Wednesday, December 11, 2013

ተሐድሶን የማጽዳጽ ዘመቻ ንቅናቄ በደብረ ብርሃን



(አንድ አድርገን ታህሳስ 2 2006 ዓ.ም)፡-  ዝዋይ ፤ ናዝሬትና ፤ ደብረ ዘይት በማመስ በስተመጨረሻ ደብረ ብርሃን ላይ ሥራው የተጋለጠበት ‹‹አባ›› ማርቆስ ጉዳዩ ከአዲስ አበባ በጠቅላይ ቤተክህነት በተላኩ ሰዎች መታየቱን ከቦታው የደረሰን ማስረጃ ያመለክታል፡፡

በ1446 ዓ.ም የካቲት 2 ቀን በደብረ ብርሃን ላይ ‹‹ለማርያምና ለመስቀሉ አንሰግድም›› የሚል አባ እስጢፋኖስ የተባለ ሰው  ደቀ መዛሙርቶቹን ይዞ ትምህርቱን ሲያስፋፋ ጉዳዩ ጆሮአቸው የገባ ንጉስ ዘርዓ-ያዕቆብ ጉዳዩ የሃይማኖት በመሆኑ ለሚመለከታቸው የኃይማኖት አባቶች ሊቃውንተ ቤተክርስቲያናት በመስጠት ሁለቱ የሃይማኖት መሪዎች እንዲነጋገሩና እንዲተማኑ የተሸነፈው ለአሸናፊው እንዲገዛ ትዕዛዝ ሰጥተው መድረኩን ለቀቁ ፡፡

Monday, December 9, 2013

በዋልድባ ላይ ለሚሰራው የሥኳር ፕሮጀክት ነዋሪዎች መነሳት ጀመሩ



የቆራሪት ከተማ
(አንድ አድርገን ታህሳስ 01 2006 ዓ.ም)፡- በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በዋልድባ ገዳም ላይ ለሚገነባው የስኳር ልማት ፕሮጀክት በመጀመሪያ ዙር 1800 አባወራዎች ከቦታቸው መነሳታቸው ታወቀ፡፡ ለተነሱ አርሶ አደሮቹ 127.5 ሚሊዮን ብር የካሳ ክፍያ ተሰጥቷል፡፡ ለእነዚህ ተነሺዎች ከወራት በፊት የገጠር ከተማ መልክ በመያዝ በተገነባችው የቆራሪት ከተማ ላይ የማስፈር ስራ ተከናውኗል ፡፡ ለዚች ከተማ ምስረታ ምክንያት ደግሞ በዋልድባ ገዳም ላይ የሚሰራው የስኳር ልማት ፕሮጀክት መሆኑ ታውቋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከቦታው የተነሱት 1800 ነዋሪዎች ከወልቃይት ወረዳ ፤ ከቃሌማ እና ፅምሪ ቀበሌ ይኖሩ የነበሩ አርሶ አደሮች ናቸው፡፡ መንግሥት እንደሚለው ለእነዚህ የልማት ተነሺዎች ለተነሱበት ቦታ በምትኩ የእርሻ ፤ የመኖሪያ  ቤት ፤ ሙሉ የቤት እና የሰብል ካሳ ክፍያ ፈጽሜያለሁ ብሏል፡፡ ለአርሶ አደሮቹ ነዋሪዎች መንግሥት 127.5 ሚሊየን ብር ካሳ መስጠቱ ታውቋል ፤ በሁለተኛ ዙር የሰፈራ ፕሮግራሙ ላይ 4ሺህ ሰዎች ከቦታው ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሰፈራው የሚቀጥል ሲሆን ለሚነሱት ከ13 ለማያንሱ አብያተ ክርስቲያናት ምትክ አዳዲስ ቤተክርስቲያን በቆራሪት ከተማ መሰራት መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በፔርሙዝ ተለውጦ አሜሪካ የተሻገረው የ400 ዓመቱ ብራና


08 December 2013 ተጻፈ   ፍቅር ለይኩን
  •  የቅርሶቻችን ዋጋ ምን ያህል ነው?

(ሪፖርተር ጋዜጣ):-  የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ)...በዓለም ጥንታዊ ቅርስነት ከመዘገባቸው የሥነ ጽሑፍ ውጤቶች መካከል በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ባለቤትነት የተመዘገቡና በብራና ላይ የተጻፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የነገረ ሃይማኖት ጽሑፎች ይገኙበታል፡፡


