Sunday, August 11, 2013

“በ22 ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ያስተዳደረ ሙስሊም የለም” የሙስሊሞች የተቃውሞ ድምጽ




(አንድ አድርገን ነሀሴ 5 2005 ዓ.ም)፡- ባሳለፍነው ዕለተ ሀሙስ በሙስሊሞች የበዓል እለት አዲስ አበባ በብዙ ቦታዎች በተቃውሞ ስትናጥ መዋሏን የተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ኢቲቪን ሳይቀር ተቀባብለው መዘገባቸው ይታወሳል፡፡ በተነሳው ግጭት ፖሊስ ብዙዎችን ማረፊያ ቤት ማጎሩም ይታወቃል፡፡ ባሳለፍናቸው 3 ቀናት ፖሊስ ጣቢያዎች የምሳ እና የእራት ሰሀን በያዙ ሰዎች ተከበው ውለዋል፡፡ በወቅቱ የታሰበበትና የተጠና ሰላማዊ ሰልፍ መሆኑን ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ ፤ የባነሮቹ ተመሳሳይነት ፤ የመፈክሮቹ ይዘት ፤ ተቃውሞ የተነሳበት ሰአትና ቦታ ሰልፉ ታሰበበት መሆኑን ያመለክል ፡፡


እንደ ስታስቲክ ኤጀንሲ መሰረት በአዲስ አበባ ውስጥ 72 በመቶ ክርስቲያኖችና 16 በመቶ ሙስሊም ማህበረሰብ ይኖራል የሚል መረጃ ቢኖረውም የወጣው ሕዝበ ሙስሊም ግን እውን ይህ ሁሉ ሰው አዲስ አበባ ውስጥ ይኖራልን ? የሚያስብል ጥያቄ አስነስቷል ፡፡ በመሰረቱ በበዓላቸው ወቅት ከዚህ በፊት በኢድ ፤ በአረፋ እና በተለያዩ ወቅቶች የዕምነቱ ተከታዮች ወደ ገጠር የመግባት ሂደት የሚስተዋል ሲሆን በዚህ በዓል ግን የተገላቢጦሽ ሆኖ አልፏል ፡፡ሰዎች ከአዲስ አበባ ወደ ገጠር የሚገቡበት በዓል ሳይሆን ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ አዲስ አበባ የመጡበት ሆኖ ተስተውሏል ፤ ይህ ሁኔታ በቁጥር ብዛታቸውን ለማሳየት እና ድምጻቸውን እጅጉን አጉልተው ለማሰማት እንደተጠቀሙበት ለመመልከት ተችሏል፡፡ ባሳለፍነው ዓመት በ2004 ዓ.ም ሀምሌ ላይ በአወሊያ ትምህርት ቤት የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬ እዚህ ደረጃ ሊደርስ ችሏል ፡፡ በወቅቱ ጥያቄው ከአወሊያ መስኪድ ከለሊቱ ስድስት ሰዓት በግላጭ በማይክራፎን ‹‹ጅሀድ›› በማወጅ ነበር ነገሩን የቆሰቆሱት ፤ ይህ የጅሀድ ጥሪን የተቀላቀሉ በርካቶች በወቅቱ ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመጋጨት ብዙዎች መታሰራቸውን ብዙዎች ላይ ቀላልና ከባድ አደጋ መድረሱን የአንድ ዓመት ትውስታችን ነው፡፡ ይህ በሆነ ከአንድ ቀን በኋላ በአዲስ አበባ በአምስቱም አቅጣጫዎች በህዝብ ማመላለሻ መኪናዎች ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ የነበሩ በርካታ የእስልምና ተከታዮችን መታወቂያቸውን ፖሊስ እየተመለከተ  ወደ መጡበት እንዲመለሱ ሲያደርግ እንደነበርም በወቅቱ ለመመልከት ችለናል፡፡ ለምሳሌ በናዝሪት መስመር ለ3 ቀናት ያህል ከአዳማ ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ የህዝብ ማመላለሻ መኪኖች ፖሊስ መታወቂያቸው እያየ ሲፈቅድና ሲከለክል ነበር ፤ በመሰረቱ የሰዎችን ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብት ሕገ-መንግስቱ ቢፈቅድም ችግር ሲፈጠር በደቦ ከሀገር ወደ ሀገር መንቀሳቀስ ምንን ያመለክታል ? እውን እነሱ እንደሚሉት አዲስ መስኪድ ለመመረቅ ወይስ በክብሪት የተነኮሰችው እሳት ወደ ሰደድ እሳትነት ለመቀየር ?

