Monday, December 9, 2013

በፔርሙዝ ተለውጦ አሜሪካ የተሻገረው የ400 ዓመቱ ብራና


08 December 2013 ተጻፈ በ  ፍቅር ለይኩን
  •  የቅርሶቻችን ዋጋ ምን ያህል ነው?

(ሪፖርተር ጋዜጣ):-  የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ)...በዓለም ጥንታዊ ቅርስነት ከመዘገባቸው የሥነ ጽሑፍ ውጤቶች መካከል በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ባለቤትነት የተመዘገቡና በብራና ላይ የተጻፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የነገረ ሃይማኖት ጽሑፎች ይገኙበታል፡፡


 እነዚህ እስከ ሺሕ ዓመታት ዕድሜን ያስቆጠሩ ብርቅና ውድ የሆኑ የሥነ ጽሑፍ ቅርሶች በተለያዩ ጊዜያት በአገሪቱ በደረሱ ተፈጥሮአዊና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ምክንያት ውድመት፣ ጥፋትና ዝርፊያ እንዳጋጠማቸው ይታወቃል፡፡ከዚህም በተጨማሪ በጥናትና በምርምር ሰበብ ከአገር የወጡ ጥንታዊ ብራናዎች አያሌ ናቸው፡፡ በአውሮፓና በአሜሪካ በሚገኙ ትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎችና አብያተ መጻሕፍት፣ እንዲሁም በግለሰቦች፣ በቅርስ አሻሻጮች እጅም ማግኘት የተለመደ ነው፡፡

Thursday, December 5, 2013

ቤተክርስትያኗ ከሳውዲ ለተመለሱት ኢትዮጵያውያን 2 ሚሊዮን ብር እርዳታ እንደምትሰጥ ገለፀች


(ኢሬቴድ ኅዳር 25 2006 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ከሳውዲ አረቢያ ለተመለሱት ኢትዮጵያውያን የሁለት ሚሊዮን ብር ጊዚያዊ እርዳታ እንደምትሰጥ አስታወቀች፡፡ ብፁእ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትሪያሪክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሀይማኖት በቀጣይም ቤተ ክርስትያኗ እርዳታዋን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡
ቅዱስ ፓትሪያሪኩ ከእኛ የሚጠበቀው የእንኳን ደህና መጣቹህ ማለት ወይም በመንፈሳዊ አስተምህሮ ማፅናናትና መርዳት ብቻ ሳይሆን መልሰው እስኪቋቋሙ ድረስ መርዳት ግዴታችን ነው ብለዋል፡፡ፓትርያርኩ እንደገለፁት ይህ የወገኖቻችን እርዳታ ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው ወቅታዊ አጀንዳ መሆኑን በመግለፅ እስካሁን በመንግሥት በኩል እየተደረገ ያለውን የተቀናጀ አቀባበል በአካል በመጎብኘታቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች በበኩላቸው ለወደፊቱም  ተመሳይ እርዳታ ለማድረግና አባታዊ ምክር ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸው ተናግረዋል፡፡ መንግስት ብቻውን የስደተኞች ወገኖቻችን ምግብና መጠለያ አይችልም ያሉት ተሰብሳቢዎቹ ለወደፊቱ በተቀናጀ መልኩ እርዳታ በማሰባሰብ የወገኖቻችን ህይወት እንዲስተካከል ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል፡፡
 ምንጭ፡-የቤተክርስትያኗ የኮሚኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት

ሰበር ዜና - የመስቀል ክብረ በዓል የዓለም ቅርስ ሆነ


ሔኖክ ያሬድ

የኢትዮጵያው የመስቀል ክብረ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ዩኔስኮ አስታወቀ፡፡ ዩኔስኮ የመስቀል ክብረ በዓልን (Commemoration feast of the finding of the True Holy Cross of Christ)

በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ኅዳር 25 ቀን ይፋ ያደረገው፣ በኢንታንጀብል (መንፈሳዊ) ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃና ክብካቤ ላይ የሚሠራው ኮሚቴው ስምንተኛውን ጉባኤ እያካሄደባት ካለው የአዘርባጃኗ ባኩ ከተማ ነው፡፡

