Wednesday, July 11, 2012

የደብረብርሃን ቅድሥት ሥላሴ ቤተክርስትያን 100ኛ ዓመት በዓል በታላቅ ድምቀት ሐምሌ 7/2004 ዓ.ም ይከብራል፡፡



ከአፄ ዘርአያዕቆብ እስከ ንጉስ አዝማች ወሰን ሰገድ
(አንድ አድርገን ሐምሌ 4 ፤ 2004ዓ.ም)፡- የቀድሞ ስሟ ደብረ ኤባ በመባል የምታወቀዋ የአሁኒቷ ደብረ ብርሃን ከተማ በዘመኑ በአፄ ዘርአያዕቆብ ዘመነ መንግስት በዚች ከተማ እስጢፋና ተከታዮቹ ለማርያምና ለመስቀሉ አንሰግድም የሚሉ ሀይማኖት ተቃዋሚዎች በማንሳታቸው የእስጢፋን ተከታዮች ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ለመመለስ በአምስት መቶ የሀይማኖት ሊቃውንት በደብረ ኤባ ጉባኤ ተደርጎ የሀይማኖት ክትትል ከተደረገ በኋላ የእምነቱ ተከታዮች የኦርቶዶክስን ሃይማኖት አንቀበልም በማለታቸው በወቅቱ እንዲለዩ መደረጋቸው ታሪክ ይናገራል፡፡

ይህ የታሪክ ክስተት ከተፈፀመ በኋላ ከተደረጉ ተአምራቶች አንዱና ዋነኛ ከኦርቶዶክስ ከተለዩ በ38ኛው ቀን መጋቢት 10/1446 ዓ.ም 3 ጊዜ ሁለቱ በስረአት ቁርባን አንዱ ካህናቱ ስበሀተ እግዚአብሔር በሚያደርሱበት ሰአት ብርሃን ከሰማይ እንደወረደ በዚህም ምክንያት የከተማዋ ስም ደብረ ብርሃን ተብሎ እንደተሰየመ ዜና መዋዕላቸው ይገልፃል፡፡

Thursday, July 5, 2012

“ማህበረ ቅዱሳን አክራሪና ጽንፈኛ ማህበር ነው” በማለት በጦላይ ጦር አካዳሚ ለአመራሮች ስልጠና ተሰጠ



(አንድ አድርገን ሰኔ 27 2004 ዓ.ም)፡- የመንግስት አካሄድ ከቀን ቀን እየከፋ እየመጣ ነው ፤ ነገሩ ከተነሳበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ የምንሰማው እና የምናየው ነገር ጥሩ አይደለም ፤ በየዓመቱ ከሰኔ እስከ መስከረም አጋማሽ በቀበሌ ፤ በክፍለ ከተማ ፤ በክልል በወረዳ ደረጃ ያሉ የኢህአዴግ አባላት ጦላይ ጦር ማሰልጠኛ ካምፕ  በመላክ ፖለቲካዊ ትምህርት እንደሚማሩ ይታወቃል ፤ ሀገሪቱ በተለያዩ ሀገራት ሰላም ማስከበር ብላ የምትልካቸው ከወታደር አንስቶ እስከ ጀኔራል ድረስ ያሉ ሰዎች ጦላይ ሳይደርሱ የፖለቲካ መርፌ ሳይወጉ ደቡብ ሱዳንም ሆነ ቡሩንዲ መሄድ አይቻልም ፤ ለተራ ወታደር ከሶስት እስከ ስድስት ወር የሚደርስ በተለያዩ ነገሮች ላይ ያተኮረ ስልጠና ሲሰጥ በአመራር ደረጃ ያሉት ደግሞ እስከ ሁለት ወር የሚያቆይ ስልጠና እንደሚወስዱ ይታወቃል ፤ የዛሬ 2 ዓመት ገደማ ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ከ800 በላይ የኦህዴድ አባላትን ወደ አዲስ አበባ በማምጣት የተለያዩ ፖለቲካዊ የስልጣን ተዋረድ ላይ ያስቀመጣቸው ኢህአዴግ ለሁለት ወር ያህል ጦላይ ማሰልጠኛ ሄደው በቪዲዮ ኮንፍረንሲንግ ሲስተም  አማካኝነት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ የተለያዩ ሚንስትር ዴታዎች አማካኝነት ስልጠና ከወሰዱ በኋላ ለሁሉም አባላት አዲስ አበባ ውስጥ በኪራይ ቤቶች የሚገኙ ቤቶችን  ያለምንም ክፍያ እንደተሰጣቸው  ይታወቃል ፤ ኪራይ ቤት ለታጣላቸው ከተማዋ ውስጥ ያሉትን  ኮንዶሚኒየም ቤቶች መርጠው አባል እስከሆኑ ድረስ እንዲኖሩበት ተሰቷቸው ፤ በአሁኑም ሰዓት ድርጅቱን በማገልገል በገጸበረከት በተበረከተላቸው ቤቶች ውስጥ ኑሯቸውን እየኖሩ ይገኛሉ ፤ አሁን እኛን ይህ ጉዳይ ለመጻፍ ሳይሆን አነሳሳችን ጦላይ የጦር አካዳሚ ምን አይነት ስልጠና እንደሚሰጥ ? ፤ ምን አይነት አመራሮች ወደ ቦታ ሄደው እንደሚሰለጥኑ ?  ለምን አላማ እንደሚታጩ ? ቦታው ያለውን ገጽታ ለናንተው ለማስገንዘብ ያህል  ነው፡፡

