Thursday, February 11, 2016

የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ዳግም ተከላ




ምንጭ ፡- ሪፖርተር ጋዜጣ (10 Feb, 2016)
የፋሺስት ሰለባው አቡነ ሚካኤል ሐውልትም ወደ አደባባዩ እንዲመለስ ፓትርያርኩ ጠየቁ

‹‹
እግዚአብሔር ይፍታችሁ፣ እግዚአብሔር ይፍታችሁ ልጆቼ፣ ለጠላታችሁ ለፋሽስት አትገዙ ልጆቼ፣… እንኳን እናንተ መሬቷም እንዳትገዛ ገዝቻለሁ፣… እመብርሃን ብቻዬን ነኝ ትእዛዝሽ ተቆራኘኝ፣… ምሳሌን የቃል ኪዳኔ ምንጭ አርጊያት፣… አንደበቴን የእውነት ብርሃን አርጊያት፣… ልጆቼ በመንፈስ ጀምራችሁ በሥጋ እንዳታልቁ፣ ለሀገራችሁ በመልካም ፍሬ ፈንታ አሜከላ እንዳትሆኗት፣… ለጠላታችሁ፣… አትገዙ፣… እንኳን እናንተ መሬቷም እንዳትገዛ ገዝቻለሁ፣… ልጆቼ እግዚአብሔር ይፍታችሁ፤››


ከስምንት አሠርታት በፊት በፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ጊዜ አራዳ ጊዮርጊስ አካባቢ በፋሺስቶች የጥይት አረር ሰማዕትነት የተቀበሉት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ከመገደላቸው በፊት የተናገሩትን፣ ያስተላለፉትን ቃለ ግዝት በዚያው አደባባይ ላይ ከ80 ዓመት በኋላ ያስተጋባው አርቲስት አብራር አብዶ ነበር፡፡ ከሦስት ዓመት በፊት በባቡር መስመር ዝርጋታ ሳቢያ ተነስቶ የነበረው የሰማዕቱ አርበኛ ጳጳስ - ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ጥር 29 ቀን 2008 ዓ.ም. በቀደመ ስፍራው ተተክሎ ከመገለጡ በፊት ነበር አብራር አብዶ የጸሐፌ ተውኔትና ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን ‹‹ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት›› ተውኔት አንዱን ቃለ ተውኔት የተወነው፡፡

Sunday, February 7, 2016

‹‹ባታውቀው ነው እንጂ የሕዝቡ ባሕል ሲናደድም ያጨበጭባል››

(አንድ አድርገን 29-05-08) :-  " አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ ፡፡ መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት ። ቀጥለውም በያዙት መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ ። የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ከተቱት ። ወዲያው ወታደሮች በሩምታ ተኩሰው ገደሉዋቸው ። ይህ እንደሆነ አስገዳዩ ኮሎኔል ተመልካቹን ሕዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ ። "

" ማታ ከአስገዳዩ ኮሎኔል ጋር ተገናኝተን ስንጫወት ‹በዚህ ቄስ መገደል እኮ ሕዝቡ ተደስቷል› አለኝ ። ‹እንዴት? › ብለው ‹አላየህም ሲያጨበጭብ› አለኝ ። እኔም ‹ባታውቀው ነው እንጂ የሕዝቡ ባሕል ሲናደድም ያጨበጭባል› አልኩት ። ‹‹እንዴት?›› ቢለኝ እጄን እያጨበጨብኩ አሳየሁት ፡፡
(ዜና ጳጳሳት ኢትዮጵያውያን ፣ ዲ/ን መርሻ አለኸኝ ፣ ገጽ 79-80)

Saturday, January 23, 2016

በ“ኦርጋን” ብንዘምር ምን አለበት?



ከጥንት ጀምሮ “የምን አለበት?” መዘዙ ብዙ ነው፥የግድ የለሾች መፈክር ነው።“እግዚአብሔር መሐሪ ስለሆነ ኃጢአት ብሠራ ምን አለበት?” እንደ ማለት ነው።ንስሐ ከመግባት ይልቅ እግዚአብሔርን መሞገት የፈለገ ሰው፡-“ኰንኖ ኃጥአን ኵሎሙ ኢይደልወከ ምንተ ፥አፍቅሩ ጸላእተ ክሙ እንዘ ትብል አንተ ፤ፈራጅ ዳኛ እግዚአብሔር፡-በጠላቶችህ ኃጥአን ላይ ልትፈርድ አይገ ባህም፥አንተ ጠላቶቻችሁን ውደዱ ብለሃልና፤” በማለት እንደተናገረውም ሊሆን ነው።ወይም ሲቆርብ ሲያቆርብ የኖረ በደለኛ ሰው፥ንስሐ ከመግባት ይልቅ፡-“ዘበልዐ ሥጋየ ወዘሰትየ ደምየ፥ ቦ ሕይወት ዘለዓለም የሃሉ ምስሌየ፤ብለህ ተናግረህ፥በወንጌል ተጽፎ ይገኛል ቃልህ፤ይኸንን ተላልፈህ ተኰነን ብትለኝ፥አብረን እንወርዳለን እኔ ምንቸገረኝ፤” በማለት እንዳፌ ዘው መሆኑ ነው። -አዳምና ሔዋን በምክረ ከይሲ ተነድተው፥በምን አለበት? የዕፀ በለስን ፍሬ መብላታቸው አልጠቀማቸውም። ዘፍ፡፪፥፲፯።

Monday, January 18, 2016

አባትነት እንዲህ ነበረ 3 ፡




አንድ አድርገን ጥር 10 2008 ዓ.ም
የእምነት አባቶቻችን የጌታ ደቀመዛሙርት ህይወታቸው እንዴት አለፈ?
1.ማርቆስ:- እስኪሞት ድረስ በአሌክሳንድርያ ግብፅ ጎዳናዎች በፈረስ ታስሮ እየተጎተተ ህይወቱ አልፋለች
2.ሉቃስ:- በግሪክ ሰቅለውት ህይወቱ አልፋለች
3.ማቲዎስ:-በቆንጨራ ተቆርጦ ሞቷል::
4.ዮሐንስ:-
5.ጴጥሮስ:-ተዘቅዝቆ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞቷል::
6.ቶማስ:- በህንድ በጦር ተወግቶ መስዋእት ሆኗል::
7.ጳውሎስ:-በአሰቃቂ ሁኔታ ተገርፎ አንገቱ ተቆርጦ ህይወቱ አልፏል::
8.ስምዖን:-ግማሽ ለግማሽ ተቆርጦ ነው ተቆርጦ::
9.ማቲያስ:-በድንጋይ ተወግሮና አንገቱ ተቆርጦ::
10.ይሁዳ:- በጦር ተወግቶ::
11.እንድርያስ:-በስቅላት ህይወቱ አልፏል::
12.ያዕቆብ:-በእየሩሳሎም አደባባይ አንገቱ ተቆርጦ የሞተ::
13.በርተለሚዎስ:-በግርፋት ህይወቱ አልፏል::
ሁሉም መልካሙን ገድል ተጋደሉ ክርስቶስን ካዱ ሲባል አይሆንም ብለው አንገታቸውን ለካራ ሰውነታቸውን በዘይት ለመቀቀል ለግርፋት ለስቅላት አሳልፈው ሰጡ