Sunday, July 28, 2013

‹‹ከነበሩት ጳጳሳት የባሰ እንጂ የተለየ ሥራ አልሰራንም ሥራችን ይመሰክራል፡፡›› አቡነ ጢሞቴዎስ

   
 (አንድ አድርገን  ሐምሌ 21 2005 ዓ.ም )፡- ከዛሬ 13 ዓመት በፊት ህዳር 8 1992 ዓ.ም አቡነ ጢሞቴዎስ ከ”ምኒልክ መጽሄት” ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ዘወር ብለን ለናንተው ለማቅረብ ወደድን ፤

ጥያቄ፡- ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተመርቀው የሚወጡ አንዳንድ ወጣቶች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን በመክዳት ወደ ሌላ ኃይማኖቶች ሲለወጡ ይስተዋላል፡፡ ተማሪዎቹ ተመርቀው ሲወጡ ኃይማኖታቸውን ለመለወጥ የሚገደዱበት ምክንያት ምንድነው? በትምህርት አሰጣጡ ላይ እምነታቸውን የሚያስለውጡ ትምህርቶች ይሰጣሉ ወይ?
አቡነ ጢሞቲዎስ፡-  አሉባልታ ይመስለኛል አስተማሪዎቹ በጣም የታወቁ የኦርቶዶክስ ሊቃውንት ናቸው፡፡ ትምህርቱም የተጣራ ነው፡፡ ነገሩ ያለው ከስድስተኛው ጥያቄ ጋር ነው ፡፡ ይኽውም ተወራ እንጂ የካደ ልጅ ካለ ባውቀው ደስ ባለኝ ነበር፡፡

ጥያቄ፡- በስልጣን ላይ በተቀመጠ መንግስት በአደባባይ የሚሰራቸውን ስህተቶች የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ከፓትርያርኳና ከጳጳሶቿ የነቀፈችበትና የእርምት እርምጃ የወሰደችበት ጊዜ የለም ይባላል፡፡ በዚህ መሰረትነ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፓትርያርክነት የሚገኙትና ሌሎቻችሁም ጳጳሶች ቀደም ብለው ከነበሩት ጳጳሶች የተለየ ነገር አልሰራችሁም የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ በዚህ ላይ የእርስዎን አስተያየት ቢያካፍሉን?
አቡነ ጢሞቲዎስ፡ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የሚሰራቸውን ስህተቶች ምን ዓይነት መሆናቸው ባይገለጹም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክና በጳጳሶቿ የነቀፈችበትና የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ የጠየቀችበት ጊዜ የለም የሚባለው ትክክል ነው፡፡ ለምን ቢሉ ከብጹእ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ በስተቀር ማንም ፓትርያርክና ጳጳስ መንግስትን አጥፍተሀል ተመለስ ያለ አልነበረም፡፡ አሁንም የለም፡፡ ምክንያቱም የቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል በሩ ሲታጠር ማንም የተነፈሰ አልነበረም፡፡ አሁንም የቤተክርስቲያኒቱ  መብት በተለየ ቦታ ጊዜ ሲደፈር ማንም የቤተክርስቲያን መሪ የተነፈሰ የለም፡፡ ይልቁንም መንግስት ለራሱ ጸጥታ ሲል በእያንዳንዱ ቦታ ጣልቃ ሲገባ ይታያል፡፡ ታዲያ እንዲህ ያለ ዝምታ ለመንግስት የሚመች አይመስልም፡፡ እንዲያውም የቤተክርስቲያኒቱን መብት ከተጠበቀ ጸጥታ ይሰፍና መንግስትም በሰላም ይገዛል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የቤተክርስቲያን መሪዎች መንግስት እዳይነቀፍ ብለው ቤተክርስትያኒቱና ክርስትያኖች መብታቸው ሲነካ ዝም ብለው ካዩ የእግዚአብሔርን አደራ አልጠበቁም ፤ መንግስትንም ባለመምከራቸው ጎዱት እንጂ አልጠቀሙትም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከነበሩት ጳጳሳት የባሰ እንጂ የተለየ ሥራ አልሰራንም ሥራችን ይመሰክራል፡፡

