Tuesday, September 23, 2014

ለገጠር አገልግሎት ለመመዝገብ ለምትፈልጉ!

አንድ አድርገን መስከረም 13 2007 ዓ.ም

በፈረንጆቹ አቆጣጠር 1950 .. በካይሮ በሚገኝ አንድ ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ አንድ አገልጋይ ቆመና ‹‹ለገጠር አገልግሎት መመዝገብ የምትፈልጉ ....›› የሚል አንድ ማስታወቂያ ተናገረ፡፡ የገጠር ገልግሎት ማለት የከተማ ሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋዮች ወደ ገጠር መንደሮች እየሔዱ የሚያስተምሩበትና የሚያገለግሉበት የአገልግሎት መስክ ነበር፡፡ ይህ ማስታወቂያ ሲነገር በወቅቱ የሃይስኩል ተማሪ የነበረ አንድ 14 ዓመት ልጅ ተመሥጦ ይሰማል፡፡ ይህ ልጅ የሰንበት ትምህርት ቤት የሕጻናት መምህራን ሆነው ከተመለመሉ ልጆች አንዱ ነበር፡፡ ስለዚህም ወደ ገጠር ሔዶ ለማገልገል ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር ይመዘገባል፡፡


ጊዜው ሲደርስም እንደ ሐዋርያት ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ ገጠር ከሚዞሩት የሰንበት ተማሪዎች አንዱ ሆኖ ማገልገሉን ቀጠለ፡፡ በዚህም ወቅት የጀመረው ሌሎችን የማገልገል ፍላጎት በጣም በመጨመሩ የዩንቨርሲቲ ትምህርቱን አጠናቅቆ በህክምና እስከተመረቀበት ጊዜ ድረስም ይህን አገልግሎቱን አላቋረጠም፡፡ ትምህርቱን ሲጨርስ ግን የህክምና ሙያውን ተጠቅሞ አገልግሎቱን ማስፋት ተመኘ፡፡ ሌሎችን የማዳን ፍላጎቱን ለማርካት ግን የግብፅ ምድር አልበቃችውም፡፡ በአፍሪካ ሀገራትም ለማገልገል ቆርጦ ተነሣ፡፡ የመጀመሪያ ጉዞውንም ወደ ኢትዮጵያ አድርጎ በአሥመራና በደብረ ብርሃንና በአዲስ አበባ እስከ 1966 ድረስ አገለገለ፡፡ ከዚያም ወደ ግብፅ ተመልሶ መነኮሰ፡፡ ከምንኩስናው በኋላም የአገልግሎት ጉዞውን ቀጠለ፡፡ ከአስቄጥስ ገዳም ተነሥቶ ወደ ናይሮቢ ኬንያ ከናይሮቢ ወደ ዛምቢያው ሉሳካ ከሉሳካ ወደ ዚምባብዌው ሐራሬ ከሐራሬ ወደ ዛየር ኪንሻሳ ከኪንሻሳ ወደ ቦትስዋና ከቦትስዋና ወደ ማላዊ ሌሴቶ ከዚያም ወደ ሌሎች ሀገራት.... በአጠቃላይ ወደ 23 የአፍሪካ ሀገራት ተጓዘ፡፡ አብያተ ክርስቲያናትን ገዳማትን መንፈሳዊ ኮሌጆችን አቋቋመ፡፡ በየሀገራቱ ቋንቋዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ መጻሕፍትን ተርጉሞ አስተማረ፡፡ በዐሥራ አራት ዓመቱ በልቡ የተጫረው የመንፈሳዊ አገልግሎት እሳት በብዙ ቋንቋዎች እና ባህሎች ውስጥ እየተቀጣጠለ ብዙ አፍሪካውያንን ወደ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እንዲገቡ አደረገ፡፡ የካይሮ ሰንበት ትምህርት ቤት ትንሹ አገልጋይ በፎቶው ላይ የምትመለከቷቸው የዛሬው የየኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን የአፍሪካ ጉዳዮች ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንቶንዮስ ማርቆስ ናቸው፡፡

Sunday, September 21, 2014

ከእሳት የተረፉ ቅርሶች

አንድ አድርገን መስከረም 12 2007 ዓ.ም


የመሐል ዘጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የተተከለው 1292.. ሲሆን በርካታ ጥንታውያን ስዕላት፣የብራና መጻሕፍትና ሌሎች ቅርሶች የሚገኙበት ቤተ ክርስቲያን ነው። ቤተ ክርስቲያኑ 1986-1989.. እድሳት ተደርጎለት 1989 ጀምሮ ሙሉ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል።


