Thursday, August 11, 2011

አሰግድ ሳህሉ ማነው ?



  • ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ አሁንም በአብ ቀኝ ቆሞ ያማልዳል፤›› አሰግድ ሣህሉ
  • ‹‹የክርስቶስ ሥጋ እና ደም ተቀበልንም አልተቀበልንም ለውጥ የለውም›› አሰግድ ሣህሉ
  • ‹‹የእውነት ቃል አገልግሎት›› የተባለ የተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ድርጅት የመሠረተ ነው
  • ‹‹ሙሉ ወንጌል›› አማኞች የጸሎት ቤት በተካሄደው ጉባኤ ላይ ከመሰሎቹ ጋራ ተካፍሎ ሲወጣ ተደርሶበታል
የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ አራማጅ - አሰግድ ሣህሉ እንደ ማሳያ
አሰግድ ሣህሉ በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን የዉሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት የተሐድሶ ኑፋቄን ለማስፋፋት፣ አንዳንድ የሰንበት ት/ቤቱን ወጣቶች ከእናት ቤተ ክርስቲያን ወደ ‹‹ሙሉ ወንጌል›› አዳራሽ ለመውሰድ ሲያደርግ የቆየውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ በጥብቅ ሲከታተል በቆየው የሰንበት ት/ቤቱ ሥራ አመራር ኮሚቴ የተዘጋጀው ባለ 40 ገጽ ሰነድ ያስረዳል፡፡ እንደ ዘገባው ማብራሪያ አሰግድ ሣህሉ ከሚኖርበት ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 11/12 የቤት ቁጥር 417 በተለምዶ ቡልጋሪያተብሎ ከሚጠራው የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል - የከርቸሌው ሚካኤል አካባቢ ያለሰበካው ወደ ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን መጥቶ በዉሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት በ1985 ዓ.ም የተመዘገበው ሰንበት ት/ቤቱ በወቅቱ ያጋጠመውን የአገልግሎት መዳከም ተመልክቶ ስውር የተሐድሶ ኑፋቄ ተልእኮውን ለማራመድ እንዲያመቸው ነው፡፡

ትንቢቱ ሲፈጸም

ትንቢቱ ሲፈጸም በመጽሐፍ ያለው፣
ወገኔ አትደንግጡ ይህ ሊሆን ግድ ነው።
ቅዱሳን ሳይቀሩ የተመረጡቱ፣
በመጨረሻው ቀን በዓለም እንዲስቱ፣
ቀድሞ በመጽሐፍ ተነግሯል ትንቢቱ።

ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሐሙስ

በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የሚያምኑ እና የሚማፀኑ ሁሉ ውዳሴዋን እና ቅዳሴዋን በመማርና በማስተማር በመፀለይም ጭምር እንዲጠቀሙበት መፅናናትም እንዲያገኙበት ከአበው ሲወርድ ሲዋረድ የቆየውን ንባቡን ከነትርጓሜው በዚህ መልክ አቅርበንላችዋል፡፡

ይህን የእመቤታችንን ውዳሴ ማርያም በዚህ በፍልሰታ በፆም ወራት ቤተክርስትያን ተገኝተው ለመስማትም ሆነ ለማንበብም ለማይችሉ በተለያየ ሀገራት ለሚገኙ ወገኖች በቀላሉ እንዲያነቡ ተደርጎ የተዘጋጀ

Wednesday, August 10, 2011

ተሐድሶ ማለት እኔ ነኝ…..አሰግድ ሳህሉ

አሰግድ ሳህሉ ነሐሴ  2003 ዓ.ም ከማራኪ መፅሄት ጋር ያደረገው ኢንተርቪው

አሰግድ ፡- ተሐድሶ ማለት ምን ማለት ነው አለችኝ ? አንዷ አገልግለን ስንወጣ ባለፈው ናዝሬት ላይ  እኔም አሰግድ ማለት ነው አልኳት፡፡ ተሀድሶ የሚባል ድርጅት ለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም መኖሩን ሳውቅ ያኔ ሌላ መልስ ይኖረኛል ፡፡ ይህን ስም የተሸከምኩት 18 ዓመት ነው ፡፡

ሙሉ ዘገባውን ይመልከቱ ........

