Friday, November 4, 2011

ፓትርያርኩ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን የሚጻረሩ ዝውውሮች እና ሹመቶች እያካሄዱ ነው


  • ከሓላፊነታቸው በተነሡት በአባ ሰቀረ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ምትክ በቅርቡ ከአሜሪካ ተመልሰው የአየር ጤና ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት አባ ኅሩይ መሸሻ የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ዋና ሓላፊ ሆነው እንደተሾሙ ተመልክቷል፤ አባ ኅሩይ በፓትርያርኩ ከቀረቡት የጵጵስና ሹመት ተስፈኞች ዝርዝር ውስጥ እንደነበሩበት ምንጮች እየገለጹ ነው።
  • ውጤታማው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም ገብረ ሥላሴ ያለሲኖዶሱ ዕውቅና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ መሆናቸው ተገልጧል፤
  • የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመንፈሳውያን ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ያለሲኖዶሱ ውሳኔ ከሓላፊነታቸው ተነሥተው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ እንዲሆኑ፤

‹‹ሰው ፊተኛ ሊሆን ቢወድ ከሁሉ በኋላ የሁሉም አገልጋይ ይሁን›› ማርቆስ 9፤35

  • እግዚአብሔር ፈራጅ አምላክ መሆኑን ረስተውታል ፡፡ 
  • በአጠቃላይ በአለማዊውም ሆነ በመንፈሳዊው ዘንድ ትህትና ፤ መከባበር ፤ ቅንነት፤ ርህራሄ መልካምነት ጠፍቶ በምትኩ ሴረኝነት፤ አድርባይነት፤ ጨካጭነት ፤ስግብግብነት ተተክቷል፡፡ 
  • የምድርን በረከት ለማግኝትም ሆነ የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ ብልጠት እና ሴራ ዋጋ የላቸውም ፤ ዋጋ ያላቸው ትህትናና ቅንነት ናቸው ፡፡
To Read in PDF Click Here

Click Read more to continue

12ኛ ቀን የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ ስብሰባ ዜናዎች

አቡነ ፋኑኤል ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን በሽምግልና በመጠቀም በዋሽንግተን ዲሲ እና በካሊፎርኒያ የሚጠብቃቸውን መሬት አንቀጥቅጥ ተቃውሞ ለማብረድ እና የአሜሪካ ሹመታቸውን ለማደላደል እየተጣጣሩ ነው፤

ቅ/ሲኖዶስ በመ/ፓ/ጠ/ጽ/ቤት አስተዳደራዊ እና መዋቅራዊ ችግሮች ላይ የቀረበው የዳሰሳ ምልከታ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በሚመራ የባለሞያዎች ኮሚቴ እንዲገመገም ወሰነ፤
  • በኤፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 34 ንዑስ አንቀጽ 5 መሠረት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን የፌዴራል መንፈሳዊ ፍርድ ቤቶችን እንደገና ለማቋቋም፣ ለማደራጀት እና ለማጠናከር የተዘጋጀውን ዐዋጅ ረቂቅ መርምሮ በማስተካከል በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሕግ ዕውቅና እንዲያገኝ ይላክ ዘንድ መርቷል፤ መንፈሳዊ ፍ/ቤቶቹ የመንግሥትን የፍትሕ አካላት ላጨናነቁት የቤተ ክህነት ጉዳዮች እፎይታ እንደሚሰጡ ተስፋ ተደርጓል፤ 
  • የጋብቻ፣ ፍቺ፣ ቀለብ አወሳሰን፣ አካለ መጠን ያልደረሱ ሕፃናት ሞግዚትነትና በቤተሰብ ተዛምዶ ላይ የሚነሡ ጥያቄዎች፣ የውርስ፣ የኑዛዜና የስጦታ ጉዳዮች፣ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ከሚሰጡት መንፈሳዊ አገልግሎት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣ ከላይ በተገለጹት ጉዳዮች ላይ በሚቀርቡ ክሶች ኪሳራ መወሰን የፍ/ቤቶቹ የወል ዳኝነት ሥልጣን ክልል የሚሸፈኑ ናቸው፡፡ 
  • በፍ/ቤቶች ጉዳያቸው የሚታየው በቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት ሥርዐት በፍ/ቤቶቹ ለመዳኘት ተስማምተው በፈቃዳቸው የቀረቡ አገልጋዮች እና ምእመናን ናቸው፡፡
  • ፍ/ቤቶቹ በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ የሚቋቋሙ ሲሆን መሪዎቹ ‹‹ርእሰ ፍትሕ›› የሚል ማዕርግ ይሰጣቸዋል፤

Thursday, November 3, 2011

አነጋጋሪውን ቪሲዲ ማን ለቀቀው?