 እነዚህ እስከ ሺሕ ዓመታት ዕድሜን ያስቆጠሩ ብርቅና ውድ የሆኑ የሥነ ጽሑፍ ቅርሶች በተለያዩ ጊዜያት በአገሪቱ በደረሱ ተፈጥሮአዊና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ምክንያት ውድመት፣ ጥፋትና ዝርፊያ እንዳጋጠማቸው ይታወቃል፡፡ከዚህም በተጨማሪ በጥናትና በምርምር ሰበብ ከአገር የወጡ ጥንታዊ ብራናዎች አያሌ ናቸው፡፡ በአውሮፓና በአሜሪካ በሚገኙ ትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎችና አብያተ መጻሕፍት፣ እንዲሁም በግለሰቦች፣ በቅርስ አሻሻጮች እጅም ማግኘት የተለመደ ነው፡፡

Thursday, December 5, 2013

ቤተክርስትያኗ ከሳውዲ ለተመለሱት ኢትዮጵያውያን 2 ሚሊዮን ብር እርዳታ እንደምትሰጥ ገለፀች


(ኢሬቴድ ኅዳር 25 2006 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ከሳውዲ አረቢያ ለተመለሱት ኢትዮጵያውያን የሁለት ሚሊዮን ብር ጊዚያዊ እርዳታ እንደምትሰጥ አስታወቀች፡፡ ብፁእ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትሪያሪክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሀይማኖት በቀጣይም ቤተ ክርስትያኗ እርዳታዋን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡
ቅዱስ ፓትሪያሪኩ ከእኛ የሚጠበቀው የእንኳን ደህና መጣቹህ ማለት ወይም በመንፈሳዊ አስተምህሮ ማፅናናትና መርዳት ብቻ ሳይሆን መልሰው እስኪቋቋሙ ድረስ መርዳት ግዴታችን ነው ብለዋል፡፡ፓትርያርኩ እንደገለፁት ይህ የወገኖቻችን እርዳታ ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው ወቅታዊ አጀንዳ መሆኑን በመግለፅ እስካሁን በመንግሥት በኩል እየተደረገ ያለውን የተቀናጀ አቀባበል በአካል በመጎብኘታቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች በበኩላቸው ለወደፊቱም  ተመሳይ እርዳታ ለማድረግና አባታዊ ምክር ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸው ተናግረዋል፡፡ መንግስት ብቻውን የስደተኞች ወገኖቻችን ምግብና መጠለያ አይችልም ያሉት ተሰብሳቢዎቹ ለወደፊቱ በተቀናጀ መልኩ እርዳታ በማሰባሰብ የወገኖቻችን ህይወት እንዲስተካከል ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል፡፡
 ምንጭ፡-የቤተክርስትያኗ የኮሚኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት

ሰበር ዜና - የመስቀል ክብረ በዓል የዓለም ቅርስ ሆነ


ሔኖክ ያሬድ

የኢትዮጵያው የመስቀል ክብረ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ዩኔስኮ አስታወቀ፡፡ ዩኔስኮ የመስቀል ክብረ በዓልን (Commemoration feast of the finding of the True Holy Cross of Christ)

በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ኅዳር 25 ቀን ይፋ ያደረገው፣ በኢንታንጀብል (መንፈሳዊ) ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃና ክብካቤ ላይ የሚሠራው ኮሚቴው ስምንተኛውን ጉባኤ እያካሄደባት ካለው የአዘርባጃኗ ባኩ ከተማ ነው፡፡

