቶችም ሆኑ የባህል ባለሙያዎችና ጋዜጠኞች በቀደሙትና ባለፉት ዓመታት ታላላቆቹ የአደባባይ በዓላት መስቀልም ሆነ በዓለም የፌስቲቫሎች መድበል፣ ‹‹የአፍሪቃው ጥምቀት›› (African Epiphany) የሚል ቅጽል ያገኘውን የጥምቀት በዓል ለማስመዝገብ ለምን ጥረት እንደማይደረግ ሲወተውቱ ኖረዋል፡፡ 
‹‹ቀን ሲደርስ አምባ ይፈርስ›› ነውና ቤተ ክህነትና ቤተ መንግሥት፣ የተለያየ ኅብረተሰብም ባደረጉት ያላሰለሰ ጥረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሀብት የሆነው የመስቀል በዓል የዓለም መንፈሳዊ (ኢንታንጀብል) ቅርስ ሆኖ ኅዳር 25 ቀን 2006 .. በዩኔስኮ በመመዝገብ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ቅርስ ሆኗል፡፡ 
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥላ ሥር ትምህርትን ሳይንስንና ባህልን እንዲከታተል 1939 .. በተቋቋመው ዩኔስኮ እንደተገለጸው ቅርስ፣ የሚዳሰስ ግዙፍ (tangible heritage) እና የማይዳሰስ መንፈሳዊ (intangible heritage) በሁለት ይከፈላል፡፡ የዓለም የቅርስ ምዝገባ ደንብና ሥርዓት 1964 .. ሲዘረጋና የዓለም ቅርስ ስምምነት ሆኖ ሲወጣ የመጀመሪያ ትኩረት ያገኙት የማይንቀሳቀሱ ግዙፍ ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ ቅርሶች ናቸው፡፡ 
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን ስምምነት ከፈረመችበት 1968 .. ሁለት ዓመታት በኋላ ከስምምነቱ ተጠቃሚ መሆን ጀምራለች፡፡ 1970 .. እስከ 2003 .. ድረስ የተለያዩ መመዘኛዎችን ያለፉ ዘጠኝ ቅርሶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰው ልጆች ቅርሶች ተብለው ተመዝግቦላታል፡፡ 
መንፈሳዊው (ረቂቅ) ቅርስ በዓለም ደረጃ ይበልጥ ትኩረት ማግኘት የጀመረው 1980ዎቹ መገባደጃ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በተለይም 12 ዓመት በፊት ዩኔስኮ ... 2003 (1996 ..) የመንፈሳዊ ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ ስምምነት ሰነድ ማውጣቱን ተከትሎ መንፈሳዊ ቅርሶች በዓለም ደረጃ መመዝገብ ጀምረዋል፡፡ 
ኢትዮጵያም ዓለም አቀፍ ስምምነቱን በየካቲት 1998 .. የፈረመች ሲሆን፣  ስምምነቱንም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) አጽድቆታል፡፡ ዩኔስኮ በጀመረው የምዝገባ ሒደት 12 ዓመት በፊት 28 ቅርሶች ዓለም አቀፍ ዕውቅና ሲሰጥ አምስቱ ከአፍሪካ ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያ ያጠናችውና ያቀረበችው ባለመኖሩ ከዝርዝሩ ውስጥ አልነበረችበትም፡፡ 
ኢትዮጵያ የበርካታ መንፈሳዊ ባህላዊ ቅርሶች ባለቤት ሆና አለማስመዝገቧን ተከትሎ የተነሣውን ጥያቄ ለመመለስ፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች መንፈሳዊ ባህላዊ ቅርሶች ላይ ኢንቬንቶሪ ሲያደርግ ከተመለከታቸው ቅርሶች መካከል አንዱ የመስቀል በዓል አከባበር ነው፡፡
የመስቀል በዓል እንዴት ተመዘገበ?
በዓለም አቀፉ ስምምነት አንቀጽ 2.2 መሠረት መንፈሳዊ ባህላዊ ቅርሶች ምዝገባ የሚካሔደው በአምስት ምድቦች (ዶሜይንስ) ነው፡፡ እነዚህም አፋዊ ትውፊቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ ቋንቋን ተጠቅሞ የሚተላለፉ፣ ትውን ጥበባት፣ ማኅበራዊ ክንዋኔዎችና ፌስቲቫሎች፣ ሀገር በቀል ዕውቀቶችና ልምምዶች ስለተፈጥሮና ስለዓለም እና ባህላዊ ዕደ ጥበባት ናቸው፡፡
