❖ ‹‹ … ሁለተኛው ዙር የእሬቻ በዓል ሥነ ሥርዐት በዝቋላ ተራራ እና በአከባቢው ይከበራል ፡፡›› – የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ
❖ ‹‹ … የእሬቻ በዓል በዝቋላ ገዳም እንደሚካሄድ በመንግሥት ብዙኃን መገናኛ የገዳ ሥርዐት ጽ/ቤት ማስተላለፍ ተገቢ አይደለም፡፡›› ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
❖ ‹‹ …ችግሩ ከመፈጠሩ በፊት በተገለጸበት የመንግሥት ብዙኃን መገናኛ ማረሚያ እንዲተላለፍ መደረግ አለበት ፡፡ ›› ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
❖ ‹‹ … ከጥንት ጀምሮ የዝቋላ ተራራ እና የጠበል ሐይቁ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ይዞታነት የታወቀ ነው ፡፡ ይህን እውነታ ወደ ጎን በመተውና የገዳሙን ሕጋዊ ባለቤትነት በመናቅ በማን አለብኝነት መንፈስ የተላለፈው ውሳኔ እኛንበእጅጉ አሳዝኖናል ፤ከፍተኛ የሆነ ሥጋትንም አጭሮብናል ፡፡ ›› ማኅበረ መነኮሳት
❖ ‹‹ … የእሬቻ በዓል በታሪካዊው ገዳም ላይ እንደሚካሄድ በመንግሥት ብዙኃን መገናኛ በመተላለፉ በገዳማውያኑና በሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን ተከታዩች ዘንድ ቅሬታን አስከትሏል ፡፡ ›› ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ
❖ ‹‹ … ይኽን ችግር በተደጋጋሚ ጊዜ ለቀድሞው ፓትርያርክ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እና ለመንግሥት አካላት ያመለክትን ቢሆንም ለችግሩ መሠረታዊ መፍትሔ እስከ አሁን ባለመሰጠቱ ለእንደዚህ ዐይነት ችግር ሊዳርገን ችሏል፡፡››ማኅበረ መነኮሳት
❖ ‹‹ … የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ግንቦት 23 ቀን 2004 ዓ.ምየገዳሙን አስተዳደር ደብረ ዘይት ድረስ ስብሰባ በመጥራት አስፈራርቷል ፡፡ ›› ማኅበረ መነኮሳት
❖ ‹‹ … ነገ ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እንዳያመራ ከአሁኑ ጥንቃቄ ሊደረግበት የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ እናምናለን ፡፡ ›› ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ
❖ ‹‹ … እናንት እኛ ቦታ ድረስ መጣችሁ እንጂ እኛ እናንተ ጋር አልመጣንም ፤ሀገራችንን ለቃችሁ ውጡ ፤ገዳሙ የነፍጠኛ ሃይማኖት እንጂ ለኦሮሞው ምኑ ነው ? ቦታው የእኛው እስከሆነ ድረስ አይደለም ሐውልት ማቆም ውሻ እንሰዋበታለን ፡፡ ››የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ
❖ ‹‹ … የዞኑ መስተዳደር ተወካዩች እና የጸጥታ ቢሮ ሓላፊዎቸ በተገኙበት የክልሉ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ እና የገዳ ሥርዐት ጽ/ቤት ሓላፊዎች ኢትዮጵያዊነታችንን እና ወንድማማችነታችንን በሚገድልና ጫና ባለበት ሁኔታ በገዳሙ ጠበል እና ታቦት ማክበሪያ ስፍራ ሐውልት እንደሚያቆሙ በዛቻ አሳውቀውናል ፡፡ ›› ማኅበረ መነኮሳት
❖ ‹‹ …ታላቁ ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደኅንነት ሲሉ ለብዙ ዓመታት የተጋደሉበት ቦታ ፣ ስማቸውና ታሪካቸው ተሸሮ ሌላ ሐውልት ሲተከል በዝምታ ለማየት አቅሙ የለንም ፡፡ … ገዳማችን ታፍሮና ተከብሮ ለእኛም ለማኅበረ መነኮሳቱም አስተማማኝ የሆነ ሕጋዊ ከለላና ጥበቃ እንዲደረግልን እንጠይቃለን ፡፡ ››ማኅበረ መነኮሳት