Tuesday, July 3, 2012

‹‹ብዙ ሃይማት አንዲት ሀገር›› ኢቲቪ የለቀቀው ውዥንብር


  •  982 ነጻ አስተያየት ወደ ኢቲቪ ከደወሉት አስተያየት ሰጪዎች ውስጥ 90 በመቶ ባዩት ነገር የተናደዱ እና የነበሳጩ ሆነው ነገኝተዋል
  • እውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መጤ ነችን?
(አንድ አድርገን ሰኔ 27 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ክብር ባህል እምነትና ስርዓት መንግስትና ቋንቋ ያቋቋመች የማትናወጥ ከመሆኗ ጋር ከሔኖክ ፤ ከኖህ ፤ ከመልከ ጼዴቅ ከነብያትና ከሀዋርያት ተላለፈውን ትምህርት ስርዓት ፤ እምነት ከትውልድ ወደ ትውልድ ስታስተላልፍ የኖረች በማስተላለፍ ላይ ያለች ፎኖተ ህይወት መሆኗ የተረጋጠ ነው፡፡  ቅዱሳን አበውን ፤ ኃያላን ነገስታትን ፤ ልዑላን መሳፍንትን ፤ ክቡራን መኳንንትን ፤ ዐይናሞች ሊቃውንትን በስጋ በነፍስ ወልዳ ያሳደገች የሌላ የማትፈልግ የራሷ የማትለቅ ዕጥፍ እናት ፤ ስንዱ እመቤት ናት፡፡

በሞንታቦ ቤተክርስትያን በር ላይ የሚካሄድ ህገ ወጥ ንግድ ከ10ሺህ ብር በላይ የሚስቀጣ አዋጅ ሊወጣ ነው



  • አዋጁ ሚኒባስ ላይ ሞንታርቦ በመስቀል በየትኛው ቦታ ላይ የሚደረግ ማንኛውም ንግድ ከብሮድካስት ባለስልጣን ፍቃድ ያስፈልገዋል ይላል፡፡
  • አዋጁ በምክክር ላይ ስላለ ቤተክርስትያን በንብረቶቿ አማካኝነት የሚሰራን ማስታወቂያ እንዳይኖር በአዋጅ ውስጥ እንዲካተትላት መጠየቅ ትችላለች፡፡
  • አዋጁ ላይ ኦርቶዶክሳውያን ማንሳት የሚገባን ጥያቄ……..?????

