(አንድ አድገን ህዳር 28 ፤
2005 ዓ.ም)፡- መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል “ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር
የታመነ ነው። ትታገሡም
ዘንድ እንድትችሉ
ከፈተናው ጋር መውጫውን
ደግሞ ያደርግላችኋል።” የፍቅር
እጦት እንጂ ሰውም በወንድሙ ላይ በክፋትና በአመፅ
አይነሳምና ቃየል አቤልን
በምቀኝነትና በጥላቻ
ተነሳስቶ እንደገደለው ሁሉ ዛሬም ብዙ ቃየላውያን በወንድሞቻቸው ላይ በትዕቢት እና በእብሪት ተነሳስተው የሚሞት
ስጋቸውን ለመግደል ያሴራሉ።
መግደል ለእነርሱ
እጅግ የቀለለ ተግባር
ነው፤ ቀድመው
ህሊናቸውን ገድለዋልና። ነገር ግን ዛሬም አሁንም በዚች ቅጽበትም
በንስሃ ለተመለሰ
ሁሉ ምህረት አለ።
ከጥፋት መንገድ
ዘወር ላለ መዳን ይሆንለታል። ነገር ግን እንደቀደመው ጊዜ በክፋትና በተንኮል
ለመመላለስ ልቡን ያደነደነ፣
ፍቅርን የገፋ፣
ምህረትን የናቀ፣ ለወገኖቹ
መጥፊያ ያሴረ፣
ጥላቻን ያነገበ እርቅን
የጠላ ሰው ወይም ቡድን የኋላ ኋላ በታላቅ አወዳደቅ መንኮታኮቱ
አይቀርም።Friday, December 7, 2012
እርቀ ሰላም ፍቅር
(አንድ አድገን ህዳር 28 ፤
2005 ዓ.ም)፡- መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል “ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር
የታመነ ነው። ትታገሡም
ዘንድ እንድትችሉ
ከፈተናው ጋር መውጫውን
ደግሞ ያደርግላችኋል።” የፍቅር
እጦት እንጂ ሰውም በወንድሙ ላይ በክፋትና በአመፅ
አይነሳምና ቃየል አቤልን
በምቀኝነትና በጥላቻ
ተነሳስቶ እንደገደለው ሁሉ ዛሬም ብዙ ቃየላውያን በወንድሞቻቸው ላይ በትዕቢት እና በእብሪት ተነሳስተው የሚሞት
ስጋቸውን ለመግደል ያሴራሉ።
መግደል ለእነርሱ
እጅግ የቀለለ ተግባር
ነው፤ ቀድመው
ህሊናቸውን ገድለዋልና። ነገር ግን ዛሬም አሁንም በዚች ቅጽበትም
በንስሃ ለተመለሰ
ሁሉ ምህረት አለ።
ከጥፋት መንገድ
ዘወር ላለ መዳን ይሆንለታል። ነገር ግን እንደቀደመው ጊዜ በክፋትና በተንኮል
ለመመላለስ ልቡን ያደነደነ፣
ፍቅርን የገፋ፣
ምህረትን የናቀ፣ ለወገኖቹ
መጥፊያ ያሴረ፣
ጥላቻን ያነገበ እርቅን
የጠላ ሰው ወይም ቡድን የኋላ ኋላ በታላቅ አወዳደቅ መንኮታኮቱ
አይቀርም።Wednesday, December 5, 2012
ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ ደብዳቤ ጻፉ
- “የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፤ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና ለሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር ” ደብዳቤውን እንዲያውቁት የተባሉት መስሪያ ቤቶች
- “ከስልጣኔ ውጪ ነው ያደረኩት ፤ በችኮላ የተጻፈ ደብዳቤ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ፤ በስሜትና በችኮላ የሆነ ነገር ነው ፤ ስለ ሰራሁት ስህተት አቡነ ናትናኤል ይቅርታ አድርጌልሃለሁ ብለውኛል” ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ
- “ይህ የእናንተ ጉዳይ አይደለም አያገባችሁም” አቃቢ መንበር አቡነ ናትናኤል
(አንድ አድርገን ህዳር 27 2005 ዓ.ም)፡-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አራተኛ ፓትርያርክ ብጹእ