"የአሮጊቷ ሳራ ልጆች"
"የአሮጊቷ ሳራ ልጆች"
እርግጥ ነው፤ እገሌ የተሐድሶን አጀንዳ እያስፈጸመ ነው፡፡እሺ እገሌስ? እነ እገሌስ ለይቶላቸዋል፤ እነ እገሌስ?….ይኽ ማን ከማን ወገን እንደሆነ ለማወቅ የሚቀርብ የየአካባቢው ጥያቄ ነው፡፡ ይኽ ጥያቄ ተመልሷል፡፡ መላሹ ክፍል ደግሞ ራሳቸው ተጠርጣሪዎቹ ናቸው፡፡ሌላውን ሰው በጥርጣሬ ዓይን መመልከት ይብቃ የተሐድሶ መናፍቃኑ እኛ እንጂ ሌላ አይደለም ብለውናል ሰሞኑን በተለቀቀ VCD::

ሰሞኑን አንድ VCD ተለቋል፡፡ይኽ VCD ማን እንዳዘጋጀው ባይታወቅም ልክ እንደ አዋሳዎቹ ሁለት ቪሲዲዎች ብዙ እውነታዎችን የያዘ ሲሆን በዋነኛነት ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም. የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች በአዲስ አበባ መንበረ ፓትርያሪክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በተሐድሶ መናፍቃን ላይ ያደረጉትን የተቃውሞ ሰልፍ ያሳያል፡፡

የ8ቱ ጉባኤያት አዳሪ ደቀ መዛሙርት በበጀት እጥረት ሳቢያ ትምህርት አቋርጠው በርሀብ ወድቀዋል


የታእካ ነገስት በዓታ ለማያም ገዳም ቀሳውስትና መምህራን ማሰልጠኛ 8ቱ ጉባኤያት አዳሪ ትምህርት ቤት 50 ደቀ መዛሙርት ከ1999 ጀምሮ በቋሚ ሲኖዶስ የተፈቀደላቸው ወርሃዊ 150ብር ድጎማ ከጥቅምት 15 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ በመቋረጡትምህርታቸውን መስተጓጎሉን እና በርካታ ተማሪዎችም በርሃብ ተዳክመው በማደሪያ ቤታቸው ወድቀው እንደሚገኙ ደቀመዛሙርቱ በተለይ ለፍትህ ጋዜጣ ገልጸዋል፡፡

Wednesday, November 2, 2011

እነሆ ቤተክርስትያን ላይ አሾህ ተተከለ


እረ. . ." የቤተ ክርስቲያን አምላክ ወደኛ ተመልከት"
ለአሜሪካ የሀገረ ስብከት የሥራ አስኪያጅነት የተጠቆሙ ሰዎች ሥምም አብሮ ደርሶናል
  • አባ ሰረቀ በሥራ አስኪያጅነት
  • ሊቀ ካኅናት ኃይለሥላሴ (ዴንቨር ) በጸሀፊነት
  • አቶ በጋሻው ደሳለኝ በስብከት ወንጌል ኀላፊነት (ከፓትሪያሪኩ የትብብር ደብዳቤ ለአሜሪካን ኤምባሲ እንዲጻፍላቸው በአባ ፋኑኤል ተጠይቀው ፈቃደኝነታቸውን ገልጸዋል) ደብዳቤው በዛሬው እለት ተዘጋጅቶ ፓትሪያሪክ ጳውሎስ እንደሚፈርሙበት ዛሬ ይጠበቃል)
  • የመከፋፈል ሥራቸውን 02/21/2004 ጀምረው በሳሪስ በሚገኘው መኖሪያ ቪላቸው ውስጥ ስብሰባ አድርገዋል(እስከ ምሽቱ ፮ ሰዓት ድረስ በአባ ፋኑኤል ቤት  ሲዶልቱ አምሽተዋል)
  • “እኔ አሜሪካዊ ነኝ ምንም አይጎድልብኝም ይብላኝ ለእናንተ”አቡነ ፋኑኤል ከሐዋሳ ሲነሱ የተናገሩት
". . .ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት. . ."  የያዕቆብ መልእክት ፩ ፥ ፪ - ፫

