(አንድ አድርገን ሰኔ 18 ፤
2004 ዓ.ም)፡- “አዲስ ራእይ” ላይ የሰፈረውን ጽሁፍ በሁለት ክፍል ማስቃኝታችን ይታወቃል ፤ ጽሁፉን ወደ ፒዲፌ ቀይረን ለአንባቢያን
ለማቅረብ ቃል በገባነው መሰረት ሙሉ ጽሁፉን ማንበብ የምትፈልጉ ሰዎች የሚቀጥሉትን ሊንኮች በመጠቀም ሙሉውን ጽሁፍ ማንበብ የምትችሉ
መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ እኛ ጽሁፉን ያየንበትን እይታ ለማቅረብ ሞክረናል እስኪ እርስዎም ይዩትና ያዩበትን እይታ ይጻፉልን
፤ ጽሁፉ ምን አይነት አላማን አንግቶ ነው የተጻፈው ? ምንስ ተጽህኖ ወደፊት ያሳድራል ? መንግስት ምን እያሰበ ይመስሎታል ?
መሰል ነገሮችን በራስዎ እይታ አይተው ሀሳብዎን ያካፍሉን….
Monday, June 25, 2012
Sunday, June 24, 2012
የእመቤታችን ተዓምር
(አንድ አድርገን ሰኔ 18 2004 ዓ.ም)፡- ቀኑ እለተ ሰንበት ሰኔ 17 2004 ዓ.ም ፤ ሰንበት እንደመሆኑ የት ሄጄ እንደማስቀድስ ሳወጣ ሳወርድ ውስጤ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያር ገዳም ቤተክርስትያን እንድሄድ አመላከተኝ ፤ ቦታው ጦር ኃይሎች ወደ ወይራ-ቤተል ሲሄዱ አጉስታ ልብስ ስፌት ፋብሪካ አለፍ ብሎ የምትገኝ ቤተክርስትያን ናት ፤ በጣም በጠዋት በመነሳት ካህናት ቅዳሴ ሳይገቡ ለመድረስ ተጣደፍኩኝ ፤ እንደ ሃሳቤም ተሳቶልኝ ቅዳሴ ሳይገቡ መድስረስ ቻልኩኝ ፤ ቅዳሴው ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ ደስ በሚያሰኝ እኛ ውስጥን ሀሴት በሚሞላ መልኩ ቅዳሴው ተጠናቀቀ ፡፡ ከዚያ ቅዳሴው ከተጠናቀቀ በኋላ የቀኑ ተዓምረ ማርያም ተነበበ ፤ ምዕመኑ ሁሉ ቆሞ ፍጹም በሆነ ፀጥታ የእመቤታችንን ተዓምር አደመጠ፡፡Friday, June 22, 2012
የ“አዲስ ራዕይ” አመለካከት (ክፍል 2) ….
ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበብ
- ከዋህቢያ ይሁን ከማህበረ ቅዱሳን ወይም ከሌላው እምነት ውስጥ ጽንፈኝነት አይመለከተኝም የሚለው በግላጭ ወጥቶ እንዲያወግዝ እድል ሊኖረው ይገባል
- ኢህአዴግ የቄሱም የሼሁም ድርጅት ነው ፡፡ ከአባልነት አንጻር የየትኛውም እምነት ተከታይ መሆን ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም ፡፡ የአንድ እምነት ሰባኪ የሆነ ሰው ኢህአዴግ አባል መሆን ይችላል የኢህአዴግ አመራር መሆንን ግን አይፈቀድም
- ደርግ ግለሰቦችን በተናጠል ሲገድል እናንተ ደግሞ ገዳማትን በማፍረስ በጅምላ እምነትንና አማኞችን የመግደል ምግባር ላይ ተሰማርታችኋል
- በርካታ አባላት ማህበረ ቅዱሳን እንደሆኑት ሁሉ በርካታ አባላትም የወሃቢያ ወይም የሌላ የእስልምና ፈለግ ተከታዮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ችግሩ የትኛውም እምነት ይከተሉ የሚለው አይደለም ፡፡ ችግሩ ያለው..............................
