Sunday, June 14, 2015

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እና የሰንበት ት/ቤቶች እየተወዛገቡ ነው

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን÷ ከሙስና እና ብልሹ አሠራር መንሰራፋት፣ ከመልካም  አስተዳደር እና ፍትሕ ዕጦት፣ ከአስተምህሮ እና ሥርዐት መጠበቅ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት /ቤት እና በየሰንበት /ቤቶች መካከል የተቀሰቀሰው ውዝግብ እንደቀጠለ ነው፡፡


በሀገረ ስብከቱ ገዳማትና አድባራት÷ ሌቦች እየተበራከቱ፣ ጎጠኝነት እየተስፋፋ፣ በመናፍቅነታቸው የተወገዱ ግለሰቦች ተመልሰው እየተቀጠሩና አስተምህሮውን እየተፈታተኑ መሆናቸውን ሰንበት /ቤቶቹ ይገልፃሉ፡፡ ‹‹ሕገ ወጥ ሰዎችን አልደግፍም›› የሚለው ሀገረ ስብከቱ በበኩሉ፤ ካህናት ሙሰኞች ናቸው  ብሎ ንደማያምን ጠቁሞ፤ ‹‹ሰዎችን ሰረቃችሁ ለማለት ማስረጃ ያስፈልጋል›› ብሏል፡፡በሀገረ ስብከቱ የሰንበት /ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ የሚመሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሰንበት /ቤት አባላት፣ ባለፈው ማክሰኞ ከሀገረ ስብከቱ የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት ጋር በሀገረ ስብከቱ ይፈፀማል በተባለው ብልሹ አሠራር ላይ ያካሄዱት ውይይት ባለመግባባት ተቋጭቷል፡፡ ሙስና እና ብልሹ አሠራርን በማጋለጣቸው ‹‹የፖሊቲካ ድርጅቶች ደጋፊዎች እና ሁከት ቀስቃሾች ናቸው፤ ፓትርያርኩን ይቃወማሉ›› በሚል እየታሰሩ እንደሆነ በውይይቱ ላይ የተናገሩት የሰንበት /ቤቶቹ፤ በሰሚት መካነ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አሠራሩን የተቃወሙ በፖሊስ ጣቢያ ታስረው ክሥ እንደተመሠረተባቸው፤ ካህናትም የንስሐ አባት እንዳይኾኗቸው በደብዳቤ መመሪያ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡በሀገረ ስብከቱ ባለሥልጣናት የሚመኩና የጥቅም ትስስር ያላቸው የአድባራትና የገዳማት ሓላፊዎች ከሦስት እስከ አራት ሺሕ ብር ያልበለጠ ደመወዝ እየተከፈላቸው ውድ ዋጋ ያላቸውን መኪኖችን እንደሚነዱና ቤት እንደሚገዙ ጠቁመው ገንዘቡ ከየት እንደመጣ ሊጣራ ይገባዋል ብለዋል። ሀገረ ስብከቱ የሙዳዬ ምጽዋት ቆጠራ በካሽ ካውንተር እንዲከናወን ማድረጉን ቢደግፉም በፐርሰንት አከፋፈል፣ በቦታ እና በሕንፃ ኪራይ፣ በሠራተኞች ቅጥርና ዝውውር ረገድ በጥቅም ትስስር የሚፈጠሩ ችግሮች እንዲፈቱ፤ በየአጥቢያው የሚታየው የጎጠኝነት መከፋፈል መፍትሔ እንዲያገኝ አበክረው ጠይቀዋል፡፡

Saturday, June 6, 2015

“ሃይማኖታዊ ግጭት ለማስነሣት ተንቀሳቅሳችኋል” የተባሉ የሰበካ ጉባኤ አባላት ፍርድ ቤት ቀረቡ





  •   ፖሊስ10 ቀንየምርመራጊዜጠይቆባቸዋል

   
በደቡብ ክልል የስልጤ ዞን ምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ፣ የቂልጦ ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤና የደብሩ ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ አባላትሃይማኖትን ከሃይማኖት ለማጋጨት ተንቀሳቅሳችኋልበሚል በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

የወረዳው ፖሊስ፣ ባለፈው ሳምንት ዓርብ እና በዚኽ ሳምንት ሰኞ ስድስት የሰበካ ጉባኤውንና የቤተ ክርስቲያኒቱን የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ አባላት በቁጥጥር ሥር በማዋል በቂልጦ ወረዳ ፍርድ ቤት አቅርቧቸዋል፡፡
ግለሰቦቹየድረሱልኝ ጥሪበሚልሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጭ ጽሑፍ ጽፈው በፌስቡክ አሰራጭተዋልሲል ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ግለሰቦቹየድረሱልኝ ጥሪ”  በሚል ደብዳቤ መጻፋቸውን ቢያምኑም በፌስቡክ አለመልቀቃቸውን ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር በዋሉት ግለሰቦች ላይ የማጣራው ነገር አለ በሚል 21 ቀን የምርመራ ጊዜ የጠየቀባቸው ቢሆንም ፍርድ ቤቱ 10 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ፈቅዶለታል፡፡

Friday, May 29, 2015

ተዓምር



 

ወደ ጻድቃኔ ማሪያም ምዕመናን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አንድ ከባድ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ መንገድ ስቶ በፎቶ ግራፉ እንደምታዩት ወደ ቁልቁለት ገደል ቢገባም በመኪናውም ሆነ በተሳፋሪ መንገደኞችለይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰ ታውቋል።