Thursday, September 13, 2012

የምህላ ጸሎቱ በአግባቡ እየተካሄደ አይደለም


(አንድ አድርገን መስከረም 3 ፤ 2005 ዓ.ም)፤-ከሳምንት በፊት ቅዱስ ሲኖዶስ ሁለት ሱባኤ ማለትም የ14 ቀናት የጸሎት አዋጅ ማወጁ ይታወቃል ፤ መግለጫው የሚለው ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሁለተናዊ ዕድገት ለሀገሪቱ ሰላምና አንድነት የሚበጅ ተተኪ አባት (ፓትርያርክ) ለቤተ ክርስቲያኗ እግዚአብሔር ባወቀ መርጦ እንዲያስቀምጥ በመላዋ ኢትዮጵያና በውጭ ሀገር በሚገኙት አህጉረ ስብከት፣ ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት ከጳጉሜን 1 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 10 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል የሚል ነው። በአሁኑ ሰዓት አንዳንድ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ቤተክርስትያናት ጋር እንዳየነው ከሆነ የቅዱስ ሲኖዶስ የጸሎት አዋጅ በአግባቡ እየተደረገ አለመሆኑን ተመልክተናል ፤ ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ አብያተክርስቲያናት የጸሎት አዋጁ እየተደረገ አለመሆኑን ከተለያዩ ቦታዎች ያገኝናቸው መረጃዎች ያመለክታሉ ፤ ለሀገሪቱ ሰላምና ለቤተክርስትያን የሚበጅ ደግ አባት እግዚአብሔር እንዲሰጠን የጸሎት አዋጅ መታወጁ መልካም ሆኖ ሳለ አዋጁን ግን ከድረ-ገጽ ፤ ከዜና ማሰራጫ ጣቢያዎች በዘለለ በሰፊው በአብያተክርስትያናቱ ቁጥር መመልከት አልቻልንም ፤  በተወሰኑት 14 ቀናት ውስጥ የምህላ ጸሎት ባለመደረጉ ተጠያቂው ማነው? ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያወጣቸውን የተለያዩ መግለጫዎች እና መመሪያዎች ተከታትሎ መከናወናቸውን የሚያረጋግጠው አካል ማነው ? ነገሮች ከወረቀት በዘለለ የሚሰሩትና የሚተገበሩትስ መቼ ነው ?

2 comments:

  1. Asfetsami Police Aqumua Yihew new Yqerachihu

    maferiyawoch

    ReplyDelete
  2. Andeen teru neger asetwelachhuale!
    lemsale Germany betemeleketu Lkidase minm aynet denta yelachewm:: yetebalewm mihela bihone ensu min yadregal belew nekewetal!

    yalew gude demo betnshu yeh yemselale

    http://ewenetaw.blogspot.de/


    Egziabhere Mhertun yawrede enji lelaa mein yebalale!

    ReplyDelete