ከነዚህ ምድቦች መካከል የመስቀል በዓል  በማኅበራዊ ክንዋኔዎችና ፌስቲቫሎች ምድብ ውስጥ በመገኘቱና ከሃይማኖታዊነቱ በተጨማሪ ባህላዊ ፋይዳንም በመያዙ ዩኔስኮ በዓለም ውክልና መዝገብ ውስጥ አስገብቶ የዓለም ቅርስ እንዲሆን፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ሥራውን አሐዱ ብሎ የጀመረው፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የተለያዩ የሀገሪቱ ማኅበረሰቦችና መንግሥታዊ ተቋማት በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ በጠየቁት መሠረት ነው፡፡ 
ሥራውን ለማከናወን በትግራይ፣ በአማራ፣ በደቡብና በሌሎች ክልሎች የመስቀል በዓል አከባበር ምዝገባ (ኢንቬንቶሪ) ካካሄደና ከጠቅላይ ቤተ ክህነት በተለይም ከቅርስ ጥበቃና ምዝገባ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያና  ከማኅበረሰቡ ሙሉ ተሳትፎ ጋር ከሠራ በኋላ  በብሔራዊ ደረጃ መስቀል የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ባህላዊ ቅርስ ተብሎ በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ነሐሴ 14 ቀን 2003 .. በቁጥር 0001 ተመዝግቧል፡፡
በዓሉ ከሀገር አቀፍ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና እንዲያገኝ ለማድረግ ባለሥልጣኑ 2004 .. ጀምሮ ለሁለት ዓመታት ባከናወናቸው ልዩ ልዩ ተግባሮች በአገሪቱ ከሰሜን እስከ ደቡብ የመስቀልን በዓል የሚመለከቱ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ፋይዳዎችን ዩኔስኮ በሚጠይቀው ቅፅ መሠረት ዘርዘርና ጠለቅ ያለ ጥናት መሥራቱን የዩኔስኮ ሰነዶች ያሳያሉ፡፡ 
ለዩኔስኮ በቅድሚያ 2004 .. የቀረቡት ሰነዶች ልዩ ልዩ ሲሆኑ፣ አንደኛው በዓሉ እንዲመዘገብ የጠየቁ ተቋማትና ማኅበረሰብ ስምና ፊርማ የያዘ ነው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤትና ልዩ ልዩ መምሪያዎች፣ ሊቃውንት ጉባኤና ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ፤ በደቡብና በሰሜን የሚገኙ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ስምና ፊርማ ይገኝበታል፡፡ ሌላው በአባሪነት የቀረበው በዋናነት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ያለውን የመስቀል አከባበርና በሌሎችም አካባቢዎች ያሉትን ልዩ ልዩ ገጽታዎችን  የሚያሳይ 10 ደቂቃ ቪዲዮ ክሊፕ ነው፡፡  በከፍተኛ ጥራት የተነሡ 10 ፎቶግራፎችም በሰነድነት ቀርበዋል፡፡
ዩኔስኮ የቀረቡለትን መረጃዎች ከመረመረ በኋላ የጐደሉና መሟላት አለባቸው ያላቸውን ባለሥልጣኑ በማሟላት ለምዝገባው የመጨረሻ ውሳኔ በዋናው ዳይሬክተር ዮናስ ደስታ ፊርማ  ሐሙስ፣ መጋቢት 5 ቀን 2005 .. ልኮ ተቀባይነትን በማግኘቱ ዩኔስኮ በአዘርባጃን ባኩ ከተማ ረቡዕ፣ ኅዳር 25 ቀን 2006 .. ባካሄደው ስምንተኛው ስብሰባው የመስቀል በዓል የሰው ልጅ መንፈሳዊ ባህላዊ ቅርስ ሆኖ በዓለም መዝገብ ውስጥ መዝግቦታል፡፡

source www.ethiopianreporter.com 


No comments:

Post a Comment