ቤተ ክርስቲያኑን ሙሉ በሙሉ ያወደመው እሳት ባልታውቀ ምክንያት የተነሳው የካቲት 5 ቀን 2002 .. ነበር።  እሳቱ ቤተ ክርስቲያኑን ሙሉ በሙሉ ያወደመ ሲሆን አብዛኞቹ የቤተ ክርስቲያኑ ጥንታዊያን የብራና መጻሕፍት እና ቅርሶች ያሉበት ዕቃ ቤት ግን ምንም አደጋ አልደረሰበትም። ታቦታቱም ምስጢራዊ በሆነ እሳት በማይደርስበት ቦታ ተቀምጠው ስለነበር ቃጠሎ አልደረሰባቸውም ።ጽላቶቹ ከቤተመቅድሱ ስር ባለ እሳት በማይደርስበት ቦታ ተቀምጠው ስለነበር የካቲት 7 ቀን 2002 .ም ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ተገኝተዋል።  የዚህን ቤተክርስያን ታሪክ ፤ ውስጡ ያሉትን ከእሳት የተረፉ ቅርሶች ፤ ብታውቋቸው ጥሩ ነው ብለን ስላሰብን የቤተክርስያኑ ሰበካ ጉባኤ ያዘጋጀውን ‹‹የገዳም ዘጌ አጭር ታሪክ ለታሪክ አጥኝዎች የተዘጋጀ›› መፅሐፍ በpdf አቅርበንላችዋል፡፡

አቡነ በትረማርያም በህይወት ሳሉ ንጉስ አምደ ፅዮን የሰጣቸው ስዕለ ማርያም 
ሲመለከቷት አይኗ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አብሮ የሚዞር የምትንቀሳቀስ ምትመስል

Friday, September 12, 2014

ቀኝና ግራቸውን ያለዩ የ21ኛው ክፍለ ዘመን በጎች


 (አንድ አድርገን መስከረም 2 2006 ዓ.ም)፤-
የልዑል እግዚአብሔር ቸርነትና አዳኝነት ከሚገለጥባቸው ምክንያቶች ወይም መንገዶች አንዱ ጠበል ነው፡፡ በገዳማትና አድባራት ቅጽር፣ በቅጽሩ ዙርያና በአካባቢው ሰበካዎች ባሉ የጠበል ቦታዎች በፍጹም እምነት የሚቀርቡ ምእመናን በጠበል እየተጠመቁ ፈውስ ያገኛሉ፤ የእግዚአብሔር ደገኛ ተኣምራት እየተገለጸ ምሕረቱ የተደረገላቸው ሁሉ በየጊዜው ድንቅ ሥራውን እየመሰከሩ ይገኛሉ፡፡

Thursday, September 11, 2014

‹‹መምህር›› ግርማ ከስዊዘርላንድ ሀገር በፖሊስ ተባረሩ


  •  መቁጠሪያ በ15 ዶላር  ቅባ ቅዱስ በ25 ዶላር ሲቸበችቡ ነበር፡፡
  • ወደ ስዊዘርላንድ ያስገቧቸው ሰዎች ከፖሊስ ክስ ይጠብቃቸዋል 


‹‹የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት በ2007 ዓ.ም ወደ ቀደመ ቦታው ይመለሳል››የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፍቃደ ኃይሌ


(አንድ አድርገን መስከረም 01 2007 ዓ.ም)  ፡- ከሁለት ዓመት በፊት በቀላል ባቡር ግንባታ ምክንያት ከቦታው ተነስቶ የነበረው የአቡነ  ጴጥሮስ ሐውልት በአዲሱ ዓመት 2007 ዓ.ም በእርግጠኝነት  ወደ ቦታው እንደሚመለስ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፍቃደ ኃይሌ ተናገሩ፡፡ ከቀናት በፊት በወርሀ ጳግሜ የ2006 ዓ.ም ስራ አፈጻጸምን በሚመለከት እና የ2007ዓ.ም  ስራ ተግባራትን በሚመለከት በጽሕፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ የተቋሙ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፍቃደ ኃይሌ የአቡነ ጴጥሮ ሐውልት ቀድሞ ከነበረበት ቦታ ላይ በአዲሱ አመት እንደሚመለስ ተናረዋል፡፡

ቦታው የባቡር መመላለሻ እንደመሆኑ መጠን ከበታች ለሚነሳው የመሬቴ ንቅናቄ በሀውልቱ ላይ ለሚያደርሰው አደጋ በሚመለከት ለስራ አስኪያጁ ለተነሳላቸው ጥያቁ በሰጡት ምላሽ ‹‹ ሐውልቱ በሚመለስበት ጊዜ በባቡሩ ምክንያት ለሚከሰተው ንቅናቄ(Vibration) በሐውልቱ ላይ ለሚያደርሰው አደጋ በሚመለከት በባለሙያዎች ተጠንቶ ሐውልቱ በቀደመ በቦታ ላይ የሚቀመጥ መሆኑን›› ስራ አስኪያጁ  ጠቁመዋል፡፡