Tuesday, February 18, 2014

አባ ሰረቀ ብርሃን ‹‹በታቦት ዝርፊያ›› ክስ ብጹዕ አቡነ ማትያስ ዘንድ ቀርበው ነበር

  • ‹‹ለዚህ መረጃ አቡነ ማትያስ ቀድሞ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ በአሁን ሰዓት 6ተኛው ፓትርያርክ፣ አቡነ ሣሙኤልና አቡነ ኢሳይያስ ህያው ምስክሮች ናቸውና›› መረጃውን የላኩልን የሎሳንጀለስ ምዕመን
  • ‹‹አባ›› ሰረቀ ታቦት ሰርቀው ተይዘዋል፡፡ ከገዛናቸው 12 ጸናጽል ያስረከቡን ስድስቱን ሲሆን 12 መቁዋሚያም 6ቱን ይዘውብን ሄደዋል፡፡
  • ‹‹አቡነ አረጋዊም የሚባል ቤተክርስቲያን የለም፡፡›› ‹‹አባ›› ሰረቀ ብርሃን በአንድ ወቅት የሰበኩት ስብከት
  •  ‹‹በወቅቱ የአሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት አቡነ ማትያስ ማኅተም ወስደው በነጭ ወረቀት ላይ እያተሙ የኔን ፊርማ እያስቀመጡ ሰዎችን ብር እየተቀበሉ ከኢትዮጵያ ወደዚህ ሲያመጡ ተደርሶባቸው..........››
    በወቅቱ አባ ሰረቀ ከጓደኛቸው ጋር ሲሰሩት የነበረ ሥራ የምዕመኑ ቃል
ከአንድ የሎስ አንጀለስ ምዕመን የደረሰን መልዕክት ነው። 

(አንድ አድርገን የካቲት 11 2006 ዓ.ም)፡- በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት ሊካሄድ የታሰበው የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ በአባ ሰረቀ ብርሃን አማካኝነት ከቅዱስ ፓትርያርኩ በተሰጠ መመሪያ መሠረት ሳይካሄድ መቅረቱ ይታወቃል፡፡ የአባ ሰረቀን  የቀድሞ ተግባር በርካታ ምዕመን ቢያውቀውም  ብጹዕ አቡነ ማትያስ የሚያውቁትን እና በሎስአንጀለስ ምዕመናን ላይ ያደረሱትን በደል የደረሰንን መልዕክት ለእናንተው ለማድረስ ወደድን፡፡ ‹አባ› ሰረቀን ከአመታት በፊት በታቦት ሌብነት ብጹዕ አቡነ ማትያስ ዘንድ ቀርበውም እንደነበርም መረጃው ያመለክታል፡፡ ስለዚህ ቅዱስነታቸው አሁን እየሰሩ የሚገኙት ቀድሞ  ለሰሚ ጆሮ የሚከብድ ዝርፊያ በቤተ ክርስቲያን ላይ ካደረገ ሰው ጋር መሆኑን ነው፡፡ እስኪ በወቅቱ የነበሩ ህያው ምስክሮች የላኩልንን መረጃ ይህን ይመስላል፡፡

Sunday, February 16, 2014

የቤተክህነቱ የእግድ "ቀጭን" ትእዛዝ ምን ያመለክተናል?


(አንድ አድርገን የካቲት 9 2006 ዓ.ም)፡-በዚህ ሳምንት ማህበረ ቅዱሳን 200 በላይ የአብነት /ቤቶች መምህራንን ከተለያዩ የሃገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር በመሆን በችግሮቻቸው ዙሪያ እንዲሁም ለቤተክርስቲያን በሚያበረክቱት ግልጋሎት ላይ ለመምከር ያዘጋጀውን ጉባኤ ከፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ በተላከች አንዲት ደብዳቤ ሊታገድ ችሏል። ለመሆኑ ይህ እግድ ምን ይነግረናል?

1
. የመጀመሪያው እና ዋናው ነገር በቤተክህነቱ ውስጥ ምን ያክል አምባገነናዊነት እንደነገሰ ያሳየናል።  ማህበሩ በድምጸ ተዋህዶ ሬድዮ ፕሮግራሙ እንዳሳወቀን በዚህ ዓመት ጉባኤውን እንደሚያካሂድ በአመታዊ እቅዱ ውስጥ እንዳካተተና በአመቱ መግቢያ ላይ ለሚመለከተው የቤተክህነቱ አካል አሳውቋል። ቤተክህነቱ በወቅቱ ይህን ማህበሩ ማከናወን እንደማይችል ማሳወቅ ይችል ነበር። ለወራት ያለምንም ተቃውሞም ሆነ አስተያየት ከቆየ በኋላ ጊዜው ሲደርስና ማህበሩም ለዝግጅቱ ከፍተኛ ወጪ ካወጣበት በኋላ ሰዓታት ሲቀሩት የእግድ ደብዳቤ ማስጠት ከአምባገነንነትም በላይ ነው። ያሳዝናል! ያሳፍራልም!

