Wednesday, March 19, 2014

የፓትርያርኩ የለውጥ ተስፋዎች ወዴት ገቡ?




የአንድ ምዕመን አስተያየት

በመጀመሪያ የአክብሮት ሰላምታዬን ለቅዱስ ፓትርያርኩ በማቅረብ የተሰማኝን  ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ ቅዱስነትዎ በመጀመሪያ የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አባት ሆነው ወደ መንበሩ በመምጣትዎና አንድ ዓመትዎን በማክበረዎ እንኳን ደስ አለዎ በማለት መልዕክቴን አስተላልፋለሁ፡፡ 

ወደ ኃላፊነት ሲመጡ ብዙ የለውጥ ተስፋዎችን በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን አስተላልፈዋል፡፡ አይዟችሁ፣ ለውጥ ይመጣል፣ ሲሉ ተናግረውም ነበር፡፡ እኔም በቤተ ክርስቲያናችን የተስፋፋውን ጎጠኝነትና ሙሰኝነት በአጠቃላይ ያለው ብልሹ አሠራር ይለወጣል ብዬ እጅግ ተስፋ አድርጌ ነበር፡፡ እርሶዎም በቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደራዊ መዋቅር ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣሉ ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር፡፡ ነገር ግን ከተወሰኑ ወራት በኋላ ድምፅዎትን መስማት፣ እርስዎንም ማየት ባለመቻሌ ፍርሃት አደረብኝ፡፡ 

በእርግጥ ቀደም ሲል የነበረው የዘረኝነትና የሙሰኝነት ሰንሰለት በአንድ ጊዜ በጥሶ አዲስ ለውጥ ለማምጣት ከባድ ሊሆንብዎ እንደሚችል እገምታለሁ፡፡ አቡነ ጳውሎስን ሲያሳስቱና ከምዕመናን ጋር ሲያጋጩ የነበሩ ጎሰኛና ሙሰኛ ግለሰቦች አሁን ምናልባት ከዚያ ቦታ ሳይነሱ እርስዎንም ወደዚያ የጥፋት ሳጥን ውስጥ አስገብትዎት መውጫ አሳጥትዎት ከሆነ እባክዎ ወደ ልቡናዎ ተመልሰው፣ ቃል የገቡባቸውን የለውጥ ተስፋዎች ለመተግበር ይነቃቁ፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል ሲነሱ መሰናክሉ ብዙ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ እርስዎም አሁን በአገራችን የተፈጠረው የዘር በሽታ ሳያደናቅፍዎና ለአሉባልታ ወሬ ጆሮ ሳይሰጡ፣ ለመስዋዕትነት እንደመጡ ተናግረዋል፡፡ የመንግሥት ፖለቲካዊ ጫናም ሳያስፈራዎ፣ መንፈሳዊ የለውጥ አባትነትዎን በተግባር ያሳዩን፡፡ የለውጥ ሥራዎ አብቦና ፍሬ አፍርቶ ለማየትና ለመጠቀም ከፍተኛ ጉጉት አለን፡፡ 

በፈጣሪም፣ በሰውም በታሪክም እንዳይወቀሱ ቃል ከገቡበት የለውጥ ጐዳና ወደ ኋላ እንዳይሉ አስተያየት ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡ 

(አቶ መብራቱ መረሳ፣ ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ) 

Sunday, March 16, 2014

ሃይማኖት ፤ ብሔር እና የቁጥር ጨዋታ


(አንድ አድርገን መጋቢት 8 2006 ዓ.ም)፡- ከሁለት ወር በፊት በኢንተርኔት ላይ በተለቀቀ አንድ የቪዲዮ ምስል ላይ አቶ ጅዋር መሀመድ በርከት ያሉ ሰዎች በሚገኙበት አዳራሽ እስልምና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ 98 በመቶ እንደሚሆን እና ኦሮሞነትን ለእስልምና ጋር አንድ ላይ አድርጎ ማስኬድ እንደሚቻል ፤ አንድም መሆን እንዳለባቸው ሲናገር ነበር፡፡ ይህን የተመለከቱ ሰዎች እውን እስልምና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ምን ያህል በመቶ ነው? ጅዋር እንዳለው 98 በመቶ ወይስ…? በማለት ጥያቄ ሲያነሱ ተስተውሏል፡፡ አቶ ጀዋር ‹‹98 በመቶ በኦሮሚያ ክልል የምንገኝ ሰዎች ሙስሊሞች ነን›› ብሎ ሲናገር ተሰብሳቢው ጆሮውን ብቻ ሰጥቶ ሲያደምጥ ይስተዋላል፡፡ ብዙ ጊዜ ራሳቸውን በአንዱ ብሔር ጠርዝ አቁመው የብሔረሰቡ ታጋይ አድርገው የሚቆጥሩ ሰዎች የማሕበረሰቡን ትክክለኛ ቁጥር ሲቀበሉ አይስተዋልም እስኪ በኢትዮጵያ ውስጥ በ1999 ዓ.ም በተካሄደው የህዝብ ቆጠራ ስሌት መሰረት የአማኝ ብዛት በዘጠኙ ክልሎች ምን ይመስላል የሚለውን መሰረት በማድረግ እንዲህ አቅርበነዋል፡፡ 

