Tuesday, January 31, 2012
Sunday, January 29, 2012
‹‹ የግብረሰዶማውያንን ነፃነት ካላበሰራችሁ እርዳታ የለም›› Ban Ki-moon
- The United Nations may soon impose economic sanctions and halt aid to Africa if countries on the continent continue to oppose the legalization of gay marriage.
UN Secretary General Ban Ki-moon
(አንድ አድርገን ጥር ማርያም ፤ 2004ዓ.ም)፡- ከቀናት በፊት በመዲናችን አዲስ አበባ በአይካሳ ጉባኤ ጋር በተያያዘ መልኩ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በአዲስ አበባ ይፋዊ ስብሰባ ማድረጋቸው የትላንት ትውስታችን ነው ፤ ስብሰባውን የተቃወሙትን ወጣቶች ፌደራል ፖሊስ አስሮ ለሁለት ቀን አሳድሮ መፍታቱ እናስታውሳለን ፤ ስብሰባውን በመቃወም የሀይማኖት አባቶች ሊያደርጉ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ በዶ/ር ቴዎድሮስ አማካኝነት እንደተጨናገፈ እና መግለጫውን ሌላ ጊዜ እንደሚሰጡ ተነጋግረው ነበር ፤ ጋዜጣዊ መግለጫ ባይሰጥም ፤ ይህ ፀያፍ ጉዳይን ቅዳሜ አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ህንፃ በተመረቀበት ጊዜ ባንኪሙን የአፍሪካ መንግስታት ግብረሰዶማውያንን እንዳያገሉ እና እንክብካቤ እንሲያደርጉላቸው ፤ ሁለተኛ ዜጋ አድርገው እንዳይቆጥሯቸው ፤ ወንጀለኞች ናቹ እንዳይሏቸው በንግግራቸው ውስጥ በማስገባት ለመሪዎች መልእክት አዘል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ኢቲቪ በህብረቱ አዳራሽ ጋዜጠኞችን ቢያሰማራም ይህችን ዜና ግን ከንግግራቸው ውስጥ በማውጣት ሰዎች እንዳይሰሙ ሌላ ሌላ ነገር ላይ በመዞር ዘገባውን አቅርቧል ፤ የእንግሊዝ መንግስት ዴቪድ ካሜሮን የግብረሰዶማውያንን ነፃነት በህገ መንግስታቸው ውስጥ ለማያስገቡ እና ለተግባራዊነቱ የማይንቀሳቀሱን ሀገራት ሀገራቸው ምንም አይነት እርዳታ እንደማትሰጥ አበክረው ተናግረዋል ፤
Thursday, January 26, 2012
አቡነ ፋኑኤልን በሚዛን
(አንድ አድርገን ጥር 17 ፤ 2004ዓ.ም)፡- ባለፈው ቅዳሜ ጥር ፲፪ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. አባ ፋኑኤል በቪኦኤ የአማርኛው ዝግጅት በአቶ አዲሱ አበበ አማካኝነት አጭር ቃለ መጠይቅ አድርገው ነበር፣ በቃለ ምልልሱም በርካታ የሆኑ ውሸት አዘል መልዕክቶችን በአቡነ ፋኑኤል ተላልፈዋል ከቃለ መጠይቁ አለፍ አፈፍ ብለን ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡ በመቀጠል ጥያቄዎችን በተከታታይ እንመልከታቸው ፡፡
(Jan 21, 2012) ከVOA ራዲዮ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ
(ከ05፡00 ደቂቃ አንስቶ እስከ 25፡00ደቂቃ )-- የ20 ደቂቃ ቆይታ አለው
ጥያቄ: አባታችን አሁን የመጡበት ሹመቶ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው?