(አንድ አድርገን ሰኔ 15 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ከትላንት በስተያ በወፍ በረር በመቃኝት “አዲስ ራዕይ” መጽሄትን በጥቂቱ ለማስዳሰስ ሞክረን ነበረ ፤ አሁን ደግሞ ምን አይነት ነጥቦች እንዳካተተ ፤ በየነጥቦቹ ስር ምን ዓይነት ሀሳቦችን እንደሚያነሳ ለማሳየት እንሞክራለን ፤ የአጻጻፍ ይዘት እና የጽሁፉን ፍሰት አብረን እንቃኛለን፡፡ የራሳችንንም ሃሳብ ጣል በማድረግም እናያለን ፤ ፅሁፉ ሲጀምር “በሰላምና ህገ-መንግስቱ ዙሪያ ሀገራዊ መግባባት መፍጠር የዜጎችና የመንግስት መብትም ግዴታም ነው” በማለት ይጀምራል፡፡
“አንድ አድርገን” ለሁለተኛ ጊዜ ተዘጋች
ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበብ www.andadirgen.blogspot.ca ይጠቀሙ
- “ጠላት የዘጋውን በር አትመልከት ፤ እግዚአብሔር እጅ ያለውን ቁልፍ ተመልከት” አቡነ ሺኖዳ
(አንድ አድርገን ሰኔ 15 2004 ዓ.ም)፡-ህገ መንግስታችን አንቀጽ 29 ቁጥር 1 ላይ “ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ
ገብነት የመሰለውን አመለካከት ለመያዝ ይችላል” ይላል አንቀጽ ቁጥር 2 ደግሞ “ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሀሳቡን የመግለጽ
ነጻነት አለው ፡፡ ይህ ነጻነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሁፍ ወይም በህትመት በስነ
ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም ማሰራጫ ዘዴ ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሀሳብ የመሰብሰብ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን
ያካትታል” በማለት ያስቀምጣል ፤Tuesday, June 19, 2012
ኢህአዴግ “በአዲስ ራእይ” መጽሄት ምን እያለ ነው?
- በተመሳሳይ አንዳንድ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች ሌላው ቀርቶ የተለየ አመለካከት ያላቸው ክርስትያኖችንም ቢሆን የሚከተሉትን እምነት ክርስትና አይደለም ብለው ከማመን አልፈው ፤ እነዚህ ተለየ አመለካከት ያላቸው ዜጎች እምነታቸውን በነጻነት እንዳያራምዱ በተለያየ ሽፋን ማፈን ይከጅላቸዋል፡፡”
- ኢትዮጵያ የክርስትያነ ደሴት ናት ከሚል ቅዥት ባለፈ አንድ “ሀገር አንድ ሃይማኖት” የሚል መፈክር ደረታቸው ላይ ለጥፈው ለመሄድ እንኳን ሀፍረት የማይሰማቸው ሆነው በአደባባይ ይታያሉ
- ወሃቢያን ወይም ሌላው የመከተል የማህበረ ቅዱሳንን ወይም ሌላ አተያይ የመያዝ መብት የዜጎች ነው
- ህዝብ እንዲያገለግል የተቀመጠ ኃላፊና ሰራተኛ በራሱ እምነት ምስሎች አጨመላልቆ የምናይበት ሁኔታ መንግስትና ሃይማኖትን ለመለየት የተቀመጠውን ድንጋጌ በቀጥታ በመጻረር በመሆኑ መወገዝ መወገድ የሚገባው ነው፡
- በክርስትና ውስጥም በአንድ ወይም በሌላ መልኩ በተለይ ከማህበረ ቅዱሳንም የተወሰኑ ከመሰረታዊ የእምነቱ አስተምህሮ ፈንጠር ያሉ .........