(አንድ አድርገን ሰኔ 24 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- በተለይ በአዲስ አበባ ልደታ ቤተክርስትያን ፤ ምስካየ ኃዙናን መድሃኔዓለም ፤ 5ኪሎ ቅድስተ ማርያም ፤ ቦሌ መድሃኔዓለም ፤ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስትያን ፤ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትን ፤ አዲሱ ሚካኤል እና መሰል ብዙ ምዕመናን በበዓላት ወቅት የሚገኙባቸው አድባራትና አብያተክርስትያናት መንገድ ላይ ሚኒባስ ተከራይተው ሞንታርቧውን ሰቅለው የተለያየ ማስታወቂያ የሚነግሩ የቤተክርስትያኒቱ አስተምህሮ የሆኑትንና ያልሆኑትን አንድ ላይ በመቀላቀል መዝሙሮችንና ስብከቶችን በመሸጥ ስውር ዓላማቸውን የሚያሳኩ ሰዎችንና ማህበራትን መመልከት ከጀመርን ሰንበትበት ብለናል ፤ ከአውደ ምህረት ሲባረሩ በቀላሉ በሚኒባሶች የፈለጉበት የሃገሪቱ ከተማ በመዘዋወር በዓላትን በማስታከክ መዝሙርና ስብከቶቻቸውን  በመሸጥ የንግድ ተግባራቸውን ሲያጧጡፉም ተመልክተን ይህን የሚያስቆም ህግ ባለመኖሩ አይተን እንዳላየን አልፈናል ፤ በተጨማሪ እነዚህ ህገወጦች ከሞንታርቦ ስፒከሮቻቸው አማካኝነት የሚለቁት የድምጽ መጠን የሰው ጆሮ መስማት ከሚችለው በላይ ስለሆነ በጊዜው በየአብያተክርስትያናቱ የሚቀደሰውን ቅዳሴ ፤ የአውደ ምህረቶችን ስብከት እና መዝሙር ለመስማት የተቸገርንበትና ሃይ የሚል የጠፋበት ጊዜ ላይ መድረሳችን ይታወቃል ፤ እነዚህንና መሰል ስውር አላማ ይዘው በ500 መቶ ብር የቀን የሚኒባስ ኪራይ ምንፍቅናቸውን በአደባባይ የሚዘሩ ፤ ፍቅረ ነዋይ አይናቸውን የጋረዳቸው ሰዎችና ማህበራትን የሚመለከት አንድ አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት አማካኝነት ህግ ሊወጣለት መሆኑን በተባራሪ ወሬ ሰማን ፤ አዋጁንም ከአንድ የማስታወቂያ ባለሙያ ወዳጃችን ረቂቁን በመቀበል ማንበብ ችለን ነበር ፤በመሰረቱ አዋጁ በጠቅላላ ሀገሪቱ ላይ የሚደረጉትን የማስታወቂያ ስራች መስመር ለማስያዝ የወጣ ቢሆንም ይህ ጉዳይ ቤተክርስትያን ላይ ስለሚደረጉ ነገሮች በጥቂቱ ስለሚመለከት የእኛን ክፍል ብቻ በማንሳት የአዋጁን ሀሳብና ቅጣቱን ለእናንተው ለማቅረብ ወደድን፡፡

‹‹ብዙ ሃይማት አንዲት ሀገር›› የኢቲቪ ፊልም አንድምታው



 (አንድ አድርገን ሰኔ 25 ፤2004 ዓ.ም)፡-ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርላማ ላይ ስለ አክራሪነት ሰፊ ማብራሪያ ከሰጡ ወዲያ መንግስት የሚያደርገው እንቅስቃሴ ከቀን ቀን እየጨመረ እየመጣ ነው ፤ መንግስት በአዲስ ራዕይ መጽሄት አማካኝነት ሀሳቡን በደንብ አድርጎ ገልጾልናል ፤  ይህን ሀሳብ በህዝቡ ዘንድ ለማስረጽ ይረዳው ዘንድ ዛሬ ሰኞ ማታ ከ2፡00 ሰዓት ዜና በኋላ ‹‹ብዙ ሃይማት አንዲት ሀገር›› የሚል ዶክመንተሪ ፊልም በኢቲቪ እንደሚለቀቅ ሰሞኑን የተመለከትናቸው ማስታወቂያዎች ይናገራሉ ፤ ይህ ወቅታዊውን ነገር መሰረት ተደርጎ የተዘጋጀ ቢሆንም አሁንም እዚህ ደረጃ የሚያደርስ ነገር በክርስትያኑ እና በሙስሊም አማኞች አማካኝነት ተፈጥሯል ብለን አናምንም ፤ ይህን ሁኔታ እዚህ ደረጃ ያደረሰው መንግስት ራሱ ነው ፤ ሙስሊም ወንድሞቻችን “መጅሊስ ይውረድ” ብለው ጥያቄ በመጠየቅ ይህን ጥያቄ ጫፍ የሚያደርስ ኮሚቴ አቋቁመው ለጥያቄያቸው ተገቢ መልስ መንግስት መስጠት ሲሳነው ነገሩን ወደ አክራሪነት በማዞር ከወቅታዊ ነገር ጋር ተገቢ ያልሆነ ትንታኔ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተወካዮች ምክር ቤት አቀረቡ ፤ በዚህ ወቅት 90 በመቶ ንግግራቸው ወሀቢያና  ሰለፊያ ሲሆኑ አንድ ቦታ ላይ ብቻ ተገቢ ያልሆነ አብሮ ሊሄድ የማይችል ምሳሌ በመስጠት የንግግራቸው ማጣፈጫ አድርገው ተጠቀሙብን ፤ ከዚያ የጠቅላይ ሚንስትሩን ንግግር  የሚቃወሙ ድምጾች ከየቦታው መሰማት ጀመሩ ፤ “የአቶ መለስን አቋም እቃወማለሁ” በማለት ሰዎች ውስጣቸውን ተነፈሱ ፤

