Tuesday, November 15, 2011

ፋይሉን ወደ መዝገብ ቤት

  • አሰግድ ሣህሉ በድብደባ ወንጀል ክስ መጥሪያ ወጥቶበት እየተፈለገ ነው፤
  • መ/ር ዘመድኩን በቀለ ለሰዓታት በእስር ቆይቶ ተለቀቀ፤
  • አሰግድ ሣህሉ ቅዱስ ሲኖዶስ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጆች ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ አጣጣለው፤
  • የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በአሰግድ ሣህሉ እና ትዝታው ሳሙኤል ላይ ክስ ሊመሠርት ነው፤

የመ/ር ዘመድኩን በቀለ መዝሙር ቤት እና መኖሪያ ቤት ብርበራ ተካሄደበት

  • ዛሬ የመከላከያ መልሱንና ክርክሩን ያቀርባል፤
  • ጠቅ/ቤተ ክህነት ክሱ ተቋርጦ መዝገቡ እንዲመለስ ፍትሕ ሚ/ርን ጠይቋል፤
  • እነበጋሻው መ/ር ዘመድኩንን በተጨማሪ ክስ ለማስቀጣት፣ “እኛን አጥፍቶ እርሱ አይቀመጥም”በሚልም ከሀገር እንዲወጣ የተለያዩ የማሸማቀቂያ ዘመቻዎችን እያካሄዱ ነው፤
  • “የምትለውን ሕግ አብረን እናየዋለን፤ መቃብርህን ቆፍረሃል፤ 12 ሆነን ንብረታችንን ሸጠንም ቢሆን አንተን ጉድጓድ እንከታሃለን፤ ከምትገባበት ጉድጓድ ማን እንደሚያወጣህ እናያለን፤”  (የፊደል ሬስቶራንት ባለቤት መ/ር ዘመድኩንን ያስፈራሩበት የዛቻ ቃል ድምፅ)፤
  • ዳኛውም በጋሻው የተሳሳተ ምስክርነት በመስጠት ፍ/ቤቱን ከማሳሳት እንዲጠነቀቅ አሳስበውታል
  • መምህር ዘመድኩን እና መምህር ደስታ ‹‹ እኛ የጻፍነው የሃይማኖት ሕጸጽን ነው፡፡ የግለሰቡ የሃይማኖት ጉዳይ ቅዱስ ሲኖዶስ በቋቋመው የብጹአን አባቶች ኮሚቴ እየታየ ነው፡፡ ይኸው ተገልጾ ክሱ እንዲቋረጥልን ደብዳቤ ይጻፍልን›› በማለት ብጹዕ ሥራ አስኪያጁን ጠይቀዋል፡፡

Monday, November 14, 2011

የአቡነ ፋኑኤል ደጋፊዎች Branch ቤተክርስትያን በመክፈት ስራቸውን ጀምረዋል

  • አቡነ ፋኑኤል እንደ ልማዳቸው በቅርብ ቀናት ቦታው ድረስ በመሄድ ይባርኩላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል 
  • ‹‹እንደፈለግን ቤተክርስትያናትን መክፈት እንችላለን በአሜሪካን ሀገር ነው ያለነው ማንም ሊከለክለን አይችልም ›› 
  • ‹‹ነገር ግን ሁሉ በአግባብና በሥርዓት ይሁን። ›› 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14፥40
    ቀሲስ ኢስሃቅ እና ቀሲስ አቡኑ Branch Manager
    ". . .እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ። የሰው ልጅ ሆይ፥ ልብ አድርግ ስለ እግዚአብሔርም ቤት ሥርዓትና ሕግ ሁሉ የምናገርህን ሁሉ በዓይንህ ተመልከት በጆሮህም ስማ የቤቱንም መግቢያ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ አድርግ። . . ."
    ትንቢተ ሕዝቅኤል ፵፬ ፥ ፭