የሩቁን ያላስተዋለ አለቃ፣ ኃላፊ ወይም መሪ፣ አስተውሎም ያላመዛዘነ፤ አመዛዝኖም በጊዜ እርምጃ  ያልወሰደ ከሆነ፤ በአደጋው ውስብስብ መረብ ውስጥ ገብቶ መተብተቡ አይቀሬ ነው፡፡ አሁንም እየተስተዋለ ያለው ይህ ነው ፤ ሲጀመር በእኩለ ለሊት በአዲስ አበባ  ‹‹ጅሀድ›› ያወጁትን ሰዎች በፍትህ መድረክ ላይ ፍርድ ስላልተሰጠ ነገሮች እዚህ ሊደርሱ ችለዋል ፡፡ እንደተጣደ ወተት መቼ ሊገነፍሉ እንደሚችሉ የማናውቃቸውን ነገሮች በዐይነ-ቁራኛ ማየት፤ ተገቢውን ማርከሻ ማወቅና በጊዜው መጠቀም ተገቢ ሆኖ ሳለ መንግሥት ሁሉን በአግባቡ እና በጊዜው ተገቢ መልስ መስጠት ባለመቻሉ እዚህም እዛም የሚሰሙ ሃይማኖታዊ መሰል ፖለቲካዊ ጥያቄዎች እየተበራከቱ ይገኛሉ፡፡

በሰልፉ ወቅት ከተነሱ በርካታ መፈክሮች ውስጥ አንዱ “በ22 ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ያስተዳደረ ሙስሊም የለም” የሚል ነበር፡፡ ይህ ጥያቄ በሀገሪቱ ላይ እስላማዊ መንግሥት እንዲቋቋም የሚፈልጉ ሰዎች ጥያቄ ነው፡፡ አሁን ሰዎቹ ሃይማኖታዊ ጭንብላቸውን እንደለበሱ የወደፊት ራዕያቸውን ለማሳካት አንዱን ጥያቄ እንዲህ ብለው አቅርበውታል፡፡ የዛሬ ዓመት ገደማ ሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ ለመመስረት ጥያቄ ማቅረባቸውም መዘንጋት የለበትም፡፡

የሃይማኖት ጉዳዮችን እንዲከታተል እና ከስር ከስር መፍትሄ እንዲሰጥ በሚኒስትር ደረጃ የተቋቋመው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ስራዎቹ ከሪፖርትነት ይልቅ መፍትሄ ሰጪ ሲሆኑ አይስተዋልም ፡፡ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ጥቂት አክራሪዎች ቤተክርስቲያን ሲያቃጥሉ ፤ ህዝበ ክርስቲያኑን በሰይፍ ሲያሳድዱ ፤  ሲብስብ የህይወትን መስዋዕትነት የሚያስከፍል ድርጊቲ ሲከውኑ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱም ሆነ መንግሥት ይህ ነው የሚባል መልስ በጊዜው መስጠት ባለመቻላቸው ሰዎቹ የልብ ልብ እንዲሰማቸው አድርጓቸዋል ፡፡ ትላንት በቤተክርስቲያኖች ላይ ለተነሳው ሰይፍ መልስ የሚሰጥ አካል ባለመኖሩ ዛሬ ዱላዎችና ሰይፎችም ወደ መንግሥት አካላት ተነጣጥረው ይገኛሉ፡፡

