Wednesday, January 2, 2013

አቶ በጋሻው ደሳለኝና አቶ ያሬድ አደመ ያለፍቃድ የሄዱበት ደብር በጉሸማ እና በፖሊስ እንዲመለሱ ተደረገ

  • “ወንጌል ያልገባቸው የኦሪት ሰዎች” አቶ በጋሻው የአካባቢው ምዕመን የተናገረው

(አንድ አድርገን ታህሳስ 24 2005 ዓ.ም)፡- ቅዱስ ሲኖዶስ ባለፈው አመት ባደረገው ጉባኤ በቤተክርስቲያናችን ውስጥ መናፍቃን ሆነው በውስጣችን የተሰጎሰጉትን ሰዎች ማውገዙ ይታወቃል ፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ የአቶ በጋሻው ደሳለኝ እና መሰሎቹን ጉዳይ ለማጣራት በማለት ለዚህኛው ዓመት መሸጋገሩን ይታወሳል ፤ በአሁኑ ሰዓት 6ተኛ ፓትርያርክ ወይስ እርቀ ሰላም በሚባልበት ወቅት አቶ በጋሻው ደሳለኝ በጎንደር አዘዞ ሎዛ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ባለፈው ቅዳሜ ማስተማሩ ለማወቅ ተችሏል ፡፡ ይህ ሰው የቀድሞ ስራዎቹ እስኪፈተሹ እና በሊቃውንተ ጉባኤ ውሳኔ እስኪሰጥበት ድረስ በየትኛውም አውደ ምህረት ላይ እንዳይቆም የተደረገ ሰው ቢሆንም አሁን ቤተክርስቲያኒቱ ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት በቦታው ቀድሞ ካፈራቸው ሰዎች ጋር በመነጋገር ከቤተክህነትና ከሀገረ ስብከቱ  ፍቃድ ውጪ ሊያስተምር ችሏል ፡፡ ቅዳሜ አስተምሮ በሚቀጥለው ቀን ያለ ፍቃድ ለምን አስተማረ? በማለት በተነሳ አለመግባባት በአካባቢው ወጣቶች ጉሸማ እና በፖሊስ አማካኝነት ቦታውን ለቆ እንዲሄድ የተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡በወቅቱም ያሬድ አደመ ለሚጠየቀው ጥያቄ የንቀትና በማሾፍ መልኩ መልስ ሲሰጥ ተስተውሏል ፤ ወጣቱም “እነዚህ ሰዎች በባለፈው የሲኖዶስ ጉባኤ እስኪጣራ ተብለው ጉዳያቸው በእንጥልጥል ያለ በመሆኑ ከሊቃውንት ጉባኤ ውሳኔ በፊት እንዳይመጡብን ፤  እነዚህ ሰዎች በሀዋሳ ምን  እንዳደረጉ እናውቃለን ለምን መጡብን?” በማለት የአካባቢው ወጣቶች ጥያቄ አንስተዋል ፡፡ አቶ ያሬድ አደመን “ እናውቅሃለን እኮ በሌላው ሃገር ሃይማኖትን ሳይሆን ገንዘብን እየሰበክ እንደዘረፍክ ከዚህ ምን ፈልገህ መጣህ?” በማለት ጥያቄ ሲጠይቁት አቶ ያሬድም ለተጠየቀው ጥያቄ በማሾፍ መልስ በሚሰጥበት ጊዜ ወጣቶቹ ብስጭት ውስጥ በማስገባቱ ወደ አልሆነ አምባጓሮ ሁኔታው እንደተቀየረ ለማወቅ ተችሏል ፤ በጊዜው ፓሊስ በቦታው በመገኝት ሰዎቹን ወደ መጡበት  እንዲመለሱ አድርጓል፡፡ ከዚያ ወጣቶቹ ከንቲባ ጽ/ቤት ድረስ በመሄድ “እነዚህ ሰዎች እዚህ ምንም የላቸውም በሰላም የቆየውን ምዕመን ሁለት ቦታ ሊከፍሉትና የአካባቢያችንን ሰላም ሊያሳጡን የመጡ ሰዎች በመነሆናቸው የአካባቢው አስተዳደር አውቋቸው ወደዚህ አካባቢ እንዳይመጡ የበኩሉን ያድርግልን” በማለት አመልክተው ፡፡ ከንቲባ ጽ/ቤቱም  ከሀገረ ስብከቱ እና ከቤተክህነት ውጪ ያለፍቃድ  የአካባቢውን ሰላም እንደ ሀዋሳው ሊያናጉ የሚፈልጉ ሰዎችን ከህዝቡ እና ከቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር ጋር በመነጋገር መልክ እንደሚያስይዘው ቃል ገብቶላቸዋል፡፡
  አሁንም እያየንና እየተመለከትን ያለነው ነገር በተሀድሶነት የሚንቀሳሱት ሰዎች እንደ እባብ የሞቱ ይመስላሉ እንጂ ጊዜ ጠብቀው ፤ ወቅቱን አገናዝበው እንደሚነሱ ነው ፡፡ በየሀገረ ስብከቱ ያለ ሀገረ ስብከት ፍቃድ ማንም የትኛውም ቤተክርስትያን መጥቶ ማስተማር እንደሌለበት የሚታወቅ ቢሆንም እነርሱን በመሰሉ ሰዎች አማካኝነት አሁንም የቀድሞውን ውዥንብር ለመፍጠር ያለመታከት እንደሚሰሩ ማሳያ ምልክት ነው፡፡ ይህ እንቅስቃሴ ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በጣም በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ እና የጠፋ ቢመስልም አፈር እንዳልገባ ግን በየጊዜው በአሳቻ ሰዓት የሚደረጉ እቅስቃሴዎች ማወቅ ይቻላል ፡፡አቶ በጋሻው ዳሳለኝ እና ግብር አበሮቹ በስተመጨረሻ ሲባረሩ አቶ በጋሻው “ወንጌል ያልገባቸው የኦሪት ሰዎች” ብሎ ሲናገር ተደምጧል፤