    ፓትርያርኩ ሦስት ከፍተኛ ሓላፊዎች የሥራ ውል እንዲቋረጥ ማዘዛቸው ተሰማ

    • ሰበቡ ለጋሾች በልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በኩል ለሐላፊዎቹ ደመወዝ የሚመድቡትን በጀት ባለመስጠታቸው ነው ተብሏል፤
    • ትእዛዙን የጠ/ቤ/ክ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ አልተቀበሉትም፤
    • “ጠቃሚ ሥራ የሚሠሩ ሰዎች ቀንድ ቀንዳቸውን እየተባሉ ይወጣሉ፤ ሰዎቹ ከጠ/ቤተ ክህነት ፈሰስ ተደርጎም ቢሆን ሥራቸውን ይቀጥላሉ›› (ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ)፤ 
    • “ቤተ ክርስቲያንንና መንግሥትን በግልጽ እንዲለያዩ ያደረገው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት 16 ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም አስተዳደራዊ በሆነ መልኩ ሲታይ 50 ሚልዮን የሚሆነውን የምእመን ብዛትና ከፍተኛ የሚባል የገንዘብና ካፒታል መጠን ይዘን ብዙም አልተራመድንም፡፡. . .ቅዱስ ሲኖዶስ ጠቅላይ ቤተ ክህነትን በስትራቴጂክ ፕላን እንዲመራ በማድረግ የዕቅዱን አፈጻጸም በየጊዜው መገምገም ሲገባው ወይም እየገመገመ የሚያቀርብለት የባለሞያዎች ቡድን መሠየም ሲገባው እስከ ዛሬም ባለመሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን የልማት አቅጣጫ፣ አስተዳደራዊ ጉዳዮች፣ የበጀት አያያዝና አፈጻጸም የማያመረቃ ሆኖ ቆይቷል፡፡” /አቶ ልዑል ሰገድ የቤተ ክህነቱን አስተዳደራዊ እና መዋቅራዊ ችግሮች ከዳሰሱበት የዳሰሳ ምልከታ ጽሑፍ የተወሰደ
    • ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ 40ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ላይ ለመገኘት ግብጽ - ካይሮ ገብተዋል፡፡ የመንበረ ማርቆስ ፖፕ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ 40 ዓመታት እና የመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ 20 ዓመታት ምንና ምን ናቸው? እንገምግመው፤ እንወያይበት፡፡ 

    የህትመት ሚዲያውና የሲኖዶስ ውሳኔዎች

    (ህዳር 2 2004 ፤ November 12 / 2011 እትም)
    • የእነ በጋሻው በሲኖዶስ መታገድ
    • በኦርጋና መዘመር ተፈቅዷልን ? ፤
    • የአባ ሰላማ ድህረ ገፅ ‹‹በሬ ወለደ›› ፅሁፍ
    • የአቡነ ጳውሎስ አቋም መቀየር
    • በኑፋቄ ‹‹ ተጠርጣሪ›› ስም ዝርዝሮች
    • ስለ ሶስቱ አህጉረ ስብከት የሲኖዶስ ውሳኔ
    • የብፁ አቡነ ሳሙኤል ምላሽ
    • የአባ ሰላማ (የጊዜው ጠላት) ክስ በሲኖዶስ ላይ
    • የ11 አብያተ ክርስትያናት መግለጫ ፤ የመንፈሳዊ ፍ/ቤቶች መቋቋም ፤ ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ...ሌሎች ነገሮች
    To Continue Click Read more

    Sunday, November 13, 2011

    “የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አከብራለሁ፣ የተመደብኩበት ቦታ እሄዳለሁ” ብፁዕ አቡነ አብረሃም


    • ብፁዕነታቸው ቤተ ክርስቲያን ልካኝ አሜሪካን መጥቼ ነበረ፤ አሁንም ቤተ ክርስቲያን ወደ ላከችኝ ቦታ እሄዳለሁ” በማለት ሲናገሩ በበዓሉ የተገኙት ምእመናን እና ካህናት በእንባ እንደተራጩ በቦታው የተገኙ የአይን ምስክሮች ገልጸውልናል::