ከአመት በፊት በፓርላማ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሁኔታውን በግልጽ ለተወካዮች ምክር ቤት ማቅረባቸው ይታወቃል፡፡ ሱኒ ፤ ሰለፊ ፤ ወሀቢያ ምን ማለት እንደሆነ ላልገባው የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ የህዝብ ተወካይ በግልጽ አስቀምጠዋል፡፡ ከሞላ ጎደል የማይመለከታቸውን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተቋማት ከመወረፋቸው በስተቀር ምስሉ ላልገባቸው ወገኖች ግንጽ እንዲሆን ጥረዋል፡፡ ነገር ግን በተግባር የተነገረውን ነገር ለማስቆመ መንግሥት እርምጃ ሲራመድ ማስተዋል አልተቻለም፡፡ የአሜሪካ መንግሥት ከአዲስ አበባ ለስቴት ዲፓርትመንት የላከው በዊኪሊክስ ተጠልፎ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው በኢትዮጵያ ውስጥ ወሀቢያን ሰፍረውበታል አስተምህሮታቸውን ያካሂዱበታል ካለባቸው ቦታዎች ውስጥ ደሴ ፤ ሀረር ፤ ጅማ እና አርሲ ይገኛሉ ፡፡ አሁንም ከአመታት በፊት የተተከለችው የአክራሪነት ፍሬ ከሳምንታት በፊት በደሴ ፍሬ እያፈራች መሆኗን መመልከት ችለናል፡፡

ግብጽ አሁን ላለችበት ውጥንቅጡ ለወጣ ሁኔታ ትልቅቁንና የአንበሳውን ድርሻ የያዘው የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ ሕገ-መግስቱን ከሼሪያ ህግ በታች በማድረጉ እና መንግስቱም እንደ ኢራን እና መሰል ሀገራት እስላማዊ መንግሥት እንዲሆን መጣሩ ነበር ፡፡ አሁንም ኢትዮጵያ ወደዚህ መስመር እንድትሄድ የሚፈልጉ የቀን ቅዠተኞች ቀላል አይደሉም፡፡ ጥያቄያቸውም ‹‹ኢትዮጵያ ያስተዳደረ ሙስሊም የለም›› ወደሚል ተሸጋግሯል፡፡ የትላልቅ ሰላማዊ ሰልፎች ጥያቄዎች በአንድ ጊዜ የሚመጡ አይደሉም ፤ ሲጀመር ‹‹የመጅሊስ ምርጫ ይካሄድ ፤ መጅሊሱ እኛን አይወክለንም›› አሉ፡፡ ሲቀጥል‹‹ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እናቋቁም›› ተባለ፡፡ ሲቀጥል መጅሊሱ እንደማይወክላቸው የሚያሳምን የህዝብ ድምጽ እናሰባስብ አሉ፤ በህዝቡም ድምጽ መጅሊሱ ፈቅዶ ‹‹ምርጫው አካሂዱ ትችላላችሁ›› አላቸው ፡፡ ሲቀጥል ‹‹ ምርጫ መካሄድ ያለበት በመስኪድ እንጂ በቀበሌ መሆን የለበትም›› የሚል ጥያቄ አነሱ ፤ እያለ እያለ  “የታሰሩት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ይፈቱ”፣ “የደሴው ሼህ ግድያ ድራማ ነው”፣ “መጅሊሱ (ምክር ቤቱ) እኛን አይወክልም”፣ “ምርጫው ፍትሀዊ አይደለም”፣ ፣ “አህበሽ የተባለው አስተሳሰብ ይቅር”፣ “መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ አይግባ”፣ “አወሊያ የሙስሊሙ ተቋም ነው” ፤ እያለ እያለ አሁን “በ22 ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ያስተዳደረ ሙስሊም የለም” የሚል ጥያቄ ላይ ደረሰ………… ነገስ ጥያቄው ምን ይሆን?

