Tuesday, April 21, 2015

ክርስትና የመናቅና የመጠላት ሃይማኖት



ከሁለት ወራት በፊት የግብፅ ክርስቲያን ወንድሞቻችንን አንገት ቀልተው ወጣቶቹንና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለሰማዕትነት ክብር ያበቁ አረመኔዎች ሰሞኑን ደግሞ ተራው የኢትዮጵያውያን ወጣቶች እና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መሆኑን በተግባር የወንድሞቻንን አንገት ከመቅላት እና በጥይት ከመደብደብ አልፈው በቃልም ሰማዕታቱን “የጠላታችን የኢትዮጵያ የመስቀል ተከታዮች” ብለው በመደንፋት ገልጸውልናል። ለሃይማኖታቸው የቆረጡ ዕድለኞቹ ወንድሞቻችንም አንገታቸውን ለስለት፣ ጀርባቸውንም ለጥይት እሩምታ በመስጠት ፈጣሪያቸውንና ቤተ ክርስቲያናቸውን በሰማዕትነት ሞት አክብረዋል። “ፈጣሪ ለምን ዝም አለ? እንዴትስ በእነዚህ ጨካኞች እጅ ሕይወታቸው እስኪያልፍ ተዋቸው?” በማለት የእምነታቸውን መላላት ያሳዩንም አሉ።

‹‹በሃይማኖታቸው ምክንያት ግፍ የሚደርስባቸው መንግሥተ ሰማያትን ይናጠቋታል›› ማቴ 11፤12


Monday, April 20, 2015

ሰማዕታትን በጸሎት ማሰብን ይመለከታል

  • ‹‹ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን ፤ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን፡፡ በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን›› ሮሜ 8 ፤ 36-37
  • "ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።"  (ማቴ 10:28)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ወመ/ጎ/ቅ/ማርያም ቤተክርስቲያን የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት በሊቢያ ላለፉት 28 ሰማዕታት ወገኖቻችን ልዩ የሆነ መርሀ ግብር ለሦስት ተከታታይ ቀናት ተዘጋጅቷል፡፡

ቀን ፡- ከዕረቡ ሚያዚያ 14 እስከ አርብ ሚያዚያ 16 2007 ዓ.ም

ሰዓት ፡ ሰርክ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ነገ ሚያዚያ 13 ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን በሊቢያ 28 ክርሰቲያኖች የተቀበሉትን ሠማእትነት ነጭ በመልበስ ጧፍ በማብራት በጸሎት እናስባችዋለን ሁላችን በቦታው በመገኘት በጸሎት እናስባቸው ፤ ላልሰሙት ሁሉ አሰሙልን ፤ መልእክቱን ለሌሎች አጋሩ
ከሰማዕታት በረከት ያሳትፈን
 ሁላችሁም ተጋብዛችኋል


የኢትዮጵያውያንን ደም የተጠማች ምድር

  • በሊብያ ያለቁት ወገኖቻችንን ማንነት አውቆ በጉዳዩ ላይ መነጋገር የቅዱስ ሲኖዶስ ኃላፊነት ነው፡፡ ግብጻውያኑ ሰማዕታት ብለው ለመሰየም የፈጀባቸው ሰዓታት ብቻ ነው፡፡ እኛም የሚገባውን ልናደርግ ይገባናል፡፡ ለመሞታቸው ምክንያት የኾነው እምነታቸው ብቻ ነውና፡፡

ከዲያቆን አባይነህ ካሴ
በሳዑዲ እና በሶርያ ምድር እንደ ጎርፍ የፈሰሰው የወገኖቻችን ደም ሳይደርቅ እንደገና ዛሬም አንገት የሚያስደፋ ትንግርት ቁጭ ብለን እየታዘብን መኾናችንን ሳየው እጅጉን ግራ ገባኝ፡፡ በየመን፣ በደቡብ አፍሪካ ደግሞም ትናንትና በሊብያ! ምድር በኢትዮጵያውያን ደም እየጨቀየች ነው፡፡ አልጀዚራ ፴ ሲል ሌሎች ደግሞ ፳፰ ይበሉ እንጂ ለእኔ ጉዳዩ የቁጥር አይደለም፡፡

Sunday, April 19, 2015

Saturday, April 11, 2015

ጥንታውያን የብራና መጻሕፍት ጥናት ለምን?




Source :- http://www.dw.de
ከማንተጋፍቶት ስለሺ እና  ከነጋሽ መሐመድ

በግእዝ የተጻፉ ጥንታውያን የብራና መዛግብት በኢትዮጵያ ለሃይማኖት ከሚሰጡት አገልግሎታቸው ባሻገር ሌሎች አገልግሎቶችንም በመስጠት ለዘመናት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። በተለይ መጻሕፍቱ ላይ የሠፈሩት ጽሑፎች ከሃይማኖታዊ እና ታሪካዊ ይዘታቸው ባሻገር በየዘመናቱ የነበሩትን ማኅበራዊ ክስተቶች ያመላክቱ እንደነበረም በጥናታዊ ጽሑፎች የተረጋገጠ ነው።
 