መልስ፡ አዎ፣ ከዚህ በፊት መጥቼ ቅዱስ ፓትሪያሪኩንም ነግሬያቸው ነበር እኔ የመጣሁት ሀገሬን ለማገልገል ነው እና በተቻለ መጠን እዚሁ ቢያረጉኝ ብዬ ነበር ነገር ግን በቅዱ ሲኖዶስ ስለታዘዝኩኝ ትዕዛዙን አክብሬ መጥቻለሁ፣ በመቀጠም እራሴው ደብዳቤ ጽፌ ወደ ሀገሬ እንዲመልሱኝ ያለምንም ችግር በመጣሁ በሦስት ወሬ ወደ ሀገሬ ተመልሻለሁ ነበር ያሉት።
Wednesday, January 25, 2012
ተሀድሶያውያኑ እንደ እባብ የሞተ በመምሰል አፈር ልሰው ለመነሳት እየሞከሩ ነው
(አንድ አድርገን ጥር 16 ፤ 2004ዓ.ም)፡- እነዚህ ሰዎች በጥምቅቱ የሲኖዶስ ጉባኤ የታገዱ እና ህገወጥ የተባሉ ሰባኪያን እና ዘማሪያን መሰል የተኩላው ለምድ የለበሱ ሰዎች (አቶ በጋሻው ደሳለኝ ፤ አሸናፊ ገ/ማሪያም ፤ አሰግድ ሳህሉ ፤ ትዝታው ሳሙኤል ፤ ምርትነሽ ጥላሁን ፤ ሀብታሙ ሽብሩ ፤ እና መሰሎቻቸው) በየትኛው በር ገብተው ነው የቤተክርስትያናችን አዳራሽ የተፈቀደላቸው ? እኛ እስከምናውቀው ድረስ ከቅዱስ ሲኖዶስ የትኛውም አውደ ምህረት ላይም ሆነ የትኛውም ቤተክርስትያን ላይ የመስበክ ፍቃድ እንዳይሰጣቸው እና ቤተክርስትያንን የማይወክሉ መሆኑን ገልፆ ቅዱስ ሲኖዶስ ለመላው አዲስ አበባ ውስጥም ላሉ ፤ ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚገኙ አብያተክርስያናት በሀገረስብከታቸው አማካኝነት እንዲደርሳቸው ተደርጎ ነበር ፤ ታዲያ ይህን ጉባዬ ለዛውም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ ማን ፈቀደላቸው?
Tuesday, January 24, 2012
የቃል ቀዳማዊነት
(የዮሐንስ ወንጌል ሁለተኛ ሳምንት )!!
“በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።” ዮሐ.1፡1-2
ዓሣ አጥማጁ ሐዋርያ ጌታ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደውን ደኃራዊ ልደቱ በሌሎች ወንጌላውያን የተነገረ ስለሆነ ቀዳማዊ ልደቱን ይነግረን ዘንድ ይቻኰላል /ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ/፡፡ በእርግጥም “የድንግል ማርያም ልጅ” ብሎ የሚያቆም ካለ እኛ እርሱን አንሰማውም፤ “በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ” ሊለንም ይገባዋል እንጂ /ሄላሬዎስ/፡፡ አንዳንድ ሰዎች “ወልድ ልጅ ሆኖ ሳለ እንዴት ከአባቱ አያንስም?” ብለው ይጠይቁናል፡፡ እኛም የማይመረመር መሆኑንና የነብዩን ቃል ጠቅሰን እንዲህ ብለን እንመልስላቸዋለን፡- “መኑ ይነግር ልደቶ- ከአብ ያለ እናት የተወለደበት ቀዳማዊ ልደቱን ማን ይናገራል? እንዴትስ ሊመረመር ይችላል? እኛ፡ አብ ለልጁ አባት ሲባል አገኘነው እንጂ እንደምን እንደወለደው አናውቅም” /ኢሳ.53፡9፣ አውግስጢኖስ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ/፡፡ ሐዋርያው “በመጀመርያው” ብሎ ሲነግረንም ከእርሱ በፊት ማንም እንዳልነበረ ለመግለጽ ነውና /ቅ.ቄርሎስ/፡፡ ምንም እንኳን “በመጀመርያ” የሚለው አገላለጽ በመጽሐፍ ቅዱስ የተለያየ ትርጕም ቢኖረውም አሁን ወንጌላዊው እየነገረን ያለው ግን ቀዳማዊ ቃል ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘላለም አንሥቶ እንደ ነበረ ነው /መዝ.90፡2፣ አርጌንስ/፡፡ ዮሐንስ “በመጀመርያው” የሚል ደካማ አገላለጽ ከመጠቀም ውጪ ሌላ የተሻለ ቋንቋ ማግኘት አልቻለም /ቅ.ቄርሎስ/፡፡