አቡነ መርቆርዮስ ከነሙሉ ክብራቸውና ማዕረጋቸው ወደቀደመ ቦታቸው እንዲመለሱ የሚጋብዝ ከኢትዮጵያው ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ
ደብዳቤ መጻፉ ተሰማ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች
መካከል ቀኖና ተጣሰ በሚል ምክንያት በሁለቱ መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ለመፍታት በሰሜን አሜሪካው የሰላም ኮሚቴው አስተባባሪነት
ሶስተኛውን የእርቀ ሰላም ድርድር ረቡዕ ህዳር 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአሜሪካ ዳላስ ውስጥ መጀመራቸው ታውቋል፡፡ ለዚህው እርቀ
ሰላም ጉባኤ ከአዲስ አበባው ፩ኛ/ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የልዑካኑ መሪ፣ ፪ኛ/ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ አባል፣ ፫ኛ/ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ አባል ፬ኛ/ ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ በጸሐፊነት የተወከሉ ሲሆን ከአሜሪካው ሲኖዶስ
፩ኛ/ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የልዑካኑ መሪ፣ ፪ኛ/ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ አባል፣ ፫ኛ/
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ አባል ፬ኛ/ ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ በጸሐፊነት ተወክለዋል፡፡ የዳላሱ ጉባኤ ከመጀመሪያው
የዋሽንግተን ጉባኤ ለየት የሚያደርገው አባቶች አብረው ጸልየውና አብረው ማዕድ ቀርበው የጀመሩት ጉባኤ በመሆኑ ተስፋ ሰጪ ነው ተብሏል፡፡ “ውግዘት” የሚለው አልፈው አብረው በአንድ ማዕድ
መቀመጣቸው እና አንድ ላይ ጸሎት ማድረጋቸው በዋነኛነት ሁለቱም ወገኖች ለሰላሙ መሳካት ፍላጎት እንዳላቸው ፤ ቀጥሎም የሰላምና
የአንድነት ጉባኤውን ጥረት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ትላንት ህዳር 26 የተጀመረው የሰላም ጉባኤ አባቶች የሚነጋገሩበት ጉዳይ እና የሚደርሱበት የስምምነት
ሃሳብ ምዕመኑ በከፍተኛ ተስፋ የሚጠብቀው ጉዳይ ሆኗል ፡፡ ይህ ደግሞ በዛሬ እና በነገ የሚታይ ውጤት ይሆናል፡፡
Wednesday, November 28, 2012
ሚስጥረኛው መንግስታችን
- “ኢጣልያኖች የምኒሊክን ሐውልት ሲያወርዱ የተመለከተ አንድ ትንሽ ልጅ ጮሆ አለቀሰ፡፡ ኢጣልያኖችም ለምን እንደጮህና እንዳለቀሰ ልጁን ጠየቁት፡፡ልጁም የንጉሴን ምስል ስላወረዳችሁ ነው አላቸው፡፡ ኢጣልያኖችም ከሙሶሎኒ ሌላ ንጉስ እንደሌለ ነግረውና ገርፈው አባረሩት…” ኒውዮርክ ታይምስ የካቲት 13 ቀን 1937 ዓ.ም እትም
(አንድ አድርገን ህዳር 20 ቀን
2004 ዓ.ም)፡- ለዚች ሀገር እጅጉን ብዙ ውለታ ከዋሉት የሀገር
መሪዎች ግንባር ቀደም መሪ ዳግማዊ አጼ
ምኒሊክ ናቸው
ቢባሉ ማጋነን አይሆንም፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ ሚኒሊክ ከጂቡቱ አዲስ አበባ ድረስ ተዘርግቶ ማየት የፈለጉት ከ10 ዓመት በላይ