Friday, November 29, 2013

ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የመኪና አደጋ ደረሰ



 
(አንድ አድርገን ጥቅምት 19 2006 ዓ.ም)፡- ዛሬ ማለዳ ከጠዋቱ 11 ሰዓት ላይ ከሰሜ ሆቴል ወደ ጊዮርጊስ ቁልቁል ሲሄድ የነበረ አንድ ከባድ የጭነት ማመላለሻ(SINO TRUCK)  መኪና ባጋጠመው የፍሬን ችግር ምክንያት ሹፌሩ መኪናውን መቆጣጠር አቅቶት ቀጥታ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቅጽርን ደርምሶ በመግባት ከፍተኛ አደጋ አድርሷል ፡፡  በወቅቱ በቦታው ላይ በእቅልፍ ላይ የነበሩ ሁለት ጎዳና ተዳዳሪዎች ወዲያውኑ ሕይወታቸው ሲያልፍ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች ላይ ከባድ የሆነ አደጋ ደርሶባቸዋል ፤ ከፍተኛ አደጋ የደረሰባቸው ሶስቱ ሰዎች ወዲያውኑ በእሳት አደጋ ሰራተኞች እና አካባቢው ላይ ባሉ ሰዎች ጥረት ራስ ደስታ ሆስፒታል ተልከው ጊዜያዊ እርዳታ ከተደረገላቸው በኋላ ጉዳቱ ከፍተኛ በመሆኑ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተወስደዋል ፡፡ በአደጋው የቤተክርስቲያኑ መግቢያ በር እና ግንብ ከፍተኛ አደጋ የደረሰበት ሲሆን በተጨማሪ ሰው በፍርስራሽ ውስጥ ይኖራል ተብሎ በመገመቱ በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ፍርስራሹን የማንሳት ስራ ሲያከናውኑ ተስተውሏል፡፡ የደረሰው አደጋ አሰቃቂ መሆኑን በቦታው የነበሩ ሰዎች ተናግረዋል፡፡

ከአደጋው በኋላ የመኪናው ሹፌር በሰጠው ቃል መሰረት የመኪናው ንፋስ እምቢ በማለቱ አደጋው የደረሰ መሆኑን ተናግሯል፤ በአሁኑ ሰዓት  ፖሊስ የመኪናው ሹፌር ላይ ተጨማሪ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

Friday, November 22, 2013

የእነ በጋሻው ጉዳይ ወደ እርቅ እያመራ መሆኑ ተገለጸ

(አንድ አድርገን ህዳር 12 2006 ዓ.ም )፡- ከዚህ በፊት በተለያየ ጊዜ በሃዋሳ ፤ ዲላ እና ሌሎች አካባቢዎች ሁከት በማስነሳትና በሃይማኖት ህጸጽ በህዝቡ በተነሳባቸው ጥያቄ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ድረስ ደርሶ የነበረው የእነ በጋሻው ደሳለኝ ጉዳይ በጥቅምቱ የሲኖዶስ ጉባኤ ላይ የመጨረሻ እልባት እንዲሰጠው በተወሰነው መሰረት ሶስት ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳትን የያዘ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጉዳዩን ሲያጠና ከቆየ በኋላ በእርቅ ለመቋጨት የሚያስችል ውሳኔ ላይ መድረሱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡
 
ከቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዩን አጣርተው የመጨረሻ እልባት እንዲያበጁለት የተመረጡት  ብፁዕ አቡነ  እስጢፋኖስ ፤ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ዘካናዳ እና  ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ለዚህ እርቅ መነሻ የሆነው 21/2/06 በቅዱስ ሲኖዶስ /ቤት አዳራሽ በተካሄደው ስብሰባ ላይ በጋሻው ደሳለኝና ያሬድ አደም በብፁዕ አቡነ ገብርኤል እግር ላይ ወድቀው ይቅርታ በመጠየቃቸውና አቡነ ገብርኤልም ‹‹ይቅር ማለት የአባት ስርአት ነው›› ብለው ቅርታውን መቀበላቸው መሆኑ ይታወሳል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በእለቱ እርቁን መጠየቅ እንደሚፈልጉና ይቅርታውንም ለመጠየቅ ሶስት በማህበረሰቡ ዘንድ ተሰሚነት ያላቸው ሰዎች ከአዋሳ እንዲጠሩላቸው ስም ጠቅስው በጠየቁት መሰረት የተባሉት ሶስቱ የሀገር ሽማግሌዎች ተጠርተው 27/02/06 .  ይቅርታ የጠየቋቸው ሲሆን ሽማግሌዎችም እንደ ግለሰብ ይቅርታውን ለመቀበል እንደማይቸገሩ ጠቅሰው፤ ነገር ግን አሁን በሕዝብ ተወክለን ስላልመጣን በሕዝብ ስም ይቅርታውን መቀበል እንደማይችሉ በጊዜው ገልጠውላቸው ነበር፡፡