ጥያቄ ፡- የቤተክህነት ቀዳሚ ተግባር መንፈሳዊ ስራ እንዲጎለብት ማድረግ ነው፡፡ ይሁንና በውስጡ በከፋ ሽኩቻዎች እየታመሰች ትገኛለች ፤ እንዲህ አይነት ውጥረት ውስጥ ያለ መንፈሳዊ ድርጅት አንዴት አድርጎ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት ይችላል? በዚህ ላይ አስተያየት ቢሰጡን?
አቡነ ጢሞቲዎስ፡- እርግጥ የቤተክህነት ቀዳሚ ተግባር መንፈሳዊ ስራ እንዲጎለብት ከዚያም በላይ የበጎ ምግባር አብነት መሆን ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከእግዚአብሔር የመጣው መዓት እግዚአብሔር መዓቱን እስኪመልሰው ድረስ ከመጸለይ በስተቀር ምንም ለማድረግ አይቻልም፡፡

‹‹በአሁኑ ሰዓት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ አስተዳዳሪነታቸውን ባሳለፍነው ሳምንት ብጹዕ አቡነ ጤሞቴዎስ መነሳታቸው ይታወቃል ፤ እስኪ ሰው በማንሳት እና ሌላ በማስቀመጠ የሚመጣ ለውጥ የሚመለስ መልስ እንዳለ እናያለን… ካቶሊካውያን በአዲስ አበባ በአንዱ ጫፍ ከሶስት መቶ ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር በላይ የሚያወጣና ደረጃውን የጠበቀ በቫቲካውያን የሚደገፍ  ከፍተኛ ዩኒቨርሲቲ እያሰሩ በሚገኙበት ሰዓት እኛ በአንዲቱ ደሳሳ ኮሌጅ ከአብነት ትምህርት ቤት መሻሏን ትምህርት ሚኒስቴር አልመሰክር ያላት  ተዝረክርከን ያዝረከረክናት ኮሌጅ ላይ እዚህ መድረሳችን ይገልማል፡፡››


·         አስፈላጊ ከሆነ ሙሉ ቃለ መጠይቁን ለማቅረብ እንሞክራለን

የነጀማነሽ ማህበር ከነብዩ ኤልያስ ለፓትርያርኩ አመጣን ያሉትን መልእክት ይፋ አደረጉ


(Addis Admass ) አርቲስት ጀማነሽ ሰሎሞንን ያካተተው የማህበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ አባላት፣ ለፓትርያርኩ ያመጣነውን “የቅዱስ ኤልያስ” መልእክት የሚቀበለን አጥተናል በማለት ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ አደረጉ፡፡ በብሔረ ሕያዋን ይኖራል ከተባለው ነብዩ ኤልያስ ተልከን መልእክታችንን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ እንዳናደርስ የጥበቃ አባላት ከልክለውናል ያሉት የማህበሩ አባላት፤ ከመልዕክቶቹ መካከል ትክክለኛው ሰንበት ቅዳሜ ስለሆነ በእሁድ ፋንታ በብሔራዊ ደረጃ ታውጆ መከበር ይገባዋል የሚል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ “ኦርቶዶክስ” የሚለውን ስያሜ የሚቃወሙት የማህበሩ አባላት፤ “ተዋህዶ” የተሰኘው እምነት ጥንታዊ የጉባኤ እለታትን ጨምሮ አራት የቅዱሳን መታሰቢያ ቀናት በብሔራዊ በዓልነት ለማስከበር ፓትሪያርኩ ከፌደራል መንግስቱ ጋር መነጋገር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