ቤተመንግሥቱን የከበበው መስቀል የሃይማኖት መሪዎቹን አነጋገረ


From Addis Admass
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮና መኖርያ ቤት በሚገኝበት ታላቁ ቤተ መንግሥት አጥር ዙሪያገባው ላይ የሚገኘው የመስቀል ቅርጽ፣ የእስልምናና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ሃይማኖቶች መሪዎችንአነጋገረ፡፡ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር ባለፈው ሳምንትቅዳሜና እሁድ በሐዋሳ ባካሔደው የምክክር መድረክ ላይ ‹‹አገሪቱና መንግሥቱ የእኩልነትና የዜጎች መንግሥትነው፤›› ያሉት የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸኽ ኪያር ሙሐመድ አማን÷ ከቀድሞውሥርዐት አንጻር አሁን የሚያበረታቱ ነገሮች እንዳሉ ገልጸዋል፡፡

ይኹንና በሴኩላሪዝምም ቢኾን ፍጹምነት ባለመኖሩ ‹‹አገር የጋራ ነው ከተባለ በኋላ የጎደለ ነገር አለ፤›› በሚልአዘውትረው ጥያቄ የሚያቀርቡላቸው ሰዎች መኖራቸውን ሸኽ ኪያር ጠቅሰዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ይቀርቡልኛልካሏቸው ጥያቄዎች መካከል ‹‹ለምሳሌ፡ታላቁ ቤተ መንግሥት በመስቀል ነው የተከበበው፤ ይህ መጥፎ ነገርሊያመለክት ይችላል›› የሚሏቸው እንዳሉ ተናግረዋል፡፡

Friday, February 14, 2014

ማኅበረ ቅዱሳን ለሦስተኛ ጊዜ ያዘጋጀው የአብነት መምህራን ጉባኤ ታገደ

  • ጠቅላይ ቤተክህነቱ 2005ዓ.ም  በሀገር ውስጥ ብቻ  የሚተዳደሩ 50 የሀገረ ስብከቶች ጠቅላላ ገቢ ወደ አንድ ቢሊየን ብር ያገኝ ሲሆን የዚህን ገቢ  1 %(አንድ በመቶ) አስር ሚሊየን ብር በዓመት ለአብነት መምህራት ደመወዝ አይከፍልም፡፡
  • በተለያዩ አህጉረ ስብከቶች የአንድ አብነት መምህር የወር ደመወዝ ትክል ከ400 ብር አይበልጥም፡

(አንድ አድርገን የካቲት 8 2006 ዓ.ም)፡- ለሦስተኛ ጊዜ ሊካሄድ የታሰበው የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ ታገደ ፤ ከፍተኛ ዝግጅት የተካሄደበት ከቀድሞዎቹ ሁለት ጉባኤያት በተለየ መልኩ ማኅበሩ የተዘጋጀበት ብዙ የሚጠበቅበት ጉባኤ ይህ ነው በማይባል ምክንያት መታገዱ ታውቋል ፡፡ በዚህ እግድ ምክንያት ከተለያዩ አህጉረ ስብከቶች የተጋበዙ ከ200 በላይ የሚበልጡ የአብነት መምህራን ጉበኤውን ሳያካሂዱ መበተናቸውን ማወቅ ተችሏል ፡፡ በዚህም ድርጊት መምህራኑ እጅግ ማዘናቸውን በቦታው የተገኙ ሰዎች ገልጸዋል፡፡ ጉባኤው እንዲካሄድ በተለያየ መንገዶች መምህራኑን ጨምሮ ረዥም ርቀት የተሄደ ቢሆንም ሙከራዎች ሁሉ ፍሬ አልባ ሆነው ሦስተኛው የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ እንደማይካሄድ ማኅበሩ ለእንግዶቹ ገልጿል፡፡

Wednesday, February 12, 2014

ኦ ብእሲት - አንቺ ሴት


በዲያቆን አባይነህ ካሴ
 (አንድ አድርገን የካቲት 06 2006 ዓ.ም)፡- ሴት የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ የተሰጠው ቦታ እጅግ ከፍ ያለ ነው፡፡ ቃሉን ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀመበት አባታችን አዳም ነው፡፡ እግዚአብሔር ከአዳም ግራ ጎን አንዲት አጥንት ወስዶ እጅግ ውብ እና ድንቅ የሆነች ሔዋንን ፈጥሮ ቢሰጠው በተደምሞ "ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል።" ሲል ጠራት፡፡ ዘፍ ፪፥፳፫። ሴት የሚለውን መጥሪያ አዳም የሰጠበት ዋናው ወይንም ዐቢይ ምክንያት ምን እንደሆነ እዚሁ ተገልጦልናል፡፡ 

እርሱም "አጥንቷ ከአጥንቴ ሥጋዋም ከሥጋዬ" ስለሆነ የሚለው ነው፡፡ የቃሉ ጥንት ከመነሻው ይኽን ይመስላል፡፡ ከቃሉ አብነት የምንረዳው የሰው ሁሉ አባት አዳም እጅግ አቅርቦ የራሱ እንደሆነች ሲያመለክት ቃሉን እንደተጠቀመበት ነው፡፡ ለዚህ አባባል ማጠናከሪያ የሚሆነን ሦስተኛ ወንድ ልጁን ለአቤል ምትክ የሚሆን ተሰጠኝ ሲል "ሴት" ብሎ መሰየሙ ነው፡፡ "ልጅንም በምሳሌው እንደ መልኩ ወለደ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው።" እንዲል፡፡ ዘፍ ፭፥፫። እርሱን ከመምሰል ጋር እንዴት እንዳያያዘው ስንረዳ ቃሉ የማቅረብ እንደሆነ ያስገነዝባል፡፡ በምሳሌው እንደ መልኩ መወለዱ ሴት የሚለውን ስያሜ ከአባቱ እንዲያገኝ በአመክንዮነት ሰለቀረበ በዚህ እንረዳለን፡፡