- እነዚህ ፅንፈኞች በርካታ ንጹሀን ዜጎችን አሳስተው በማነሳሳትና አንዱ በሌላው ለመዝመት የተዘጋጁ በማስመሰል የፍጥጫ ድባብ እንዲነግስ የሚሰሩ ናቸው
(አንድ አድርገን ሰኔ 12 /2004ዓ.ም)፡-PART 1
አዲስ ራዕይ በየሁለት ወሩ በአማርኛ
ቋንቋ እየተዘጋጀች በኢኮኖሚያዊ ፤ ፖለቲካዊ ፤ ማህበራዊ ፤ ዓለም ዓቀፋዊና ፤ ድርጅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ማብራያና ትንታኔ
ይዛ የምትቀርብ የኢህአዴግ የትንታኔ መጽሄት ነች፡፡ የዚች መጽሄት አዘጋጅ “የኢህአዴግ ህዝብ ግንኙነት ክፍል” ሲሆን አሳታሚው
ደግሞ “ኢህአዴግ” መሆኑን የመጽሄቷ የፊት ገጽ ላይ የሰፈረው ጽሁፍ ይናገራል ፡፡ |
Monday, June 18, 2012
ቅ/ሲኖዶስ በተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅነት ያወገዛቸው 7 ድርጅቶችና 16 ግለሰቦች ውሳኔ ለአህጉረ ስብከት ተሰራጨ
· መናፍቃኑ በማንኛውም የቤተ ክርስቲያናችን የክህነት፣ የክብርና የማዕርግ ስም
አይጠሩም።
· የቤተ
ክርስቲያኒቱን የከበረ ስሟን በማጉደፍ ታሪኳንና ክብሯን በመዳፈራቸው በሕግ ይጠየቃሉ።
· መናፍቃኑ እና ድርጅቶቹ ላሰራጯቸው ኅትመቶች የማስተባበያ ጽሑፎች ይዘጋጃሉ።
· ሊቃውንት
ጉባኤ ከማንኛውም አካል ለሚሰነዘረው ሃይማኖት የሚያጎድፍ ክብረ ነክ ጽሑፍ ምላሽ ለመስጠት በሚችልበት አኳኋን በጥራትና በስፋት
ይጠናከራል።
· ከተወገዙት
ድርጅቶች መካከል የ”አንቀጸ ብርሃን” ድርጅት መሥራች በኾነውና በእጅጋየሁ በየነ አቅራቢነት የፓትርያርኩ መልእክቶች
ጸሐፊ እስከመኾን ደርሶ በነበረው አሸናፊ መኰንን ላይ የተላለፈውን የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ለመቀሠጥ የተደረገው የሸፋጮች ሙከራ
ከሽፏል (ሙከራውን የሰነዱን ገጽ 38 እና 39፣ ተ.ቁ 16ን በማነጻጸር
ይመልከቱ)
· “አሁን የተሐድሶ መናፍቃኑ ዝናራቸውን ጨርሰው የአገልጋዮችን ስም ማጥፋቱን ተያይዘውታል፤
ያወገዝናቸው ስለጠላናቸው ሳይሆን ስለካዱ ነው፤ ሰውን ማስታመም የሚቻለው በምግባር ድክመቱ እንጂ በሃይማኖት ክሕደት
አይደለምና፡፡” /ብፁዕ አቡነ አብርሃም የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ለሀ/ስብከታቸው ሰባክያነ ወንጌል እና ምእመናን ይፋ ሲያደርጉ
ከተናገሩት/
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 9/2004 ዓ.ም፤ ጁን 16/ 2012/ READ THIS
ARTICLE IN PDF)፦ የርክበ
ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለቤተ ክርስቲያንና ለሃይማኖት ጉዳይ በተለይም ለምእመናን አንድነት ቅድሚያ በመስጠት፣
በጉዳዩ ላይ በስፋት በመነጋገር፣ ግንቦት 15 ቀን 2004 ዓ.ም፣ በፕሮቴስታንታዊ
ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ድርጅቶች፣ ግለሰቦች እና መጽሐፎቻቸው ላይ በአንድ ድምፅ ያስተላለፈውን የውግዘት ውሳኔ
የያዘው ቃለ ጉባኤ ለመላው አህጉረ ስብከት ተሰራጨ፡፡
የመንበረ
ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሰኔ 7 ቀን 2004 ዓ.ምሰ ጀምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙ 48 አህጉረ ስብከት ባሰራጨው ቃለ ውግዘት የተካተቱት መናፍቃን ድርጅቶች
ሰባት ሲኾኑ የግለሰቦቹ ብዛት ደግሞ 16 ነው፡፡Wednesday, June 13, 2012
የአቶ የጌታቸው ዶኒ ክስና የፍርድ ሂደት
(አንድ አድርገን ሰኔ 06/2004ዓ.ም)፡- በጌታቸው ዶኒ አቀነባባሪነት የባቦጋያ ምስራቀ ፀሀይ መድሃኒአለምን ቦታ
አስመላሽ ጥቂት ኮሚቴዎች ላይ “የማስፈራራት ዛቻ አድርሰውብናል ፤ ሙዳይ ምጽዋት ገልብጠዋል” በማለት አቶ ጌታቸው ዶኒ እና የቤተክርስትያቱ
