Tuesday, December 6, 2011

የአሁኑ ጊዜ መዝሙሮች ፤ የፕሮቴስታንት ቅጅዎች

..
እናስተውል.........
በፊት በፊት የመዝሙር ግጥሞች ሲፃፉ እግዚአብሔር እንዲመራቸው በፆምና በፀሎት እግዚአብሔርን መጠየቅ የነበረ ሲሆን አሁን አሁን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተብሎ የሚወጣው መዝሙር ግጥም ከመናፍቃን የመዝሙር ካሴት ግጥም ኮፒ እየተደረገ መቅረብ ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡ በተጨማሪም ሆን ተብሎ ለቸብቸቦ የሰውን ስሜት እንዲገዛ ተደርጎ ከመፃፉም ባሻገር አንዳች ነገር ለመዝሙር ሰሚው ወንጌልን የማስተላለፍ ሚናው በሙሉ ጠፍቷል ፡፡ ለምሳሌ ለማሳያ ያህለል ዘርፌ ከበደ አወጣሁት ካለችው መዝሙር ሁለት ያህል ግጥሞች አቶ በጋሻው ደሳለኝ ፃፍኩ ያለው ሲሆን በጊዜው እነዚህ ግጥሞች ከመናፍቃኑ ካሴት ምንም ለውጥ ሳይኖራቸው የተገለበጡ በመሆኑ የግጥሙ ባለቤት ግጥሜ ተሰርቆብኛል ሲል አቶ በጋሻው ደሳለኝን ፍርድ ቤት መክሰሱ የሚታወስ ቢሆንም የፍርድ ቤት ሂደቱ በአጭር እንደቀረ ያለፈ ትውስታችን ነው፡፡

አቶ በጋሻው ደሳለኝ የመናፍቃንን ካሴት እየቃረመ ለእኛ ማቅረቡን የለመደው የቀን ተቀን ስራው መሆኑን ለማወቅ ‹‹የመስቀሉ ስር ቁማርተኞችን›› የሚለውን መፅሀፍ ለመፃፍ የፓስተር መለሰ ወጉን የስብከት ካሴት ቁጥር 107 ገልብጦ የተጠቀመ ሲሆን ይህን ስራውን በዘርፌ ካሴት ላይም ደግሞት ለማየት በቅተናል፡፡ ለማስረጃ ያህል የሚቀጥለውን ካሴት ስቲከር ይመልከቱ 



የአርሴማ ቅድስት ክርስትያኖችን የማፅናናት ዘመቻ

  • ‹‹አጽናኑ፥ ሕዝቤን አጽናኑ ይላል አምላካችሁ።›› ትንቢተ ኢሳይያስ 40 ፤ 1
በቅርቡ በቃጠሎ የወደመችውን የቅድስት አርሴማን ቤተክርስትያን አካባቢው ላይ የሚገኙትን ክርስትያኖች ለማፅናናት እና እኛም የእናንተው ወገን ነን ፤ በሁሉም በኩል ከጎናችሁ ነን ፤ የደረሰው ነገር አሳዝኖን እናንተን ለማፅናናት ነው ወደዚህ ቦታ የመጣነው ለማለት ወደ ቦታ በሶስት መኪኖች ከሆሳዕና ከተማ ወደ 200 ሰው የሚጠጉ ክርስትያኖች ቦታ ድረስ ሄደው የሆነውን ነገር ለመመልከት ችለዋል ፡፡ ቦታ ላይ ሲደርሱ የሚሳለሙት ቤተክርስትያን እንደምታዩት ሆኖ ነበር የጠበቃቸው ፤ ሁሉም መሪር ሀዘን ነበር የተሰማቸው ፤ ላይችል አይሰጥምና እኛም ይህን ፈተና ችለንና ተቋቁመን ፤ በፊት ከነበረው የቤተክርስትያኗ እይታ የተሸለ ተደርጎ እንደሚሰራ ባለሙሉ ተስፈኞች ነን፡፡ በጊዜው አውደ ምህረት ባይኖርም ፤ ቦታው ላይ መዝሙር በመዘመር እግዚአብሔርን ነፍሳቸውንም ደስ አሰኝተዋታል ፡፡ በዕለቱ አንድ እናት የሠጡትን ቀለበት በሚያስገርም ሁኔታ 24,452.50(ሃያ አራት ሺ አራት መቶ አምሳ ሁለት ብር ከ50 ሳንቲም) በጋራ መዋጮ ተጫርቶ ገንዘቡን ለቤተክርስቲያኑ ማሰሪያ ማገባት ችለዋል፡፡ ያለውን ሁኔታ በካሜራ ከቀረው ብዙ ፎቶዎች 20 ፎቶዎችን ለናንተው አድርሰናል ፡፡ 