14 comments:

  1. LEloch Tomarioch lela Lelawen yebetekerstian Guday Yeketatelu Enante Endezi ayenetune Yemenafkan Enkesekasa Update aregun it is very important to protecte our church from them so please Koyetw bezu gudate selemiadersu hulume akababiwen benkate kemanfekan "Tadesowoch" neketo yetbeke enantem kale eywet yasemalen and GETA EGEZIABHERE Nestu haymanotachenen kemenafikan yetebkelen amen.

    ReplyDelete
  2. "ወንጌል ያልገባቸው" ነው ያለው ነገር ግን በመሰረቱ ወንጌል ያልገባው እሱና መሰሎቹ ናቸው እናት ቤተ-ክርስትያን ላይ በክፋት የተነሱ መናፍቃን እነሱ አስተምረው ነው ወይ ቤተ-ክርስትያን እየሁሉ ዘመን ያስቆጠረችው

    ReplyDelete
  3. የወቅቱን አጋጣሚ ተጠቅመው ብዙ ጉዳት ሊያደሱ ስለሚችሉ በተቻለ መጠን አካባቢውን በንቃት ከተሃድሶ መናፍቅ ይጠብቅ እላለው

    ReplyDelete
  4. ato begashaw ena lebaw yared be awassa adarash keftew eyecheferu ena eyascheferu endehone kesemonun ke wede awassa semahu ewunet new?ebakachuh enezihn ebaboch teketateluachew.

    ReplyDelete
  5. gib kemayawkut ager hedo korbet antifulgn ale alu,lemn belu secoretm leader.

    ReplyDelete
  6. that's true. yes they are giboch!

    ReplyDelete
  7. Please try to update us about those thadiso enkisikase. What is new about the patroit M/r Zemedekun who exposed them well with video and Audio evidences. Is he still servoing at prison? I pray that he out and work for the chruch again. It is very important to expose these blind people who want to reform our chruch. Aba selama blog is doing as much as they can to ruin our dogma...I guess those blog are supported by guys like Begashaw, so called Mul,uigeta w/geberiel etc. They will never sucessed while MK is there to defend them in all aspect. We are with you and protect our chruch from those protestant people but who pretend as pro-ortodox

    ReplyDelete
  8. Yihn sitsamu lataminu tichilalachu Ato Begashaw ina maselochu behawasa Filimon yemibal adarash bemakfat eyechafaru ina iyaschafaru naw betalay yewahun wata bemanafikan pastaroch iyesusin malemamed yemibal siltana iyasatu naw

    ReplyDelete
  9. What is wrong guys? are you guys opposing the preaching of the bible? This web site is anti Christ.

