
Wednesday, June 29, 2016
ሦስቱ ስርዓተ ቤተክርስቲያንን ንደው የጵጵስና ማዕረግን የተመኙ ‹‹አባቶች››

በቁስላችን ላይ ጥዝጣዜ እንዳይጨመርብን
በቀሲስ ስንታየሁ አባተ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ከርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በወርኀ ግንቦት 2008 ዓ.ም ባካሄደው ርክበ ካህናት በቅርቡ ኤጲስ ቆጶሳትን ለመሾም መወሰኑንና ለዚህም ዕጩዎችን የሚያቀርብ ኮሚቴ መሠየሙን በመግለጫው አሳውቋል። በርካቶች አኅጉረ ስብከት ብፁዓን ኤጲስ ቆጶሳቶቻቸውን በእርግና፣ በሕመም፣ በሞትና በመሳሰሉት ምክንያቶች በማጣታቸው ያለ አባት መቅረታቸውና አገልግሎታቸው መስተጓጎሉ ይታወቃል። ከችግሩ የተነሣም አንዳንድ ኤጲስ ቆጶሳት ሁለት ሦስት አኅጉረ ስብከት ደርበው እንዲይዙ ተደርጓል። ይህ ደግሞ በብፁዓን አባቶች ላይ የሥራ ጫናን ፈጥሯል፤ የአኅጉር ስብከት አገልግሎት የተቀላጠፈ እንዳይሆንም የበኩሉን አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል።
Monday, June 27, 2016
ከኤጲስ ቆጶሳት እጩ አንዱ ‹‹አባ ተክለ ማርያም አምኜ››

‹‹ያለ ነውጥ ለውጥ አይገኝም› ከእጩዎቹ ውስጥ የተገኙት አባ ናትናኤል
(አንድ አድርገን ሰኔ 20 2008 ዓ.ም )፤- አባ ናትናኤል ይባላሉ በአሁኑ ወቅት ለጵጵስና እየተጠቆሙ
ካሉ አባቶች ውስጥ ስማቸው ይገኛል፡፡ አባ ናትናኤል ከዚህ በፊት
ያላቸው የኋላ ታሪክ ምን ይመስላል የሚለውን ምዕመናን እንዲያውቁትና አስመራጭ ኮሚቴው በራሱ መንገድ ማጣራት ያካሂድ ዘንድ ፤ ለቤተክርስቲያን ያለፉት አመታት የተከናወኑት ድርጊቶች ዳግም
እንዳንመለከታቸው አሁን ላይ ሆነን ሃላፊነታችንን ከመወጣት ምዕመኑን ከማንቃት አንጻር እንዲህ አቅርበነዋል፡፡

Friday, June 3, 2016
በዚህች ቤተ ክርስቲያን ላይ እጁን ያነሣ አካል እርስዎን ሾመብን - እውን ይህች ቃል ከሲኖዶስ ተሰማችን?
ዲ/ን አባይነህ ካሴ
የቅዱስ ሲኖዶሱን ጉባኤ ገባ ወጣ እያሉ ብቻቸውን የተሰበሰቡ ይመስል የብቻቸውን ሀሳብ ለማስወሰን በከፍተኝ ትጋት የምልዐተ ጉባኤውን ሀሳብ እየጨፈለቁ ወደ ራሳቸው ብቻ እንዳጋደሉ የጸኑት፣ ከቆሙበት ሳይነቃነቁ በየ አጀንዳው ገትረው የያዙት አባ ማትያስ በተግሣጽ ቃል እንደተሸነቆጡ ተሰማ፡፡ እንዲህ ያለው ነገር የሚገባ ነውና ለምን ኾነ በለን አንደነቅም፡፡ እጅግ በሚገርም ሁኔታ ዛሬ የተሰማው ብዙ ሽፍንፍን ሲበጅለት የነበረው ነገር ግን አነጋጋሪ ነው፡፡
ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከተላለፉት ቃላተ ተግሣጻት መካከል አንዱ ”የሚያሳዝነው በዚኽች ቤተ ክርስቲያን ላይ እጁን ያነሣ አካል አኹንም እርስዎን ሾመብን፤ አኹንም ከጀርባ ኾኖ ያበጣብጠናል፤ ወደ ሰላም፣ ወደ ልማት፣ ወደ ዕድገት እንዳትሔድ፤ ዘወትር የብጥብጥ ዐውድማ እንድትኾን እየሠራ ያለ አካል መኖሩን እኛም እናውቃለን፣ ሕዝቡም ያውቃል፡፡” የሚለው ነው፡፡
Wednesday, June 1, 2016
ዛሬ ካሳ ተክለ ብርሃንን የመሰሉ ገብረ ጉንዳኖች ለአባቶች ይዘውላቸው ከሚመጡት መፍትሄ ይልቅ ነገ የሚያመጡባቸው ችግርና ቀዳዳ ገዝፎ ይታያል

ለዘመናት የገነባነውን ማንነት ፤
የተላበስነውን ስብዕና ፤
ያቆየነውን ግብረ ገብነት ፤
ያቆዩልንን ሀገር የኖርንበትን ሃይማኖት ፤
የተረከብነውን ትውፊት እና በአል ከዘመኑ ጉንዳኖችና የአይጥ መንጋዎች መጠበቅ የሁላችንም ግዴታ መሆን መቻል አለበት፡፡ ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ አልፋ አሁን ለእኔ እና ለእናንተ ቋንቋ ፤ ዜማ ፤ ሥርዓት ፤ ትውፊትና እምነትን አስተላልፋልናለች ፡፡ እኛም ይህን የተረከብነውን ላለማስተላለፍ እንቅፋት የሚሆኑብንን ከበላያችን ያሉ ገብረ ጉንዳኖችና በውስጣችን ያሉ የአይጥ መንጋዎችን ሳንፈራ ለልጆቻችን ማውረስ ሃይማኖታዊ እና ሀገራዊ ግዴታ አለብን፡፡ ትላንት ቤተ ክርስቲያን ህልውናዋን በሚያናጋ መልኩ በብርቱ ፈተና አልፋለች፡፡ ዛሬም እንደ ቀድሞ ያህል ባይሆን እንኳን የዛሬ ከርሳቸው እንጂ የነገ ክስረታቸው ባልታያቸው ዙሪያዋን በከበቧት የአይጥ መንጋዎች ፤ በጎውን በማይመኙላት ገብረ ጉንዳኖች ዘንድም እየተፈተነች ትገኛለች፡፡ ነገም ይባስ ወይም ይቅለል አሁን ላይ በማናውቀው ፈተና ውስጥ ቤተክርስቲያኒቱ ታልፋለች፡፡ ታዲያ በዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ ከአንድ ኦርቶዶክሳዊ አማኝ የሚጠበቀው የራሱን ክርስቲያናዊ ሃላፊነት መወጣት ብቻ ነው፡፡ የዛኔ ፈተናውን ማስቀረት ባንችል እንኳን ፈተናውን የምንቋቋምበትን ትከሻ እንገነባለን፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)