Friday, November 29, 2013

ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የመኪና አደጋ ደረሰ



 
(አንድ አድርገን ጥቅምት 19 2006 ዓ.ም)፡- ዛሬ ማለዳ ከጠዋቱ 11 ሰዓት ላይ ከሰሜን ሆቴል ወደ ጊዮርጊስ ቁልቁል ሲሄድ የነበረ አንድ ከባድ የጭነት ማመላለሻ(SINO TRUCK)  መኪና ባጋጠመው የፍሬን ችግር ምክንያት ሹፌሩ መኪናውን መቆጣጠር አቅቶት ቀጥታ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቅጽርን ደርምሶ በመግባት ከፍተኛ አደጋ አድርሷል ፡፡  በወቅቱ በቦታው ላይ በእቅልፍ ላይ የነበሩ ሁለት ጎዳና ተዳዳሪዎች ወዲያውኑ ሕይወታቸው ሲያልፍ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች ላይ ከባድ የሆነ አደጋ ደርሶባቸዋል ፤ ከፍተኛ አደጋ የደረሰባቸው ሶስቱ ሰዎች ወዲያውኑ በእሳት አደጋ ሰራተኞች እና አካባቢው ላይ ባሉ ሰዎች ጥረት ራስ ደስታ ሆስፒታል ተልከው ጊዜያዊ እርዳታ ከተደረገላቸው በኋላ ጉዳቱ ከፍተኛ በመሆኑ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተወስደዋል ፡፡ በአደጋው የቤተክርስቲያኑ መግቢያ በር እና ግንብ ከፍተኛ አደጋ የደረሰበት ሲሆን በተጨማሪ ሰው በፍርስራሽ ውስጥ ይኖራል ተብሎ በመገመቱ በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ፍርስራሹን የማንሳት ስራ ሲያከናውኑ ተስተውሏል፡፡ የደረሰው አደጋ አሰቃቂ መሆኑን በቦታው የነበሩ ሰዎች ተናግረዋል፡፡

ከአደጋው በኋላ የመኪናው ሹፌር በሰጠው ቃል መሰረት የመኪናው ንፋስ እምቢ በማለቱ አደጋው የደረሰ መሆኑን ተናግሯል፤ በአሁኑ ሰዓት  ፖሊስ የመኪናው ሹፌር ላይ ተጨማሪ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

Friday, November 22, 2013

የእነ በጋሻው ጉዳይ ወደ እርቅ እያመራ መሆኑ ተገለጸ

(አንድ አድርገን ህዳር 12 2006 ዓ.ም )፡- ከዚህ በፊት በተለያየ ጊዜ በሃዋሳ ፤ ዲላ እና ሌሎች አካባቢዎች ሁከት በማስነሳትና በሃይማኖት ህጸጽ በህዝቡ በተነሳባቸው ጥያቄ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ድረስ ደርሶ የነበረው የእነ በጋሻው ደሳለኝ ጉዳይ በጥቅምቱ የሲኖዶስ ጉባኤ ላይ የመጨረሻ እልባት እንዲሰጠው በተወሰነው መሰረት ሶስት ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳትን የያዘ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጉዳዩን ሲያጠና ከቆየ በኋላ በእርቅ ለመቋጨት የሚያስችል ውሳኔ ላይ መድረሱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡
 
ከቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዩን አጣርተው የመጨረሻ እልባት እንዲያበጁለት የተመረጡት  ብፁዕ አቡነ  እስጢፋኖስ ፤ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ዘካናዳ እና  ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ለዚህ እርቅ መነሻ የሆነው በ21/2/06 በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አዳራሽ በተካሄደው ስብሰባ ላይ በጋሻው ደሳለኝና ያሬድ አደም በብፁዕ አቡነ ገብርኤል እግር ላይ ወድቀው ይቅርታ በመጠየቃቸውና አቡነ ገብርኤልም ‹‹ይቅር ማለት የአባት ስርአት ነው›› ብለው ቅርታውን መቀበላቸው መሆኑ ይታወሳል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በእለቱ እርቁን መጠየቅ እንደሚፈልጉና ይቅርታውንም ለመጠየቅ ሶስት በማህበረሰቡ ዘንድ ተሰሚነት ያላቸው ሰዎች ከአዋሳ እንዲጠሩላቸው ስም ጠቅስው በጠየቁት መሰረት የተባሉት ሶስቱ የሀገር ሽማግሌዎች ተጠርተው በ27/02/06 ዓ.ም  ይቅርታ የጠየቋቸው ሲሆን ሽማግሌዎችም እንደ ግለሰብ ይቅርታውን ለመቀበል እንደማይቸገሩ ጠቅሰው፤ ነገር ግን አሁን በሕዝብ ተወክለን ስላልመጣን በሕዝብ ስም ይቅርታውን መቀበል እንደማይችሉ በጊዜው ገልጠውላቸው ነበር፡፡

Thursday, November 21, 2013

ዐረቢያ፥ የቄዳር ግፊያና ግፍ።


ከኃይለሚካኤል፥ ኅዳር ፱ ቀን ፪፲፻፮ ዓ. ም.

ከእስልምና እምነት መምጣት በፊት ዐረቦች የሚኖሩት መካ፣ ያትሪብ፣ መዲና ወዘተ ተብለው ይጠሩ በነበሩ ሠፈሮች አካባቢ ነበር። ዐረቦች የአስተዳደር ሥርዓት ፣ የህግ ሥርዓት  ወይም የእደ ጥበብ ስምሪት አልነበራቸውም። መንግሥትና መንግሥታዊ አስተዳደር  የሚባል ነገርም አያውቁም ነበር።[1] ቁሬሺ፣ ባኑ ሃሺም፣ ባኑ ኡማያ ወዘተ በሚባሉ ጎሳዎች ተለያይተው ግን ይጣሉ ነበር።[2] ጣዖት አምላኪዎችም ነበሩ።  ካባ የተባለ ድንጋይም ያመልኩ ነበር። እስከ አራት መቶ ዓ.ም. አካባቢ ዐረቦች ለሚናገሩት ቋንቋ መፃፊያ ፊደል አልነበራቸውም። ከእስልምና መምጣት አስቀድሞ በንግግር ግጥም መፎካከር   የዐረቦች ባህል ነበር።[3] እጅግ በጣም ግጥም የሚገጥመውን ሰው መጅኑን እያሉ ይጠሩት ነበር። ዐረቦች ከእስልምና በፊት የነበረውን ዘመን ጃሂሊያ ወይም የድንቁርና ዘመን ብለው ይጠሩታል።