ቅዱስ ኤልያስ በ2000 ዓ.ም ከመንግስተ ሰማያት ወደ ቅድስት ምድር ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት አስተምሯል ያሉት የማህበሩ በቅዱስ ኤልያስ፣ በሄኖክና በመልከፄዴቅ የተባረኩ በመሆናቸው እውቅና ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል፡፡ የዳዊት መዝሙር ላይ በመመስረትና፣ ፓትሪያርኩ የቅዱሳን ሊቃውንት ክብረ በዓላት በብሔራዊ ደረጃ ለማስከበር በቦታው መገኘት ይገባቸዋል በማለት ፓትርያርኩን አሳስበዋል፡፡ የማህበር አባላት በኢትዮጵያ ደረጃ መስከረም 7፣ 12፣ 21 እና የካቲት 21 ብሔራዊ በዓላት እንዲሆኑ ነው ፓትሪያሪኩን ለመጠየቅ የፈለጉት፡፡

Wednesday, July 17, 2013

የተክለሀይማኖት አስተዳደርና ምዕመናን እየተወዛገቡ ነው


(Addis Admass :- ) የደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ጊዜያዊ የልማት ግንባታ፤ በአስተዳደሩ፣ በምዕመናኑና በሠንበት /ቤቱ መካከል ውዝግብ አስነሳ፡፡ ቤተክርስቲያኑ በዋናው አስፋልት መንገድ በኩል 12-20 የሚደርስ ህንፃ ሰርቶ እንዲጠቀም ቢፈቀድለትም ዋናውን ግንባታ ለመጀመር አቅሙ ስለማይፈቅድ ጊዜያዊ ገቢ ማስገኛ ሱቆች ተሠርተው ቤተክርስቲያኑ እንዲጠቀም የተወሠነው ውሳኔ ለውዝግቡ መነሻ እንደሆነ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ ጊዜያዊ ልማቱን ቤተክርስቲያኑ ባለው በጀት ሠርቶ መጠቀም እየቻለ፣ በደብሩ አስተዳደርና ዋና ፀሀፊ የውስጥ ለውስጥ ድርድር ለአንድ ባለሃብት መሠጠቱን በመቃወማችን ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰብን ነው ብለዋል - ምዕመናንና የሰንበት /ቤት ተወካዮች፡፡የደብሩ አስተዳደርና ዋና ፀሀፊው ከባለ ሀብቱ ጋር በመደራደር አንድ ትልቅ መጋዘንና 10 ሱቆችን ለራሱ፣ ሌሎች 10 ሱቆችን ለቤተክርስቲያኑ ሠርቶ ሊያስረክብ እንዲሁም ለራሱ የሠራውን 10 ዓመታት በነፃ ሊጠቀም መዋዋላቸው አግባብ አይደለምሲሉ ምዕመናንና የሰንበት /ቤት ተወካዮች ተቃውሟቸውን ገልፀዋል፡፡

Monday, July 15, 2013

በዋልድባ ገዳም የሚገኝው የሥኳር ፕሮጀክት ነዳጅ ማራገፊያ የመሬት መንሸራተት አጋጠመው



(አንድ አድርገን ሐምሌ 8 2005 ዓ.ም)፡- መንግሥት በአምስት አመቱ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዘመኑ ውስጥ በ32 ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር በላይ  አስር የሥኳር ፋብሪካዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ውስጥ እገነባለሁ ብሎ በእቅድ መያዙ ይታወቃል ፤ መንግሥት ከፍተኛ አትኩሮት ከሰጣቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ በኋላ የሥኳር ፕሮጀክቶቹ በሁለተኝነት ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ ብዙ ውዝግብ ያስነሳው ፤ ብዙ ዋጋ ያስከፈለው አሁንም እያስከፈለ ካለው የሥኳር ፋብሪካ ውስጥ በዋልድባ ገዳም የሚገነባው አንዱ ነው፡፡ እነዚህን ፕሮጀክቶች በበላይነት የሚመራው መቀመጫው መሀል ካሳንቺስ ያደረገው በአቶ አባይ ጸሀዬ የሚመራው የስኳር ኮርፖሬሽን መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከፕሮጀክቶቹ አንዱ እና ዋንኛው የሆነውን የዋልድባን የስኳር ፋብሪካ ግንባታን በመቃወም ብዙ መነኮሳት ከበአታቸው በመሰደድ በያሉበት ሆነው ስራውን እየተቃወሙ ይገኛሉ ፤ ፕሮጀክቱን ለመስራት በየጊዜው የሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የመጡ ኮንትራክተሮች ውል በመቋጠር እንደገና በመፍታት አሁን ላይ ሶስተኛው ስራ ተቋራጭ ስራው እያካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ 