የአቡነ ፋኑኤል ቅጥፈት
(Jan 21, 2012) ከVOA ራዲዮ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ
(ከ05፡00 ደቂቃ አንስቶ እስከ 25፡00ደቂቃ )-- የ20 ደቂቃ ቆይታ አለው
Monday, January 23, 2012
Sunday, January 22, 2012
ለጥምቀት በአል ታቦተ ህጉ ከመንበሩ አልንቀሳቀስ አለ
(አንድ አድርገን ጥር 14 2004ዓ.ም)፡- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስተ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የጥምቀት በዓል ከከተራ ቀን አንስቶ እስከ መጨረሻዋ ሰዓት ድረስ በመላው ሀገሪቱ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ በሰላም ሊያልፍ ችሏል፡፡ ብዙ አዳዲስ ክስተቶችን ከባለፈው ዓመት ጨምሮ ይዞ መጥቶ ነበር ፤ ብዙ ያልተሰሙና ከዚህ በፊትም ያልታዩ ነገሮች ተከስተዋል፤ በአዲስ አበባ በመገናኛ አካባቢ የሚገኘው የቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስትያን የተፈጠረው ነገር የሚገርምም የሚደንቅም ነበር ፤ በቤተክርስትያኑ ውስጥ በዋናነት የቅዱስ እግዚአብሔር አብ ፅላት ሲኖር በድርብነት ደግሞ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፤የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ፤ የፃድቁ አባታችን የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስና ፤ የመድሀኒዓለም ታቦታት አንድ ላይ ይገኛሉ ፤ ከዚህ በፊት የቅዱስ ገብርኤል እና የእመቤታችንን ታቦተ ህጎችን ጥር 10 ወጥተው ጥር 11 ወደ ማደርያቸው ሲመለሱ የእግዚአብሔር አብ ታቦት ግን ጥር 12 ወጥቶ ጥር 13 ወደ መንበሩ ይመለስ ነበር ፡፡ በዚህኛው የጥምቀት በአል አከባባር ላይ ግን የቤተክርስያኑ ካህናት አባቶች ከበአሉ ከቀናት በፊት ተሰባስበው እስከ ዛሬ ድረስ የእመቤታችን እና የቅዱስ ገብርኤልን ታቦተ ህጎች ነበር የምናወጣው አሁን ለምን ቀይረን የመድሀኒአለምን እና የፃድቁን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስን ታቦተ ህጎች በመቀየር እናውጣ ተባብለው ሁሉም በሀሳቡ ተስማምተው ይለያያሉ ፡፡ ጥር 10 ቀን ደረሰ ፤ መዘምራን ፤ ህፃናት ፤ የአካባቢ ወጣቶች ፤ አዛውንት እናት አባቶች ፤ ብቻ ሁሉ ሰው የታቦታቱን መውጣት እየተጠባበቀ ቤተክርስትያኑን በመክበብ በሰንበት ተማሪዎች ዝማሬ ፤ በእናቶቻቸን እልልታ በጣም በደመቀ ሁኔታ የታቦቱን መውጣት ሲጠባበቁ ሳሉ ታቦተ ህጉን ለማውጣት ወደ ውስጥ የገቡ ካህናት አባቶች ግን ያጋጠማቸው ሌላ ነገር ነበር፡፡
Wednesday, January 18, 2012
