የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሀገራችን
ስልጣኔ በር ከፋች
ሆና የኖረች
ከመሆንዋም በላይ ዛሬ
ላለው የዘመናዊ
ስልጣኔም መሠረት የጣለች
ባለውለታ ናት፡፡ ቀደምት
የቤተ ክርስቲያን አበው ደከመን
ሰለቸን ሳይሉ ዕረፍተ
ዘመን እስከገታቸው ድረስ ሲያገለግሉ ኖረው ቤተ ክርስቲያኒቱ አሁን ከምትገኝበት የዕድገት ደረጃ አድርሰዋታል፡፡
በዚህ ዘመንም
የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች
ሁሉ ይህን
አስበው የተማሩትን ሃይማኖትና
ሥርዓት ጠብቀውና አስጠብቀው
ለሚመጣው ትውልድ ለማቆየት
ኃላፊነት ያለባቸው መሆኑ
ግልጽ ነው፡፡
በእርግጥ ይህንን ሥርዓተ
ቤተ ክርስቲያን የማስጠበቅ ሂደት
በውስጥም ሆነ በውጭ
ሆነው ለማደናቀፍ
ሌት ተቀን
የሚዳክሩ ጠላቶች መኖራቸው
እሙን ነው፡፡