Friday, June 29, 2012

"የዋልድባን ልማት በግድም በውድም መቀበል ይኖርባችኋል" መንግስታችን


  • "እርሶ እኛን አይወክሉንም እና ልንሰማዎትም ሆነ ቡራኬዎትን አንቀበልም" ከመነኩሳት ወገን      ለብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ
  • "በዋልድባ ገዳም ምንም ድርድር አናደርግም" የአካባቢው ነዋሪ
  • በርካታ ወጣቶችም በመንግሥት ታጣቂዎች ታፍሰው ተወስደዋል
ባለፈው ቅዳሜ በዓዲርቃይ ከተማ ላይ በዋልድባ አካባቢ ሊሰራ በታቀደው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ዙሪያ የአካቢው ነዋሪዎችን፣ የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኤልሳዕ በተገኙበት፣ የመንግሥት ተወካዮች፣ የማኅበረ መነኩሳቱ ተወካዮች በተገኙበት እንዲሁም ከቤተክህነት ተወካዮች በተገኙበት የማስፈራራቱ እና በግድ የማሳመኑ ስራ እንደቀጠለ ነው። ሰሞኑን በደረሱን መረጃ መሰረት መንግስት ለልማቱ እፈልጋቸዋለው ከሚላቸው የዋልድባ ገዳም ክልል ውስጥ የሚፈርሱን መካናት የሚከተሉት ናቸው፡

  • ከአበረንታት
    • ማርገፅ ቅዱስ ሚካኤል  ቤተክርስቲያን
    • ድል ሰቆቃ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን
    • እጣኑ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም  ቤተክርስቲያን
    • ሙሉ ቤት ቅዱስ ሚካኤል  ቤተክርስቲያን
  • ከአባ ነፃ
    • ዲዋር ግዛ ቅዱስ ተክለሃይማኖት  ቤተክርስቲያን
    • ማይ ሸረፋ አቡነ አረጋዊ  ቤተክርስቲያን
    • አዲ ፈረጅ አብዮ እግዚ  ቤተክርስቲያን
    • ማይ ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ  ቤተክርስቲያን
    • ታች እጣኖ ቅዱስተ ማርያም  ቤተክርስቲያን
    • ላይ ኩርማ አቡነ አረጋዊ  ቤተክርስቲያን
    • ጎድጓድ ቅዱስ ጊዮርጊስ  ቤተክርስቲያን
    • ቃሊማ አቡነ ሳሙኤል  ቤተክርስቲያን
    • ቃሊማ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን
    • ቃሊማ ቅድስት ሥላሴ  ቤተክርስቲያን
    • ማይ ዓርቃይ ቅዱስ ሚካኤል  ቤተክርስቲያን እና ሌሎችም ስማቸው ያልተገለጸ አብያተ ክርስቲያናት እንደሚነሱ ዘገባው ደርሶናል።

