(አንድ አድርገን ነሐሴ 15 2006 ዓ.ም )፡- ዳግማዊ ምኒልክ (ሕዝቡ በፍቅር እምዬ ይላቸው ነበር) ኅዳር ፳፯ቀን ፲፰፻፹፰(1888)ዓ.ም. ወላይታ ከጦና ዋና ከተማ ደልቦ ደረሱ፡፡ እዚኽ የመገኘታቸው ምስጢር የወላይታው ንጉሥ ጦና ‹አልገብርም› ብሎ በመሸፈቱ እሱን ለማረም ነበር፡፡ “…አገር ከጠፋ በኋላ ሲያቀኑት ያስቸግራል፡፡ ገንዘብም በግድ ካልሆነ በቀር በፈቃድ የሰጡት አያልቅም፡፡ አገርህን አታጥፋ፡፡ግብርህን ይዘኽ ግባ፡፡” ብለው በሽምግልና ቢሞክሩም መልሱ እምቢታ በመሆኑ አጤ ምኒልክ ዳሞት ተራራ ላይ ያሰፈሩትን ጦራቸውን አዘው በአንድ ጊዜ ወላይታን አስጨነቋት ፣ ንጉሥ ጦናም ቆስለው ተማረኩ፡፡የሚገርመው ግን መፍቀሬ ሰብዕ እና የዲፕሎማሲ ሰው የሆኑት አጤ ምኒልክ “አይ ወንድሜን እንዲያው በከንቱ ሕዝብ አስጨረስክ” ብለው የንጉሥ ጦና ቁስል እንዲታጠብና እንዲታከም ካስደረጉ በኋላ የተማረከው የባላገሩ ከብት እንዲመለስ አድርገው ፣ ንጉሥ ጦና እስኪያገግሙ በእግዚአብሔር ቸርነትና ብርቱ በሆነው ተጋድሎአቸው የረቱትን ጠብቀው የወላይታን ሕዝብ ሰብስበው “…እንግዲህ ወዲህ የሚያስተዳድርህ ልጄ ወዳጄ ጦና ነውና ተገዛለት፡፡ አውቆ ሳይሆን ሳያውቅ እኔን የበደለ መስሎት ሰው አስጨረሰ እንጂ ከድሮም ከአያቶቻችን ቂም የለንምና መልሼ እሱን ሾሜልሃለው፡፡…እንግዲህ ወዲህ ብታምጽ በራስህ ዕወቅ፡፡ ግብሬን አግባ፡፡…” የሚል አዋጅ አስነግረው የወጉዋቸውን ጦናን ሾመው ጥር ፲፩ ቀን አዲስ አበባ ገቡ፡፡(አጤ ምኒልክ መጽሐፍ በጳውሎስ ኞኞ)Monday, July 21, 2014
ወላይታ ፡ የፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት መገኛ
(አንድ አድርገን ነሐሴ 15 2006 ዓ.ም )፡- ዳግማዊ ምኒልክ (ሕዝቡ በፍቅር እምዬ ይላቸው ነበር) ኅዳር ፳፯ቀን ፲፰፻፹፰(1888)ዓ.ም. ወላይታ ከጦና ዋና ከተማ ደልቦ ደረሱ፡፡ እዚኽ የመገኘታቸው ምስጢር የወላይታው ንጉሥ ጦና ‹አልገብርም› ብሎ በመሸፈቱ እሱን ለማረም ነበር፡፡ “…አገር ከጠፋ በኋላ ሲያቀኑት ያስቸግራል፡፡ ገንዘብም በግድ ካልሆነ በቀር በፈቃድ የሰጡት አያልቅም፡፡ አገርህን አታጥፋ፡፡ግብርህን ይዘኽ ግባ፡፡” ብለው በሽምግልና ቢሞክሩም መልሱ እምቢታ በመሆኑ አጤ ምኒልክ ዳሞት ተራራ ላይ ያሰፈሩትን ጦራቸውን አዘው በአንድ ጊዜ ወላይታን አስጨነቋት ፣ ንጉሥ ጦናም ቆስለው ተማረኩ፡፡የሚገርመው ግን መፍቀሬ ሰብዕ እና የዲፕሎማሲ ሰው የሆኑት አጤ ምኒልክ “አይ ወንድሜን እንዲያው በከንቱ ሕዝብ አስጨረስክ” ብለው የንጉሥ ጦና ቁስል እንዲታጠብና እንዲታከም ካስደረጉ በኋላ የተማረከው የባላገሩ ከብት እንዲመለስ አድርገው ፣ ንጉሥ ጦና እስኪያገግሙ በእግዚአብሔር ቸርነትና ብርቱ በሆነው ተጋድሎአቸው የረቱትን ጠብቀው የወላይታን ሕዝብ ሰብስበው “…እንግዲህ ወዲህ የሚያስተዳድርህ ልጄ ወዳጄ ጦና ነውና ተገዛለት፡፡ አውቆ ሳይሆን ሳያውቅ እኔን የበደለ መስሎት ሰው አስጨረሰ እንጂ ከድሮም ከአያቶቻችን ቂም የለንምና መልሼ እሱን ሾሜልሃለው፡፡…እንግዲህ ወዲህ ብታምጽ በራስህ ዕወቅ፡፡ ግብሬን አግባ፡፡…” የሚል አዋጅ አስነግረው የወጉዋቸውን ጦናን ሾመው ጥር ፲፩ ቀን አዲስ አበባ ገቡ፡፡(አጤ ምኒልክ መጽሐፍ በጳውሎስ ኞኞ)Sunday, July 20, 2014
ምንፍቅናን በ‹‹ምክር›› ወይስ በ‹‹ንስሐ›› ?
(አንድ አድርገን ሐምሌ 13 2006 ዓ.ም)፡- በደብረ ብርሃን ቅድስት
ሥላሴ ቤተክርስያን አስተዳዳሪ “መልአከ ብርሃናት አባ” ማርቆስ ብርሃኑ ከምዕመኑ እና ከማኅበረ ካህናት በተነሳባቸው አስተዳደራዊ
እና ሃይማኖታዊ ህጸጽ ጥያቄ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትአስፈላጊውን ማጣራት ካደረገ በኋላ በ28/02/06 ዓ.ም
አባ ማርቆስን ከአስተዳዳሪነት ሥራቸውን ከደመወዝ ጋር ማገዱ ይታወቃል ፡፡ ጉዳዩም በመንበረ ፓትያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት እንዲታይ
መወሰኑ ይታወቃል…
መንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት የሰጠው ውሳኔ እንደሚቀጥለው አቅርበነዋል
“መልአከ ብርሃናት አባ” ማርቆስ ብርሃኑ ከምዕመኑ እና ከማኅበረ ካህናት የተከሰሱባቸው ዋና ዋና ነጥቦች
- ‹‹አማላጅነት የጌታ ተግባር ነው፤ ኢየሱስ አማላጃችን ነው እሱ ሁሉን ፈጽሞልናል›› ብለው መስበካቸውን
- ‹‹ማርያምን ስሰብክላችሁ ደስ ይላችኋል ፤ ስለ ኢየሱስ ግን ይከፋቸዋል ፤ ማርያም እኮ ከእግዲህ ዋጋ የላትም›› ብለው ማስተማራቸውን
- ተአምረ ማርያም ፤ ድርሳናት ፤ ገድላት በጸበል ቤት እንዳይነበቡ ማገዳቸውን በርካታ ምዕመናንና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያና በምስክርነት ቆመው መስክረውባቸዋል፡፡
Friday, July 18, 2014
ቋሚ ሲኖዶስ ለፓትርያርኩ ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ሰጠ
- አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለመጥራት ታቅዶ ነበር፡፡
- ፓትርያርኩ በአ/አበባ የአድባራት አለቆች ዝውውት ስሕተት መፈጸማቸውን አምነዋል፡፡
- ‹‹የቤተክርስቲያንን ሥራ ይጎዳል በሚል እንጂ ተመራጩ ነገር ከእሳቸው ጋር(ፓትርያርኩ) ጋር መሥራት ማቆም ነበር፡፡›› የቋሚ ሲኖዶስ አባል የተናገሩት
- ፓትርያርኩ ከአሁኑ መንገዳቸው ካልተጠቆማቸው ፤ ስህተታቸው ካልተነገራቸው ቤተክርስቲያኒቱን አደጋ ላይ ሊጥሏት ይችላሉ፡፡
አንድ አድርገን ሐምሌ 12 2006
ዓ.ም፡-
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ