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ በሚሆን አሜን

ሰሞኑን ከቅዱስ ሲኖዶስ አካባቢ የመጣው ዜና እጅግ አስደንጋጭ፣ አሳዛኝ፣ ሚዛናዊ ያልሆነ እንደሆነ ለማናችንም ግልጽ ነው፥ እኛ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን እስቲ ተጠየቁ እረ ለመሆኑ ከመቼ ጀምሮ ነው
  • ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ሲጥሱ እና ሲያስጥሱ፣
  • ለፕሮቴስታንታዊያን ተሀድሶ ቡድኖች እውቅና በመስጠት የነበሩ፣
  • ሕገ ወጥ ሰባኪያንን እና ዘማሪያንን (ኑ በእኔ ሀገረ ስብከት ማንም ሊከለክላችሁ አይችልም) በማለት ሲያበረታቱ እና ሲያዋቅዱ የነበሩ፣
  • የግል ንብረትን እና ሃብትን ብቻ ማጋበስ የለመዱ፣
  • ከዋሺንግተን ዲሲ ደብረ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን $ 150,000.00 ገንዘብ የዘረፉ፣
  • በዋሺንግተን ዲሲ ላይ የውጪ ግንኙነት የተባለውን ጽ/ቤት (አሁን ቅዱስ ሲኖዶስ የዘጋውን) ያዋቀረ እና የመሰረቱት

የዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት አብያተ ክርስቲያናት እና ካህናት ቅ/ሲኖዶስ ውሳኔውን እንዲያጤን ጠየቁ


(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 22/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 2/2011/ )፦ የቅዱስ ሲዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥቅምት 21/2004 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ለዲሲ እና ለካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስነት የተመደቡትን የአቡነ ፋኑኤል ሹመት የቀሰቀሰውን የምዕመናንን ቁጣ ተከትሎ በሀ/ስብከቱ  ሥር የሚገኙ  11 አብያተ ክርስቲያናትም አስቸኳይ ስብሰባ አድርገው ድምጻቸውን አሰምተዋል፤ ለቅዱስ ሲኖዶስም ባለ 5 ገጽ መልእክት አስተላልፈዋል። “በሰሜን አሜሪካ አሁን የሚታየው ችግር ተወሳስቦ ተወሳስቦ አሁን ያለበት ደረጃ የደረሰው ከመጀመሪያው ጀምሮ  የቤተ ክርስቲያን መዋቅር የማስጠበቅ ተግባር ተጠናክሮ ባለመሰራቱና በወቅቱ መፍትሔ ሊሰጣቸው የሚገቡ  አስተዳደራዊ ችግሮች ሳይፈቱ በመቅረታቸው ነው” ያለው መግለጫው

‹‹ዳሞ ደስ ይበልኪ ተሠርገወ ደብርኪ››

BY HENOCK YARED
‹‹ዳሞ ደስ ይበልኪ
ተሠርገወ ደብርኪ››

ትግርኛን ከግእዝ ጋር አስተባብሮ ‹‹ደስ ይበልሽ ደብረዳሞ፤ ተራራሽ አምባሽ አሸበረቀ፤ ተዋበ፤›› እያለ ግጥሙን ያቀረበው አንድ የአካባቢ ነዋሪ ነው፡፡

ጭራ ዋጣውም (ባለማሲንቆው አዝማሪ) በበኩሉ
‹‹አረጋዊ ፀሓዬ
መፅኤአለኹ ናብ መፅብዓዬ››

(አረጋዊ ፀሐዬ ወደ ስለቴ መጥቻለሁ)
ጭራ (ማሲንቆ) እና ድምፁን ሲያስማማ በዙርያው ያሉት ምዕመናንም እየተቀባበሉ መዘመራቸውን አልተውም፡፡ ይህም የተሰማው፣ የተስተጋባው ጥቅምት 14 ቀን 2004 ዓ.ም. ዓመታዊው የአቡነ አረጋዊ በዓል በተከበረበት ዕለት በጥንታዊውና ታሪካዊው ደብረ ዳሞ ገዳም በተገኘበት ጊዜ ነው፡፡
የዘንድሮው በዓል ለየት ያደረገውና ምእመናኑን፣ ቱሪስቶችን፣ የአካባቢውንም ነዋሪዎች ሁሉ የላቀ ደስታ ያስጎናፀፋቸው ሦስት ዓይነት ግንባታዎች ተከናውነው መመረቃቸው ነው፡፡