አሁንም እሳቱ እየወረደ ይገኛል
(አንድ አድርገን ጥር 10 ፤ 2004ዓ.ም )፡- በከምባታ ሐዲያ ጉራጌ እና ስልጤ አህጉረ ስብከት በሐዲያ ዞን ሊሙ ወረዳ ናራ መድኃኔ ዓለም አጥቢያ ከቀናት በፊት እሳት በአካባቢው ላይ እንደሚወርድ ሰምተናል ፤ እስከ 09/05/2004 ዓ.ም ድረስ እሳቱ መውረዱን አለማቋረጡንም ለማወቅ ችለናል ፤ የእሳቱ ፀባይ ከጣሪያ ጀምሮ ማቃጠል ይጀምራል ወደ ታች በመውረድ እስከ መሰረቱ ይበላዋል ፤ አመድም ያደርገዋል ፤ እንዲህ አይነት እሳት ከዓመት በፊት በሀረርጌ ክልል የተከሰተ አይነት እሳት ነው ፤ በአካባቢው መናፍቃን በብዛት ያሉበት ቦታ ነው ከአካባው ሰዎች ጠይቀን ለማወቅ እንደቻልነው ፤ እሳቱ እስካሁን የወረደው እየወረደም ያለው መናፍቃኑ እና ኢ-አማንያኑ ቤቶች ላይ ነው ፡፡ መጀመሪያ አካባቢ ይህን ድርጊት የፈጸሙት ክርስያኖቹ ናቸው ብለው የአካባቢው ፖሊሶች ጥቂት ሰዎችን ወደ እስር ቤት እንደወሰዷቸው ለማወቅ ችለናል ፤ ነገር ግን እነዚህ ሰዎችም ታስረውም እሳቱ ቤቶቹን መብላት አላቆመም ነበር ፤ ይህን ዜና የሰሙት የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በአስቸኳይ ቤታቸው ለተቃጠለባቸው ሰዎች ድንኳን እንዲጣል እና ማረፊያ እንዲሆናቸው ትእዛዝ አስተላልፈው ነበር ፡፡ የክልል ፕሬዝዳንት በሁኔታው ግራ ከተጋቡት የመንግስት ተወካዮቻቸው ጋር ችግሩ የደረሰባቸውን በድንኳን ማረፊያቸው ሊጎበኙ የመጡ ሲሆን ቤታቸው የተቃጠለባቸውን ሰዎች እየጎበኙ ሳሉ እነርሱ ያሉበት አካባቢ በጥቂት ሜትሮች ርቀት ላይ እሳቱ ከሰማይ ሲወርድና ቤቶቹን ሲበላ ሊመለከቱ ችለዋል፡፡ የታሰሩትንም ሰዎች እነርሱ እዳላቃጠሉ ከሰማይ የሚወርድ እሳት ስለሆነ በነፃ ሊለቋቸው ችለዋል፡፡ አሁንም እሳቱ እየወረደ ይገኛል፡፡ ቁጣህን አብርደው ምህረትህን አውርደው ማለት አሁን ነው፡፡
Tuesday, January 17, 2012
አሁን እዚህ ሀገር ህግ አለ?
(አንድ አድገን ጥር 8 2004 ዓ.ም)፡- በደብረዘይት የሚገኘውን የመድሀኒዓለም የጥምቀት ቦታ መንግስት ከአቡኑ ጋር በመስማማት ቆርሰው ለባለሀብት በመስጠት ሪዞርት ሲያሰሩበት ማንም ያልተናገራቸው ‹‹ለምን ለአንድ ቀን ያለ መንግስት ፍቃድ በ2003ዓ.ም ለጥምቀት ታቦታችሁን እዚህ ቦታ አሳረፋችሁ›› በሚል ሰበብ በኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ ዙሪያ ቡራዩ ከተማ የሚገኝው ፊሊዶሮ ቅድስት ልደታ ገዳም አስተዳዳሪ የሆኑት ቆሞስ አባ ሳሙኤል ግዛቸው ህገወጥ የመሬት ወረራ ፈፅመዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸው የ3 ዓመት እስር ተፈርዶባቸዋል፡፡ ታቦተ ህጉን 2000 ካሬ በማትሞላ ቦታ ላይ የዛሬ ዓመት 2003ዓ.ም ላይ ነበር አርፎ ምዕመኑ በዓሉን ያከበረው ፤ በዓመት 1 ጊዜ የሚመጣውን የጥምቀት በዓልን ለማክበር ታቦተ ህጉን መንግስት ቦታ ካልሰጠን የት እናሳርፍ ? እንዴት ይሄ ከህገ ወጥ መሬት ወረራ ጋር ይያያዛል ? አንድ ቀን ታቦት ስላሳረፍንበት ህገ ወጥ የመሬት ወረራ አደረግን ማለት ነው እንዴ? ህጉስ እንዴት ያየዋል? ቤተክህነቱስ ምን ይላል?