አሁን የሀገሪቱ አስተዳዳሪ በስም አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የOnly Jesus እምነት ተከታይ ናቸው ፤ ምክትሎቻቸው ሦስቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ውስጥ ሁለቱ የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው ፡፡  የምክር ቤቱ ቁንጮ አቶ አባዱላ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ናቸው ፤ የኢህአዴግ ጽ/ቤት አላፊም ሙስሊም ነው፡፡ ከኦሮሚያ ክልል ከተመረጡ 169 የህዝብ ተወካዮች ከ70 በላዮቹ የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው ፤ (ምንጭ ፡-የምክር ቤቱ ድረ-ገጽ http://www.hopr.gov.et/HPR/faces/c/mps.jsp) በጠቅላላው ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ከ547 መቀመጫ ውስጥ ከ220 በላይ የእስልምና ተከታዮች ናቸው ፤ ካሉት 16 ቋሚ ኮሚቴዎች  አቶ ሳዲቅ አደም  የሕግ፤ የፍትህና አለስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፤ ወ/ሮ ፈቲያ ዩሱፍ  የባህል፤ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙኃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበርና ፤ ወ/ሮ አይሻ እስማኤል የባህል፤ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙኃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር ፤ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ  የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ም/ሊቀመንበር ፤ አቶ መሐመድ አብዶሽ  የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ፤ አቶ መሐመድ ዩሱፍ  አርብቶ አደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ፤  ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል  የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር በመሆን ካሉት 16 ቋሚ ኮሚቴዎች ሰባቱን እነሱ እንደተቆናጠጡት አጥተውን ይሆን ? እነዚህ ቋሚ  ኮሚቴዎች ናቸው በሀገሪቱ ውስጥ ያሉት ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የሚቆጣጠሩት ፤ በም/ቤቱ የአማካሪ ኮሚቴ አባላት የ21 ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ዘጠኙ ሙስሊሞች መሆናቸውን ሳያውቁ ቀርተው ይሆን ?  ከዚህ በላይስ እንዴት አድርገው መውረር ነው የፈለጉት?  ‹‹አንድ አድርገን›› ይችን ለመረጃ ያህል ያወጣች የሀገሪቱ የበላይ ህግ የሚወጣበት ቦታ ምን አይነት ስብጥር እንዳለው ለማመላከት ሲሆን ጥያቄውን መጠየቅ እንኳን ቢኖርበት በማን መጠይቅ እንዳለበት ከማመላከት ውጪ ነገ መሪዎቻችንና ተመራጮቻችን እነማን እንደሚሆኑም ለማሳየት ጭምር ነው፡፡ ታዲያ እነዚህ ሰዎች አላማቸው ምን ይሆን ? እነዚህ ሰዎች እንደፈጣን ቢፍቋቸው ጥያቄያቸው ሌላ ሆኖ እንደሚገኝ ልናውቅ ይገባል፡፡

የምክር ቤቱ የባህል፤ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙኃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እና ምክትል ሰብሳቢዎች ሁለት ጊዜም ሲቀያየሩ ሁለቱም የእስልምና እምነት ተከታይ ነበሩ፡፡ በተጨማሪ የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር አቶ መሀመድ ድሪል በአሁኑ ወቅት የግብጽ የኢትዮጵያ ሙሉ  አምባሳደር ለአስር ዓመታት መስሪያ ቤታቸውን አስተዳድረው ሲያበቁ በ2002 ዓ.ም በፊት ለፊት ወንበር አስቀምጠውት የሄዱት ሌላውን ሙስሊም ነበር ፤ የፓርላማው ቋሚ ኪሚቴ እና ባህልና ቱሪዝም ያስተሳሰራቸው መስመር የጠያቂ እና ተጠያቂነት ብቻ ሳይሆን እምነትም ያስተሳሰራቸው ይመስላል፡፡ (አስፈላጊ ከሆነ ከላይ እስከ መካከለኛው አስተዳደር ድረስ ምን ያህል ቦታ እንዳላቸው ከመረጃ ጋር ማቅረብ ይቻላል)፡፡ አንዱ ገበሬ ‹‹አንቺ ክምር ያለሽ መስሎሻል ተበልተሸ አልቀሻል›› ነበር ያለው

ሌላ ጊዜ እንመለስበታለን… ለዛሬ ቸር ሰንብቱ….
እግዚአብሔር አገራችንን ሰላም ያድርግልን

12 comments:

  1. ሰላም እንደምን ዋላችሁ።
    እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።

    እስልምናን በተመለከተ ይህን ሊንክ ይመልከቱ።

    http://oftsion.org/They%20Stir;%20They%20Get%20Stirred.html

    የአንድ አድርገን አዘጋጆች የኢሜል አድራሻ ከሰጣችሁኝ ፒዲኤፉን ልልክላችሁ እችላለሁ።

    እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

    ኃይለሚካኤል።

    ReplyDelete
  2. God bless you. It is a great article.

    Many people have been raising this issue for long time. Also we have been begging the government and church officials to find peaceful solution for the killing and forceful conversion of Christians. But we have been told to shut our mouth.

