Saturday, February 21, 2015

The New Martyrs of Libya added to the Coptic Synaxarium

 
‹‹አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ።  በታላቅ ድምፅም እየጮኹ። ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ። ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው››
 የዮሐንስ ራእይ  6 ፤ 9-11



የግብፅ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዱስነታቸው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ አማካይነት ይፋ ባደረገው ዜና ከቀናት በፊት በሊቢያ ባሕር ዳርቻ መስዋዕትነት የተቀቡሉትን ሰማዕታት ዕውቅና ሰጥታ መታሠቢያቸውም በየወሩ በስምተኛው ቀን ዓመታዊ መታሠቢያቸው ደግሞ በየካቲት ፰ ቀን (February 15) ታስቦ እንዲውል ውሳኔ አስተላልፈው ስሞቻቸውንም በመጽሐፈ ስንክሳራቸው ጨምረውታል።
 
በረከታቸው ይደርብን።  እኛንም እግዚአብሔር በሃይማኖት በምግባር ያጽናን።  አሜን።
 

His Holiness Pope Tawadros II announced the inclusion of the 21 Coptic New Martyrs of Libya in the Synaxarium of the Coptic Orthodox Church today. Every year, they will be commemorated on 8 Amshir in the Coptic calendar, which corresponds to 15 February in the Gregorian calendar, the same day as the Feast of the Presentation of our Lord in the Temple

Source:- http://lacopts.org


Thursday, February 19, 2015

በእንጦጦ ማርያም ሙዚየም የወርቅ መስቀሎች ጠፍተዋል መባሉ ተቃውሞ አስነሳ

አንድ አድርገን የካቲት 12 2007 ዓ.ም
ከሪፖርተር ጋዜጣ የተወሰደ
 -‹‹የተባለው ሁሉ ሐሰትና ምንም የጠፋ ነገር የለም›› የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳዳሪ
-‹‹ከመንግሥትና ከሀገረ ስብከቱ አጣሪ ኮሚቴ ተሰይሞ እየተመረመረ ነው›› የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት 

ለርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ ከተለያዩ ምዕመናን በስለትና በስጦታ የተሰጡና እስከ አራት ኪሎ ግራም ሊመዝኑ ይችላሉ የተባሉ ሁለት የወርቅ መስቀሎችና አንድ የወርቅ ሐብል፣ በቅርስነት ከተቀመጡበት ሙዚየም ውስጥ መጥፋታቸውን የደብሩ ካህናትና የአካባቢው ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡ 
የቤተ ክርስቲያኗ ካህናት፣ ሠራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች የደብሩን አስተዳዳሪና ሌሎች ኃላፊዎች ተባብረው ወርቆቹን ማጥፋታቸውን፣ በቤተ ክርስቲያኗ ሠራተኞች ላይ በደልና ብልሹ አሠራር እንዲደርስ ማድረጋቸውን በመግለጽ ተቃውሟቸውን ለመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት፣ ለሀገረ ስብከቱ ቅርሳ ቅርስ ክፍል፣ ለአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮና ለጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምርያ በፊርማ የተረጋገጠ ተቃውሟቸውን አስገብተዋል፡፡ 

Wednesday, February 18, 2015

ኢስላሞች ለምን ሰውን ያርዳሉ ወይም ይገድላሉ?

 አንድ አድርገን የካቲት 11 2007 ዓ.ም

 ከአሚና መሀመድ (የዛሬዋ ወለተ ማርያም)
·        አሁን ሥልጣን ላይ ከመውጣታቸው በፊት የግብፆቹ ሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ ኃላፊዎች በአንድ ወቅት ሃይማኖታዊ አስተሳሰባቸውን የገለጹበት መንገድ እንዲህ የሚል ነበር፡- “ዓላማችን አላህ ነው፣ ሕገ መንግስታችን ቁርአን ነው፣ መሪያችን ነቢያችን ነው፣ መንገዳችን ደግሞ ጂሃድ ነው”

“ባገኛችሁባቸው ስፍራ ሁሉ ግደሉዋቸው” ቁርአን 2፡191 “Kill disbelievers [Christians] wherever you find them, take them captive, torture them” Qur’an 9:5 "Allah is our objective, the Quran is our Constitution, the Prophet is our leader, and Jihad is our way." ጂሃድ (jihad- the Way of Islam) ስለ ጂሃድ ከመነጋገራችንና እኔም ምንም ዓይነት ትንታኔ ከመስጠቴ በፊት ይህንን ርዕስ የምታነቡ አንባቢያን ሁሉ ተከታዮቹን የመሐመድ ትእዛዞች ልብ ብላችሁ እንድትመለከቷቸው እፈልጋለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ የኅሊናውን ፍርድ ለእናንተው እተዋለሁ፡፡ (ጥቅሶቹን በቀጥታ ከቁርዓኑና ከሐዲሱ የወሰድኳቸው ሲሆኑ ሁሉም ትእዛዞችና ንግግሮች የመሐመድ ናቸው፡፡ የአማርኛውን የቁርዓኑን ጥቅሶች በ1997 ዓ.ም ነጃሺ ካሳተመው ቁርአን ላይ በቀጥታ የወሰድኳቸው ስለሆነ ከእንግሊዝኛው ቁርአን ጋር ያለው መልዕክት አንድ ላይሆን ስለሚችል የእንግሊዝኛውን ጥቅስ በደንብ ቢመለከቱት የተሸለ ነው፡፡ የሐዲሱን ጥቅሶች በተመለከተ ግን ከእንግሊዝኛው የሐዲስ ጥቅስ ላይ ፅንሰ ሀሳቡን ብቻ ነው የወሰድኩት እንጂ ቀጥተኛ የቃል በቃል ትርጉም አልተጠቀምኩም) እነዚህ ቀጥሎ የዘረዘርኳቸው የመሐመድ “ፍለጠው፣ ቁረጠው” የሚሉ የቁርዓንና የሐዲስ የግድያ አንቀጾች ስለ ምድራዊ ሕይወት የተነገሩ እንዳይመስላችሁ! ይልቁንም አንድ ሙስሊም (ጂሃዲስት) ኢስላም ባልሆኑ ሌሎች ሰዎች ላይ እነዚህን የግድያ አንቀጾች ተግባራዊ ያደረገ እንደሆነ ጀነት ለመግባቱ እርግጠኛ እንዲሆን ነቢያቸው መሐመድ ሰማያዊ ተስፋ ሰጥተውታል፡፡ ጥቅሶቹን እንያቸው፡-