በባቦጋያ መድሃኒአለም የቦታ ጉዳይ 13 ሰዎች ላይ እያንዳንዳቸው ሰባት ወር ተፈረደባቸው


  • ከ400 በላይ ምዕመናን በእንባ ወደ እስር ቤት ሸኝተዋቸዋል፡፡
  • የፍርድ ቤቱ ውሳኔ የበላይ አካል ተጽህኖ አለበት ፤

(አንድ አድርገን ሰኔ 22 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- በፍርድ ቤቱ ውሳኔ በጣም አዝነናል ፤ ሲጀመር አንስቶ በባቦጋያ መድሃኒዓለም ቦታ እና በኩሪፍቱ ሪዞርት መካከል ያለው የቦታ ውዝግብ በየጊዜው ማቅረባችን ይታወቃል፤ አቅማችን በፈቀደው መጠን ጉዳዩን ሰዎች ዘንድ እንዲደርስ የመፍትሄ አካላት እንዲሆኑ ያላሰለሰ ጥረት አድርገናል ፤ ከወራት በፊት የቤተክርስትያኑን ቦታ በአካባቢው ምዕመናን ጉዳዩን ዳር እዲያደርሱ የተወከሉ ሰዎች በፍርድ ቤት “እናንተ መጠየቅ አትችሉም ቤተክርስትያኒቱ የወከለቻችሁ አካላት አይደላችሁም” በማለት ለኩሪፍቱ ሪዞርት ባለቤት እንደተወሰነለት ገልጸን ፅፈን ነበር ፤ 

Thursday, June 28, 2012

እባካችሁ ተፋቱልን



by Birhanu Admass Anleye (ከፌስ ቡክ ላይ የተወሰደ)
  ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ሃይማኖት ዐምድ ‹‹ ፖለቲካና ሃይማኖት›› በሚለዉ ርእሰ ጉዳይ ከተስተናገደ በኋላ በመጽሔቱ የቦታ ዉስንነት ምክንያት የቀነስኳቸዉን ሁለት አንቀጾች በማካተት የቀረበ ነዉ፤ መልካም ንባብ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዐቢይ ጾም የሚዉሉት እሑዶች እያንዳንዳቸዉ አንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ተአምርን የሚያስታዉስ ስም አላቸዉ፡፡ ለምናገረዉ ታሪክ መነሻ የሆነዉ አራተኛዉ እሑድም መጻጉዕ ይባላል፡፡ በዚህም ጌታችን በምድር ላይ በሽተኞችን የፈወሰበት ተአምራት፣ 38 ዓመት ያህል አንድ አልጋ ላይ ተኝቶ መዳኑን ሲጠባበቅ ከኖረ በኋላ በጌታ በተፈወሰዉና በተለምዶ ‹‹ መጻጉዕ›› (በሽተኛዉ ማለት ነዉ እንጂ የመጠሪያ ስም አልነበረም) እየተባለ በሚጠራዉ ሰዉ ታሪክ መነሻነት ይታሰባል፡፡ በወንጌል እንደተጻፈዉ ጌታ ወደ በሽተኛዉ ከደረሰ በኋላ አስቀድሞ ልትድን ትወዳለህን ሲል ጠየቀዉ፡፡ መልሱን ከሰማ በኋላም ‹‹ ተነሣ አልጋህን ተሸክመህ ሒድ›› ሲል አዘዘዉና ያ በሽተኛ ወዲያዉ ተነሥቶ ድኖ አልጋዉን ተሸክሞ ሔደ፡፡ ታዲያ በዐብዮቱ ዋዜማ አካባቢ በነበረዉ የመጻጉዕ እሑድ እንዲህ ሆነ ይባላል /ዮሐ 5፤1-10/ ፡፡ በዕለቱ ንጉሡም በተገኙበት ቅዳሴዉ ከተቀደሰ በኋላ በተነበበዉ ወንጌል ላይ የሚያስተምሩት እስካሁን የሊቅነትና የእዉነተኛ ኦርቶዶክሳዊ ስብከት መለኪያ ተደርገዉ ከሚጠቀሱት እጂግ በጣም ጥቂት የሀገራችን ሊቃዉንት አንዱ የነበሩት  መልአከ ሰላም ሳሙኤል ተረፈ ‹‹ተንሥእ ወንሣእ ዐራተከ  ወሑር፤  ተነሥ አልጋህን ተሸክመህ ሒድ›› በሚለዉ ኃይለ ቃል መነሻነት ትምህርቱን ይሰጣሉ፡፡ በጊዜዉ ነበርን፤ የተደረገዉን አይተናል ሰምተናል የሚሉ ሰዎች እንደ ነገሩኝ ንጉሡ በዚህ ትምህርት በጣም ተበሳጭተዉ ነበር፡፡ ምክንያቱም ‹‹ አልጋህን ተሸክመህ ተነሥና ሂድ›› የሚለኝ እኔን ነዉ ብለዉ በጊዜዉ ከነበረዉ የሶሻሊስት ርእዮተ ዓለም አራማጅ የተማሪዎች እንቅስቃሴዎች ጋር አገናኝተዉ ስለተመለከቱት የተሰበከዉ በሙሉ ወንጌል ሳይሆን አዲሱ ፖለቲካ መስሏቸዉ ነበር ይባላል፡፡ መልአከ ሰላም ሳሙኤልም ብዙ ሳይቆዩ ስለሞቱ ለአንዳንድ ሰዎች  ትምህርቱን ለሞታቸዉ ምክንያት አድርገዉ እንዲናገሩ ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡

Wednesday, June 27, 2012

1061 የሃይማኖት ድርጅቶች የመቋቋሚያ ፍቃድ ጠይቀዋል


ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበብ


(አንድ አድርገን ሰኔ 20 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- የፌደራል ጉዳዮች  ሪፖርት በቅርቡ አንድ ሰው አምጥቶልን ማንበብ ችለን ነበር  ፤ ሪፖርቱ ከሃይማኖት ጽንፈኝነት ፤በሀገሪቱ ላይ በሃይማኖቶች መካከል የተከሰተውን ችግርን እንዴት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ እንደፈታው የሚያትት ጉዳይ ይገኝበታል ፤ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግቢ ተማሪዎች ሃይማኖታዊ በዓል ለማክበር በጠየቁበት ጊዜ ያቀረቡት ጥያቄ አግባብ አለመሆኑን ከሚመለከታቸው የሃይማኖት አባቶች ጋር በመወያየት የበዓል አከባባሩ ከግቢ ውጪ መሆን እንዳለበትና በጊዜው በዓሉን በዩንቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዳልተከበረ ያስቀምጣል ፤ በመቀጠልም በጅማ አካባቢ የተከሰተውን ችግር ለመፍታት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ለአካባቢው ነዋሪዎች በርካታ ስልጠናዎችን እንደሰጠ እና ከ7000 በላይ ጽሁፎችን ከበርካታ ለማህበረሰቡ እንዳሰራጨ ይናገራል ፤ በአሁኑ ሰዓት ከየሃይማኖት ተቋማቱ በማሰባሰብ የሃይማኖት አንድነት ጉባኤ በየጊዜው መደረጉ በአሁኑ ሰዓት የሚታዩ ችግሮችን ከመፍታትና መስመር ከማስያዝ አኳያ መስሪያ ቤቱ በዚህ ላይ ትልቅ ስራ እንደሰራ አስፍሯል፤ በተጨማሪም በጥምቀት በዓል ወቅት የሃይማኖትን እኩልነት በሚጻረር መልኩ አንዳንድ የኦርቶዶክስ አማኞች በቲሸርቶቻቸው ላይ ያሰፈሯቸው ጽሁፎች እንደ አንድ ችግር በማንሳት በዚህ ላይ የሚመለከተው አካል ሁሉ ህገ መንግስቱን ከማስከበር እና የሃይማኖት እኩልነትን ከማረጋገጥ አኳያ አብሮ መስራት እንዳለበት ያትታል፡፡

Tuesday, June 26, 2012

የቁጥር ነገር


ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበብ

(አንድ አድርገን ሰኔ 19 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- በርካታ ጊዜያት መንግስት እና አለማቀፋዊ ተቋማት የቁጥር ነገር አያስማማቸውም ፤ IMF ወይንም World Bank የሀገሪቱ እድገት በዚህኛው ዓመት 6 ከመቶ አይበልጥም ብሎ ሲተነብይ መንግስት ደግሞ “አይሆንም እኛ ለተከታታይ 6 ዓመታት 11.2 በመቶ ነው ያደግነው” በማለት ዓመታዊ ያልተሰላ ሂሳብ ያቀርባል እና በየዓመቱ ሰኔ አልፎ ሀምሌ ሲመጣ የቁጥር ነገር ዋናው የመከራከሪያ ያለመስማሚያ ነጥብ ሆኖ መመልከት የዘወትር ተግባራችን ከሆነ ሰንበትበት ብሏል፡፡ አሁን እኛ አነሳሳችን ስለ እንደዚህ ዓይነት ነገር ለመናገር አይደለም  ፤ ባይሆን ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ ይህ “የቁጥር ነገር” በሙስሊም ወንድሞቻን ዘንድ እንዴት እየቀረበ መሆኑን ለማስገንዘብ እና ለማሳየት በማሰብ ነው “የቁጥር ነገር” በማለት የተነሳነው፡፡