አስተዳዳሪ ቀሲስ መስፍን ፍርድ ቤት ክስ መመስረታቸው ይታወቃል ፤
አቶ ጌታቸው ዶኒ በሀሰት ምስክርነት ያቀረባቸው ሰዎች በብር የተገዙ እና እሱ የፈለገውን እንዲመሰክሩለት ያሰበ ሲሆን ነገሮች እርሱ
እንዳሰበው ሊሄዱለት አልቻሉም ፤ ፤ አንድ ሰባኪ ወንጌል በፍርድ
ቤት ለምስክርነት ቀርቦ በሀሰት እንደመሰከረና ቀሲስ መስፍን የምስክሮችን ቃል እየሰሙ ውጭ ላለ ሌላ የሀሰት ምስክር ሲናገሩ እጅ ከፍንጅ በመያዛቸው ለአንድ ቀን መታሰራቸውንና
በ2000 ብር ዋስ መለቀቃቸውን ጠቅሰን መጻፋን ይታወቃል ፤ አቶ ጌታቸው ዶኒ በምስክርነት በቀረበበት ወቅት ሲመሰክር ከአቃቢ ህግ
የቀረበለትን መስቀለኛ ጥያቄ ላይ አንደበቱ ሲያያዝ ተመልክቷል ፤ ፍርድ ቤቱ የምስክሮችን ቃል ሰምቶ ከጨረሰ በኋላ በ27/09/2004ዓ.ም
ተከሳሾች የመከላከያ ምስክራቸውን እንዲያሰሙ ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር ፤ በጊዜውም የሁሉም ተከሳሽ ምስክሮች ሙዳይ ምጽዋት ተሰበረ
በተባለበት እለት ተከሳሾች ከተማ ውስጥ እንዳልነበሩና አንዱ ተከሳሽ
በዓል ለማክበት ሳማ ሰንበት እንደነበረ ለፍርድ ቤቱ ምስክሮቹ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል ፤
Tuesday, June 12, 2012
በርካታ ቤቶችን የበላው የሐዲያ ቃጠሎ እስካሁን መንስዔው አልታወቀም
(*** Reporter ***):- በደቡብ ክልል ሐዲያ ዞን በታህሳስ ወር በተለያዩ ቀናት 140 ቤቶችን የበላው የእሳት ቃጠሎ መንስዔ በእስካሁኑ ሒደት አልታወቀም፡፡ በዞኑ ሰሮ፣ ሻሼጌ፣ ጌሌቦ፣ ሚሻና ጊቤ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ቤቶች በታህሳስ ወር ውስጥ በ15 ተከታታይ ቀናት ድንገተኛ እሳት እየተነሳ መውደማቸው ይታወሳል፡፡ የቃጠሎው ሁኔታ አነጋጋሪ ሆኖ የሰነበተ ከመሆኑም በላይ፣ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አካባቢውን እንዲጎበኙ ምክንያት ሆኗል፡፡
የዞኑ ፖሊስ ባልደረባ ኢንስፔክተር ክብነህ አበበ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አቶ ሽፈራውአካባቢውን በጐበኙበት ቀንም ቤቶች ተቃጥለው ነበር፡፡ ፖሊስ አስፈላጊውን ክትትልናምርመራ እንዲያደርግ አቶ ሽፈራው ለዞኑ ፖሊስ መመርያ ሰጥተዋል፡፡ በዚህ መሠረት ፖሊስ ደፈጣ በማድረግ የእሳቱን መንስዔ ለማወቅ ጥረት ቢያደርግም፣ የተገኘ ፍንጭ አለመኖሩን ኢንስፔክተር ክብነህ ገልጸዋል፡፡ “ሰው ነው የሚለኩሰው? የሚለውን ለማጣራት ሙከራ አድርገን ነበር፡፡ ሰው ስለመለኮሱ ግን መረጃዎች ልናገኝ አልቻልንም፤” ሲሉኢንስፔክተሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
Monday, June 11, 2012
ዝቋላን መልሰን እናልማ
“ይህን
ቦታ ወደ ቀድሞ ሁኔታ የመመለስ ሃላፊነት አለብን”
ወደ ገዳሙ የሚደረገው የጉዞ ቀን ቅዳሜ ሰኔ 24 2004 ዓ.ም ሲሆን የመመለሻ ቀን ደግሞ እሁድ ሰኔ 25 ይሆናል ፤ ይህን የተቀደሰ አላማ ላይ አሻራዎን ለማሳረፍና ከአባታችን ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በረከት ለመቀበል የምትፈልጉ ሰዎች የትራንስፖርት ወጪዎትን ብቻ በመሸፈን ማህበሩ ባዘጋጀው የጉዞ መርሀ ግብር ላይ በመገኝት የታሪካዊውን ገዳም ደን መልሶ የማልማት ፕሮግራም ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ዛፍ የመትከል መርሀ ግብሩ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ሰዎች ጉድጓድ ለመቆፈር የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችን (ገሶ ፤ ዶማ ወይም አካፋ) መያዝ ይጠበቅቦታል ፤
“የማይቀርበት ታላቅ የበረከት ስራ….”