    When Orthodox Christians get killed and their churches and properties burn down, our government ignored our concerns. When the same thing happens to Protestants, and the fundamentalist came after the government, the issue is already out of hand.

    See what happened to Muslim majority countries including Sadi Arba. They wiped out the original Christians and other believers by using sword. If we don’t defend ourselves as our fathers did, the same thing will happen to us and our children.

    Our Ethiopian Muslim brothers and government need to clean themselves from Muslim fundamentalist ideology. Otherwise we need to defend our existence: if they kill one Christian anymore, we will pay it back by ten times; if one church burns by terrorist, they will lose ten (10) theirs. This kind of measure will only force the terrorist to think again before they do any damage against us. The government also starts stake responsibility. However if the we gave another side of our face to slap, the result will be ግብጽ ና ሳውዲ አረቢያ፥

    (በግብጽ እስልምና ብቻ አንደብሄራው አምነት ታውጆ ለኢማሞች ፤ መንግስት ደሞዝ እየከፈለ መስጊድ ይሰራል፤ ለክርስትያኖች ግን እንካን አንዲህ ሊደርግ ቤ/ክ ለመስራት የ አገርትዋ ፕሬዝዳንት መፍቀድ አለበት፥፥ ሳውዲ አረቢያ፥- ከእስልምና በስተቀር ማንኛውም እምነት መከተል አትፈቅድም፡፡ መንግስት በራሱ ወጪ መስጊድ ይሰራል ለኢማሞች ደመወዝ ይከፍላል፡፡ መንግስት ከ500 በላይ የወኑ ሰዎችን ቀጥሮ ክርስቲያኖችን እምነታንቸውን አንዲለውጡ ያደርጋል፡፡ በአገሪትዋ ወስጥ ወደ 1 ሚሊዬን ክርስቲያኖች (ሰራተኞች) ቢኖርም የጌታን ልደትም ወነ ትንሳኤ ማክበርን የተከለከለ ነው፥፥ ይች አገር የቀድም ስማዋ "Najran" ነበር ፡፡ ክርስትያኖች ከአስልምና አስቀድሞ የሚኖሩባት የነበረች)

    ReplyDelete
  3. Absolutely right!keep render us such a researched report!

    ReplyDelete
  4. Tebareku Girum Dinik yehone tsinat new
    Ethiopian Begirgir yemusilim Hager eiyadereginat new Mengist churchn Yegoda Mesilot- Bete Kirisityann ye Amara- Ye Gurage eyale liyatsefa simokir Musilimun welido Asadege Zare berasu lay metsabet yalachihut neger tikikil new- hulum Masirejachihun beki new Ahunim bertu Hara tewahidom Ye bete kihinetin neger tito yihinin meketatel yinoribetal Ahun tewahedo Hayimanotachinin -Ethiopa Hagerachinin yeminayibet Gez New enj Aba ekele teshomu -Aba ekel Tesharu Yeminilibet Gez Ayimesilegim

    ReplyDelete
  5. Esat Radio-Semayaw Part-Medirek -Wozet--Musilimun sidegifu yiwlalu Tekawam Mehon Hagerinina Hayimanotin Matsifat Neey ?Menigisit Bekeg Tekawami Begira Honew Ethiopian &tewahedon Bematsifat lay Nachew Zegebachihu sile Asdeseteg Digam Asiteyayet Setsehu Ahunim weyanenina Tekawamin Asarifulin Negeru yasegal

    ReplyDelete
  6. በክርስቲያኖች ላይ የተደረገው ከዚህ በፊት የሚያሳዝን ነው ዛሬ ላይ ይህንን እያደረጉ አይደለም ::አሁን ገና ተበሳበሳቸሁ ምን እያላችሁ ነው ሙስሊሞች እኮ መብታቸውን መጠየቅ ይችላሉ ነገር ግን የ እንምራ ጥያቄ ከሆነ ፖለቲካዊ ይሆናል የዛ ግዜ መንግስት ርምጃ ሊወስድ ይችላል ::በተረፈ እናንተ አንዳድርገኖች ግን የ ኢህአዴግን ቱልቱላ አትድገሙብን