Tuesday, November 1, 2011

ቅ/ሲኖዶስ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ በምልአተ ጉባኤው የተገሠጹትን አቡነ ፋኑኤልን ለአሜሪካ ሾመ



ቅዱስ ሲኖዶስ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ላይ የቀረቡት ማስረጃዎች ተመርምረው አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ እንዲጠራ ወሰነ
  • ፈቃድ የሌላቸው ሕገ ወጥ ሰባክያን በማንኛውም መድረክ ማገልገል አይችሉም፤ እነርሱን በሚጋብዙ አለቆች እና የስብከተ ወንጌል ክፍሎች ላይ ጥብቅ ርምጃ ይወሰዳል፤ ጉዳዩ የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነት እና ሰላም በመንሳት ካለው ባሕርይ ውጤት አኳያ ከግብረ ሽበራ ጋርም በተያያዘ ሊያስጠይቅ ይችላ ብሏ
  • የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ አራማጅ ማኅበራትበቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡ ቅዱስ ሲኖዶስ አስጠነቀቀ

የጻድቁ ተክለ ሃይማኖት፣የንጉሥ ጦና፣በአማን ቅዱስ የሆኑ የመናኙ ፓትርያርክ ተክለ ሃይማኖት መፍለቂያ፤ወላይታ


(By Mitiku Abera ) ዳግማዊ ምኒልክ(ሕዝቡ በፍቅር እምዬ ይላቸው ነበር) ኅዳር ፳፯ቀን ፲፰፻፹፰(1888)ዓ.ም. ወላይታ ከጦና ዋና ከተማ ደልቦ ደረሱ፡፡ እዚኽ የመገኘታቸው ምስጢር የወላይታው ንጉሥ ጦና አልገብርም ብሎ በመሸፈቱ እሱን ለማረም ነበር፡፡“…አገር ከጠፋ በኋላ ሲያቀኑት ያስቸግራል፡፡ገንዘብም በግድ ካልሆነ በቀር በፈቃድ የሰጡት አያልቅም፡፡አገርህን አታጥፋ፡፡ግብርህን ይዘኽ ግባ፡፡”ብለው በሽምግልና ቢሞክሩም መልሱ እምቢታ በመሆኑ አጤ ምኒልክ ዳሞት ተራራ ላይ ያሰፈሩትን ጦራቸውን አዘው በአንድ ጊዜ ወላይታን አስጨነቋት፣ንጉሥ ጦናም ቆስለው ተማረኩ፡፡የሚገርመው ግን መፍቀሬ ሰብዕ እና የዲፕሎማሲ ሰው የሆኑት አጤ ምኒልክ “አይ ወንድሜን እንዲያው በከንቱ ሕዝብ አስጨረስክ”ብለው የንጉሥ ጦና ቁስል እንዲታጠብና እንዲታከም ካስደረጉ በኋላ የተማረከው የባላገሩ ከብት እንዲመለስ አድርገው፣ንጉሥ ጦና እስኪያ በእግዚአብሔር ቸርነትና ብርቱ በሆነው ተጋድሎአቸው የረቱት አገግሙ ጠብቀው የወላይታን ሕዝብ ሰብስበው“…እንግዲህ ወዲህ የሚያስተዳድርህ ልጄ ወዳጄ ጦና ነውና ተገዛለት፡፡ አውቆ ሳይሆን ሳያውቅ እኔን የበደለ መስሎት ሰው አስጨረሰ እንጂ ከድሮም ከአያቶቻችን ቂም የለንምና መልሼ እሱን ሾሜልሃለው፡፡…እንግዲህ ወዲህ ብታምጽ በራስህ ዕወቅ፡፡ ግብሬን አግባ፡፡…”የማል አዋጅ አስነግረው የወጉዋቸውን ጦናን ሾመው ጥር ፲፩ቀን አዲስ አበባ ገቡ፡፡(አጤ ምኒልክ መጽሐፍ በጳውሎስ ኞኞ)