    በሲልቨር እስፕሪንግ ሜሪላድ ኆኅተ ምሥራቅ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የቅዳሴ ቤት ለማክበር የተገኙት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብረሃም ወደ ኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ ወደ መደባቸው ሀገረ ስብከት እንደሚሄዱ ገለጹ:: ብፁዕነታቸው የተመደቡበት ቦታ የሚገልጽ ደብዳቤ ህዳር 1፣ 2004 ዓ/ም እንደደረሳቸው ገልጸው፤ ነገር ግን ለዚህ ሀገረ ስብከት ስለተመደበ አባት ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል:: ብፁዕነታቸው አንዳንድ ጅምር ሥራዎች ሥላሉዋቸው እስከ ታህሣሥ ወር አጋማሽ ድረስ ለመቆየት ለቅዱስ ሲኖዶስ ደብዳቤ መጻፋቸውም ጭምር ገልጸዋል:: በዕለቱም ትምህርታቸው “እኔ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት እና ቀኖና ይከበር ብዬ እያስተማርኩ፤ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን የምጥስበት ምክንያንት ምንም የለኝም” በማለተ ተናግረዋል:: አንዳንድ ሰዎች “ዛሬ ለምን የቅዳሴ ቤቱን አከበርክ”? ብለው ይጠይቁ ይሆናል፤ ነገር ግን ዛሬ የተገኘሁበት ምክንያት አስቀድሞ የተያዘ መርሀ ግብር በመሆኑ እንዲሁም ደግሞ ከሀገረ ስብከቱ መነሳቴ እንደ እናተው ዜና ከማንበብ ውጪ ሌላ ምንም የደረሰኝ መልዕክት ስላልነበረ ነው:: ሥለዚህ በዛሬው እለት የቅዳሴ ቤት ማክበሬ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን የወጣ አይደለም ብለዋል::

    Saturday, November 12, 2011

    የዝውውር መስኮቱ መቼ ነው የሚዘጋው ?

    • “የቀረበብኝ ‘የሐሰት ውንጀላ’ ለመሥራት ስለማያስችለኝ የዕረፍት ጊዜ ይሰጠኝ”  (አባ ሠርቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል) 
    • የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ድርጅታዊ ዲዛየን እንዲፈተሽ የጠየቁት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ የኮንትራት ውል እንዲቋረጥ ታዟል 
    • በድሬዳዋ ቅዱስ ገብርኤል ሕንፃ ቤተክርስቲያን ግንባታ ከ1.8 ሚልዮን ብር በላይ የደረሰበት አልታወቀም 
    (አባ ሠርቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል)
    • የመንፈሳዊ ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው በፓትርያርኩ በመሾማቸው ተቃውሞ ያቀረቡት አካላት፣ “እንከን የሌለበትን ንጹሕ እምነታቸውን ጥላሸት የቀቡ ከሳሾቻቸው” ማንነት እና የክሱ ዝርዝር እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፤ 
    • ‹ውንጀላው› እስከሚጣራ ድረስ “እጅግ መራራ ተጋድሎ በከፈሉበትና ውጤት ባሳዩበት” የቀድሞ ቦታቸው እንዲቆዩ አልያም የዕረፍት ጊዜ እንዲሰጣቸው አመልክተዋል፤ 
    • “እውነትንና ፍትሕን” ከቤተ ክርስቲያን እንደሚሹ “እውነትና ፍትሕ” ከቤተ ክርስቲያን ከጠፋ ግን ሕገ መንግሥቱን ተጠቅመው መብታቸውን በማስከበር ከሳሾቻቸውን ለመበቀል ዝተዋል ::
    • ከአዲሱ የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሓላፊ ጋራ ርክክብ ያደርጋሉ፤