ይህን አላማ ለመርዳት ወይም መርሀ ግብሩ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሰዎች ለበለጠ መረጃ (0911-201649 ፤ 0911-216440 ፤ 0913-255249 ፤ 0911-015623 ፤
0924-373474) በመደወል ሙሉ መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡
Sunday, June 10, 2012
ኢትዮጵያ ግብረሰዶምንና አራማጆቹ ምዕራባዊያንን አወገዘች
‹‹ትልቁ ሀብታችን ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ነው›› አቡነ ጳውሎስ
*Reporter* ትናንት በአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ በ‹‹ግብረሰዶምና ተያያዥ ማኅበራዊ ቀውሶች›› ላይ ለመነጋገር በተጠራው አገራዊ ኮንፈረንስ የተገኙት የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የፓርላማ አባላት፣ ወጣቶችና ሌሎች የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ‹‹ግብረሰዶምንና ግብረሰዶም የሚያስፋፉ ምዕራባዊያንን›› አወገዙ፡፡ በዚሁ ታሪካዊና አንገብጋቢ በተሰኘው አገራዊ ኮንፈረንስ ላይ ከ2,000 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ አምስቱ ዋና ዋና የሃይማኖት ተቋማት የኦርቶዶክት ተዋህዶ፣ የእስልምና፣ የካቶሊክ፣ የወንጌላዊት መካነ ኢየሱስና የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ያወጡትን የግብረሰዶማዊነት የተቃውሞ መግለጫ በአንድ ድምፅ እንደግፋለን ብለዋል፡፡ ግብረሰዶማዊነትን ካልተቀበላችሁ በማለት የሰብዓዊ መብት ጥያቄ የሚያነሱና ዕርዳታ እንከለክላለን ለሚሉ የምዕራብ አገሮችም ‹‹ዕርዳታቸው በአፍንጫችን ይውጣ›› የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በስብሰባው ላይ የተገኙት የሃይማኖት ተቋማትን በሙሉ ወክለው ጉባዔውን በፀሎት የከፈቱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ፣ ‹‹ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት ሕግ ሳይጻፍ ጊዜ ጀምሮ ከእግዚአብሔር ጋር ትውውቅ ነበራቸው፤ የዛሬ ሳይንቲስቶችም ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ መሆንዋን ይናገራሉ፤›› በማለት በዓለም ላይ ያሉ ሕዝቦች በሙሉ እርስ በርስ ተረጋግጠዋል፤ ብቸኛ ነፃ አገር ኢትዮጵያ ነች ብለዋል፡፡ ‹‹አሁንም የተረገጡትና የማንነት ቀውስ ያለባቸው ወገኖች ተናገሩ ብላ የምትሰማ አይደለችም፡፡ ባህላችን አልተለወጠም፣ ታሪካችን አልተቀነሰም፣ ማንነታችን አልተበረዘም፤ እንዲሁ ዝም ብለን የምንለወጥ አይደለንም፤›› ሲሉ አስታውቀዋል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)