የመንግስትን መሬት እንደ ግል ንብረታቸው ተጠቅመው ሸንሽነው ለማህበራት መሰሎች ያከፋፈሉ ፤ 280 ሚሊየን ብር መንግስት ማግኝት ያለበትን ገቢ ያስቀሩ ሰዎች የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ እና የላፍቶ ክፍለ ከተማ ባለስልጣናት የነበሩ ሹሞች በ 7 ዓመት የእስራት ፍርድ ሲፈረድባቸው ፊሊዶሮ ቅድስት ልደታ ገዳም አስተዳዳሪ የሆኑት ቆሞስ አባ ሳሙኤል ግዛቸው ግን ለምን ያለ መንግስት ፍቃድ በ2003ዓ.ም የጥምቀት በዓል ቀን የመንግስት ቦታ ላይ ታቦት ያሳርፋሉ በሚል ተልካሻ ምክንያት 3 ዓመት ሊፈርዱባቸው ችለዋል፡፡
Monday, January 16, 2012
እንዲህም አስበው ነበር
(አንድ አድርገን ፤ ጥር 7 ፤ 2004)፡- በአሁኑ ሰዓት በታላቅ ድምቀት ጥምቀት ከሚከበርባቸው ከተሞች ጎንደር አንዷ ናት ፤ በጥምቀት እለት የሚወጡ ታቦታት በዛ ስለሚሉ አከባበሩም ከሌላው ቦታ ይልቅ ልዩ ስለሚሆን የውጭ ዜጎች ጥምቀትን ለማየት ወደ ጎንደር ማቅናት ከጀመሩ ቀናት ተቆጥረዋል፡፡ የጥምቀትን በዓል ምክንያት በማድረግ የካርኒቫል ዝግጅት የተጀመረው ባለፈው ዓመት ነበር ፡፡ መጀመሩ ባልከፋ ነገር ግን የካርኒቫሉ አዘጋጆች እና የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ከስርአተ ቤተክርስትያን ውጪ በሆነ መልኩ ለአብያተክርስትያኖቹ ትእዛዝ አስተላልፈው ነበር ፤ ትዕዛዙም ‹‹ለካርኒቫሉ ድምቀት ሲባል ከ04/05/2004 ጀምሮ እስከ 10/05/2004 ዓ.ም ድረስ ታቦታቱ ወደ ጥምቀተ ባህር ቀስ በቀስ እያሉ ቢወጡ›› ብለው መመሪያ አስተላልፈው ነበር ፤ ነገር ግን በምዕመናን እና በካህናት በደረሰባቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ምክንያት ሀሳባቸውን ሊያጥፉ እና አላልንም ፤አልወጣንም ብለዋል፤
ሀገሪቱ ያላትን የእምነት ስርዓት እና ትውፊቶቻችንን ለውጭ ዜጎች ማስተዋወቅ ተገቢ ነው ፤ ሀገሪቱ ከቱሪዝም የምታገኝውን ገቢ እና የጎብኝን ፍሰት ከመጨመር አኳያ ጉልህ ሚና ያለው ስራ ነው ፤ ነገር ግን የእኛን ስርዓት ለእኛ ትታችሁልን እናንተ የሚመለከታችሁን ብቻ ብትሰሩ መልካም ነው፡፡ነገሩም ብዙ ቢያነጋግርም በአንድ አቋም ስርዓተ ቤተክርስትያን መፋለስ የለበትም በሚሉ ምእመናን ምክንያት ነገሩን ረገብ ሊያደርጉት ችለዋል፤ መንግስት ካርኒቫሉን ለማድመቅ እና ከፍተኛ ገቢ ለማግኝት ማሰቡን አንቃወምም ፤ ነገር ግን ሁሉ ነገር በስርዓት ቢሆን ጥሩ ነው የሚል ሀሳብ አለን ፤ እስካሁን በዘመናችን ከጥር 10 በፊት ለጥምቀት