    Friday, November 11, 2011

    የአቡነ ጳውሎስ ገድል

    • ‹‹...የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት ስለ ቤተክርስትያን ሲል በቀድሞው ፓትሪያሪክ ላይ የወሰደውን እርምጃ ደግፈናል››
    • ‹‹ከሰው ጋር ተስማምተው ሥራ መሥራት ስላልቻሉ በነጻ ቀለብ እየተሠፈርላቸው ሲኖሩ ነበር››
    • አባ ጳውሎስ የደርግና የወያኔ ሰላይ ነበሩ፡፡
    • አባ ጳውሎስ ወደ ውጭ አገር ሲሄዱ መኪናቸው በአውሮፕላን ተጭኖ እንዲሄድ ያደርጋሉ

    ክፍል 1
    (አንድ አድርገን ፤ ህዳር 1 2004 ዓ.ም) ገድል ጥሩ ለሰሩ ሰዎች ብቻ ይፃፋል ያለው ማነው? አሁን ባለንበት ሰዓትም ቤተክርስትያን ደም እንባ ያስለቀሷት አባቶች ገድላቸው እንደ ስራቸው ተመዝኖ ለታሪክ መቀመጥ መቻል አለበት የሚል አመለካከት አለኝ ፡፡ የአቡነ ተክለሃይማኖት ገድል 25ኛ ካህን ሆነው የስላሴን መንበር ለማጠን የደረሱ ምድራዊ መላእክት የተባሉ ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው የእምነታችን እንቁ አባት መሀሆናቸውን ይነግረናል ናቸው፡፡ ለአቡነ ጳውሎስ እንደ ቀደሙት አባቶቻችን ስራቸው በእግዚአብሔር ፊት ሚዛን የደፋ፤ የተሰጣቸውን አደራ በቅጡ ያልተወጡ ፤ እግዚአብሔርን እና ምዕመኑን ደስ የሚያሰኝ ስራ ባይሰሩ እንኳን  ያደረጉት እኩይ ተግባር ተፅፎ መቀመጥ አለበት ፡፡የአባ ጳውሎስም ስራቸው አንዲት ሳትቀር ትክክለኛ ማንነታቸውን የሚናገር ለትውልድ በመፅሀፍ መልክ ቢዘጋጅ ነገ ለሚነሱ አባቶች እንደመማሪያ ፤ ቤተክርስትያን ያለፈችበትንም የመከራ ዘመን ያውቁበታል፤ የውጩን ሳይሆን የውስጥ ችግሯን ይረዱበታል ፤ ከመሰል አባቶች ራሳቸውንንም ትውልዱን ይጠብቁታል የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡ እኛ ግን ጥሩ ጥሩውን እንጂ በዘመናችን ጥሩ ያልሆነውን ፅፈን ለትውልድ የማስተላለፍ ባህሉን ያዳበርነው አይመስለኝም ፡፡ ቤተክርስትያን በዩዲት ጉዲት ፤ በግራኝ መሀመድ ዘመን የደረሰባትን መከራ ፤ ችግር፤ ስቃይ አባቶቻችን ለኛ ከትበው አስቀምጠውልን እኛም ልናውቀው ችለናል ፡፡ የአቡነ ጳውሎስ ትክክለኛ መልካቸውን ሳንጨምር፤ ሳንቀንስ ፤ሳናጋንን ፤ ሳናሳንስ ለመጪው ትውልድ ብናስቀምጥለት ምን ጉዳት አለው? ብዬ በማሰብ ስለሳቸው የማውቀውን ያህል ፤ ካነበብኩት ፤ መጽሀፍቶች ከነገሩኝ ፤ እውነታ ያላቸው ሰነዶች ካስረዱኝ ፤ አንደበታቸው ከተናገረው ፤ የተለያዩ እውነትን መሰረት ያደረጉ ድህረ ገፆች ካነበብኳቸውስለ እሳቸው  ለመፃፍ አሰብኩ፡፡

    Thursday, November 10, 2011

    አቡነ ፋኑኤል በሰሜን አሜሪካ ከፍተኛ ማዕበል ይጠብቃቸዋል ይወጡት ይሆን ?

    • ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ከፍተኛ ተቃውሞ ይጠብቃቸዋል፣ቅዱስ ሲኖዶስ በሰሜን አሜሪካን የቤተ ክርስቲያን ችግር ንክኪ የሌለባቸው አባቶች እንዲመድብ ፊርማ እየተሰባሰበ ነው
    ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል
    የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 02/2004 ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሚገቡነት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ከፍተኛ ተቃውሞ እንደሚጠብቃቸ እየተነገረ ነው:: ብፁዕነታቸው ከዚህ በፊት የሰሩዋቸው ኢ-ክርስቲያናዊ ተግባራት በዚህ አካባቢ በሰፊው የሚታወቅ ስለሆነ ተቃውሞው የከፋ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል:: በሰሜን አሜሪካ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ማኅበር፣ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኙት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት፣ በገለልተኛ አስተዳደር ስር የሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና በሰሜን አሜሪካ የማኅበረ በዓለ ወልድ አባላት ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ይጠብቃቸዋል ተብሎዋል:: “የግል ቤተ ክርስቲያን ያለው አባት እንዴት ቤተ ክርስቲያን አንድ ሊያደርግ ይችላል”? የሚል ጥያቄ እየተነሳ መሆኑም እየተነገረ ነው::

    Wednesday, November 9, 2011

    የፓትርያርክ ጳውሎስ ቁማርና የቤተክርስቲያን ተስፋ

    (by Wendemsesha Ayele Kesis ) ቁማር ከመዝናናት ሌላ ጥቅም ለማግኘት ሲባል የሚጫወቱት ሕጋዊና ሕገወጥ ጫወታ መሆኑና ማንኛውንም ጫወታ በቁማርነትም ሆነ በመዝናኛነት ለይቶ የመጫወቱ ድርሻ የተጫዋቹ መሆኑ ግልጥ ነው፤ ካርታን ለመዝናኛነትም፣ ሲያስፈልግ ደግሞ በሕገወጡ ቁማርነትም መጫወት እንደሚቻል። ይህም መንፈሳዊውን ሥልጣን በያዘው ሰው ዘንድ መነገሩ እጅግ የሚያሳስብና የሚያሳዝን ነው። «አባት»ን ቁማርተኛ ብሎ ለሚናገረውም ሁለት ጊዜ ብቻ ሳይሆን አሥር ጊዜ አስቦ ዓላማንም ለይቶ የሚጸናውን ከያዙ ላያሳፍር ብሎም ሊጠቅም ይችላል። ተሳድቦና ዘልፎ ለመርካት ወይም ብስጭትን ለመወጣት ሊረዳ ቢችልም ከኅሊና ዕዳ ነፃ ለመሆን ግን እውነተኛ መረጃ ይፈልጋል፤ እንደነ በጋሻውም በአደባባይ ለመገላበጥ አይገደድም። እኛምይህን ታሳቢ አድርገን እንቀጥል።

    ከረጅሙ ታሪካቸው ባጭሩ
    አባ ጳውሎስ አሁን በሕይወት ከሌሉ አንድ ዘመዴ ጋር የሃይስኩል ተማሪ ሆነው በቅድስት ሥላሴ ት/ቤት ሲማሩ የነበሩበትንና ከያኔው ግርማ /አሁን አቡነ ገሪማ/ ጋር ሆነው ሁለቱ ጓደኞቻቸው በጥቁር ራስነት እሳቸው ግን ያኔም በምንኩስና ሲኖሩ ድብቅነት ይታይባቸው ነበረ። ጵጵስና ከተሾሙ በኋላ ሳይቀር ቆባቸውንና ቀሚሳቸውን አውልቀው በሱሪና ኮት እንደተራ ሰው ከተማ የሚዞሩበት አጋጣሚም ነበረ፤ ምክንያቱን ራሳቸው ይወቁት።