ከአላባ እና ከምባታ አካባቢ ምዕመናን የተሰማ የመጨረሻ ቃል….
የጵጵስና ማዕረግ አስመራጭ ኮሚቴው ከቅዱስ ሲኖዶስ የተቀበለው ከባድ ሃላፊነት በመመልከት
ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አባቶች ሊሆኑ ይችላሉ ያላቸውን መነኮሳትና ቆሞሳት በመቀበል ባስቀመጠው መመዘኛ መሰረትማለት ምንኵስናቸውና ገዳማዊ ሕይወታቸው አጠራጣሪና በቂ ማስረጃ የሌላቸው፤ በትውልድ አገራቸው በሥርዓተ ተክሊል ያገቡና ጋብቻቸውን ያፈረሱ፤ ጋለሞታዎች፤ ባለትዳሮችን የሚያማግጡ፤ ከተለያዩ ሴቶች የወለዱ፤
በአብነቱም በዘመናዊውም ትምህርት የተጭበረበረ ማስረጃ የያዙ፤ ከተለያዩ አብያተ-ክርስቲያናት በምዝበራቸው የተባረሩ ፤ ጵጵስናውንም የዚኹ ሽፋን አድርገው ሀብት ለማድለብ የሚቋምጡ፤ በጠንቋይነትና አስጠንቋይነት፤ በመተተኛነት ለነፍስ መጥፋት ምክንያት የኾኑ፤ በእምነታቸው ጉልሕና ተጨባጭ ሕፀፅና ነቀፌታ ያለባቸው፤ ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃንም በኅቡእ የሚሠሩና ሽፋን የሚሰጡ፤ እጩዎችን በወንፊት ነፍቶ ብዙዎችን
በመቁረጥ እዚህ ደረጃ ላይ 31 ያላቸውን በማስቀረቱ ሳናመሰግን አናልፍም፡፡ ነገር ግን እኛ በደንብ የምናውቃቸው ለዓመታት ምዕመኑን
ሲያስለቅሱ የነበሩ አባ ሚካኤል ገ/ማርያም በዚህ መስፈርት ተመዝነው እዚህ ደረጃ መድረሳቸው አግራሞትን ፈጥሮብናል፡፡