ታቦት ሲወጣ አላየንም ወደፊትም ማየት አንፈልግም ፤ አባቶቻችን አደራ ብለው ያስረከቡንን ቀኖና እና ዶግማ ሳናሳንስ ሳንጨምር ለልጅ ልጆቻችን የማውረስ ታሪካዊ ሀላፊነት አለብን ፤ህገ መንግስቱ በሀይማኖት ጉዳይ መንግስት ጣልቃ እንደማይገባ ይናገራል ፤ ይ ቢሆንም ቅሉ በተለያየ መንገድ ቤተክርስትያን ከመንግስት ጫና ተላቃ አታውቅም ፤ በግልፅ ባይሆን እንኳን ስውር የማይታዩ እጆች ከመንግስት በኩል የተሰበሰቡበት ጊዜ የለም፡፡ በአሁኑ ሰዓት ጎንደር ታላቁን በዓል ለማክበር የሰርጓ ቀን የደረሰ ሴት ይመስል እየተዋበች ትገኛለች ፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ፤ ወጣቱ ፤ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በአንድ ላይ በመሆን በዓሉ የደመቀ ሆኖ እንዲያልፍ የቻሉትን ሁሉ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
‹‹የመረጃ ምንጭዎ ሆነን እንሰራለን ››
Sunday, January 15, 2012
ይህን ማየት የማይናፍቅ ማን አለ?
ምዕመናን ለታቦቱ ክብር የለበሱትን ነጠላ ሲያነጥፉ
የዘንድሮ ወጣቶቹ
(አንድ አድርገን ፤ ጥር ስላሴ 2004ዓ.ም)፡- ከሁለት ዓመት በፊት ነበር ለጥምቀት ወደ ጥምቀተ ባህር ለሚሄዱ ታቦታት መረማመጃ ይሆን ዘንድ ምንጣፍ ማንጠፍ በአንዳንድ አብያተክርስትያናት አካባቢ የሚገኙ ጥቂት ወጣቶች አማካኝነት ቢጀመርም በአሁኑ ሰዓት በመላው አዲስ አበባ እና የክልል ከተሞች ላይ እየተለመደ ይገኛል፡፡እግዚአብሔር ይመስገን ባለፉት 2 ዓመታት ለጥምቀት አስፋልት ላይ የሚነጠፍ ምንጣፍ በቅዱስ ራጉኤል ፤ በቅዱስ ጊዮርጊስ ፤በቅዱስ ኡራኤል ፤ በየካ ሚካኤል እና ሌሎች የቤተክርስትያን ወጣቶች አማካኝነት ተነጥፈው ለአይን በሚማርክ ሁኔታ ማየት ችለናል፡፡ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ታቦታቱ የሚሄዱበት መንገድ በጣም ረዥም ስለሆነ ያን የሚያህል ረዥም ምንጣፍ ገዝተው ማንጠፍ ሳይችሉ ቢቀሩም የቻሉትን ያህል አንጥፈው የተቀረውን ደግሞ በሸክም ወደፊት ታቦታቱን በመቅደም አስፋልት ጠርገው ፤ ሳር ጎዝጉዘው ፤ ምንጣፍ ሲያነጥፉ ፤ አበባ ሲበትኑ ፤ ሽቶ ሲረጩ ሲመለከቱ አንዳች መንፈሳዊ ቅናት ውስጥዎት ያርደዋል፡፡
‹‹ሬሳ ማቃጠሉ ቢለመድ መሬትን ይቆጥባል›› ፕሮፌሰሩ ምን ነካቸው
