- ስለማኅበራት የሰጡትን አስተያየት መልሰው እንዲያጤኑት ተጠየቀ
- ‹‹ማኅበራትበትኩረትሊመሩናጉዟቸውምእየተፈተሸሊስተካከልይገባል›› - መንግሥት
(አዲስ አድማስ
የካቲት 29 2006 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ
ማትያስ ‹‹ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው ቤተ ክርስቲያንን እንምራ እያሉ
ነው፤ ቤተ
ክርስቲያኒቱ ትውፊትና ሥርዓት አላት፤እንዲህ ማለት
አይችሉም›› በማለት የሰጡትን አስተያየት መልሰው እንዲያጤኑት በንግግራቸው ቅር
የተሰኙ የመንፈሳውያን ማኅበራት አገልጋዮች ጠየቁ፡፡አገልጋዮቹ ለአዲስ አድማስ እንደተናገሩት፣ አቡነ ማትያስ ይሄን አስተያየት የሰነዘሩት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ከኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ጋር በመተባበር የካቲት 21 እና 22 ያዘጋጁት ሀገር አቀፍ የስብከተ ወንጌል የምክክር ጉባኤ በተካሔደበት ወቅት ነው፡፡