ክልል
ኦርቶዶክስ %
ፕሮቴስታንት %
ካቶሊክ %
ሙስሊም %
ትግራይ
96.7
0.0
0.3
2.9
አፋር
1.4
0.4
0
98.1
አማራ
83
0.1
0
16.8
ኦሮሚያ
27.5
17.8
0.5
49.9
ሶማሊ
0.1
0.0
0.0
99.1
ቤንሻንጉል ጉሙዝ
29.8
12.6
0.6
48.2
ደቡብ
17.8
56.7
2.5
14.2
ጋምቤላ
14
73.4
3.1
3.7
ሐረሪ
1.8
0.3
0.0
97.9
አዲስ አበባ
74.7
7.8
0.5
16.2
ጠቅላላ
43.5
18.6
0.7
33.9
v  0.0 % ማለት ምንም አማኝ በክልሉ የለም ሳይሆን ከሌሎች ጋር በተነጻጻሪነት ሲቀርብ ወደ ዜሮ ይጠጋል ለማለት ነው፡፡

Saturday, March 15, 2014

አብደው ሊያሳብዱን የሚፈልጉት ‹‹ማህበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያሳውያን››



  • “ቅዱስ ኤልያስ ይዞት የመጣውን መፅሐፍ” ቤተ ክርስትያን እንድትቀበል ተጠየቀ
  • መጽሐፉ ለአቡነ ማትያስና ለጠ/ሚ ኃይለማርያም እንዲደርሳቸው ተደርጓል
  • ደብዳቤው ለእስራኤሉ ጠ/ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታናሁ እና ለተመድ ተልኳል፡፡

   (አዲስ አድማስ መጋቢት 6 2006 ዓ.ም)፡- ከተፃፈ ከ2 ሺህ ዓመታት በላይ አስቆጥሯል የተባለውንና ስለ ቅዱስ ኤልያስ መምጣት ምስጢር የሚተነትነውን መጽሐፍ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተቀብላ ወደተለያዩ ቋንቋዎች በማስተርጎም ምዕመናኖችን እንድታስተምር፣ “ማህበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ” ለቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በጻፈው ደብዳቤ ጠየቀ፡፡   ማህበሩ፤የመጽሐፉን ኮፒዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እና ለብፁዕ አቡነ ማትያስ  ህዝቡን እንዲያስተምሩበት ከሚያሳስብ ደብዳቤ ጋር መላኩን አስታውቋል፡፡

Thursday, March 13, 2014

ተረፈተሀድሶ በደብረ ብርሃን


(አንድ አድርገን መጋቢት 2 2006 ዓ.ም)፡- ባገኙት አጋጣሚ ራሳቸውን በቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ በመሰግሰግ ከዋኖቻቸው የተሃድሶ መናፍቃን የሚሰጣቸውን ተልዕኮ በሰጧቸው ስትራቴጅ መሰረት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከቱ ህግ ክፍል ኃላፊ መ/ር አክሊል አንዱነው፡፡ እስካሁን በብጹዕ አቡነ ኤፍሬም ጸሎትና ተሀድሶ በሃገረ ስብከታቸው እንዳይገቡ በወሰዱት ቆራጥ አመራር ሀገረ ስብከቱ ተጠብቆ እንዲቆይ ያደረጉ ቢሆንም መጋቤ ሀዲስ ይልማ ቸርነት የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ በነበሩበት ወቅት ‹‹ጥሩ ማገልገል ይችላሉ›› በማለት ወደ ሀገረ ስብከቱ አባ ማርቆስ ብርሃኑ እና መ/ር አክሊል በሀገረ ስብከቱ ሾልከው እንዲገቡ እድል አግኝተዋል፡፡

Saturday, March 8, 2014

ፓትርያርኩ የአመራርና ውሳኔ ሰጭነት አቅማቸው አጠያያቂ ኾኗል ተባለ


  • ‹‹ቅዱስነትዎም ከሥራ ጓደኞችዎ ጋር ከየት መጣህ ሳንባባል በአንድነት እየተመካከርን ነው ማገልገል ያለብን  ፤ ከዚያ ወርደን መገኝት የለብንም›› አቡነ ኤልሳ ለአቡነ ማትያስ ከተናገሩት የተወሰደ
(ፋክት የካቲት 29 2006 ዓ.ም)፡- ከዓመት በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 6ተኛ ፓትርያርክ ኾነው የተመረጡበት አንደኛ ዓመት በዓለ ሢመት ፤ የካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም የተከበረላቸው ብጹዕ  ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በሕገ ቤተክርስቲያን ከሚታወቀው አስተዳደራዊ መዋቅር ውጪ ለአማካሪነት አቅርበዋቸዋል በተባሉት አካላትና ግለሰቦች ማንነት ሳቢያ በአንድ በቅዱስ ሲኖዶስ አባል ትችት ተዘነዘረባቸው፡፡
 
የፓትርያርኩ የመጀመሪያ ዓመት በዓለ ሢመት በተከበረበት ዕለት ማምሻውን በጠቅላይ ቤተ ክህነት በተዘጋጀ የራት መርሐ ግብር ላይ ትምህርት እንዲሰጡ የተጋበዙት የሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳ ‹‹እርስዎ ከማን ጋር ወርደው ነው እተማከሩ ያሉት?›› ሲሉ ፓትርያርኩን መጠየቃቸውና የምክር ቃል መለገሳቸው ታውቋል፡፡