Tuesday, August 9, 2011

ከወቅቱ የተሐድሶ አጀንዳ በስተጀርባ



ሙሉ ዘገባውን  ይመልከቱ   ........

የዚህ መልስ ግን ለአባ ጳውሊ አልመጣለትም



     አባ እንጦንስ አባ ጳውሊን ሊጠይቀው በሄደ ጊዜ አባ ጳውሊን ‹‹ እስኪ ይህ ሥርዓተ ምንኩስና ከእኔ በኋላ ይቀራል ወይስ ይቀጥላል የሚለውን ከእግዚአብሔር ጠይቅልኝ›› አለው፡፡ አባ ጳውሊም በጸሎት እግዚአብሔርን ጠየቀለት፡፡ ከጸሎቱም በኋላ የአባ ጳውሊ ገጽ በደስታ ተሞላ፡፡ አባ እንጦንስም ‹‹ ምን አየህ›› ብሎ ጠየቀው፡፡ አባ ጳውሊም ‹‹ ነጫጭ ርግቦች አንተ እየመራኻቸው በጠፈር ላ ሲሄዱ አየሑ›› አለው፡፡ አባ እንጦንስም ‹‹ ምንድን ናቸው›› ሲል ጠየቀው፡፡ ‹‹ በቆብ የምትወልዳቸው ንጹሐን ጻድቃን መነኮሳት ናቸው›› አለው፡፡

የቤተክህነቱ ጨለምተኛ ምሁራዊ ድባብ

  • ዛሬ ቤተክርስትያኒቱ ከእነሱ የበለጠ አለቃ አያሌውን ከሙታን መንደር ትጣራለች ፡፡ የቤተክርስትያኗ መቁሰል አልታይ ብሏችዋልና፡፡ 
  • ለዛሬ የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን መሰረታዊ ችግሮች ‹‹ ያለ አቡነ ተክለሀይማኖት ፤ ያለ አቡነ ፍሊጶስ ደብረ ሊባኖስ ምንድነች ? ያለ አቡነ እየሱስ ሞአ ፤ ያለ አቡነ ክርስቶስ ሞአ ደብረ ሀይቅ ምንድነች ? ያለ አቡነ ኤዎስጣቲዎስ ያለ አቡነ ፊሊጶስ ደብረ ባዚን ምንድነች ? ›› ያሰኙንን አይነት ሊቃውንት አጥብቀን እንፈልጋለን ፡፡ 

የተሐድሶ ሴራ በሐዋሳ( ቁጥር 1)








ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ረቡዕ

በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የሚያምኑ እና የሚማፀኑ ሁሉ ውዳሴዋን እና ቅዳሴዋን በመማርና በማስተማር በመፀለይም ጭምር እንዲጠቀሙበት መፅናናትም እንዲያገኙበት ከአበው ሲወርድ ሲዋረድ የቆየውን ንባቡን ከነትርጓሜው በዚህ መልክ አቅርበንላችዋል፡፡

ይህን የእመቤታችንን ውዳሴ ማርያም በዚህ በፍልሰታ በፆም ወራት ቤተክርስትያን ተገኝተው ለመስማትም ሆነ ለማንበብም ለማይችሉ በተለያየ ሀገራት ለሚገኙ ወገኖች በቀላሉ እንዲያነቡ ተደርጎ የተዘጋጀ


ድንግል ትንሳኤሽን...በዘማሪ ቴዎድሮስ ዮሴፍ



ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ
ገብተናል ሱባኤ በአንድነት በመንፈስ
ለእኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያለው እውነት
አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነ ምህረት

ሞትማ በሞት ተሸንፏል
በአንቺ ላይ ምን ስላጣን ያገኛል
መልካም የጽሞና ጊዜ እና የለውጥ ወቅት ይሁንላችሁ ድንግል ማርያም ከእናንተ ጋራ ትሁን አሜን