Friday, June 27, 2014

ጠባቂዬ ቅዱስ ገብርኤል ከመዓት እንዳወጣኝ አምናለሁ


አቶ ቴዎድሮስ አሸናፊ የሳውዝ ዌስት ሆልዲንግስ ፕሬዚዳንት እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡ ሳውዝ ዌስት ሆልዲንግስ የኢንቬስትመንት ቡድን ሲሆን በሥሩ (ሳውዝ ዌስት ዴቨሎፕመንት፣ ሳውዝ ዌስት ኢነርጂ) ሳውዝ ዌስት ቴክኖሎጂስ የተሰኙ ኩባንያዎቹ በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የኢንቬስትመንት ዘርፎች ተሰማርተዋል፡፡ በተጨማሪም ሳው ዌስት የተሰኘ ፋውንዴሽን ለመመሥረት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሪፖርተር ከአቶ ቴዎድሮስ ጋር ቆይታ አድርጎ ነበርሁለቱን ጥያቄ እነሆ

ሪፖርተር፡- 1999 .. የአውሮፕላን አደጋ ገጥምዎት ነበር፡፡ ስላደጋው ይንገሩን? 
አቶ ቴዎድሮስ፡- በወቅቱ ፔትሮናስ በጋምቤላ የሚያካሂደውን የነዳጅ ፍለጋ ሥራ ጐብኝተን ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ ሳለን የአውሮፕላኗ ሞተር ተበላሽቶ ቆመ፡፡ 11,000 ጫማ ከፍታ ወደ መሬት ተከሰከስን፡፡ በአደጋው ጓደኛዬ የፔትሮናስ የኢትዮጵያ ቢሮ ሥራ አስኪያጅ የነበረው መሐመድ አሪስ ሕይወቱ አለፈ፡፡ 

ሪፖርተር፡- በርስዎ ላይ ጉዳት አልደረሰም? 
አቶ ቴዎድሮስ፡- አንድም አጥንቴ ሳይሰበር ከአደጋው ተርፌያለሁ፡፡ በሆስፒታል አላደርኩም፡፡ ከአደጋው ሁለት ቀን በኋላ ወደ ሥራ ገበታዬ ተመልሻለሁ፡፡ ከአደጋው ጠባቂዬ ቅዱስ ገብርኤል ከመዓት እንዳወጣኝ አምናለሁ፡፡

Thursday, June 19, 2014

የጳጳሳቱ ማረፊያ


(አንድ አድርገን ሰኔ 13 2006 ዓ.ም)፡-
116ኛው የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ 6ኛ በፓትርያርክነት ዘመናቸው ይቀመጡበት የነበረው በቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል የሚገኝ አንድ ያረጀ ክፍል ነበር፡፡ በዚህ ክፍል ሲኖሩ አንድ የካቶሊክ መነኩሴ ሊጎበኛቸው መጣ፡፡ ፓትርያርኩን ማረፈያ ቤትና ዕቃዎቻቸውን ሲመለከት ለክብራቸው የሚመጥን ባለመሆኑ ደነገጠ፡፡ (ፓትርያርክ የሚሆኑ አባቶች በደህና ማረፊያ ሊኖሩ ይገባል  ይህም  ለእነርሱ ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያን ክብር ሲባል ነው፡፡) መነኩሴው አቡነ ቄርሎስን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው  ‹‹እባክዎን በእንዲህ ዓይነት ቤት ውስጥ መኖር ለእርስዎ የሚመጥን አይደለም፡፡ ፈቃድዎ ከሆነ እኔ ቤትዎን ላድስልዎትና ምርጥ ምርጥ ዕቃዎችን ላስገባልዎት?›› ፓትርያርኩ ይህንን ጥያቄ ሲሰሙ ፈገግ ብለው  በፍቅር ዓይን ከተመከቱት በኋላ ‹‹የእኔ ልጅ እጅግ አመሰግናለሁ!  እርግጥ  ነው ይህ  ቤት በጣም  የተጎሳቆለ  ነው፡፡  እንደዚህም ሆኖ ግን ጌታችን ከተወለደበት በረት ይሻላል!!›› አሉት፡፡

በእኚህ አባት እግር የተተኩት ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳ ደግሞ በግብፅ መንግሥት በታሰሩ ጊዜ  ምእመናኑ  ከእስር ቤት ወጥተው ማረፊያ ቤት እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ሰልፍ ወጥቶ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ አቡነ ሺኖዳ  ለሕዝቡ ንግግር አድርገው ማረፊያ ይሰጣቸው በሚል የተወጣውን ሰልፍ እንዲበትኑ ተጠየቁ፡፡ እኚህ  አባትም ሕዝቡን  እንዲህ ሲሉ አረጋጉት፡፡ ‹‹ለእኔ ማረፊያ እንዲሰጠኝ ብላችሁ ሰልፍ ወጥታችኋል  ነገር ግን በፍቅር ከተሞሉት ከእናንተ ልቦች የተሻለ ማረፊያ ለእኔ አያስፈልገኝም!››  አሏቸው፡፡
ከሄኖክ ኃይሌ


ይህ የሆነው በ116ኛው የኮፕት ፓትርያርክ በአቡነ ቄርሎስ እና በ117ኛው ፓትርያርክ በአቡነ ሺኖዳ ጊዜ ነው፡፡ በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት አባቶችን ማየት እድለኝነትን ይጠይቃል፡፡ መንጋውን በአግባቡ እየመሩ ከመቶ በላይ መንፈሳዊ መጻሕፍት ለእመነቱ ተከታዮች እየጻፉ ፤ በየሳምንቱ ቋሚ መርሐ ግብር በመያዝ ወንጌል እየሰበኩ ፤ አክራሪ ሙስሊሞች ቤተ ክርስቲያቱ ላይ የሚያነሱትን ችግር ተቋቁመው ከአስር በመቶ የማይበልጡ የእምነቱን ተከታዮች መንፈሳዊ ልዕልናው ከፍ እንዲል የሚሰሩትን ሥራ መመልከት እጅግ ደስ  ያሰኛል፡፡ ወደ እኛ ቤተክርስቲያን ስንመጣ ደግሞ በርካታ ችግሮች የተጋፈጡባት ቤተ ክርስቲያን ብዙ የመነጋገሪያ አጀንዳ አንስቶ ሸክሟን ማቅለል ሲገባ ‹‹የጳጳሳት ንብረት ውርስ››ን በሚመለከት በሲኖዶስ ደረጃ አጀንዳ ይዞ መነጋገር ያለንበትን የመንፈሳዊ ደረጃ ዝቅጠት ያሳየናል (አንዳንድ አባቶች በአዲስ አበባ ከ500 ካሬ ሜትር በላይ የተንጣለለ ቪላ እና G+1 በስማቸው የተመዘገበ ንብረት ባለቤቶች ስለሆኑ)፡፡


‹‹በፍቅር ከተሞሉት ከእናንተ ልቦች የተሻለ ማረፊያ ለእኔ አያስፈልገኝም!›› በማለት ምንም  ዓለማዊ ሀብት ንብረት ሳያፈሩ የተሰጣቸውን ሓላፊነት በሚወጡ አባቶችን እኛ ለምን አጣን?  እኛን እጅግ የሚገርመን በጥቂት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በግብጽ ኮፕት ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ያለው ዘርፈ ብዙ-------------------------------------------- ልዩነት ነው፡፡