ክርስቲያን ሕግን የመተርጎምና የማስፈጸም መብት ያለው ቋሚ ሲኖዶስ ፤ ውሳኔዬን አክብረው አላስከበሩኝም ፤ ጠብቀው አላስጠበቁኝም
ላላቸው ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተገለጸ፡፡
Tuesday, July 15, 2014
Saturday, July 12, 2014
የላሊበላን አብያተ-ክርስቲያናትና የፋሲል ቤተመንግስትን በናኖ ቴክኖሎጂ ለማደስ ታቅዷል
From Addis Admass
ጥንታውያኑ የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትና የጎንደር ፋሲለደስ አብያተ መንግስታት ህንፃዎች ለዘመናት ሳይፈራርሱ እንዲቆዩ ለማድረግ ያስችላል በተባለው ናኖ ቴክኖሎጂ ለማደስ ታቅዷል፡፡ በጎንደር ዩኒቨርሲ የእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን መስፍን፤ ቴክኖሎጂው በዓለም ላይ እየተስፋፋ እንደሆነ ጠቁመው፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲም የናኖ ቴክኖሎጂ ማዕከል አቋቁሞ በቅድሚያ በአብያተ ክርስቲያናቱና ቤተመንግስቱ ህንፃዎች ላይ ቴክኖሎጂውን ቻመተግበር እቅድ መያዙን፤ በቀጣይ ዓመትም ፕሮጀክቱ እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡
Monday, July 7, 2014
መለያየት የወቅቱ የቤተ ክርስቲያን አደጋ
የአንድ ምዕመን አስተያየት
(አንድ አድርገን ሰኔ 30 2006 ዓ.ም )፡- መስቀል ለእኛ ለምናምንበት ድህነትን ያገኘንበት፤ ተለያይተው የነበሩትን እግዚአብሔርና ሰዎችን እንዲሁም ሰዎችና ሰዎችን አንድ ያደረገና ያስታረቀ ለሰው ልጆች ሰላምን፤ ፍቅርን፤ እርቅን፤ አንድነትን ፤ ጽድቅን ያደለ ሁሌም ከልባችን የማይጠፋ ውለታ የተዋለበት ነው፡፡ ይሁንና ጌታ በመስቀሉ ያደለንን ነጻ ስጦታ ገፍተን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በተቃራኒው ጠብንና መለያየትን እያስፋፋን ወደ ከፋ ደረጃ እየሄድን እንገኛለን፡፡
ቤተ ክርስቲያን ባለፉት ዘመናት ብዙ ፈተናዎችና አደጋዎችን አልፋለች፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው በእግዚአብሔር እርዳታ አባቶቻቸንንና ምእመኖቿ በጋራ ባደረጉት ከፍተኛ ተጋድሎ የተነሳ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ብዙ የምንታወቅበት ነገር ምንም አይነት ልዩነት ቢኖረን ሀገርንና ሃይማኖትን ሊነካ የውጭ ጠላት ሲመጣ ተባብረን አሳፍረን በመመለሳችን ነው፡፡ ይህ የውስጥ አንድነት ለጥንካሬያችን መሰረቱ ነው፡፡
Thursday, July 3, 2014
ንብረትነታቸው የቦሌ ቡልቡላ መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን የሆኑ 53 የንግድ ቤቶች ፈረሱ