(አንድ አድርገን ጥር ስላሴ ፤2004ዓ.ም)፡-ሰሞኑን መንግስ በመሬት ላይ ያወጣው ሀገር አቀፍ የሊዝ አዋጅ ምክንያት በማድረግ ድሀውም ሀብታሙም ፤ ተከራዩም አከራዩም ፤ የገባውም ፤ ያልገባውም፤ የማያገባውም ፤ከተማ ውስጥ ያሉ ኤፍ ኤም ጣቢያዎቻችን ፤ አዋጁ ዱብ እዳ የሆነባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ፤ የመንግስት ህግ አስፈፃሚዎች፤ ብቸኛው ኢቲቪ ጣቢያችን ብቻ የሁሉም ሰው የመነጋገሪያ አርእስት ከሆነ ሰንበትበት ብሏል፡፡ ባልታሰበው አዋጅ አንጀታቸው ቅቤ የጠጣ ሰዎች እንዳሉ አንጀታቸው ያረረም ዜጎች ጥቂቶች አይደሉም፡፡ አሁን የኔ አላማ በቴሌቪዥን የሰለቸንን ወሬ ፤ ገና ሲመጣ Remote Control የምናነሳበትን ጉዳይ ለመድገም አይደለም፡፡ በዚህ ዙሪያ ላይ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም በፍትህ ጋዜጣ ቅፅ 5 ቁጥር 170 ፤ ጥር 4 2004 ዓ.ም ላይ ያሰፈሩትን ፅሁፍ አንብቤ ‹‹ምነ ነካቸው›› ያስባለኝን ሀሳብ ለእናንተው ለማካፈል እንጂ ፡፡ ለማንኛውም እርስዎም እንዲያነቡት አንዱን አንቀፅ እንደወረደ አቅርበንዎለታል፡፡
የተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን የማፈራረስ ሴራ
በመጀመሪያ ከ3 ሳምንታት ቆይታ በኋላ ብሎጋችን ሊከፍትልን ችሏል ፤ መቼ እንደሚዘጋ ባናውቅም እስካለህ ድረስ መረጃ እናንተው ዘንድ ማቅረብ እንቀጥላለን
እግዚአብሔር ይመስገን
“የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ላንተ ይብስብሀል”
Addisu Tesfaye Mengistu
የህወሀት( ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ) መስራችና ኮማንደር የነበሩት ያያኔው ታጋይ ፤ ያሁኑ ዶክተር አረጋዊ በርሄ በቅርቡ A Political History of the Tigray People’s Liberation Front ( 1975-1991) የተሰኘ መጽሐፍ አሳትመዋል። መጽሐፉ አስራ ሁለት ምእራፎችና 355 ገጽ ያሉት ሲሆን በይዘቱም በርካታ ጉዳዮችን ይዳስሳል።
የመጽሐፉ ደራሲ ደግሞ የህወሀት የፖሊት ቢሮ አባልና ከህወሀት ጥንሥስ ጀምሮ ፖሊሲ አውጪ አመራር ስጭና አዋጊ ስለነበሩ በተራ አባላቶቸ የማይታወቁ በርካታ ሚስጥሮችን ይፋ አድርገዋል። መጽሀፉ ÷ ስለ ብሔር ፓለቲካ አደገኛነት ÷ ስለ ማሌሊት ማኒፌስቶ 1976 አና ትግራይን ስለመገንጠል የነበረውን ውዝግብ÷ ስለ ስብሀት ነጋና መለስ ሚስጥራዊ ሰንስለቶች÷ ስለ ጦርነቱ ÷ ከኤርትራው ኢሳያስ ጋር ስለነበረው ፍቅርና ጠብና አሁን ድረስ እያዋጉ ስላሉት መሰረታዊ ምክንያቶችና ሌሎች ብዙ አስገራሚ ሚስጥሮችን ይተነትናል።
Subscribe to:
Posts (Atom)