ቤተክርስቲያን ላይ ብዙ ጉዳት ያደረሰው ቀበሮ መነኩሴ በእስርና በገንዘብ ተቀጣ


(አንድ አድርገን ሚያዚያ 1 2005 .)በደብረ ብርሐን ከተማ‹‹አባ›› በረከት የሚባል ሰው በገዳማት እና በአድባራት ላይ ብዙ ጉዳትእንዳደረሰ ገልጸን ከወራት በፊት መጻፈችን ይታወሳል፡፡ ‹‹አባ›› በረከትመጀመሪያ ጎንደር ይኖር የነበረ ከዚያም ደንጨት ዮሐንስ ገዳምሲያገለግል የነበረ ሰው ሲሆን ከመንዝ አካባቢ እንደመጣ የጀርባ ታሪኩይናገራል ፡፡ የካቲት 2004 . በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በደብረብርሐን ከተማ በደብረ ማዕዶት ቅድስት አርሴማ ገዳም በመግባትሲያገለግል እንደነበር መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ገዳም የሚመጡበርካታ እህቶችን በማታለል ዝሙት ለመፈጸም ሲንቀሳቀስስለተደረሰበት ይህን ድርጊቱን እንዲያቆም ከወንድሞች ምክርተሰጥቶትም ነበር፡፡  በቤተመቅደስ ውስጥ ድፍረትና ክህደትየተሞላበት የአማኙን እምነት የሚቀንስና ለትልቅ ድፍረት የሚያደፋፍርእንቅስቃሴዎች ሲያደርግ እንደነበር በጊዜው በቦታው የነበሩ የአይን እማኞች  ገልጸዋል ፡፡ አርሴማ ገዳምላገለግል ነው ብሎ ሲገባ አብራው የመጣች ወለተ መስቀል የምትባል  መነኩሴ የነበረች ሲሆን  በገዳሙበነበረው ቆይታ ለገዳማውያን አገልጋይ ካህናት ‹‹ከአንድ እናት ማህጸን የወጣን እህቴ ነች›› እያለ ሲያወራ እናሲያስወራም ነበር ፡፡(ሴትየዋ በአሁኑ ሰዓት ከ‹‹አባ›› በረከት የልጅ እናት ሆናለች)፡፡

Tuesday, July 9, 2013

ተሀድሶያውያን በክብረ መንግሥት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ‹‹መተዳደር የምንፈልገው በቦርድ ነው›› በማለት ለመንግሥት ማመልከቻ አስገቡ




(አንድ አድርገን ሐምሌ 3 2005 ዓ.ም)፡- በአሁኑ ሰዓት በሰፊው የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ መልሶ በማገርሸት ከሚገኝባቸው አጥቢያ አብያተ ቤተክርስቲያናት መካከል ሐረር ቅዱስ ሚካኤል ፤ ሆሳዕና ቅዱስ ሚካኤል እና ክብረ መንግስት ቅዱስ ሚካኤል ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ከእነዚህ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት መካከል ግን የክብረ መንግስት ቅዱስ ሚካኤል በከፍተኛ ሁኔታ በማገርሸቱ ምክንያት በቅዱስ ሲኖዶስ አንተዳደርም የሚሉ ጥቅት ግለሰቦች ( በአሜሪካው የተሐድሶ ክንፍ መሪቀሲስ’’ ተስፋዬ መቆያና እና የዱባዩ የተሐዲሶ ክንፍ መሪቀሲስተስፉ የሚመሩ የተሐዲሶ መናፍቃን) በአሁኑ ጊዜ ለክብረ መንግሥት የመንግሥት አካል የምንተዳደረው በቦርድ ነው በማለት ማማልከቻ አስገብተዋል፡፡