በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጊዜው እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ18ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ነበር፡፡ ለአንዳች ተልዕኮ የተነሡ ሞራቪያውያን (የቼክ ሪፐብሊክ ዜጎች የሆኑ) ፕሮቴስታንት ሚስዮናውያን ወደ ግብጽ ገቡ፡፡ ጌታችን ከእናቱ ጋር ወደ ተሰደደባት ፣ በፈጣን ደመና ተጭኖ እየበረረ ወደ ደረሰባት ፣ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ ወዳስተማረባት ሐዋርያዊት የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ‹ጌታን እንሰብካለን› ብለው ዘመቱ፡፡ የእነዚህ ሚስዮናውያን እንቅስቃሴም በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ላይ ላለፉት ሁለት መቶ ዓመታት ሲነድና ሲበርድ ለቆየው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ሴራ መነሻ ነበር፡፡