    ReplyDelete
  7. ውድ አንድ አድርገኖች/አቃቢ ህግ ውድቅ ያደረገውን ክስ መንግስት ይዞ ብቅ በማለቱ ውነት መስሏችሁ ይሆን እናንተም ሙስሊሞችሁን መጠራጠር የጀመራችሁ?እነሱ መንግስት እንሁን አላሉም መጅሊስ ሙስሊሙን ያገልግል ልክ እንደሲኖዶሳችሁ የፈለጋችሁትን ጳጳስ በቤተክርስቲያን እንደምትመርጡት እኛም የፈለግነውን መጅሊስ በመስጅድ እንምረጥ/አወሊያ ብቸኛ የሙስሊሙ ተቋም ወደ ህዝብ ይመለስ/አህባሽ እምነትበመንግስት አፈሙዝ አይጫንብን የሚል ጥያቄ ስላነሱ ብቻ እነሱን በጥርጣሬ አይን ማየቱ ጥሩ አይመስልም!እወት ከናንተም አይጠበቅም።
    ተበድለናል ብለን ለመብታችን ድንጋይ ሳንወረዉር እየታገልን እየሞትን እየተደበደብን እየቆሰልን እያያችሁ አይደል?ውሃ እና መጠለያ በማቀበል የተባበሩን የናንተው ወንድሞች መሆኑን እረስታችሁ እንደ ወያኔ አታብጠልጥሉን!አመሰግናለሁ አስተያየቴን ስላወጣችሁት!

    ReplyDelete
    Replies
    1. I don't think you realize the reality or blindly deny it. Please look at what is good for all of us instead of being biased. We are living together. We can see the change in our social life! If you are a true Ethiopian, you need to worry for those groups behind the Muslims questions.

      You know it. We also know it as well.

      Delete
  8. እጅግ ጥንቃቄ የሚ
    ፈልግ ጉዳይ በቀላሉ መግለፃችሁ ተገቢ አይደለም……እባካቹህ ጥንቃቄ አድሬርጉ ለዉነት ቁሙ

    ReplyDelete
  9. አሸባሪዎች የሉም ማለት አይደለም ከሆነም ወያኔና አንዳን ሙስሊሞች ናቸው ነገር ግን ጥያቄያቸውን ፖለቲካዊ መልክ ማስያዝ ነውር ነው

    ReplyDelete
  10. Thank you - Andeaderegen! You guys put the reality. Some people are working to destroy our country using the religion issues. Most people don't know what is the consequence of their action. One time I was in Dessie, Wollo, for work 15 years ago. One of my Muslim co-worker told me about those people. I was socked when he told me about what this groups are thinking about Lalibela... We were concerned about the future of our country and discussed our imagination how this groups will get their upper hand and what gonna happen if they are successful. When I remember back then our discussion, it's exactly what is happening right now... You guys also give a good information, it should be unfolded the evil act of these people... They started working long time ago! We all Ethiopian should be wake up! Once it becomes out of control, there is no way to get back our country! The oppositions in diaspora also should think what they are doing! They should not be always against the gov't. There is lots of things that should considered before supporting the movements.

    BTW, let me share you what I found on one blog about this groups strategy: It's exactly what they are doing now. Everyone who loves his country should consider those points.