    ReplyDelete
  10. tro new yebatkrstyan amlak yefradebahw men enlaln lela

    ReplyDelete

  11. 01/03/13
    ይድረስ ለደጀ ሰላም
    በእግዚአብሔር ፀጋ ሰላምና ጤና የምመኝላችሁ አንድ አድርገኖች እንደምን ሰንበታችኋል?
    ይህቺን አጭር መልዕክት ለንባብ ታበቁልኝ ዘንድ ከይቅርታ ጋር እለምናችኋለሁ።
    ደጀ ሰላሞች ማንም ሀሳቡን እንዲገልፅ ፍቃዳችሁ እስከሆነ ድረስ ስብዕናን ያልነካ ግን እናንተ ለቤተ ክርስቲያን እንቆረቆራለን እንደምትሉት
    ሁሉ ሌላውም የተሰማውን የመግለፅ መብት እስከሰጣችሁት ድረስ የግድ እናንተን ደግፎ ወይም እናንተ የምትፈልጉትን መፃፍ አይጠበቅበትም።
    ሰለዚህ ከአደራ ጋር ወደፊት የትኛውንም ደግፎ ቢፅፍ ለአንባቢያን የማድረስ ኤቲክሱን እንዳትዘነጉ ላሳስብ እወዳለሁ። የናንተም ሆነ የአንድ አድርገን
    ተከታታይ ነኝ ከአሜሪካ ለሁለታችሁም መልካም የአገልግሎት ዘመን ይሁንላችሁ። አመሰግናለሁ

    ReplyDelete
  12. እነዚህ ሌቦች በሐዋሳ የሰንበት ት/ቤቱን ለሁለት እንዲከፈል አድርገውታል :: ለአካባቢው እንግዳ ብሆንም አባቶችና ሌሎች ትላልቅ ሰዎች ጠይቄ እንደተረዳሁት ባለፈው ዓመት እዛው ቆመው ነው ወጣቱን እርስ በራሱ ያጨፋጨፉት:: ና ተብሎ:: ስለዚህ ቤታችንን በንቃት እንጠብቅ::

    ReplyDelete
  13. ENANTE YEWALDIBAN TILALACHHU EZIHU BE AMERICA COLUMBUS DEBRESELAM KIDUS GEBRIEL CHURCH BE ASTEDADARINET YETEKEMETUT KESIS YARED GEBREMEDHIN YEBETEKRISTIANUN MEMENANINA MEZEMRAN BEMEKEFAFELINA LELOCH BEAKRABIA BALU CHURCHOCH LEMIN HEDACHU BEMALET MEZEMRANUN ENDAIZEMRU BEMEKELKEL, MEMANANUN BEMEKEFAFEL BE BECHURCHU WISTE FIKER ENDAYNOR BE MEDREK LAY TIKEKELEGNAWN YE WENGEL TIMIHERT KEMASTEMAR YILEK BMESADEB MEMENANEN KECHURCHU ENDIGELELUNA LEMENAFIKAN EYEDERAGUACHEW YIGEGNAL. BETELEYEM YE BETEKRISTIANU NIBRETENA GENZEBIM EMDIBAKIN KEFTEGNA ASTEWSWO ADIRGEWAL. LECHIGIRU MEFTHE ENDIHON KEMEMENANU TYAKE BIKERBIM FEKADEJNA HONEW LEMEWEYAYETINA MEFTHE LEMESHAT ALTEGEJNUM. CHIGRU EYESEFA HEDO CHERCHU KEMEZEGATU ENA MEMENANU KEMEBETATENU BEFIT MEHBERE KIDUSAN(YE MEAHBERU ABAL SILEHONU) MEFTIHE ENDIFELEGENA LEWEYYETEM MEDREK ENDIKEFT ENASASIBALEN. KEMEMENAN

    ReplyDelete
  14. YIDRES LE LE ABA SELAMA

    EJNA BE AMERICA COLUMBUS DEBRE SELAM KIDUS GEBRIESL CHURCH YEMNIGEJN MEMENANM TEMESASAY BISOT ALEN, YEHEWM YE DEBRU ASTEDADARI YEHONUT KESIS YARED G/MEDHIN TIMHERTATCHEWNA TEGBARACHEW BEFSUM YEMAYGENJ HONO MEMENANINA MEZEMRANIN LEMANAFIKAN MESALEKIA EYADEREGUT YIGEJALU, YIHEWM BATIBIA BALUT DEBROCH LEMIN HEDACHU ZEMERACHU LEMIN TABOT ANEGESACHU BEMALET DIRO YEKEREWN YE AMBAGENENET BAHRIY BEMASAYET EJNAW DEMOZ EYEKEFELNACHEW ESACHEW FELACH KORACH HONEWBINALINA LEZIHUM MEMENAN LINAGEGRUACHEW BIFELGUM BEMESADEB ABAREWCHEWAL, SILZIH MEMANANU KEMEBETENU BEFIT BETCRISTIANACHININ ENADEN. YE BETEKRSTRIANU GENZEB ENA NIBRET EYETEZEREFE NEW. LEWYEYET MEDEREKUN KIFT ADIRGULEN. YEMICHAL KEHONE MEFTHE FELGULEN. KEMEMENAN

    ReplyDelete