የሀገረሥብከቱ ሥራአስኪያጅ   መጋቢ ሀይማኖት አብርሐም   ስልክ  0911551516 ሲሆን ቤተክርስትያኗን የምትረዱበት መንገድ በዚህ ስልክ ደውለው ማነጋገር የምትችሉ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡


Monday, December 5, 2011

የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን በዋሻ ውስጥ ተገኝ


በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሰማነው እግዚአብሔር አሁንም  አብሮን እንዳለ በምህረቱም እየጎበኝን እያለ መሆኑን ነው፤ በጠላት ወረራ ጊዜ የተቀበረውን የቅዱስ ገብርኤልን ቤተክርስትያ በማውጣት አሳይቶናል ፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን:: እግዚአብሔር አልተወንም ፤ አይተወንም የሚያስብል ተዓምር ነው የተደረገው፡፡

ይህ ጥንታዊ ዋሻ በውስጡ አካቶ ይዟቸው የሚገኝው አስደናቂው ነገር ርዝመቱ በውል ያልታወቀ የግብር ቤትና ፤ የክርስትና ቤት በውስጡ የሚገኝ ሲሆን ፤ ከኢጣልያን ወረራ እና ከግራኝ መሀመድ በመሸሽ የተቀበረ ቅርስና ፅላት ተገኝቶበታል፡፡ ይህንን ጥንታዊ ዋሻ ያገኙት አባት በራዕይ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፅላት በውስጡ እንዳለ ተነግሯቸው ቁፋሮ ለመጀመር በሱባኤ ላይ እንዳሉ ለማወቅ ችለናል፡፡ ሌላው አስደናቂው ነገር ከዋሻው መካከል ላይ የብርሀን መግቢያ የተፈጥሮ ክፍተት ያለው መሆኑ ድንቅ ያሰኛል፡፡ የዋሻው ጠረጋ ሲጀመር የአባቶች አፅም ፤ የብራና መፃህፍት ፤ የፅንአ ቁርጥራጭ ፤ የሰም ስብርባሪ በውስጡ እንደተገኝ ለማወቅ ችለናል፡፡ በተጨማሪም 
በዋሻው የውስጥ ክፍል ቅኔ ማህሌት ፤ ቅድስት ፤ መቅደስና ቤተልሔም ይገኙበታል ::
 ለመላው ህዝበ ክርስትያን በሙሉ አስደናቂውን እና ተዓምረኛውን የዋሻ ገብርኤል ቤተክርስትያን በአቃቂ ቃሊቲ ከቶታል ሳሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ወረድ ብሎ መብራት ሀይል ማዶ ላይ የተገኘውን የጥንት ዋሻ ቤተክርስትያን ብዙ ገቢረ ተዓምራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህውም በፀበሉ ፤ በእምነቱ ፤ በንፍሮ ውሀው ብዙ ህሙማና አጋንንት እየፈወሰ ስለሚገኝ በቦታ ተገኝተው ከበረከቱ እና ከገቢረ ተዓምሩ ተካፋይ በመሆን የቦታውን ታሪክም በአካል እንዲያዩ በቅዱስ ገብርኤል ስም ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡ 
አድራሻ፡- ቃሊቲ ቶታል ከሳሎ ጊዮርጊስ ወረድ ብሎ መብራት ሐይል ማዶ ገላን ጉዳ መተሊ ቅዱስ አሮንና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን
 ለበለጠ መረጃ 0913-464936 ደውለው የተሻለ መረጃ ማግኝት ይችላሉ

 ‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስትያናችንን ይጠብቅ››

Saturday, December 3, 2011

የግብረሰዶማውያኑ ስብሰባ የፈጠረው ትኩሳት



(From Reporter) ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ የሚጀመረው 16ኛው ዓለም አቀፍ የኤችአይቪ/ኤድስና የአባላዘር በሽታዎች(አይካሳ) ጉባዔን አስታክኮ፣ መሰንበቻውን የግብረሰዶማውያን ቡድን እያካሄደ ያለውን እንቅስቃሴ ከተለያዩ ወገኖች ተቃውሞ ሲቀርብበት ነበር፡፡

ስለተቃጠለው ቤተክርስቲያን የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘገባ


በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ በስልጤ ዞን በስልጤና ሀድያ ሀገረ ስብከት የጋራሬ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተቃጥላ ሙሉ በሙሉ መውደሟን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ጠቆሙ፡፡ እንደምንጮቻችን ገለፃ፤ ቤተክርስቲያኒቷ ህዳር 18/2004 ከሁለት ትምህርት ቤቶች በመጡ ወጣት የእስልምና እምነት ተከታዮች ጋዝ ተርከፍክፎባት ሙሉ በሙሉ ተቃጥላለች፡፡

ግብረ ሰዶማውያኑ በሀገረ እግዚአብሔር እየተወያዩ ነው


  • ዓላማው ግብረ ሰዶማዊነትን በአፍሪካ ማስፋፋት ነው
  • መንግሥት ስብሰባው በኢትዮጵያ እንዳይካሄድ አልተከላከለም
ኢትዮጵያ ከምታስተናግደው “16ኛው ዓለም አቀፍ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና የአባላዘር በሽታዎች ጉባኤ በአፍሪካ” (ICASA) አንድ ቀን ቀደም ብሎ በዛሬው ዕለት ይካሄዳል የተባለው የአፍሪካ ግብረ ሰዶማውያን የቅድመ ኮንፈረንስ ማነቃቂያ ስብሰባ ከፍተኛ ትችት እና ተቃውሞ ቢገጥመውም እስከ ትላንት ድረስ 40 ሰዎች የተካፈሉበት ስብሰባ ለሦስት ቀናት የተካሄደ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ 200 ግብረ ሰዶማውያን የሚሳተፉበት ስብሰባ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡


ስብሰባው በተመድ የስብሰባ ማዕከል እንደሚካሄድ አዘጋጁ በድረ ገጹ አስፍሯል፡፡ ቀደም ሲል ስብሰባው እንደሚካሄድበት የተነገረው ጁፒተር ዓለምአቀፍ ሆቴል በበኩሉ፤ የተጠቀሰው ስብሰባ ፈጽሞ በሆቴሉ ውስጥ እንደማይከናወን አስታውቋል፡፡

Thursday, December 1, 2011

ከዚህም አስበልጠን እንሰራዋለን


የአርሴማ ቅድስተ የቀድሞ እይታዋ

‹‹ሐጥያታችንን አጽድቁልን›› ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ


  • አዲስ አበባ ላይ ሊደረግ የታሰበው ስብሰባ ያለምንም እንቅፋት እንደሚካሄድ ለማወቅ ችለናል::
  • አዲስ አበባ ቢሮ ለመክፈት እቅድ እንዳላቸው ሁላ ሰምተናል፡:
  • መንግስትም ይህን ሁሉ በማድረግ ረብጣ ዶላር ከምዕራባውያኑ በብዙ መልኩ ሊያገኝ ይችላል::
የለህም እንዳልል ይመሻል ይነጋል
አለህም እንዳልል እንዲህ ይደረጋል 