    አገራችን ኢትዮጲያን እንዲሁም አህጉሪቱን አፍሪካን እና መላው አለምን የእስላም አጥር ለማድረግ እና በቁጥጥራቸው ስር ለማስገባት የአጭር እና የረጅም ጊዜ እቅድ ነድፈው በታላቅ ትጋት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ ከሚንቀሳቀሱባቸው እቅዶች መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
    1. ገንዘብ ስላላቸው ኢንቨስት ማድረግ
    2. እርዳታ ሰጪ ድርጅቶችን መጠቀም
    3. ከወለድ ነፃ ባንክ በመክፈት ማበደር
    4. የተለያዩ ፀረ ክርስትና ፁሁፎችን በካሴት፤ በመፅሄት፤በመፅሐፍ፤ በቪዲዮ፤ በሲዲ በተለያዩ ቋንቋዎች ማሳተምና በነፃ ማሰራጨት
    5. በተለያዩ አረብ አገራት ያሉ የቴሌቭዥን ስርጭቶቻቸውን ለዚህ ፕሮግራም በከፍተኛ ሁኔታ መጠቀም፡፡
    6. በተለያዩ ሀገሮች ላይ መስጊዶችንና ታላላቅ የእስልምና ት/ቤቶችን መክፈት
    7. ከታላቁ የስልጣን ቦታ እስከታች ድረስ በመያዝ ለእስላማዊ እንቅስቃሴ ፍጥነት እገዛ ማድረግና የሌላውን እምነት ተከታይ ላይ ተፅእኖ መፍጠር ከተፅእኖዎቹም መካከል ቀብርና ቤተ ክርስቲያን መስሪያ ቦታ መከልከልና ወዘተ ይገኙበታል፡፡
    8. በገጠርና በከተማ ሰዎችን በገንዘብ ማስለም
    9. ሴቶችን እና ወንዶችን በጋብቻ ወደ እስልምና መቀየር
    10. በንግድ ቦታዎችና በገቢያዎች የሶላት ስፍራን መለየት እና መስራት
    11. በየመንገዱ በመስገድና ተሰብስቦ በመሄን የስነልቦና ጦርነት (Psychological War) መፍጠር፡፡
    12. በብዛት በመውለድ ከገጠር ወደ ከተማ በመፍለስ ቁጥራቸውን ከፍ ማድረግና ሼሪያን ለማሳወጅ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ፡፡
    13. በየሀገሩ ሽብር መንዛትና የበላይነትን ለመቆጣጠር መጣር፡፡
    14. ዳዋ በቡድን ስብከት መውጣት
    15. የንግድ ቦታዎችን በግለሰብ ስም በመመራት እና በሊዝ በመግዛት ለመስጊድ ማሰሪያነት ማዋል
    16. ለዘብተኛውን እና ባህላዊ እስላም እያስተማሩ አክራሪ ማድረግና ለቁርአናዊ ተልእኮ ማዘጋጀት(ሱረቱ አል-አንፋ 8፡39).
    17. ፖለቲካውን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት ማድረግ እና ገዢውን ፓርቲ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በመንዛት የተጀመሩትን ልማቶችን በማንቋሸሽ እንዲሁም ሰንደቅአላማ(ባንዲራ) በማቃጠል እና በመቅደድ ሀገራዊ ስሜትና ክብርን የሚጎዳ ነገር መፈፀም እንዲሁም ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን ሀይማኖትን ከፖለቲካ ጋር መቀላቀል
    18. ሰዎችን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ስለ እስላማዊ እንቅስቃሴ ማስተማር
    19. ሰዎችን በችግራቸው በመርዳት እና ህፃናትን ሰብስቦ በማሳደግ ወደ እስልምና መቀየር
    20. ምንም አይነት እስልምና በሌለበት መስጊዶችን መስራትና ሚሽነሪ ማሰማራት
    21. ወጣቶችን በመመልመል ከቁርአናዊ ተልእኮ ዝግጁ ማድረግ
    22. ክርስትናን ከምእራባዊያን ቅኝ ገዢዎች ጋር በማገናኘት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ መንዛት
    23. አጋጣሚውን ሁሉ በመጠቀም እስልምናን ለማስፋፋት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ፡፡
    24. እስላማዊ የትብብር ኮሚቴዎች በሀገራት መካከል ማደራጀት
    25. አክራሪ እስላማዊ ያልሆኑ መንግስታትን በአክራሪ እስላማዊ መሪዎች ለመተካት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ፡፡ ለምሳሌ በ 1986 ዓ.ም በኢትዮጲያ ውስጥ የግብፁን መሪ ሁስኒ ሙባረክን ለመግደል ጥረት ማድረግ እንዲሁም በቅርቡ የተገደሉትን የሀይማኖት እና የመቻቻል አባት የሆኑትን የደሴው ሼክን ማስገደልና ሌሎችንም እቅድ ውስጥ በማስገባት መንቀሳቀስ፡፡

