(አንድ አድርገን
ግንቦት 22 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- የየባቦጋያ ምስራቀፀሐይ መድሀኒዓለም የመሬት ጉዳይ አሁን አሁን ድራማ እያስተናገደ ይገኛል ፤ እነ ጌታቸው
ዶኒ ህዝብ የወከላቸውን የአካባቢው ክርስትያኖችን ነጣጥሎ የማዳከም ስራቸውን ተያይዘውታል ፤ ፍርድ ቤቱ ቦታው ያለ አግባብ ለሪዞርት
ባለቤቱ እንደተሰጠ በመቃወም ላቀረቡት ጥያቄ “ቤተክርስትያኒቱ ራሷ ትጠይቅ ፤ እናንተ የቤተክርስትያን ህጋዊ ወኪል አይደላችሁም” የሚል ድፍን ያለ መልስ ከፍርድ ቤት በጊዜው እንደተሰጣቸው
ገልጸን ነበር ፡፡ ይህ ጉዳዩ ፍርድ ቤቱ እንዲህ ቢልም ክርስትያኖቹ እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ በህገወጥ መንገድ የተወሰደውን ከ10ሺህ ካሬ
በላይ የመድሀኒዓለምን ቦታ ለማስመለስ የቻሉትን ያህል እየጣሩ መሆኑን
ለማወቅ ችለናል፡፡
አቶ ጌታቸው
ዶኒ የመሬቱን ጉዳይ ወጥረው የያዙትን የቤተክርስትያን የቁርጥ ቀን ልጆች ላይ ከአዲሱ የቤተክርስትያን አስተዳዳሪ ጋር በመመሳጠር
“አስፈራርተው ዛቻ አድርሰውብናል ፤ ለህይወታችን እንሰጋለን እና ሙዳየ ምጽዋት ገልብጠው ዘርፈዋል” በሚል የሀሰት ክስ አቅርበውባቸው
ነበር ፤ የባቦጋያ መድሀኒአለም ጉዳይ ላይ “አስፈራተው ሙዳይ ምጽዋት ዘርፈዋል” የተባሉትን ግለሰቦች ፍርድ ቤት
16/09/2004 ዓ.ም ቀርበው ነበር ፤ አንደኛ ምስክር ሆነ የቀረቡት አዲሱ ቤተክርስትያኒቱ አስተዳዳሪ ቀሲስ መስፍን ፤ ሁለተኛ
ምስክር አቶ ጌታቸው ዶኒ ፤ ሶስተኛ ምስክር የደብሩ ሰበካ ወንጌል ፤ ሲሆን አራተኛ ምስክር ደግሞ በብር የተገዛና አቶ ጌታቸው
ዶኒ የመከረው ሰው ነበር፡፡