Wednesday, November 20, 2013

እነ በጋሻውን በእርቅ ወደ ቤተክርስቲያኒቱ የመቀላቀል ስራ እየተከናወነ ይገኛል



(አንድ አድርገን ህዳር 11 2006 ዓ.ም)፡-
  • ግራ ቀኙን ያማከለ ውይይት በሀዋሳ ተካሂዷል ተብሏል
  • የእርቅ ጉባኤውን ሶስት ሊቃነ ጳጳሳት መርተውታል፡፡
  • ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ከሲኖዶስ የተወከሉ ናቸው፡፡
  • ‹‹ከእውቀት ማነስ አስተማሩ እንጂ የሃይኖት ህጸጽ ተገኝቶባቸዋል የሚያስብል ስራ አልተገኝባቸውም›› አባቶች የተናገሩት
  • ይዘው የወጡትን ሰዎች ይዘው እንዲመለሱ ጉባኤው ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡
  • የዕርቅ ስራው እየተሰራ የሚገኝው በፌደራል ጉዳዮች ተጽህኖ ነው የሚሉ ሰዎች አሉ ፡፡
  • ‹‹ወይ በእርቀ ሰላም ቀላቅሏቸው ወይም የእምነት ፍቃድ እንስጣቸው›› የፌደራል ጉዳዮች አቋም
  • በቤተክርስቲያኒቱ ከሰበካ ጉባኤ ውጪ በሰንበት ትምህርት ቤት ፤ በልማት ጉባኤ ሁለት ሁለት ሰዎች እንዲመድቡ ተፈቅዶላቸዋል፡፡
  • በዚህ መልኩ ዕርቁ እንዲከናወን ለ28/03/2006 ዓ.ም ጊዜያዊ ቀጠሮ ተይዟል፡፡
እስኪ ይጠብቁን

Saturday, November 16, 2013

ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው

  • ‹‹ለችግረኛውና ለምስኪኑ ጽድቅ አድርጉ›› መዝሙረ ዳዊት 82 ፤ 3


(አንድ አድርገን ህዳር 08 2006 ዓ.ም)፡- መቄዶኒያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ ከ300 በላይ በየጎዳናው ወድቀው የነበሩና የተረሱ የአዕምሮ ህሙማንና አረጋውያንን በተለይ የአልጋ ቁራኛ የሆኑትን አረጋውያንን ከወደቁበት ጎዳና ፤ ከተረሱበት ቦታ በማንሳት በአዲስ አበባ ኮተቤ ብረታ ብረት አጠገብ  መጠለያ አዘጋጅቶ እስከ ህይወት ፍጻሜያቸው ድረስ ለመንከባከብ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡

Friday, November 15, 2013

የ2005 ዓ.ም የቤተክርስቲያኒቱ ሀገራዊ ገቢ አንድ ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር ተጠጋ




(አንድ አድርገን ህዳር 6 2006 ዓ.ም )፡- ዐዋጅ ነጋሪ ተብሎ ጥቅምት 2006 ዓ.ም በሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ  የተዘጋጀው መጽሔት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስር በሀገር ውስጥ ብቻ  የሚተዳደሩ 50 የሀገረ ስብከቶች ጠቅላላ ገቢ የሚያሳይ መረጃ ይዞ ወጥቷል፡፡ በሰባካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ የወጣው ስታስቲክሳዊ መረጃ   የእያንዳንዱን አህጉረ ስብከት የ2005 ዓ.ም የዘመኑን ገቢ ያሳያል፡፡ እንደ መረጃው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በገቢ መጠን ከሁሉም በከፍተኛ ሁኔታ ልቆ ይታያል ፡፡ ጠቅላላ ገቢውም 322,739,515 ( ሶስት መቶ ሃያ ሁለት ሚሊየን ሰባት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ አምስት መቶ አስራ አምስት) ሲሆን  ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ቀጥለው  
1.     አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት               322,739,515.29
2.    ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት                  46,330,546.99
3.    የምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት              32,843,596.64
4.    ሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት              29,805,415.24
5.    ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት                25,853,270.26
6.    ምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት            21,894,699.00
7.    ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት                20,456,331.63
8.    አርሲ ሀገረ ስብከት                      19,297,272.45
9.    መቀሌ ሀገረ ስብከት                     18,352,795.05
10.  ምስቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት               17,522,762.00
11.    ደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት              16,896,645.44