በባህር ዳር ከተማ ከመጋቢት 22 እስከ 23 ቀን 2007 ዓም በተኪያሄደው ኹለተኛው የግእዝ ሀገር ዐቀፍ ጉባኤ ላይ በርካታ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ነበር። «ጥንታውያን የብራና መጻሕፍት ሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት» በሚል ርእስ ጥናታዊ ጽሑፋቸውን ያቀረቡት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ነው።
በባህል እና ቱሪዝም አዘጋጅነት ባህር ዳር ከተማ ውስጥ በተከናወነው ኹለተኛው የግእዝ ሀገር አቀፍ ጉባኤ ላይ በርካታ ምሁራን ጥናታዊ ጽሑፎቻቸውን አቅርበዋል። «ጥንታውያን የብራና መጻሕፍት ሰነዶች እንደ ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት» በሚል ርእስ የተሰናዳውን ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ናቸው።

Friday, April 10, 2015

አቶ አሸናፊ የጻፋቸው ኦርቶዶክሳዊ ያልሆኑ ትምህርቶች ከቤተክርስቲያ ደጃፍና ከምዕመናን እጅ የሚወገዱበት መንገድ ያሳስበናል




አንድ አድርገን ሚያዚያ 01 2007 ዓ.ም

ከሦስት ዓመት በፊት ግንቦት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ አንድ ወሳኝ ውሳኔ መወሰኑን ይታወቃል ፤ በውሳኔውም በርካቶች ከቤተክርስቲያን ጋር የጀርባ ቅማል ሆነው ምንፍቅናቸውን ሲዘሩ የነበሩ ሰዎች በግልጽ ጉባኤ የተወገዙበት ቀሪዎቹ ደግሞ መዝገባቸው በይደር የቆየበት እንደሆነ የምናስታውሰው ነው፡፡ በጊዜው  በፕሮቴስታንቶች እየተደገፉ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዐተ እምነት፣ ክርስቲያናዊ ትውፊትና ታሪክ በኅቡእና በገሃድ ተደራጅተው ለማፍረስና ለማፋለስ እየተንቀሳቀሱ  ድርጅቶች ፍጹም ውግዘት የሚገባቸውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች በመለየት ማኅበረ ሰላማ፣ ማኅበረ በኵር፣ የምሥራች አገልግሎት፣ አንቀጸ ብርሃን፣ የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ተሐድሶ ኅብረት፣ አሸናፊ መኰንን፣ አግዛቸው ተፈራ፣ ጽጌ ስጦታው እና ግርማ በቀለ የመሰሉት ሰዎችና ላያቸው ማር የተቀቡ ውስጣቸው ግን ነጣቂ የሆኑ ተቋማት ተለይተው መለየታቸው ይታወቃል፡፡

Tuesday, April 7, 2015

አቶ በጋሻው ደሳለኝ እና መሰሎቹ በሀረር ራስ ሆቴል ከሚያዚያ 16-18 የሚቆይ ጉባኤ ከለባት ሊያዘጋጁ ነው


  • የመግቢያ ዋጋ 300 ብር

በምንፍቅና ትምህርት ምክንያት ጉዳያቸው ቅዱስ ሲኖዶስ የደረሰው እና እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው የሚባል መፍትሄ ያልተሰጣቸው ፤ ላያቸው ተዋሕዶ ውስጣቸው ተሀድሶ የሆኑ ሰዎች መናገሻ ከተማ ባደረጓት ከተማ ሀረር ላይ የተጎዱ ቤተ ክርስቲያንን ምክንያት በማድረግ በመጪው ወር ከሚያዚያ 16-18 የሚቆይ ‹‹ጉባኤ›› ሊያዘጋጁ መሆኑን በቦታው ተገኝተን ያገኝነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ባሳለፍነው እለተ ሰንበት በታላቅ ድምቀት የተከበረው የመድኃኒዓለም እና የሆሳዕና በዓል ላይ በሀረር መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ሰርክ ጉባኤ ላይ በተገኝንበት ወቅት መርሀ ግብር መሪው ለምዕመኑ ባስተላለፈው መልዕክት መሰረት ‹ጸጋው የበዛላቸው ፤ እግዚአብሔር አብዝቶ የባረካቸው ወንድሞቻችን የገጠሪቱን ቤተ ክርስቲያን ለመርዳት በማኅበረ እስጢፋኖስ አማካኝነት ከሚያዚያ 16-18 ድረስ በሀረር ራስ ሆቴል አዳራሽ ታላቅ የምሳ ግብዣ እና የወንጌል መርሀ ግብር ስለተዘጋጀ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል ፤ ወጣኒያን ማህበሩን እንድትቀላቀሉ መልዕክተን አስተላልፋለሁ ፤ በጉባኤው ላይ ‹ጸጋ› የበዛላት ‹ዘማሪት› ትርፌ እና ‹መጋቢ ሐዲስ› በጋሻው ደሳለኝ ይገኛሉ›› ካለ በኋላ ‹ጉባኤውን ለመታደም የመግቢያ ዋጋ 300 ብር ›› ነው በማለት ምዕመኑ ‹ጉባኤ›ያቸውን እንዲሳተፍ  መልዕክት አስተላልፏል፡፡