    ReplyDelete
  11. 26. ቁጥራቸው አናሳ በሆነበት ሀገራት በፍጥነት ማደግና የወደፊት ህልማቸው ሼሪያን ለማሳወጅ ከፍተኛ ጥረት እና ጥድፊያ ማድረግ፡፡
    27. በጎሳ ወይም በዘር ሰዎችን ወደ እስልምና መቀየር ለምሳሌ ጃዋር መሀመድ
    28. በወቅታዊ ችግሮችና ፖለቲካዎች መካከል ጣልቃ በመግባት በሮችን ለዚህ ተልእኮ ማስከፈት
    29. የገንዘብ እጥረት ያለባቸውን የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በገንዘብ በመደገፍ በመቀናጀት መስራት፡፡
    30. ሰዎችን ወደ አረብ ሀገር በማስወጣትና ስራ በማስያዝ ነፃ የትምህርት እድል በመስጠት ወደ እስልምና መቀየር
    31. በአፍሪካ ያሉትን ባህላዊ ሀይማኖት ተከታዮችን ግብ አድርጎ መንቀሳቀስ
    32. የሕዝብ ብዛት የሚገኘው በገጠር ስለሆነ በተለይ ዋናውን ትኩረት ገጠር ላይ ማድረግ
    33. በተቻለ መጠን መሀመድን መፅሐፍ ቅዱሳዊ ለማድረግ የተለያዩ ፅሑፎችን መፃፍና ማሰራጨት
    34. ታላላቅ የእስልምና ት/ቤቶችን በየቦታው መክፈት
    35. ከገጠር ወደ ከተማ በመፍለስ የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን መግዛት አንድ እስላም በእምነት እሱን ከማይመስል ሰው ጋር የልብ ቅርርብ እንዳያደርግ ማስተማር (ሱረቱ አልማይዳ 5፡51)
    36. በአንዳንድ ስፍራ ቤተክርስቲያኖችን እና የክርስቲያኖችን ሬሳ ቆፍሮ በማውጣት ማቃጠል እና ክርስቲያኖችን መግደል፡፡
    37. የብዛታቸውን መረጃ (statistical information data) በተመለከተ ሀሰት የሆኑ ዘገባዎችን ማሰራጨትና የማዛባት ስልት መጠቀም እና የስነ ልቦና ጦርነት ማካሄድ (32.8%ናቸው በኢትዮጲያ)፡፡
    38. በቴኳንዶ ት/ቤቶች ውስጥ በስውርና በግልፅ ወጣቶችን በማስተማር ለጅሀድ ጦርነት ዝግጁ ማድረግ
    39. እያንዳንዱ እስላም አለማቀፋዊ እስላማዊ አስተሳሰብ እንዲኖረው ማስተማር
    40. የአረብኛ ቋንቋ ትምህርት የማስፋፋት ስልት
    41. ቤተክርስቲያንን የመርገም ስልት
    42. ታሪክን የማዛባት ስልት
    43. የእስልምና ታሪክን የመድገም ስልት
    44. የቁርአን ትምህርት ካሪኩለም (ስርአተ ትምህርት)ውስጥ ይግባልን ማለት
    45. የሳምንቱ የእረፍት ቀን እሁድ መሆኑ ቀርቶ አርብ ይሁንልን ማለት
    46. የጦር መሳሪያ የማደራጀት ስልት
    47. መረጃ የሚለዋወጡባቸውን ሚስጥራዊ ቤቶች የመጠቀም ስልት
    48. በቴሌቪዥንና በሬዲዮ ክርስትናን የማጥላላት ዘዴ
    49. በክርስቲያኖች ተጨቁነናል የሚል ጩኸት በተደጋጋሚ ማሰማት
    50. ከተሞችን የመውረር ስልት (ማጥለቅለቅ)
    51. መረጃዎችን የራስ የማድረግ ስልት (የግል ሬዶዮ ፕሮግራም እና ማህበራዊ ድህረ ገፆችን
    (Face Book, Twitter And Skype) በመጠቀም መረጃዎችን ማቀበል፡፡
    52. ሙስሊሞች በኢኮኖሚ የበላይነት እንዲኖራቸው የማገዝ ስልት
    53. የኢንቨስትመንት ፤የንግድ ሽርክና የዲፕሎማሲያዊ ስልት
    54. በሌሎች አረብ ሀገራት መደገፍ( ሳውድአረቢያ ፤ኩዌይት ፤ ኳታር ፤ሊባኖስ ፤ኢራን ፤ፓኪስታን፤ ቱርክ ፤ማሌዢያ ፤ሶማሊያ፤ ሱዳን ፤ግብፅ እና አልጄሪያ)

    ReplyDelete