http://www.addisadmassnews.com
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መቀመጫ የኾነችው የቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፥ ጥፋቶች ታርመው ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራር እንዳይሰፍን በሚሹ ጥቂት የአስተዳደር ሰራተኞች፣ በህይወት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር ከአድማ ያልተናነሰ እንቅስቃሴ እየተደረገበት
መኾኑን አስታወቀ፡፡ የመልካም አስተዳደር ጅምሩን ከፍጻሜ ለማድረስ የቤተ
ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የአስተዳደር ክፍሎች እገዛ
እንዲያደርጉለትም ጠይቋል፡፡
ለብክነት፣ ለዘረፋ እና ለሙስና ከተመቻቸ አሰራር እንዲሁም በገዳሟ ቀደም ሲል ከመልካም አስተዳደር ዕጦት የተነሳ የተከሰቱ ጥፋቶችን ለማረም ልዩ ልዩ መመሪያዎችንና የውስጥ ደንብ ረቂቆችን ማዘጋጀቱን ሰበካ ጉባኤው ለሀገረ ስብከቱ የዋና ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ባቀረበው ሪፖርት ገልጿል፡፡ ይኹንና ለቁጥጥር የሚያመች ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበትን አሰራር ለማስቀጠልና ለማስፈጸም እንዳይቻል ጥቂት የአስተዳደር ሰራተኞች ማኅበረ ካህናቱን በመከፋፈል፣ “ከሰበካ ጉባኤው ጋር ተባብራችኋል” በሚል ከሥራና ከደመወዝ በማገድ፣ በማስጠንቀቂያዎች በማሸማቀቅ፣ መረጃዎችን በማዛባት የሚፈጥሩት ግጭት ኹኔታውን አስቸጋሪ አድርጎብኛል ብሏል፡፡