የግብረ ሰዶም ሕጋዊነት መጽደቅ ምክንያት በማድረግ  ህዝባዊ ፌሽታ

(By Zelalem Mengestu ):- የሰውን ዘር በእግዚአብሔር ቁጣ ያስጠፋው፤ከኃጢያት ሁሉ የከፋው ኃጢያት፤ለባሕሪ የማይገባ ፤የእግዚአብሔርን የቁጣ ጽዋ ቶሎ የሚሞላ፤ለማይረባ አእምሮ ተላልፈው በተሰጡ ሰዎች የሚፈጸም የኃጢያት ቁንጮ፤የዘመናችን ሕጋዊ ኃጠያት እየሆነ ከመጣ ዘመናትን ያስቆጠረ ቢኖር ግብረሰዶማዊነት ነው። ዛሬ ዛሬ በአለማችን ስለግብረሰዶምነት ሽንጣቸውን ገትረው የሚከራከሩ ማህበራት፤የሃይማኖት አባቶች ነን ባዮች፤ፓለቲከኞች..ብዙ ብዙ..ተፈልፍለዋል።በዚህ ዘመን በአንዳንድ አገሮችና አብያተ ክርስቲያናት ለምሳሌ በአለምና በተለያዩ አገሮች ያሉ የአንግሊካን ቤተክርስቲያን ሳይሆን ቤተሰይጣን ውስጥ ያሉ ምእመናን መሪዎቿ በዚህ ተግባር ውስጥ ተሳታፊ መሆናችውና እውቅና እየተሰጣቸው መምጣቱን ምን ያህል አለም እንደረከሰች እናያለን።


ታቦት

በዲ/ን ኢንጂነር አባይነህ ካሴ
ከአኮቴት የቴሌቪዥን መርሀ ግብር የተወሰደ

የወላዲተ አምላክ ድንቅ ተአምር



(አንድ አድርገን ፤ ህዳር 21 2004 ዓ.ም)፡- ዛሬ ፃድቃኔ ማርያም ሄጄ በአይኔ ያየሁትን ተአምር ልፅፍላችሁ ወደድኩኝ፡፡ ቀኑ ቅዳሜ ነው ፤ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ወደ ፃድቃኔ ለመሄድ የሚነሱበት ቀን ስለሆነ መጀመሪያ የሚወጣው አውቶቡስ እንዳያመልጠን ከባለቤቴ ጋር በጠዋት ነበር አውቶቡስ ተራ የደረስነው ፤ ነገር ግን ሰው እዛ ያደረ ይመስል 12፡00 ላይ አውቶቡሱ ሞልቶ መንቀሳቀስ ጀምሮ ነበር፡፡ ባለቤቴም ‹‹አይ በዚህም ሰዓት ደርሰን አመለጠን ይገርማል ተወው ባክህ እመቤቴ እንደፈቀደች›› አለችኝና ሁለተኛው አውቶቡስ ላይ ገባን፡፡ ይህኛው ደግሞ ቀጥታ ዘላቂ ሰው ስላጣ የመንገድ ሰዎችንም በመጫን ነበር የሞላው፡፡ ጉዞ ወደ ፃድቃኔ ማርያም ፤ ውዳሴዋን ደግመን ጉዞ ጀመርን፡፡ መኪናው ሲያወርድ ፤ ሲጭን 9፡00 አካባቢ  ደብረ ምጥማቅ ደረስን ፤ እዚህ እንውረድና በአቋራጭ እንሂድ ተባብለን ሰላ ድንጋይ ሳንደርስ ወረድን ፡፡ እቃችንን ለአንድ የሀገሬው ሰው አሸክመን አቋራጩን ተያያዝነው ፡፡ ልጁ እንዲህ አለን ‹‹ ዛሬ ግን ማደሪያ የምታገኙ አይመስለኝም በጣም ብዙ ሰው ነው የመጣው አለን›› :: ‹‹ችግር የለውም ውጪ አንጥፈን እናርፋለን ለመተኛት መች መጣን›› አልነው፡፡