- የቤተክርስቲያኒቱ ካህናት በፖሊሶች በጥፊ ሲመቱ ነበር፡፡
- የፈረሰው ንብረት ዋጋ 6 ሚሊየን ብር ይጠጋል ተብሎ ተገምቷል፡፡
(ኢትዮ ምኅዳር ሰኔ 25
2006 ዓ.ም)፡- ንብረትነታቸው የቡልቡላ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን የሆኑ 53 የንግድ ቤቶች የግንባታ ፍቃድ የላቸውም በሚል
ሐሙስ ሰኔ 19 ቀን 2006 ዓ.ም መንግሥት በላካቸው ግብረ ኃይል መፍረሳቸው ተቃውሞ አስነሳ፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቷ ካህናት ልብሰ
ተክህኖ ለብሰው ፤ መስቀልና ጥላ ይዘው እንዳይፈርስባቸው ቢጠይቁም በወቅቱ ተቀባይነት ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አፍራሽ
ግብረ ሃይል የንግድ ቤቶቹ በሚፈርሱበት ሰዓት ፤ ቤተ ክርስቲያኗ ባሰማችው ደውል የተሰበሰቡት ምዕመናን ካህናትና የሱቆቹ ተከራዮች
በቦታው በመገኝት የረዥም ጊዜ ገደብ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ ከፖሊስ
ጋር በመጋጨታቸው አስር የሚጠጉ ካህናትና የተለያዩ ግለሰቦች በዱላ እና በጥፊ እየተደበደቡ ወደ መኪና ሲገቡ የተመለከትን ሲሆን
በወቅቱ በስፍራው ላይ የተገኙት ጋዜጠኞች በመፍረስ ላይ ያሉትን ቤቶች ፎቶ ግራፍ እንዳያነሱ እና ተበዳዮችን እንዳያነጋግርሩ ተደርጓል፡፡
Wednesday, July 2, 2014
‹‹አንቀናጅ ፤ አብረንም እንሥራ››
የማኅበሩ መልዕክት
ከሚለው ገጽ
ከሐመር መጽሔት የተወሰደ
ግንቦት 2006 ዓ.ም
ማኅበራችን የአገልግሎት ማኅበር ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር አስፈላጊነቱን አምኖ ፤ የአገልግሎት መስመሩንም
በደንብና መመሪያ አስምሮ በመፍቀድ ያቋቋመውም ከዚህ አገልጋይነቱ የተነሳ ነው፡፡ በመኾኑም ማኅበሩ በይፋ ከተመሰረተበት 1984
ዓ.ም ጀምሮ ቤተ ክርስቲያኗን በአባላቱ ሞያ ፤ ጉልበትና ገንዘብ
እያገለገለ ለዛሬ ደርሷል፡፡ ሕዝቡን ለአገልግሎት በሚጠራና በሚያተጋ አምላክ ፈቃድም ወደፊት አገልግሎቱን እንደሚቀጥል ያምናል፡፡
ሐዋርያዊት በኾነችው ቤተ ክርስቲያን ሥር ለአገልግሎት የቆመው ማኅበራችን ፤ አገልግሎት የጋራና በምትገለገለው ቤተ ክርስቲያን
ዕቅፍ ሥር ያሉ ሁሉ ሊተባበሩት የሚገባ መኾኑን በአፅንዖት ያምናል፡፡ ይህንንም ከምስረታው ጀምሮ በተግባር ሲገልጥ ቆይቷል፡፡ በቤተ
ክርስቲያናችን ዕቅፍ ውስጥ በመኾኑ ከሚመስሉትና ዓላማውን ከሚጋሩት ማኅበራትና አካላት ጋር ልዩ ልዩ ቅንጅቶችን በመፍጠር እያገለገለ
ከዛሬ ደርሷል፡፡ ወደፊትም ይቀጥላል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)




