Tuesday, February 17, 2015

እንባችንን ከዓይኖቻችን ላይ ያብሰዋልና ክብር ለእርሱ ይሁን፡፡ ኢሳ25፡8

‹‹እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ›› ዮሐ 844 በትላንትናው ዕለት አሕዛባዊው ጽንፈኛ አይ ኤስ፤አይ ኤስ (isis) 21 የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ የፈጸመው አሰቃቂ ግድያ እጅግ በጣም አሳዝኖናል ፡፡ መንበረ ማርቆስ ግብጽ ልጆችዋ በሚዲትራንያን ባሕር ላይ አንገታቸው እየተቀላ በደም ጎርፍ ሲጥለቀለቅ ማየት ምንኛ አሳዛኝ ይሆን !!! የአትናትዮስ ልጆች የእነ ጳውሊ መቃርስና እንጦንስ ፍሬዎች ሰማዕትነትን በጸጋ ሲቀበሉ በዓይን በብረታችን አየን ፡፡ ይህ ዓይነቱ ጸረ ክርስትና እንቅስቃሴ የመጀመርያይቱን / አስታወሰኝ ፡፡ ሮማዊው ኔሮን ክርስትናን ያጠፋ መስሎት ሰይፉን አስልቶ ክርስያኖችን አያደነ ቢሰይፋቸውም ለሞት ከመሽቀዳደም በቀር ሥጋውን ለማትረፍ ያሻ አልነበረም ፡፡ ቤተ ክርስትያንን ቶኮምቡ (ከምድር በታች ባሉ ጉድጓዶች) ለመግባት በተገደደችበት በዚያ ዘመን ክርስትና ግን ይበልጥ እያበበ መላውን ሮማ እስኪያሰጋ ድረስ ሰደድ ሆኖ ነበር ፡፡ ዛሬም ተረፈ ኔሮኖች ክርስትናን ያጠፉ መስሎአቸው በጭምብል ይጋልባሉ ፡፡ ክርስትና ግን አይደለም ዛሬ ጥንትም መገለጫዋ መከራ ነውና እስከ ምጽዓተ ክርስቶስ አትጠፋም ፡፡ ክርስትናን ሰይፍ የሚያሸንፈው ቢሆን ኖሮ እነ ትራጃን ድምጥያኖስና ዲዮቅልጥያኖስ በተሳካላቸው ነበር ፡፡ ወትሮውንም ክርስትና የጸናችው በሠማዕታት ደም ነው !!! 

Sunday, February 15, 2015

አቶ ያሬድ አደመ በደረቅ ቼክ ማጭበርበር ታሰረ


አንድ አድርገን የካቲት 9 2007 ዓ.ም

በአዋሳ ገብርኤል እና በደቡብ ኢትዮጵያ የተፈጠረውን የተሐድሶ እንቅስቃሴ በግምባር ቀደምነት ጠፍጥፎ በመፍጠር የሚታወቀው ከዚያም አልፎ ከአገር ውጭም በተለይ በዱባይ ከመሰሎቹ ጋር በመሆን ከሊቀጳጳሱ እውቅና ውጭ በአዳራሽ ቤተ ክርስቲያን በመክፈት የሚታወቀው የተሐድሶያውን ፊት አውራሪ አቶ ያሬድ አደመ ባደረገው የደረቅ ቼክ ማጭበርበር ጉዳይ አቃቂ ቂሊንጦ እስር ቤት ወርዷል ። በጉዳዩም ላይ በመቀጠል በጋሻው ደሳለኝ አሸናፊ ገብረማርያም እና ሌሎች ሁለት ለጊዜው ስማቸው ያልተጠቀሱ ሰዎች ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ባለው ጉዳይ ይጠየቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡


አቶ ያሬድ ከዚህ ቀደም " መዝሙረ ተዋሕዶ " በሚል ርእስ የዘማርያንን የመዝሙር መጽሐፍ በማሳተም ለደራስያኑም ሆነ ለዘማርያኑ ምንም አይነት ክፍያ ሳይፈጽም ላባቸውን ሜዳ እንዳስቀረ ይታወቃል ይህ ሰው ከቤተ ክርስቲያኗ እና ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ በመናፍቃን ግልፅ የሆነ የማያቋርጥ ድጋፍ የሚንቀሳቀሰውን እና በየሳምንቱ እሁድ እሁድ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ " ታኦሎጎስ " የተሰኘ የተሐድሶ ፕሮግራም የሚተላለፍበትን ድርጅት አቶ በጋሻው ደሳለኝ እና ከበሪሁን ጋር በሽርክና የሚያንቀሳቅስ ሲሆን የቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ፈቃድም  በበሪሁን ስም መሆኑም ይታወቃል

ከዚህ ቀደም የአርቲስት አቦነሽ መዝሙር በራስ አምባ ሆቴል በተደረገው የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ አንድ ሲዲ ከመቶ ሺህ ብር በላይ በጨረታ የሸጡ ሲሆን አሁን በአርቲስቷ ስም ብዙ ብር በማግበስበስ ኪሳቸውን ከሞሉ በኋላ ለአቦነሽካሴትሽ አልተሸጠም› እንዳሏት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ይናገራሉ፡፡


በኢትዮጵያ ወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ደረቅ ቼክ ማጭበርበር ከሦስት ዓመት በላይ ለሚሆን ጊዜ ዘብጥያ እንደሚያወርድ ይታወቃል