በርካታ ዋጋ የከፈሉበትና የደከሙበት የባቡር ዝርጋታው በርካታ መቶ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ የአዲስ አበባ ምስራቅ
መውጫ አቃቂ ከተማ እንደደረሰ ህይወታቸው እንዳለፈ ታሪክ ይናገራል
፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርም የዛሬ 100 ዓመት ሚኒሊክ ሊያዩት ያሰቡትን ባቡር እሳቸውም ማየት ቢመኙትም ስራው በእሳቸው ዘመን
ተጀምሮ ስራው ሳይጠናቀቅ ለህዝቡ ሚስጥር በሆነ ህመም ህይወታቸው
ሊያልፍ ችሏል፡፡ የሚኒሊክ ሞት ህዝቡን ክፉኛ ይረብሸዋል ሀገሪቱ ላይም አለመረጋጋት ያመጣል ተብሎ ስለታሰበ ከሞቱ በኋላ ከ1902 -1906 ዓ.ም ድረስ ሞታቸው ለህዝብ
ሚስጥር ነበር በማለት ታሪክ ይነግረናል ፤ የጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊም ህዝቡ ነሐሴ 15 2004 ዓ.ም አረፉ ተብሎ ቢነገረውም ፤ ሌሎች ጉዳዩን በቅርብ እናውቃለን የሚሉ ሰዎች ከሞቱ
40 ቀን አልፏቸው ሞታቸው ይፋ እንደወጣ ይናገራሉ፡፡ Tuesday, November 27, 2012
በእንተ ሐውልት
From :- Abel Wabella
ለአንዳንድ ኦርቶዶክሳውያን
(አንድ አድርገን ህዳር 19 ፤ 2005 ዓ.ም)፡- የሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስን ሐውልት መነሳት አስመልክቶ ጥቂት ያሳዘኑኝ ጉዳዮች አሉ፡፡ የመጀመሪያው “ሐውልቱ መነሳቱ ካልቀረ ቢነሳ ችግር የለውም” የሚለው ነው፡፡ ለኔ እንደሚገባኝ እንዲህ ማለት አቡኑ የከፈሉትን መስዋዕትነት ማቃለል እና ዋጋ ማሳጣት ነው ፡፡ ይህን የምልበት ምክንያት መጀመሪያ ስርዓቱ (ሕወሓት መር) ቤተ ክርስቲያኒቷን ሆን ብሎ ከስሯ ለመንቀል እንደሚንቀሳቀስ የታወቀ ነው፡፡ ከትጥቅ ትግል እስካሁን ድረስ ይህ አቋሙ አልተለወጠም ፤ ትላንት ደብረ ዳሞ ገብተው ቤተ ክርስቲያኒቷን እንዲሰልሉና እንዲሰነጥቁ የሐሰት መነኮሳት እያሰለጠነ ሲያሰርግ የነበረው ስብሐት ነጋ ዛሬ ደግሞ ትልቁ ስኬታቸው የኦርቶዶክስ እና የአማራ(አማራ የሚባል ነገር?) “የበላይነት”(quote unquote ) ማስቀረት እንደሆነ በድፍረት ተናግሯል፡፡ ይህ የሚያሳየው ስርዓቱ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የጠነከረውን በትር ቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ እንደሚያሳርፍ ነው፡፡ ስኳር ፋብሪካ ሲባል ተነስቶ ዋልድባ ላይ ፣ መንገድ ሲባል ደግሞ ተነስቶ የሰማዕቱ ሐውልት የሚታይ ከሆነ ለምን ? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡ በሰለጠነው አለም የአንድ ግለሰብ መኖሪያ አከባቢ አዲስ ነገር ሲሰራ የሚሰራው ነገር በሰውዬው የወትሮ እንቅስቃሴ፣ አስተሰሳሰብ ፣ ልማድ ላይ ያለው ተጽእኖ ታይቶ በንድፍና በሞዴል ቀርቦለት የግል አስተያየቱን እንዲሰጥ ይጠየቃል፡፡ የአንድ ግለሰብ፣ የአንድ ነፍስ፣ የአንድ ንፋስ መብት! እኛ ግን ብዙ ሚሊዮኖች ሳለን እንደማንኛውም ተራ ዜና፣ እንደ ማንኛውም የሐማስ ሮኬት ከሬዲዮ መስማታችን እጅግ ያሳዝናል፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ ሐውልቱ እንደማንኛውም ድንጋይ እናነሳዋልን ሲሉን ተሸቀዳድመን “የሚመለስ ከሆነ” ብለን እሺ ማለታችን እጅግ የሚያሳፍር ነው፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)